TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"...የግድቡን 2ኛውን ዙር የውሃ ሙሌት ለማደናቀፍ የሚጥሩ ኃይሎች እንደማይሳካላቸው አውቀው ተስፋቸውን ሊቆርጡ ይገባል" - የሰራዊቱ አባላት

የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት ለሀገሪቱ ሰላም እና ለህዳሴው ግድብ ዕውን መሆን የማንከፍለው መስዋዕትነት የለም ብለዋል።

ይህንን ያሉት በቀጣናው ላይ ተልዕኳቸውን በመወጣት ላይ የሚገኙ የሠራዊት አባላት ናቸው።

የሰራዊት አባላቱ የሀገሪቱ ሰላም ሆነ ልማት በውጪ ኃይሎች ፍላጎት እና በውስጥ ባንዳዎች ተላላኪነት አይደናቀፍም ብለዋል።

የህዳሴውን ግድብ ሁለተኛውን ዙር የውሃ ሙሌት ለማደናቀፍ የሚጥሩ ኃይሎች እንደማይሳካላቸው አውቀው ተስፋቸውን ሊቆርጡ ይገባልም ሲሉም ተናግረዋል።

መላው ኢትዮጵያውያን ተስፋ የጣሉበትን የህዳሴ ግድብ ከማናቸውም ጥቃት ለመከላከል ተልዕኮ ተቀብለው በቀጣናው መሰማራታቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው ለስኬታማነቱም ዝግጁነታችን ከመቼውም ጊዜ በላይ የላቀ መሆኑን ገልፀዋል።

#FDREDefenseForce

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን 528 ቤቶች በዚህ አመት ለዕጣ ማዘጋጀቱን አስታወቀ።

ይህን ያሳወቁት የመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ሜ/ጀ ኩምሳ ሻንቆ ናቸው።

ፋውንዴሽኑ ሲመሰረት የሰራዊቱን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመፍታት እና ሰራዊቱን የቤት ባለ ቤት ለማድረግ ታስቦ መሆኑን አስታውሰዋል።

በአሁኑ ሰዓት 3 ሺ12 ቤቶች ግንባታ ላይ ሲሆኑ 528 ቤቶች ደግሞ በዚህ አመት ለዕጣ ተዘጋጅተዋል።

ሜ/ጀ ኩምሳ እንዳሉት ፦ በቃሊቲ ቁጥር 1 ሳይት 584 ቤቶች ፣ ቃሊቲ ቁጥር ሁለት 504 ቤቶች በአጠቃላይ በአዲስ አበባ ዙሪያ 1ሺ88 ቤቶች ግንባታ ላይ ሲሆኑ ፣ ግንባታቸው 56% ደርሷል።

በቢሾፍቱ አካባቢ 2 መቶ ባለ 1 እና ባለ 2 መኝታ ቤቶች እየተገነቡ ነው። አፈጻጸማቸው 76 በመቶ ደረሷል፤ በአሁኑ አመት መጨረሻ ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በአዳማ ሳይት ፣ 2 ብሎክ 80 ቤቶች ግንባታ ላይ መሆናቸውንና አፈጻጸሙ 73% በመድረሱ በዚህ አመት መጨረሻ ይጠናቀቃል ብለዋል።

በሀዋሳ ሳይት አራት ኮንራክተሮች መኖራቸውን ገልጸው ፣ 320 ቤቶች በግንባታ ላይ መሆኑንና 95% መድረሱን ተናገረዋል።

በመቐለ ሳይት 11 ብሎክ 440 ቤቶች ከ1 እስከ 3 መኝታ ቤቶች ግንባታ ላይ መሆኑን ገልፀው 'ህወሓት' በፈጠረው የፀጥታ ችግር ምክንያት የግንባታ ስራው ተጓቷል ፤ የማቴሪያል ዝርፊያና አንድ ተሸከርካሪ ተወስዷል ብለዋል።

በአሁኑ ሰዓት ፋውንዴሽኑ ግንባታው 60 በመቶ የደረሰውን ፕሮጀክት ለማጠናቀቅ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር እንደሚጠናቀቅ አሳውቀዋል።

በባህርዳር ሣይት በ2012 ዓ/ም 312 ከባለ 1 እስከ 4 መኝታ ቤቶች ተጀምረው በአሁኑ ሰኣት 52% መድረሱን ተናግረዋል፡፡

#FDREDefenseForce

@tikvahethiopia
#FDREDefenseForce

"የመከላከያ ሠራዊት ባለፉት ዓመታት ለህዳሴ ግድቡ ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አድርጓል" - የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት የሕዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር ኀይሉ አብርሃም እንደተናገሩት መከላከያ ሠራዊት ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ለግድቡ ድጋፍ አድርጓል፡፡ ለግድቡ የጀመረውን ድጋፍም አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡

መላው ኢትዮጵያውያን ለህዳሴ ግድቡ 15 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ መደገፋቸውን ያስታወሱት አቶ ኃይሉ መከላከያ ሠራዊት ሉዓላዊነትን እና ሰላም ከማረጋገጡም ባሻገር ባለፉት አስር ዓመታት ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አድርጓል ብለዋል፡፡

መከላከያ ሠራዊት የግድቡን አካባቢ ከሌሎች የሰላም ኃይሎች ጋር ተቀናጅቶ በመጠበቅ ሀገራዊ አደራውን በመወጣት ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

ግድቡ በአሁኑ ላይ ከ80% በላይ ደርሷል፤ የመጀመሪያዎቹ ሁለት ተርባይኖችም የሙከራ ምርታቸውን መስጠት እንደሚጀምሩ መግለፃቸውን የሀገር መከላከያ ሰራዊት በፌስቡክ ገፁ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#FDREDefenseForce

የመከላከያ ሚኒስቴር የ33ኛ ዙር ምልምል ወታደሮችን በአሁኑ ሰዓት በማስመረቅ ላይ ይገኛል።

በብርሸለቆ መሠረታዊ ውትድርና ማሠልጠኛ ት/ቤት ሲሰለጥኑ የነበሩ ወታደሮች የተሰጣቸውን ስልጠና አጠናቀዋል።

ተመራቂዎቹ ከመደበኛው ሠራዊቱ ጋር በመቀላቀልከ ውስጥ እና ከውጭ የሚቃጣን ወረራ በመመከት እንዲሁም የኢትዮጵያን አንድነት አጠናክው ያስቀጥላሉ ተብሎ ይጠበቃል ሲል የሀገር መከላከያ ሰራዊት አሳውቋል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሰራዊት
@tikvahethiopia