TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
214 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ለተሰንበት_ግደይ

ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት ሄንግሎ ላይ በቶኪዮ ኦሎምፒክ የሚሳተፉ አትሌቶቿን ለይታለች።

የሄንግሎ የዕለቱ መርሐ ግብር የመጨረሻ ውድድር የነበረው ደግሞ የሴቶች 10,000 ሜትር ውድድር ነበር።

በሴቶች 10 ሺህ ሜትር በተካሄደ ውድድር ለተሰንበት ግደይ ድንቅ ብቃቷን በማሳየት ውድድሯን 29:01.03 በሆነ ደቂቃ በመግባት በበላይነት አጠናቃለች።

ለተሰንበት ግደይ ኢትዮጵያን በኦሎምፒክ እንደምትወክል ከማረጋገጡ ባለፈ ሪከርዱን የግሏ ማድረግ ችላለች ።

በውድድሩ ከቀናት በፊት በሲፋን ሀሰን የተሰበረውን የ 10,000 ሜትር ሪከርድ ቀናቶች ሳይቆጠሩ ሪከርዱ በኢትዮጵያ ስር እንዲሆን አድርጋለች።

ቲክቫህ ስፖርት t.iss.one/joinchat/VvwzStMNcNHmhK0x

@tikvahethsport
#LetesenbetGidey

የዓለም የ10,000 ሜትር የሴቶች ሪከርድ ወደ ሀገሩ ተመልሷል - ለተሰንበት ግደይ 29:01.03

#ETHIOPIA

@tikvahethiopia
#LetesenbetGidey

ከ 249 ቀናት በፊት የ 5,000 ሜትር ሪከርድን የግሏ ማድረግ የቻለችው ለተሰንበት ግደይ ዛሬ ከስምንት ወራት ቆይታ በኋላ ሌላ ደማቅ ታሪክን ፅፋለች።

የሳምንታት እድሜ በቀረው የቶኪዮ ኦሎምፒክ አትሌት ለተሰንበት ግደይ ከሲፋን ሀሰን ጋር የምታደርገው ውድድር ከወዲሁ በጉጉት ይጠበቃል።

ቲክቫህ ስፖርት : t.iss.one/joinchat/VvwzStMNcNHmhK0x

@tikvahethsport
#ማኪ_ፋሽን

0991212121
♦️የጫማ ዝርዝሮችን ከነዋጋቸዉ ለማየት ቴሌግራም ቻናላችንን_ይቀላቀሉ
https://t.iss.one/makkifashionethiopia
♦️እንዲሁም Facebook ፔጃችንን_ይከተሉ
https://www.facebook.com/makkifashionethiopia
♦️በተመጣጣኝ ዋጋ ይምጡ ይሸምቱ ይዘንጡ
አድራሻ: ቦሌ መድሐኒያለም ሰላም ሲቲ ሞል ምድር ላይ
ብዙ አማራጮች ስላሉ ሱቃችንን ይጎብኙ ባሉበትም_እናደርሳለን
♦️የስራ ሰአት ከሰኞ-እሁድ ከጠዋቱ 3:00- ምሽት 1:30
#PressBrifing

ዛሬ ሰኔ 2/2013 "ከሠዓት 9:30" የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት መግለጫ እንደሚሰጥ አሳውቋል።

ይኸው መግለጫ በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ዩትዩብ ቻናል ላይ የቀጥታ ሽፋን እንደሚያገኝ ተጠቁሟል።

@tikvahethiopia
#Tigray

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በትግራይ ክልል የመደፈር ጥቃት የተፈፀመባቸው ሴቶች እና ልጃገረዶች ቁጥር ከ1,400 መብለጡን ገለፀ።

በፌዴራል መንግስቱ የተሾሙት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የፍትህ እና የሴቶች ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ኢተነሽ ንጉሰ ፥ ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ህክምና ተቋማት የሄዱ ሴቶች እና ልጃገረዶች ቁጥር 1,408 መድረሱን ተናግረዋል።

እንደትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር መረጃ ፦
- በመቐለ 716
- ከዓዲግራት 362
- ከአክሱም 85
- ከሽረ 48
- ከማይጨው 37
- ከመሆኒ 18 የተመዘገቡትን ጨምሮ አጠቃላይ 1,408 ሴቶች እና ልጃገረዶች ተደፍረዋል።

የዓይደር ሆስፒታል ዋና ስቶፕ ሴንተር አስተባባሪ ሲስተር ሙሉ መስፍን ፥ በትግራይ ውስጥ በሴቶች ላይ የሚፈፀመው ጥቃት ከመሻሻል ይልቅ እየተባባሰ መሄዱን አመልክተዋል።

ወደ ዓይደር ሆስፒታል ሄደው ስለታከሙ እና በመታከም ላይ ስለሚገኙ ጉዳተኞች ሲስተር ሙሉ መስፍን ሲገልፁ "ተሻሽሏ የሚባል ነገር የለም" ብለዋል።

በኤርትራም ፤ በኢትዮጵያም ወታደሮች ተደፍረው ፅንስ ለማቋረጥ ወደሆስፒታሉ የሄዱ 238 ሴቶች እና ልጃገረዶች መኖራቸውን ሲስተር ሙሉ ተናግረዋል።

ፅንስ ሲያቋርጡ በደም እና በሌላም የሰውነት ፈሳሽ መፍሰስ ምክንያት የተወሳሰበ የጤና እክል ያጋጠማቸው ፣ በኩላሊት መጎዳት ምክንያት ለዳይለሲስ ህክምና የገቡ ሴቶች መኖራቸውን ጨምረው ገልፀዋል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/Tigray-06-09

@tikvahethiopia
#EskinderNega

የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ የፓርቲው ፕሬዘዳንት እና እጩ የሆኑት እስክንድር ነጋ በአዲስ አበባ ቃሊቲ ከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ቤት ውስጥ ታስረው የሚገኙበት ሁኔታ ከፍተኛ ስጋት እንደፈጠረበት አመልከተ።

የአቶ እስክንድር ነጋ አያያዝ ሲከታተል መቆየቱን የገለፀው ባልደራስ ፥ በተለይ ከግንቦት 27 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ ቀድሞ ታስረውበት ከነበረው "ዋይታ" ተብሎ ከሚጠራው ዞን በደረሰባቸው የሰብዓዊ በደል ምክንያት 8ኛ ዞን ተብሎ ወደሚጠራው ቦታ እንዲዘዋወሩ ተደርጓል ብሏል።

አቶ እስክንድር አሁን ታስረውበት ባለበት ቦታ በእስረኞች የደህንነታቸው ሁኔታ፣ አደጋ ላይ እንደወደቀ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ማረሚያ ቤቱ ድረስ በመሄድ ለማረጋገጥ እንደቻሉ ፓርቲው ገልጿል።

አቶ እስክንድር እየገጠማቸው ያለውን የደህንነት አደጋ፣ ማረሚያ ቤቱ ሆነ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕጉ እያወቁ መፍትሄ ለመስጠት ባለመፈለጋቸው አዝኛለሁ ብሏል ባልደራስ።

ያንብቡ : https://telegra.ph/Balderas-06-09

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

የጉራጌ ልማትና ባህል ማህበር በአዲስ አበባ ክ/ ከተሞች ሲያከናውን የቆየውን የልማትና ባህል ኮንፈረንስ ማጠቃለያ ፕሮግራም በወዳጅነት ፓርክ እየተካሄደ ይገኛል።

በዚህ ፕሮግራም ላይ ይገኛሉ ተብለው ያልተጠበቁት የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል።

ከመድረኩ ላይ እንደተሰማው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በስራ ጫና ምክንያት በቦታው ይገኛሉ ተብሎ ያልተጠበቀ ነበር ነገር ግን በድንገት በመገኘት ለፕሮግራሙ ተሳታፊዎች መልዕክት አስተላልፈዋል ፤ ከፕሮግራሙ አዘጋጆችም ስጦታ ተበርክቶላቸዋል።

@tikvahethiopia
የሀዋሳ ታቦር ተራራ በባለሃብቶች እንዲለማ ለማድረግ እየተሰራ ነው ተባለ።

የሀዋሳ ልዩ መለያ የሆነው 'ታቦር ተራራ' ባላሀብቶች መዋዕለ ነዋያቸውን የሚያፈሱበትና የኢንቨስትመንት የስበት አካል እንዲሆን እይተሰራ መሆኑን የከተማይቱ ም/ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ተናግረዋል።

ምክትል ከንቲባው፥ የታቦር ተራራ ባለሃብቶች እንዲያለሙትና "ገበታ ለሀገር" ፕሮጀክትን ሚስተካከል ልማት የሚከናወንበት ስፍራ እንዲሆን እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል።

ሀዋሳ የመላው ኢትዮጵውያን ከተማ ከመሆን አልፋ የቱሪስቶች መዳረሻ በመሆኗ ሰፊ የኢንቨስትመንት ሥራ በማከናወን ሀገርን ተጠቃሚ ማድረግ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።

ምክትል ከንቲባው፥ ታቦር ተራራን ጨምሮ በሃዋሳ አቅራቢያ የሚገኙ ሃብቶችን ሥራ ላይ የማዋል ብርቱ ጥረት መጀመሩን ጠቁመው በቀጣይ ዘርፈ ብዙ ስራዎች እንደሚከናወኑ ገልፀዋል። #EPA

@tikvahethiopia
#Huawei

The Ministry of Science and Higher Education and Huawei have signed an agreement aimed at talent cultivation for the development of ICT industry, and the nurturing of highly skilled labor.

The two parties agreed to work on Huawei ICT Competition expected to bring 1,000 students from 39 universities to compete for the national prize.

Know more about and register for the ICT Competition: https://cutt.ly/Fnebwt5
Post 2
"ትግራይ ውስጥ ሰዎች በረሃብ እየሞቱ ነው" - ዴቪድ ባስሌ

በተባበሩት መንግስታት የዓለም የምግብ ፕሮግራም (WFP) ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ባስሌ በጦርነት በትግራይ ክልል ውስጥ ሰዎች በረሃብ #እየሞቱ መሆኑን በይፋዊ የትዊተር ገፃቸው ላይ አሳውቀዋል።

"ጊዜው እያለቀ ነው ያሉት" ባስሌ ፤ የሰብአዊ ድጋፍ ተደራሽነትን ከፍ ለማድረግ እና አደጋን ለመከላከል ያልተገደበ እቅስቃሴ ሊኖር ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።

አሁኑኑ ሁሉም ወገኖች በዚህ ላይ ቁርጠኝነትን በማሳየት ጥሩ ውጤት ማምጣት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

ትላንትና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተ.መ.ድ) ዋና ጸሃፊ አንቶንዮ ጉተሬዝ በርካታ የኢትዮጵያ ትግራይ ክልል አካባቢዎች ረሃብ አፋፍ ላይ መሆናቸውን መገራቸውን ይታወሳል።

@tivahethiopia