ኤርትራ የባይደንን አስተዳደር ወቀሰች።
የኤርትራ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ትግራይ ክልል ውስጥ ላለው ጦርነት ላለፉት 20 ዓመታት የትግራይ ሕዝብ ነፃነት ግንባርን ሲደግፉ የቆየ ያሉትን የአሜሪካ መንግስት አስተዳደር ተጠያቂ ማድረጉን APን ዋቢ አድርጎ ዶቼ ቨለ አስነብቧል።
በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ለሚካሄደው ጦርነት ኤርትራን ተጠያቂ ማድረጉም መሠረተ ቢስ ነው ሲሉ የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኡስማን ሳሌህ መግለጫ ሰጥተዋል።
ኡስማን ሳሌህ ትናንት ሰኞ ለተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት በፃፉት እና በምክር ቤቱ በተሰራጨዉ ደብዳቤ የፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር በክልሉ ጣልቃ በመግባት እና በማስፈራራት «ተጨማሪ ግጭትን እና አለመረጋጋትን ያስከትላል» ሲሉ ከሰዋል።
የአሜሪካው አሶሽየትድ ፕሬስ «በግምት ስድስት ሚሊዮን ሕዝብ ይኖርበት ከነበረዉ የትግራይ ክልል በጦርነቱ ምክንያት አንድ ሦስተኛውን አካባቢዉን ለቅቆ ሸሽቶአል፤ በሺዎች የሚቆጠሩ በጦርነቱ እንደተገደሉም ይገመታል። በአሁኑ ወቅት የመንግሥት ወታደሮች ለበርካታ ግፎች ተጠያቂ ናቸው ከሚባሉት ከጎረቤት ኤርትራ ወታደሮች ጋር በትብብር ላይ ናቸዉ» ሲል ስለመፃፉ ዶቸ ቨለ አስነብቧል።
@tikvahethiopia

#AntonioGuterres #Tigray
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተ.መ.ድ) ዋና ጸሃፊ አንቶንዮ ጉተሬዝ በርካታ የኢትዮጵያ ትግራይ ክልል አካባቢዎች ረሃብ አፋፍ ላይ መሆናቸው ተናገሩ፡፡
ዋና ጸሃፊው የትግራይ ሁኔታ በዚህ ከቀጠለ እጅግ አስከፊ ወደ ሆነ ደረጃ መሸጋገሩ አይቀሬ ነው ሲሉ አሳስበዋል፡፡
የተጋረጠውን የረሃብ አደጋ ለመግታት ሰብአዊ እርዳታ ማዳረስ እንዲሁም በቂ ፈንድ ማድረግ እንደሚያስፈልግም ዋና ጸሃፊው በትዊተር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልእክት አስታውቋል፡፡
"አሁን የሚከናወኑ ተግባራት ለበርካታ ሰዎች የመኖርና አለመኖር ጉዳይ መሆናቸውን መረዳት ተገቢ ነው"ም ነው ያሉት የተ.መ.ድ ዋና ጸሃፊ አንቶንዮ ጉተሬዝ፡፡
የጉተሬዝ ትግራይን የተመለከተ መግለጫ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በትግራይ ያሉ የግጭቱ ተዋናዮች ተኩስ እንዲያቆሙና ያልተገደበ የስብአዊ እርዳታ ተደራሽነት እንዲኖር ጥሪ እያደረገ ባለበት ወቅት መሆኑን አል ኣይን በድረገፁ አስነብቧል።
የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ቢሮ/ኦቻ/ እየተካሄደ ባለው ግጭት ሳቢያ በትግራይ ያለው የሰብዓዊ ቀውስ አሳሳቢ መሆኑን እና በኢትዮጵያ ከ1970ዎቹ ወዲህ ከፍተኛ የረሀብ አደጋ እንዳንዣበበ ባለፈው ሳምንት አሳትውቋል።
#AlAIN

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሰኔ 1 ቀን 1997 ዓ/ም !
" ኢህአዴግ " ስልጣን ከያዘ በኃላ ለ3ተኛ ጊዜ የተካሄደውን #የ1997ቱ ሀገር አቀፋዊ ምርጫ ተከትሎ በተፈጠረው ቀውስ ሳቢያ ሰኔ 1/1997 በመንግስት የተገደሉ ዜጎች ዛሬ 16ኛ ዓመት መታሰቢያቸው ነው።
በወቅቱ "ኢህአዴግ" ይህን መሰሉ አንባገነናዊ ተገባር የፈፀመው ስልጣኑን ለማስጠበቅ ፣ ስልጣኑን የሚያስጠብቀውም በመሳሪያ ኃይል እንጂ በህዝብ ድምፅ እንዳልሆነ የተቀናቃኝ ፖለቲካ ኃይሎች በተለያየ ጊዚያት ተናግረዋል።
ሰኔ 1 ቀን 1997 በግፍ በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች የተገደሉ ዜጎች ለነፃነት፣ ለዴሞክራሲ፣ ለፍትህ፣ ለሀገራዊ አንድነት ዋጋ የከፈሉ እንደሆኑ ይነገርላቸዋል፤ በየዓመቱም በዚህ ቀን ይታሰባሉ።
ፖለቲከኞች ፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾ ይህን የሰኔ 1 ቀን 1997 ዓ.ም ክስተት ለሁሉም ትምህርት የሚሰጥ እና መቼም ቢሆን ሊደገም የማገባው ብዙ ትምህርትም ሰጥቶ ያለፈ እንደሆነ ይናግራሉ።
በወቅቱ (ሰኔ 1 ቀን 1997 ዓ.ም) በግፍ የተገደሉ ፣ የቆሰሉ፣ ለእስርና እንግልት የተዳረጉ ዜጎች ኢትዮጵያን ያስተዳደር በነበረው "ኢህአዴግ" በሚባለው ፓርቲ ወቅት ሲሆን ፓርቲው ከዓመት በፊት በኢትዮጵያ ምድር ህልውና እንዳይኖረው ተደርጎ፣ ከስሟል።
በውስጡ የነበሩ ድርጅቶችም ከአንዱ (#ህወሓት) በቀር አንድ ላይ ተዋህደው ውህድ ፓርቲ ፈጥረው ኢትዮጵያን እያስተዳደሩ ነው።
Video Credit : Biniyam Hirut

የዓለም አቀፍ ዜና አውታሮች ድረገፆች ተቋረጡ።
ዓለም አቀፍ የዜና አውታሮች የሆኑት የፋይናንሻል ታይምስ ፣ የኒው ዮርክ ታይምስ እና የብሉምበርግ ኒውስን ጨምሮ የሌሎችም የዜና አውታሮች ድረገፆች አገልግሎታቸው ተቋረጠ።
የCNN እና የፈረንሳይ ሌሞንዴ ድረገፆችም 4 ሰዓት አካባቢ የስህተት ምልክት ታይቶባቸዋል። አልጀዚራ ድረገፅም ተመሳሳይ ችግር ገጥሞት ነበር።
የብሪታኒያው ዘጋርዲያን በድረገፁና በአፕሊኬሽኑ ላይ ችግር ገጥሞት እንደነበረ ገልጿል ሌሎች የብሪታኒያ የዜና አውታሮች ድረገፆች ወዲያው መስራት አቁመው ነበር።
በርከት ባሉት ዓለም አቀፍ ዜና አውታር ድረገፆች ላይ ምን እንደተፈጠረ እና ለምን እንደተቋረጡ ለጊዜው አልታወቀም።
#አልጀዚራ

የጀርመን ድጋፍ ለኢትዮጵያ :
ጀርመን 8.5 ሚሊዮን ዩሮ በኢትዮጵያ በግጭትና በአየር ንብረት ለውጥ ለተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች ህይወትን ለመታደግ ድጋፍ አድርጋለች።
የተባበሩት መንግስታት የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) ከጀርመን ህዝብ 8.5 ሚሊዮን ይሮ በኢትዮጵያ በግጭት እና በአየር ንብረት ለውጥ ለተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች ህይወትን ለመታደግ ያደረገዉን መዋጮ አወድሷል።
የተጠቀሰዉ ገንዘብ ከ2021 እስከ 2023 ዓ.ም ድረስ የሚሰጥ ሲሆን ድጋፉ ጀርመን ለምስራቅ አፍሪቃ ቀጠና በምታደርገዉ የገንዘብ ድጋፍ አካል ዉስጥ የተካተተ ነዉ።
ይህ ከጀርመን ህዝብ የተገኘዉ ርዳታ በትግራይ የዓለሙ የምግብ ፕሮግራም «WFP» የአስቸኳይ የምግብ እና የተመጣጠነ ምግብ ከሚሰጠዉ ድጋፍ ጋር የተያያዘ ነዉ።
ልገሳዉ እስከ 2.1 ሚሊዮን ሕዝብ የአስቸኳይ ጊዜ ርዳታ ምላሽን ለመስጠት አስተዋፅዖ ያደርጋል ተብሎአል።
በትግራይ ክልል በአጠቃላይ 5.2 ሚሊዮን ህዝብ ወይም ከጠቅላላው የትግራይ ህዝብ 91 በመቶ የሚሆነው አካባቢዉ ላይ በሚታየዉ ግጭትና ጦርነት ምክንያት አስቸኳይ የምግብ ርዳታን ፈላጊ ነዉ።
ልገሳዉ በተጨማሪ በሃገሪቱ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ለስደተኞች በሚሰጠዉ ርዳታ እና በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ውስጥ በከፍተኛ የአየር ንብረት መዛባት ለተጎዱ ማህበረሰቦች ሕይወት አድን እና ሕይወትን የሚቀይር የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ ርዳታን ለማድረስ ያለመ ነዉ።
የዓለም የምግብ ድርጅት (WFP) እስከ ዓመቱ መጨረሻ በትግራይ ክልል ርዳታዉን ለማዳረስ 203 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ያስፈልገዋል። ከዚህ በተጨማሪ በሚቀጥሉት ስድስት ወራት በሶማሌ ክልል የሚደረገውን የምግብ ርዳታ ሥራ ለማካሄድ ተጨማሪ 97 ሚሊዮን ዶላር ይፈልጋል።
መረጃው የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ነው።

TIKVAH-ETHIOPIA
የዓለም አቀፍ ዜና አውታሮች ድረገፆች ተቋረጡ። ዓለም አቀፍ የዜና አውታሮች የሆኑት የፋይናንሻል ታይምስ ፣ የኒው ዮርክ ታይምስ እና የብሉምበርግ ኒውስን ጨምሮ የሌሎችም የዜና አውታሮች ድረገፆች አገልግሎታቸው ተቋረጠ። የCNN እና የፈረንሳይ ሌሞንዴ ድረገፆችም 4 ሰዓት አካባቢ የስህተት ምልክት ታይቶባቸዋል። አልጀዚራ ድረገፅም ተመሳሳይ ችግር ገጥሞት ነበር። የብሪታኒያው ዘጋርዲያን በድረገፁና በአፕሊኬሽኑ…
#Update
ዛሬ ለሠዓታት ተቋርጠው የነበሩት ዓለም አቀፍ የዜና አውታር ተቋማት ድረገፆች (የብሉምበርግ ኒውስ ፣ የፋይናንሻል ታይምስ ፣ የኒውዮርክ ታይምስ) መስራት ጀምረዋል።
ከዓለም ዜና አውታር ድረገፆች በተጨማሪ የዩናይትድ ኪንግደም (UK) መንግስት ድረገፅ gov.uk ፣ አማዞን መገበያያ፣ ሬዲት ተመሳሳይ ችግር ገጥሟቸው ነበር።
ችግሩ እጅግ በበርካታ የዓለም ክፍል የታየ ቢሆንም በርሊን ውስጥ ድረገፆቹ ሳይቋረጡ ሲሰሩ ነበር ብሏል ዘጋርዲያን።
አሁን ላይ ለሰዓታት ያህል ተቋርጠው የነበሩት ድረገፆች መስራት የጀመሩ ሲሆን ለችግሩ መፈጠር ምክንያቱ "ፋስትሊ" የተሰኘው የኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢ ድርጅት ነው ሲል ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።
" ፋስትሊ " ኩባንያ ድረ ገጾችን ከጥቃቶች የመከላከል አግልግሎት በመስጠት እንዲሁም በድረ ገጾች ላይ የጎብኚዎች ቁጥር ሲበዛ የድረ ገጹ ፍጥነት እንዳይቀንስ በመሥራት ይታወቃል።
የአንድ ኩባንያ ችግር የበርካታ ድረ ገጾች አገልግሎት እንዲቋረጥ ማድረጉ መነጋገሪያ ሆኗል።
ኢሴት በተሰኘ ኩባንያ ውስጥ የሳይበር ደህንነት ባለሙያ የሆኑት ጄክ ሞር፤ በርካታ መሠረት ልማት ፈሰስ የተደረገባቸው ድረ ገጾች በአንድ ኩባንያ እጅ ላይ እንዲወድቁ ማድረግ አግባብ አይደለም ሲሉ ስለመናገራቸው ቢቢሲ ዘግቧል።

የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ አዲስ አበባ ገቡ።
የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ለይፋዊ ስራ ጉብኝት ነው አዲስ አበባ የገቡት።
ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
ፕሬዝዳንቱ በቆይታቸው ከኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ስራ ሃላፊዎች ጋር በሁለትዮሽና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።
@tikvahethiopia
የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ለይፋዊ ስራ ጉብኝት ነው አዲስ አበባ የገቡት።
ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
ፕሬዝዳንቱ በቆይታቸው ከኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ስራ ሃላፊዎች ጋር በሁለትዮሽና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።
@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ማክሮን በስራ ጉብኝት ላይ እያሉ በጥፊ ተመቱ።
የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን የስራ ጉብኝት ላይ እያሉ በጥፊ ተመቱ።
ፕሬዚደንቱ በደቡብ ምስራቅ ፈረንሳይ #ደሮም_ከተማ ጉብኝት በማድረግ ላይ እያሉ ነው በጥፊ የተመቱት።
ማክሮን በተከለለ አጥር ውስጥ የነበሩ ሰዎችን ሰላም ለማለት ጠጋ ሲሉ ነው ክስተቱ የተፈፀመው።
ፕሬዚዳንቱ በጥፊ ሲመቱ “ Down with Macron-ism ” የሚሉ ቃላት ይሰሙ ነበር።
ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ሁለት ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የፈረንሳይ ዜና አውታሮች ዘግበዋል።
Video Credit : AlexpLille

#GlobalPartnershipforEthiopia ግሎባል ፓርትነርሺፕ ፎር ኢትዮጵያ 850 ሚሊየን ዶላር ለመንግስት ገቢ ማድረጉን የኢትዮጵያ ኮሙዩኒኬሽን ባለሥልጣን አስታወቀ። 'ግሎባል ፓርትነርሺፕ ፎር ኢትዮጵያ' በኢትዮጵያ ውስጥ የግል የቴሌኮም ኦፕሬተርነት ዘርፍ ለመሳተፍ ጨረታ ማሸነፉ ይታወሳል። የኢትዮጵያ ኮሚኒኬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ኢ/ር ባልቻ ሬባ ፥ በጨረታ ሰነዱ በተቀመጠው…
#Update
በኢትዮጵያ መንግስት እና የቴሌኮም አገልግሎት ለማቅረብ ፍቃድ ባገኘው (ግሎባል ፓርትነርሺፕ ፎር ኢትዮጵያ) ጥምረት መካከል የፍቃድ ስምምነት ፊርማ ተካሄደ።
ኢትዮጵያ በቴሌኮም ዘርፍ እንዲሳተፍ በኬንያ ሳፋሪኮም ለሚመራ "ግሎባል ፓርትነርሽፕ ፎር ኢትዮጵያ" ለተሰኘ ጥምረት ፍቃድ መስጠቷ ይታወሳል።
የፊርማ ሥነ ሥርዓቱ የተከናወነው ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ እና የኬንያው ፕሬዝደንት ኡሁሩ ኬንያታ በተገኙበት መድረክ ላይ ነው።
የኢትዮጵያ ኮሙንኬሽን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ባልቻ ሬባ፤ ከቮዳኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ሻሚል ጆሱ፣ ከሳፋሪኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፒተር ኢድግዋ እንዲሁም ከሲሚቶሞ ዋና ስራ አስፈፃሚ ጋር ስምምነቱን ተፈራርመዋል።
ኩባንያው ጫረታውን ያሸነፈበትን 850 ሚሊዮን ዶላር ለመንግስት ገቢ ማድረጉን የኢትዮጵያ ከሚዩኒኬሽን ባለስልጣን መግለፁ ይታወሳል።
#ENA #BBC

#Ethiopia #COVID19
ኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ካደረገችው 4,426 የኮቪድ19 የላብራቶሪ ምርመራ 151 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል፤ ይህም አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር 273,175 አድርሶታል።
በ24 ሰዓት 7 ሰዎች ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን በአጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 4,220 ደርሷል።
የኮቪድ-19 ክትባት የተከተቡ ዜጎች 1,894,717 ደርሰዋል።

#MoSHE
የኢፌዴሪ ሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ የሚገኘው ደብዳቤ #ሀሰተኛ ነው አለ።
ዛሬ በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ ለደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ እንደተጻፈ የሚገልጽ ደብዳቤ በማህበራዊ ሚዲያዎች እየተዘዋወረ ነው።
ደብዳቤው “የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ስለመስጠት” የሚል አርዕስት ያለው ሲሆን ደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ የአማራ ተወላጅ ተማሪዎችን ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እውቅና ውጭ ምደባ ማካሄዱን እንዲያቆም የሚያስጠነቅቅ ይዘት አለው።
በዚህ ጉዳይ ላይ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶን ለ "ኢትዮጵያ ቼክ" በሰጡት ቃል ደብዳቤው ሀሰተኛ መሆኑ ተናግረዋል።
ሚኒስትሩ ፥ ደብዳቤው ተጻፈ በተባለበት የታሕሳስ ወር የ2012 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ገና መሰጠት አልተጀመረም ነበር ብለዋል።
በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ወደዚህ ዓመት የተሸጋገረው የ2012 ዓ.ም ፈተና ከካቲት 19 ጀምሮ እስከ መጋቢት 2 ቀን 2013 ዓ.ም የተሰጠ ሲሆን ውጤቱ ይፋ የተደረገው በመጋቢት ወር አጋማሽ እንደነበር አስታውሰዋል።
ሚኒስትሩ ፥ የተማሪዎች የዩኒቨርስቲ ምደባ በሚያዚያ ወር የተከነወነ መሆኑ በመግለፅ ደብዳቤው ተጻፈ በተባለበት ታሕሳስ ወር ምንም አይነት የተማሪዎች ምደባ እንዳልነበር አስረድተዋል።
ዶ/ር ሳሙኤል ደብዳቤውን እርሳቸው እንዳልጻፉት ገልጸዋል።
ዶ/ር ሳሙኤል በታህሳስ ወር የተማሪዎችን ምደባ የተመለከተ ደብዳቤ ሊጻፍ እንደማይችል አክለዋል።
ደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ ማምሻው በፌስቡክ ገጹ በለጠፈው አጠር ያለ መልዕክት “ዩኒቨርስቲያችንን በተመለከተ በማህበራዊ ሚዲያዎች የተሰራጩ ወሬዎች አሳሳችና የውሸት መሆናቸውን እንገልጻለን” ብሏል።
#ኢትዮጵያቼክ