TIKVAH-ETHIOPIA
ኢትዮጵያ በሁለት ቀን ብቻ 743 ዜጎቿን ከሳዑዲ አረቢያ አስወጥታለች። ኢትዮጵያ ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ በችግር ላይ ያሉ ወገኖችን በስፋት ወደ ሀገራቸው መመለስ ከጀመረች ወራት ተቆጥረዋል። አሁንም ዜጎችን ወደሀገራቸው የመመለስ ስራ ተጠባክሮ የቀጠለ ሲሆን በሁለት ቀን ብቻ 743 ዜጎቿን ወደሀገራቸው መልሳለች። አገራቸው ከተመለሱት ከ 743 ኢትዮጵያውያን መካከል 334ቱ #ከሪያድ ትላንት የተመለሱ ሲሆኑ…
#Update
ኢትዮጵያ ዛሬ ተጨማሪ 311 ዜጎቿን ከሳዑዲ አረቢያ በማስወጣት ወደሀገራቸው መለሰች።
311ዱ ኢትዮጵያውያን ከጂዳ ነው ወደሀገራቸው የተመለሱት።
ኢትዮጵያ አጠናክራ በቀጠለችው በችግር ላይ የሚገኙ ዜጎቿን ከሳዑዲ አረቢያ የማስወጣት ስራ ከቀናት በፊት በሁለት ቀን ውስጥ 743 ዜጎች ወደሀገራቸው መመለሳቸው መገለፁ አይዘነጋም።
ፎቶ : ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
@tikvahethiopia

#Ethiopia #COVID19
ኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ካደረገችው 5,709 የኮቪድ19 የላብራቶሪ ምርመራ 347 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል፤ ይህም አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር 272,632 አድርሶታል።
በ24 ሰዓት 8 ሰዎች ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን በአጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 4,193 ደርሷል።
የኮቪድ-19 ክትባት የተከተቡ ዜጎች 1,865,958 ደርሰዋል።

ትራምፕ ከፌስቡክ እና ኢንስታግራም ለ2 ዓመት ታገዱ።
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከፌስቡክና ከኢንስታግራም ለሁለት ዓመታት መታገዳቸውን ፌስቡክ ኩባንያ ዛሬ አስታወቀ።
ፌስቡክ እገዳው መጀመሪያ ከተጣለበት እ.አ.አ ጥር 7 ጀምሮ ለሁለት ዓመት ተግባራዊ የሚሆን ነው ብሏል።
ኩባንያው ፕሮቶኮሎቹን በሚጥሱ ህዝብ በሚከተላቸው አካላት ላይ “ከፍተኛ ቅጣቶችን” ተግባራዊ እያደረገ መሆኑን አክሏል።

"ጀዋር መሀመድ የጥርስ ሀኪም ጋር እንዲወሰዱ ፍርድ ቤቱ ካዘዘ ከሁለት ወር በላይ ሆኖታል፤ ግን አልወሰዷቸውም" - ቤተሰቦቻቸው
አቶ ጀዋር መሀመድ የጥርስ ሀኪም ጋር እንዲወሰዱ ፍርድ ቤት ካዘዘ ከሁለት ወር በላይ ቢሆንም አሁንም ድረስ እንዳልተወሰዱ ቤተሰቦቻቸው አሳውቁ።
"በዚህ ምክንያት በጣም ታምሞ ምግብ እየበላ አይደለም" ሲሉ ቤተሰቦቹ አሳውቀዋል።
አክለውም ፥ እነ አቶ በቀለ ገርባም "ጀዋር መሀመድ ህክምና አግኝቶ መብላት እስኪችል እኛም አንበላም" በማለት የረሀብ አድማ መጀመራቸውን ተናግረዋል።
"ምግብ ለመቀበል ፈቃደኛ ባለመሆናቸው የወሰድንላቸውን ምግብ ይዘን ተመልስናል፡፡ ጀዋር መሀመድ ወደ ሆስፒታል እስኪወሰድ ድረስ ምግብ አንቀበልም ብለዋል።" ሲሉ አሳውቀዋል።
መረጃው ከኦሮሞ የፖለቲካ እስረኞች ጠበቆች ቡድን ነው የደረሰን።

የአፍሪካ ህብረት ምርጫ ታዛቢ ቡድኖች አ/አ ገብተዋል።
የአፍሪካ ህብረት ከኢትዮጵያ መንግሥት በደረሰው ጥያቄ መሠረት የአጭር እና የረዥም ጊዜ የምርጫ ታዛቢዎች ቡድኖችን መላኩን የህብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማህማት ማስታወቃቸውን ቪኦኤ ዘግቧል።
ሰኔ 14 የሚካሄደውን አጠቃላይ ብሄራዊ ምርጫ የሚታዘቡት ከተለያዩ የህብረቱ አባል ሃገሮች የተውጣጡ 8 አባላት የሚገኙበት የረዥም ጊዜ ክትትል ቡድን ሐሙስ እና ረቡዕ አዲስ አበባ መግባቱን የአፍሪካ ህብረት ባወጣው የፕሬስ መግለጫ አመልክቷል።
ቡድኑ በኢትዮጵያ ቆይታው ቁልፍ የሚባሉ የምርጫ ሂደቱ ክፍሎች ላይ ቅኝት እንደሚያደርግና ትንተና እንደሚሰጥ ተጠቁሟል።
በተለይ የፖለቲካውን አየር፣ የምርጫውን የህግ ማዕቀፍ፣ የምርጫ ዝግጅቱን ውጤታማነትና ግልፅነት እንዲሁም የአስተዳደርና የመገናኛ ብዙኃን ነፃነትንና በመላ ሂደቱ ውስጥ ለተሣትፎ መብቶች መከበር የሚሰጠውን ትኩረት ጨምሮ የዘመቻውን አካሄድ ሁኔታ እንደሚያካትት አስታውቋል።
የረዥም ጊዜ ታዛቢ ቡድኖች በሃገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች እንደሚሰማሩ የአፍሪካ ኅብረት ጠቁሞ ምርጫው ሊካሄድ ወደ አንድ ሳምንት ሲቀር ብርካታ የአጭር ጊዜ ታዛቢ ቡድኖች አዲስ አበባ እንደሚገቡ ገልጿል።
ኢትዮጵያ ውስጥ የሚሠማራው የአፍሪካ ህብረት ታዛቢ ተልዕኮ በህብረቱ ድንጋጌዎች መሠረት በምርጫው ሂደት ላይ መረጃ የመሰብሰብና የመተንተን መብትና ችሎታ እንዳለው የፕሬስ መግለጫ በተለያዩ ጊዜዎች የወጡና የተፈረሙ ውሎችና መግለጫዎችን አጣቅሶ አስታውቋል።
ምንጭ፦ ቪኦኤ

ትራምፕ ከፌስቡክ እና ኢንስታግራም ለ2 ዓመት ታገዱ። የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከፌስቡክና ከኢንስታግራም ለሁለት ዓመታት መታገዳቸውን ፌስቡክ ኩባንያ ዛሬ አስታወቀ። ፌስቡክ እገዳው መጀመሪያ ከተጣለበት እ.አ.አ ጥር 7 ጀምሮ ለሁለት ዓመት ተግባራዊ የሚሆን ነው ብሏል። ኩባንያው ፕሮቶኮሎቹን በሚጥሱ ህዝብ በሚከተላቸው አካላት ላይ “ከፍተኛ ቅጣቶችን” ተግባራዊ እያደረገ መሆኑን አክሏል።…
"... በሚቀጥለው ጊዜ ኋይት ሀውስ 'ስገባ' በእሱ ጥያቄ ከማርክ ዙከንበርግ እና ባለቤቱ ጋር የእራት ግብዣ ብሎ ነገር አይኖርም" - ዶናልድ ትራምፕ
የቀደሞው የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከፌስቡክ እና ኢንስታግራም ለሁለት ዓመት መታገዳቸውን ተከትሎ መግለጫ አውጥተዋል።
ዶናልድ ትራምፕ ባወጡት መግለጫ "የፌስቡክ ውሳኔ 75 ሚሊዮን ሰዎችን ጨምሮ ለመረጡን ብዙ ሰዎች ስድብ ነው ..." "በዚህ ሳንሱር እና ማፈን እንዲቀጥሉ ሊፈቀድላቸው አይገባም። በመጨረሻም እኛ እናሸንፋለን። ሀገራችን ከእንግዲህ ይህን በደል መሸከም አትችልም!" ብለዋል።
ትራምፕ በሰጡት መግለጫ በፌስቡክ መስራች ላይ ትችት ሰንዝረዋል።
በቀጣዩ የአሜሪካ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ ብርቱ ተፎካካሪ ለመሆን ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን የገለፁት ትራምፕ ዳግም ወደ ኋይት ሀውስ ሲመጡ ከማርክ ዙከርበርግ እና ባለቤታቸው ጋር እራት እንደማይኖራቸው ተናግረዋል።
ትራምፕ ፥ "በሚቀጥለው ጊዜ በኋይት [ስገባ] በእሱ ጥያቄ ከማርክ ዙከንበርግ እና ባለቤቱ ጋር የእራት ግብዣ ብሎ ነገር አይኖርም። ሁሉም ነገር ሥራ ይሆናል!" ብለዋል።
የፌስቡክ ውሳኔ ትራምፕ ከ2024 ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በፊት ወደ መድረኩ እንዲመለሱ ያስችላቸዋል።
ከ ፌስቡክ በተጨማሪ ትራምፕ በጥር ወር ካፒቶል ሂል ረብሻ ምክንያት ከትዊተር፣ ዩቲዩብ፣ ስናፕቻት፣ ትዊች እና ከሌሎች ማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች ታግደዋል።
ምንጭ፦ ቢቢሲ

#Happening_now
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በኤፍራታና ግድም ወረዳና አጣዬ ከተማ አስተዳደር እና በኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ነዋሪዎች መካከል ተፈጥሮ የነበረውን ግጭት #በእርቅ_ለመፍታት ያለመ የሰላም ውይይት መካሄድ ጀምሯል።
የሰላም ውይይቱ እየተካሄደ የሚገኘው በአጣዬ ከተማ ነው።
የእርቀ ሰላም ውይይቱን ሌተናል ጀኔራል ደስታ አብቼ እየመሩት ይገኛሉ።
በተጨማሪ የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ አህመድ ያሲን ፣ የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ጀማል ሀሰን እና የአጣዬ ከንቲባ አቶ አገኘሁ መክቴ ከአወያዩቹ መካከል ይገኛል።
የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ነዋሪዎችና አመራሮች ፣ የአጣዬ ከተማ ነዋሪዎችና አመራሮች እየተሳተፉበት እንደሚገኙ ከሰሜን ሸዋ ዞን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአዲስ ተማሪዎች ምዝገባ ሰኔ 1 እና ሰኔ 2/2013 (በኦንላይን) መሆኑን ገለፀ።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2013 ትምህርት ዘመን በመደበኛ የዲግሪ ትምህርት መርሃ-ግብር በትምህርት ሚ/ር መስፈርት መሠረት አዲስ የተመደቡ ተማሪዎች ሰኔ 01 ቀን 2013 ዓ.ም እና ሰኔ 02 ቀን 2013 ዓ.ም በ https://portal.aau.edu.et በመጠቀም #የኦንላየን ምዝገባ እንዲያከናውኑ አሳሰበ።
ተማሪዎቹ በተመደቡበት የዩኒቨርስቲ ካምፓስ ሪፖርት የሚያደርጉት ሰኔ 19 እና ሰኔ 20 2013 ዓ.ም እንደሚሆን እና የገጽ ለገጽ ትምህርት ሰኞ ሰኔ 21 ቀን 2013 እንደሚጀምር ተገልጿል።
መረጃው የአዲሰ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ጽ/ቤት ነው።
ተጨማሪ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጉዳዮችን እንዲሁም ጥሪዎችን ቲክቫህ እና ካርድ በጋር በሚሰሩበት t.iss.one/joinchat/RYD_4tbNBwRoKR2h (በቲክቫህ ኢትዮጵያ የዩኒቨርሲቲ ገፅ ማግኘት ይቻላል።
@tikvahethiopia @tikvahuniversity

ለ2014 በጀት ዓመት 561.7 ቢሊዮን ብር ረቂቅ በጀት ፀደቀ።
ዛሬ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለ 2014 በጀት ዓመት የ 561. 7 ቢሊዮን ብር ረቂቅ በጀት አፅድቋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገፃቸው ላይ በጀቱ ምርታማነትን ለማሳደግ ትልቅ ትኩረት የሰጠ መሆኑንና ፤ ከ10 ዓመቱ መሪ የልማት ዕቅድ ጋር የተጣጣመ እንደሚያደርገው ገልፀዋል።

በጉራፈርዳ ወረዳ 6 የጸጥታ ኃይሎች በታጣቂዎች ተገደሉ።
6 የደቡብ ክልል ልዩ ኃይል አባላት በቤንች ሸኮ ዞን በሚገኘው ጉራፈርዳ ወረዳ ውስጥ ትላንት በታጣቂዎች ተገድለዋል።
የልዩ ኃይል አባላቱ የተገደሉት በወረዳው ስር ባለው ወጀምታ ቀበሌ ነው።
"ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ድረገፅ" ቃላቸውን የሰጡት የጉራፈርዳ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሲሳይ ሻሎም ፥ ጥቃት የተፈጸመባቸው የደቡብ ክልል ልዩ ኃይል አባላት፤ በወጀምታ ቀበሌ ልዩ ስሙ ሰንበሊጥ በተባለ ቦታ ባለ ካምፕ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።
8 የልዩ ኃይል አባላት፤ ትላንት ከጠዋት 2 ሰዓት ገደማ፤ አንድ የካምፑን ሰራተኛ አጅበው ውሃ ለመቅዳት ወደ ወንዝ ሲሄዱ ተኩስ እንደተከፈተባቸው አስረድተዋል።
በጥቃቱ ስድስት የልዩ ኃይል አባላት ሲገደሉ አብሯቸው የነበረው የካምፑ ሰራተኛ ጉዳት ደርሶበት ህክምና ላይ ይገኛል ብለዋል።
ለአጀባ ከተሰማሩት የጸጥታ ኃይሎች ውስጥ 2ቱ ምንም ጉዳት እንዳልደረሰባቸውም ሲሉ ገልፀዋል።
ተጨማሪ ያንብቡ : ethiopiainsider.com/2021/3451/
(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

የደቡብ ክልል የ8ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 28 እስከ ሰኔ 30 ይሰጣል።
በደቡብ ክልል የ8ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 28 እስከ 30 2013 ዓ.ም እንደሚሰጥ የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡
ቢሮው አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ የተማሪዎች መመዝገቢያ ቅጽ እንግሊዝ ሀገር ከሚገኝ DRS ድርጅት ግዢ እንደተፈጸመና ቢሮ መግባቱን አሳውቋል።
የቅጽ አሟላሉን በተመለከተ በክልሉ ለሚገኙ ሁሉም የፈተና ክፍል ኃላፊዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠቱን ቢሮው ገልጿል።
በክልሉ የሚገኙ 16 ዞኖችና 7 ልዩ ወረዳዎች ፎርሙን ወስደው በመንግስትና በግል ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎችን እያስሞሉ ነው ተብሏል።
የፈተና ዝግጅት ተጠናቆ የህትመት ስራ እየተሰራ ይገኛል።
ፈተናው በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች ከሰኔ 28 እስከ ሰኔ 30/2013 ይሰጣል ተብሏል። #SRTA

ኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ካደረገችው 4,505 የኮቪድ19 የላብራቶሪ ምርመራ 173 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል፤ ይህም አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር 272,805 አድርሶታል።
በ24 ሰዓት 8 ሰዎች ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን በአጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 4,201 ደርሷል።
የኮቪድ-19 ክትባት የተከተቡ ዜጎች 1,878,367 ደርሰዋል።

ቴምቲዮፔ ባሎጉን ጆሹዋ ህይወታቸው አለፈ።
ታዋቂው ናይጄሪያው የሃይማኖት ሰባኪ ቴምቲዮፔ ባሎጉን ጆሹዋ ትናንትና ህይወታቸው አለፈ።
ቴምቲዮፔ ባሎጉን ጆሹዋ ወይም በተለምዶ ቲቢ ጆሹዋ ማረፋቸውንም ይፈዊ በሆነው ፌስቡክ ገፃቸውም ላይ "አምላክ አገልጋዩን ቲቢ ጆሹዋን ወደቤቱ ወስዷል" በሚልም ሰፍሯል።
ስመ ጥር የሆኑት የኢቫንጀሊካን ሃይማኖት ሰባኪ በትናንትናው ዕለት የቤተክርስቲያን ፕሮግራማቸውን ከጨረሱ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ምሽት ላይ ማረፋቸው ተገልጿል።
በተከታዮቻቸው ዘንድ የነብይነትን ማዕረግ ያገኙት ቲቢ ጆሹዋ በአህጉሪቷ ውስጥ ተፅእኖ መፍጠር ከቻሉ የኢቫንጀሊካል ሰባኪዎች አንዱ ናቸው ።
በአፍሪካ ውስጥም ያሉ ታዋቂ ፖለቲከኞችንም በተከታይነት ማፍራት ችለዋል።
"ቸርች ኦፍ ኦል ኔሽንስ" የሚባል የእምነት ተቋምን የመሰረቱ ሲሆን እንዲሁም በቴሌቪዥንም በሚያደርጓቸው ስብከቶችም በርካታ የእምነቱ ተከታይ ምዕመናንን ማፍራት ችለዋል።
በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በሌጎስ የሚያደርጓቸውን ሳምንታዊ የአገልግሎት ስርዓት ይከተላሉ ነበር።
ቴምቲዮፔ ባሎጉን ጆሹዋ በ57 ዓመታቸው ነው ህይወታቸው አለፈ።