#Update
ሚቀጥለው ሳምንት የአሜሪካ እንዲሁም የአውሮፓ ህብረት ሀገራት የሰብዓዊ ዕርዳታ እና ልማት አመራሮች በትግራይ ሁኔታ ላይ እንደሚመክሩ ተሰምቷል።
ውይይቱ በቀጥታ ስርጭት የሚተላለፍ እንደሆነ ይጠበቃል።
ስብሰባው በትግራይ ክልል ባለው የሰብዓዊ ቀውስና ሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ዙሪያ የጋራ መግባባት ለመፍጠር እና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) ማዕቀፍ ውስጥ አስቸኳይ ሰብዓዊ ዕርዳታ ላይ ወሳኝ ርምጃዎች እንዲወሰዱ ለማድረግ ያለመ መሆኑ ተነግሯል።
ምንጭ፦ devex.com
@tikvahethiopia

#Ethiopia #COVID19
ኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ካደረገችው 4,376 የኮቪድ19 የላብራቶሪ ምርመራ 249 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል፤ ይህም አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር 272,285 አድርሶታል።
በ24 ሰዓት 7 ሰዎች ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን በአጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 4,185 ደርሷል።
የኮቪድ-19 ክትባት የተከተቡ ዜጎች 1,853,259 ደርሰዋል።

በማህበራዊ ሚዲያ ላይ አበበች ጎበና አርፈዋል ተብሎ እየተሰራጨ ያለው ዜና የተሳሳተ ነው።
አበበች ጎበና በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሕክምናቸውን እየተከታተሉ ሲሆን ጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ፡፡
(ዶክተር ያሬድ አግደው)
@tikvahethiopia
አበበች ጎበና በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሕክምናቸውን እየተከታተሉ ሲሆን ጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ፡፡
(ዶክተር ያሬድ አግደው)
@tikvahethiopia
#Oromia #TookkumaanMisoomaaf
የኦሮሚያ ልማት ማህበር (ኦልማ) በአዲስ አበባ ከተማ በወረዳ እና በክፍለ ከተማ ደረጃ ሲያከናውን የነበረውን ኮንፈረንስ ማጠቃለያ መርሃ ግብር በአንድነት ፓርክ በማድረግ ላይ ነው።
በመርሃ ግብሩ ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ ጠ/ ሚ ዐቢይ አህመድ ፣ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው፣ ም/ከንቲባ አዳነች አቤቤ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በመሳተፍ ላይ ናቸው።
እንዲሁም ኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት በማድረግ ላይ ያሉት የአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዚደንት ተገኝተዋል።
ለልማት ማህበሩ አስተዋጽኦ ያበረከቱ አካላት በዝግጅቱ ላይ እውቅና እንደሚሰጣቸው ይጠበቃል።
#አዲስሚዲያቴትዎርክ

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነ የበረራ ቁጥር ኢቲ 3905 አውሮፕላን ናይጄሪያ ሌጎስ ደርሶ ካረፈ በኋላ ወደ መቆሚያ ስፍራው እየሄደ ሳለ ከመንገዱ ወጥቶ እንደነበር ተገለጸ።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ እንዳደረጋገጠው ወደ ካርጎ የተቀየረው የመንገደኞች ቦይንግ 777-300 ግዙፍ አውሮፕላን ካጋጠመው ከስተት በኋላ ወደ ሥራ ተመልሷል።
አውሮፕላኑ ከአዲስ አበባ ወደ ናይጄሪያ ሌጎስ ከተማ ጭነት ይዞ ከበረረ በኋላ በሌጎስ ኤርፖርት አርፎ ወደ መቆሚያው እየሄደ ሳለ የአውሮፕላኑ በስተግራ በኩል ያለው ጎማ ከአስፓልቱ መውጣቱን አየር መንገዱ አስታውቋል።
በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የተለቀቀ ተንቀሳቃሽ ምስል የአውሮፕላኑ በስተግራ በኩል ያለው ጎማ ጭቃ ውስጥ ገብቶ አሳይቷል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ክስተቱን ተከትሎ ባወጣው መግለጫ አውሮፕላኑ ምንም አይነት ጉዳት ሳያጋጥመው በመብረር ወደ አዲስ አበባ መመለሱን አስታውቋል።
አየር መንደጉ የሌጎስ ኤርፖርት ሠራተኞች ላደረጉት ድጋፍ ምስጋናውን አቀርቧል።
አውሮፕላኑ ከአስፓልቱ እንዲወጣ ያደረገው ምክንያት ምን እንደሆነ በአየር መንገዱ መግለጫ ላይ አልተመለከተም።
ፍላይትግሎባል' ድረገጽ ክስተቱ ባጋጠመበት ወቅት በአውሮፕላን ማረፊያው የነበረው የሜትሮሎጂ መረጃ ምንም አይነት አስቸጋሪ የአየር ጠባይ መኖሩን አላሳየም ማለቱን ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።
ምንጭ፦ ቢቢሲ
Video Credit : GoldMyne

#GlobalPartnershipforEthiopia
ግሎባል ፓርትነርሺፕ ፎር ኢትዮጵያ 850 ሚሊየን ዶላር ለመንግስት ገቢ ማድረጉን የኢትዮጵያ ኮሙዩኒኬሽን ባለሥልጣን አስታወቀ።
'ግሎባል ፓርትነርሺፕ ፎር ኢትዮጵያ' በኢትዮጵያ ውስጥ የግል የቴሌኮም ኦፕሬተርነት ዘርፍ ለመሳተፍ ጨረታ ማሸነፉ ይታወሳል።
የኢትዮጵያ ኮሚኒኬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ኢ/ር ባልቻ ሬባ ፥ በጨረታ ሰነዱ በተቀመጠው ድንጋጌ መሰረት 14 ቀናት ባልሞላ ጊዜ ድርጅቱ ጨረታውን ያሸነፈበትን ዋጋ ለመንግስት ገቢ ማድረግ እንደሚጠበቅበት አስረድተዋል።
በዚህ መሰረት ግሎባል ፓርትነርሺፕ ፎር ኢትዮጵያ ያሸነፈበትን 850 ሚሊየን ዶላር ለመንግስት ገቢ ማድረጉን ኢንጂነር ባልቻ ገልጸዋል።
ጨረታውን ያሸነፈው ድርጅት ለጨረታው ማስኬጃ ከእንግሊዝና አሜሪካ የፋይናንስ ተቋማት 500 ሚሊየን ዶላር ብድር አግኝቷል።
ዳይሬክተሩ ሁለተኛውን የቴሌኮም ኦፕሬተር ጨረታ ለማውጣት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ለኢዜአ ተናግረዋል።

ቦረና ወረዳ ውስጥ ህገወጥ የጦር መሳሪያ ተያዘ።
በደቡብ ወሎ ዞን ቦረና ወረዳ ህገወጥ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር መዋሉን የወረዳው ፖሊስ ገለፀ።
በወረዳው 033 እንድራስ ቀበሌ በሚባለው ቦታ አንድ ከደሴ ወደ ቦረና መካነሰላም በመጓዝ ላይ የነበረ ኮድ 3 የሠሌዳ ቁጥር " 20509 አ.ማ " የህዝብ ማመላለሻ በተለምዶ አባ ዱላ መኪና ፦
- 3 ሺ 441 የብሬን ጥይት፣
- 95 ፍሬ የፍሌ ቨር ሽጉጥ ጥይት ፣
- 3 ቺች አውቶማቲክ መሳሪያ
- 2 ተጨማሪ የችቺ ካዝና ፣
- 1 የክላሽ ካዝና በካርቶን እና በካልሲ በመቋጠር በሻንጣ በማድረግ ሲዘዋወር የነበረን ህገወጥ የጦር መሳሪያ በተደረገ የፓትሮል እንቅስቃሴ ከነተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን ገልጿል።
ፖሊስ ጉዳዩን እያጣራሁ ነው ብሏል።
መረጃው የቦረና ወረዳ ኮሚኒኬሽን ነው።

#WorldBank #Ethiopia
ኢትዮጵያና የአለም ባንክ የ10 ነጥብ 89 ቢሊየን ብር የብድር ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

የብድር ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ እና የዓለም ባንክ የኢትዮጵያ፣ የሱዳን፣ የደቡብ ሱዳንና የኤርትራ ተጠሪ ኦስማን ዲዮን ማፈራረማቸውን ኤፍ ቢ ሲ አስነብቧል።

TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update
የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ከፍተኛ አመራሮች ፤ፕሬዚዳንት አቶ እስክንድር ነጋ ፣ አስቴር ስዩም ፣ ስንታየሁ ቸኮል እና አስካለ ደምሌ የዕጩነት የማረጋገጫ እንዳገኙ ፓርቲው ከደቂቃዎች በፊት በይፋዊ ፌስቡክ ገፁ አሳውቋል።

በአማራ ክልል የ8ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 23 - ሰኔ 25/2013 ዓ.ም እንደሚሰጥ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ገለጸ፡፡
ቢሮ ይህን የገለፀው ዛሬ የ2013 ዓ/ም የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ፈተናን አስመልክቶ መግለጫ በሰጠበት ወቅት ነው።
መግለጫዉን የሰጡት የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኀላፊ ሙላው አበበ ሲሆኑ የ2013 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሰኔ 25/2013 ዓ.ም እንደሚሰጥ ተናግረዋል።
በክልሉ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ለተማሪዎቻቸው ፈተናዉን የሚወስዱበትን ቀን እንዲያሳውቁ ምክትል ኀላፊው አሳስበዋል።
በትምህርት ወደኋላ የቀሩ ተማሪዎች የማካካሻ ትምህርት እንዲሰጣቸው፤ ተማሪዎች የፈተናውን ቀን አውቀው ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ነው አቶ ሙላው የገለጹት።
ፈተናው በሚሰጥበት ቀንም ኾነ የፈተናው የጥያቄ ወረቀት የማጓጓዝ ሂደቱ ሰላማዊ እንዲኾን በየዘርፉ የሚገኙ የጸጥታ አካላት ኀላፊነታቸዉን እንዲወጡ ጠይቀዋል።
በአማራ ክልል ከ420 ሺ በላይ ተማሪዎች የ8ኛ ክፍል ፈተናን እንደሚወስዱ መታወቁን የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዘግቧል።