"...በመደበኛ ስራዬ ላይ ነው የምገኘው" - ዶ/ር ሙሉ ነጋ
ትግራይን በጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚነት እየመሩ የሚገኙት ዶ/ር ሙሉ ነጋ ከስልጣን መነሳታቸውን የሚግልፁ መረጃዎች በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጩ ይገኛሉ።
ዶክተር ሙሉ ነጋ ፥ "ወሬውን አልሰማሁም" ሲሉ ለአል ዓይን /AlAIN ድረገፅ ቃላቸውን ሰጥተዋል።
አሁን ላይ በመደበኛ ስራቸው ላይ የሚገኙ መሆናቸውን የተናገሩት ዋና ሥራ አስፈጻሚው ከኃላፊነታቸው ስለመነሳታቸው የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ተናግረዋል፡፡
ዶ/ር ሙሉ ፥ “አሁን ላይ በሥራ ስብሰባ ላይ እገኛለሁ” ሲሉ ነው የገለፁት።
“የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተ ሙሉ ነጋ ከኃላፊነት ተነስተዋል” በሚል በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የተለቀቀውን መረጃ በርካቶች እየተቀባበሉት ይገኛሉ ስለጉዳዩ እውነትነት ኃላፊነቱን በሰጣቸው የመንግስት አካል የተባለ ነገር የለም።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
የብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ እና የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የበላይ ጠባቂ ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ሥርዓተ ቀብር ተፈፅሟል።
የብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ ቀብር ስነሥርዓት የተፈፀመው ዛሬ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ነው።
በስነስርዓቱ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ፣ ብፁአን ሊቃነ ጳጳሳት ፣ የቤተ እምነት ተወካዮች እንዲሁም ወዳጅ ዘመዶቻቸው ተገኝተው ነበር። - EOTC TV

ፔካ ሀቪስቶ ኢትዮጵያ ገብተዋል።
በፊንላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፔካ ሀርቪስቶ የተመራው የአውሮፓ ህብረት ልዑክ አዲስ አበባ ገብቷል።
ፔካ ሀርቪስቶ ወደኢትዮጵያ ከመምጣታቸው ከሰዓታት በፊት በትዊተር ገፃቸው ፥ በቆይታቸው በአዲስ አበባ እንዲሁም ትግራይ ክልል ጉብኝት እንደሚያደርጉ ገልፀው ነበር።
በትግራይ ክልል ያለው የሰብዓዊ ቀውስም ፈጣን መፍትሄ እንደሚፈልግ ፅፈዋል።
ዛሬ ኢትዮጵያ ከገቡ በኃላ ከኢትዮጵያ ፕሬዜዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ጋር ተገናኝተው መምከራቸው ታውቋል። ፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ስለትግራይ ሁኔታ ገለፃ አድርገውላቸዋል።
የፕሬዜዳንት ፅህፈት ቤት እንዳሳወቀው ልዑካን ቡድኑ ፦
- በትግራይ ያለውን የዕርዳታ እና የሰብዓዊ መብት አያያዝ ይመለከታል።
- በታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ይወያያል።
- ወደ ትግራይ በመሄድ ያለው ሁኔታ የማየት እቅድ አለው።
ቡድኑ በቆይታው የተረዳውን እና የደረሰበትን ድምዳሜ በሚያዚያ ወር አጋማሽ ለህብረቱ የሚኒስትሮች ስብሰባ እንደሚያቀርብ አስታውቋል።
የልዑካን ቡድኑ ከሁለት ወራት በፊት ለተመሳሳይ ዓላማ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ እንደነበር የፕሬዜዳንት ፅህፈት ቤት አስታውሷል።

የተከዜ የውሃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ሥራ ጀመረ።
ለወራት ያህል ከአገልግሎት ውጪ ሆኖ የቆየው የተከዜ የውሃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ዛሬ ሥራ መጀመሩን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ።
የኃይል ማመንጫ ጣቢያው ከብሔራዊ የኃይል ቋት (ግሪድ) ጋር የሚገናኝበት መስመር በመቋረጡ ምክንያት ነበር ኃይል ማመንጨት አቁሞ የነበረው።
ከተከዜ - መቐለ በተዘረጋው የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ሲደረግ የነበረው ጥገና በመጠናቀቁ ዛሬ ቀን ከ7:18 ሰዓት ጀምሮ በጊዜያዊነት ከሲስተም ጋር ሳይገናኝ ራሱን በራሱ እየተቆጣጠረ (Isolated mode) ኃይል መስጠት መጀመሩ ተገልጿል።
በአሁኑ ሰዓት ጣቢያው ካሉት አራት ዩኒቶች መካከል በሁለት ዩኒቶች እስከ 108 ሜጋ ዋት ድረስ ኃይል እየሰጠ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ገልጿል።
@tikvahethiopia

የትግራይ አብዛኛዎቹ ከተማዎች በጨለማ ተውጠዋል። ከትላንት ሀሙስ ከሰዓት ጀምሮ በትግራይ መቐለን ጨምሮ በበርካታ ከተሞች የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጧል። የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን በአብዛኞቹ የትግራይ ክልል ከተሞች የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡን ገልፀው ፥ "ኤሌክትሪክ የተቋረጠው ከመሆኒ 40 ኪ.ሜ ላይ ወደ መቐለ ባለ መስመር ላይ ሊሆን እንደሚችል ነው የተቋሙ…
#Tigray
ካለፈው ሃሙስ ከሰዓት ጀምሮ በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የኤክትሪክ አገልግሎት ዳግም መጀመሩ ተገልጿል።
የኤሌክትሪክ አገልግሎቱ ዳግም የጀመረው "ከተከዘ የኃይል ማመንጫ" ወደ መቐለ የሚሄደው መስመር ተጠግኖ የተከዜ ኃይል ማመንጫ ስራ በመጀመሩ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል።
ቀደም ሲል ከአላማጣ - መኾኒ - አሸጎዳ - መቐለ የሚሄደው መስመር ላይ ባጋጠመ ችግር ምክንያት በትግራይ ኤሌክትሪክ ተቋርጦ እንደነበረ መገለፁ አይዘነጋም።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT

#Attention😷
ባለፉት 24 ሰዓት 33 ሰዎች በኮቪድ-19 መሞታቸው ሪፖርት ተደረገ።
በተመሳሳይ ከተደረገው 8,187 የላብራቶሪ ምርመራ 2,163 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
ትላንት 2,179 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
በአጠቃላይ 221,544 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 3,058 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 166,135 ሰዎች አገግመዋል።
የፅኑ ታማሚዎች ቁጥር በእጅጉ ጨምሮ 906 ደርሷል።
#Purpose

የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ነገ ይፋ ይደረጋል።
የ2013 ዓ/ም የተማሪዎች የዩኒቨርስቲ መግቢያ 'መወሰኛ ነጥብ' ነገ መጋቢት 30/2013 ዓ.ም ይፋ እንደሚደረግ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ማምሻውን አስታውቋል።
@tikvahethiopia
የ2013 ዓ/ም የተማሪዎች የዩኒቨርስቲ መግቢያ 'መወሰኛ ነጥብ' ነገ መጋቢት 30/2013 ዓ.ም ይፋ እንደሚደረግ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ማምሻውን አስታውቋል።
@tikvahethiopia
"...የመራጮች ምዝገባ ያልተጀመረው የምርጫ ቁሳቁስ ባለመቅረቡ ነው" - ወ/ሮ ወለላ መብራት
በአማራ ክልል እስካሁን ድረስ የመራጮች ምዝገባ ያልተጀመረባቸው ቦታዎች መኖራቸውን በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ማህበራዊ ዘርፍ አማካሪና የክልሉ የምርጫ ጉዳይ ኦፊሰር ወ/ሮ ወለላ መብራት አስታውቀዋል።
የመራጮች ምዝገባ በአገር አቀፍ ደረጃ መጋቢት 16 ቀን 2013 ዓ.ም መጀመሩ ቢገለፅም ፥ በክልሉ ያልተጀመረባቸው ቦታዎች እንዳሉ ያመለከቱት ወ/ሮ ወለላ ፥ የመራጮች ምዝገባ ያልተጀመረው የምርጫ ቁሳቁስ ባለመቅረቡ እንደሆነ አመልክተዋል።
ለአብነትም ለአዲስ አበባ ከተማ ቅርብ ነው ወደሚባለው ሰሜን ሸዋ እንኳን ቁሳቁሱ የደረሰው ገና ከትናንት በስቲያ ነው ያሉት ወ/ሮ ወለላ ፤ እንዲያም ሆኖ ቁሳቁሶቹን ከምርጫ ክልሎች ወደየምርጫ ጣቢያዎቹ በማድረሱ በኩል የክልሉ መንግሥት እገዛ እያደረገ ነው ብለዋል።
የክልሉ መንግሥት በክልሉ ያለውን የምርጫ ቦርድ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቁሳቁሶቹን በፍጥነት እንዲያደርስ ግፊት በማድረግ ላይ እንደሚገኝ የጠቆሙት ኃላፊዋ፣ መዘግየቱ በምዝገባው ቀን ላይ ጫና ሊፈጥር እንደሚችል ስጋታቸውን ገልጸዋል።
ከዚህ ውጪ በክልሉ ያጋጠመ ችግር እንደሌለ ጠቁመዋል። በክልሉ ቀደም ብሎ የምርጫ ቁሳቁስ የደረሰባቸው አካባቢዎች ጥቂት ቢሆኑም ምዝገባው መጀመሩን አስታውቀዋል።
በክልሉ ከሰላም ጋር በተያያዘ አብዛኛው አካባቢ ችግር የለም፤ ያሉት ወ/ሮ ወለላ ፥ "ምርጫ ቦርድ ስጋት ናቸው የሚባልባቸው ቦታዎች ላይ መረጃ ስጡን ባሉን መሰረት ጥያቄውን ለሚመለከተው የሰላምና ደህንነት ቢሮ ሰጥተናል ፤ ችግሩ ይፈታል ብለን እናስባለን ሲሉ" ለኢፕድ ተናግረዋል።
More : https://telegra.ph/Election2013-04-08

#TGDCA
የቱርክ ተመራቂዎች የልማት እና የበጎ አድራጎት ማኅበር (TGDCA) ከአሶሳ አስተዳደር ጋር ተባብረው ከ1 ሺህ 210 ለሚሆኑ አቅመ-ደካማ የህብረተሰብ ክፍሎች የምግብ ነክ ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጋቸውን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ኮሚኒኬሽን አሳውቋል።
ድጋፉ በተለያዩ ችግሮች ውስጥ ለሚገኙና የኢኮኖሚ አቅም ለሌላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች የተሠራጨ ሲሆን ፣ 1 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር የሚገመት የዳቦ ዱቄት፣ ሩዝ እና የምግብ ዘይት መሆኑም ተገልጿል፡፡
የቱርክ ተመራቂዎች የልማትና በጎ አድራጎት ማኅበር (TGDCA) እንዳሳወቀቅ የገንዘብ ድጋፉ የተገኘው ከ "ሃሰን ኢንተርናሽናል" ከተባለ በጎ አድራጊ ድርጅት ነው።
በቀጣይ በአሶሳ ዙሪያ ለሚገኙ 1 ሺህ 800 አቅመ-ደካማ የህብረተሰብ ክፍሎች 2 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብር የሚገመት ድጋፍ ለማድረግ ዝግጅት መደረጉን ድርጅቱ አሳውቋል።

የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ነገ ይፋ ይደረጋል። የ2013 ዓ/ም የተማሪዎች የዩኒቨርስቲ መግቢያ 'መወሰኛ ነጥብ' ነገ መጋቢት 30/2013 ዓ.ም ይፋ እንደሚደረግ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ማምሻውን አስታውቋል። @tikvahethiopia
የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ነጥብ ይፋ ሆነ።
የ2013 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት በዛሬው ዕለት ይፋ ሆኗል።
በተፈጥሮ ሳይንስ ለወንድ 380 ሲሆን ለሴት ደግሞ 368 መሆኑ ተገልጿል፡፡
በማህበራዊ ሳይንስ ለወንድ 370 ሲሆን ለሴት 358 መሆኑ ይፋ ተደርጓል።
#MoSHE
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የ2013 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት በዛሬው ዕለት ይፋ ሆኗል።
በተፈጥሮ ሳይንስ ለወንድ 380 ሲሆን ለሴት ደግሞ 368 መሆኑ ተገልጿል፡፡
በማህበራዊ ሳይንስ ለወንድ 370 ሲሆን ለሴት 358 መሆኑ ይፋ ተደርጓል።
#MoSHE
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የከፍተኛ ትምህርት ተቋም የመግቢያ ነጥብ :
በተፈጥሮ ሳይንስ ፦
- ለወንድ 380 ፤ ለሴት 368
- ለታዳጊ ክልሎች ደግሞ ለወንድ 368 ለሴት 358
- ለአካል ጉዳተኞች ለወንድ 350 ፤ ለሴት 345
- ለአርብቶ አደሮች አካባቢዎች 358
- በትግራይ እና መተከል ለወንድ 358 ፤ ለሴት 350
በማህበራዊ ሳይንስ ፦
- ለወንድ 370 ፤ ለሴት ደግሞ 358
- ለታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ለወንድ 358 ፤ ለሴት 348
- ለአካል ጉዳተኞች ለወንድ 340፤ ለሴት 335
- በትግራይና መተከል ለወንድ 348 ፤ ለሴት 340
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
በተፈጥሮ ሳይንስ ፦
- ለወንድ 380 ፤ ለሴት 368
- ለታዳጊ ክልሎች ደግሞ ለወንድ 368 ለሴት 358
- ለአካል ጉዳተኞች ለወንድ 350 ፤ ለሴት 345
- ለአርብቶ አደሮች አካባቢዎች 358
- በትግራይ እና መተከል ለወንድ 358 ፤ ለሴት 350
በማህበራዊ ሳይንስ ፦
- ለወንድ 370 ፤ ለሴት ደግሞ 358
- ለታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ለወንድ 358 ፤ ለሴት 348
- ለአካል ጉዳተኞች ለወንድ 340፤ ለሴት 335
- በትግራይና መተከል ለወንድ 348 ፤ ለሴት 340
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#MoSHE
በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች መደበኛ ባልሆነ ፕሮግራም ማለትም (በክረምት ፣ በማታ ፣ በሳምንት መጨረሻ ፣ የርቀት ፣ በበይነ መረብ) እና በግል ተቋማት በመደበኛ እና መደበኛ ባልሆኑ አማራጮች ለመማር አነስተስተኛው የመቁረጫ ነጥብ ፦ ለወንዶች 330 እና ከዚያ በላይ ለሴቶች ደግሞ 320 እና ከዚያ በላይ እንዲሆን ተወስኗል።

በግል ተቋማት የህክምና መስኮችን ለመማር አነስተኛው የመቁረጫ ነጥብ (ከተፈጥሮ ሣይንስ መስክ ለሚመጡ ብቻ) ለሁለቱም ፆታ 450ና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ መሆን ይጠበቅባቸዋል።

በ2013 ዓ/ም 147,640 (88,153 ወንድ ፤ 59,487 ሴት) ተማሪዎች ምደባ ያገኛሉ። እነዚህ ተማሪዎች በ46ቱ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ቅበላ ይደረግላቸዋል።
በተጨማሪም በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ከተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት መስክ ወደ ማህበራዊ ሳይንስ የትምህርት መስክ መቀየር እንደሚቻል MoSHE አሳውቋል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopia