TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Update

በደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ "ደጊት ጥብቅ ደን" ላይ መጋቢት 17/2013 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ የተከሰተው የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር መዋሉን ወረዳው አስታውቋል።

በእሳት አደጋው ከአራት (4) ሄክታር በላይ በሆነ መሬት ላይ የሚገኝ ጥብቅ ደን ላይ ጉዳት መድረሱ ተገልጿል።

ከመልክዓ-ምድራዊ አቀማመጡ አመቺ አለመሆንና በደኑ ውስጥ ተቀጣጣይ ሳር መብዛቱ የማጥፋት ስራውን ፈታኝ አድርጎት እንደቆየ ተገልጿል።

እሳቱ እንዲጠፋ የወገል ጤና ከተማ ወጣቶች እና የአካባቢው ማህበረሰብ ከፍተኛ አስተዋዕፆ በማድረጋቸው ምስጋና ቀርቦላቸዋል።

የእሳቱ መንስኤ ገና እየተጣራ ቢሆንም ከ"ከሰል ማክሰል" ጋር የተያያዘ ሊሆን እንደሚችል ተጠቁሟል። #ENA

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በትግራይ 10 ሺ ያህል ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ፈተና አልወሰዱም።

በትግራይ ክልል የ2012 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ፈተና ተፈታኝ የነበሩ እና ለፈተና መቀመጥ ያልቻሉ 10,000 ያህል ተማሪዎች ከሁለት ወር በኋላ ይፈተናሉ ተብሏል።

በትግራይ ክልል የ2012 ተፈታኝ የሆኑ ከ12,000 በላይ ተማሪዎች ለፈተና እንዲቀመጡ ቢጠበቅም የተፈተኑትን ግን 2,130 ብቻ መሆናቸውን የሃገር አቀፍ ትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ዲላሞ ኦቶሬ ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ገልፀዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ ፥ "መፈተን ከነበረባቸው ከ12,000 በላይ ተማሪዎች በክልሉ ባለው የሰላም ችግር ምክንያት የተፈተኑት 2,130 ብቻ በመሆናቸው ቀሪዎቹ 10,000 ያህል ተፈታኞች #ከ2013_ተፈታኞች ጋር እንዲፈተኑ ተወስኗል" ብለዋል።

የ2013 ዓ.ም ፈተና ከሁለት ወር በኋላ ይሰጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 የሃገር አቀፍ ትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች ኤጀንሲን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#እጅግ_ከፍተኛ_ጥንቃቄ😷

ባለፉት 24 ሰዓት 16 ሰዎች በኮቪድ-19 መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል።

በተመሳሳይ ከተደረገው 8,296 የላብራቶሪ ምርመራ 1,976 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

ትላንት 1,435 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

በአጠቃላይ 204,521 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 2,841 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 156,625 ሰዎች አገግመዋል።

በአሁን ሰዓት 828 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#Purpose
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
አቶ አታኽልቲ ስልጣናቸውን ለቀቁ።

የመቐለ ከተማ ጊዜያዊ ከንቲባ አታኽልቲ ኃይለስላሴ በገዛ ፍቃዳቸው ስልጣን መልቀቃቸውን አዲስ ስታንዳርድ ድረገፅ ዘግቧል።

አቶ አታኽልቲ ፥ ስልጣናቸውን በገዛ ፍቃዳቸው እንደለቀቁ ለድረገፁ በሰጡት ቃል አረጋግጠዋል።

ስልጣናቸውን ሊለቁ የቻሉበትን ዝርዝር ምክንያት ነገ ያሳውቃሉ ተብሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በትግራይ ሊዘረፍ የነበረ የእርዳታ እህል ተያዘ።

ትግራይ ክልል ሊዘረፍ የነበረ 430 ኩንታል የእርዳታ እህል በህበረተሰቡ ትብብር እና ጥቆማ የትግራይ ፖሊስ ኮሚሽን መያዙ ተሰማ።

ከትግራይ መዲና መቐለ ወደ ምዕራባዊ ዞን 'ሰለክለካ' የእርዳታ እህል ከጫኑ 16 መኪናዎች አንዱ ከህግ ውጭ ወደተባለው ቦታ ሳያደርስ በመቐለ ከተማ የእርዳታ እህሉን ለማራገፍ ሙከራ ሲያደርግ ህብረተሰቡ ባደረገው ጥቆማ ተይዟል።

እንደ ትግራይ ፖሊስ መረጃ፥መኪናው ንብረትነቱ የ "ትራንስ ኢትዮጵያ" ሲሆን የታርጋ ቁጥሩ ኮድ 3-9672 የተሳቢው ቁጥር 2848 ኢት ነው።

መኪናው ወደ ሰለክለካ 430 ኩንታል እህል ጭኖ እንዲሄድ የነበረ ሲሆን ነገር ግን በመቐለ ከተማ ሰሜን ክ/ከተማ በሚገኝ የትራንስ መጋዘን በማስገባት ከደላሎች እና ነጋዴዎች ጋር በመነጋገር እህሉ ሊሸጥ ነበር የታቀደው፤ ይህን ለማድረግ በህገወጥ መንገድ 2 ሲኖትራክ መኪና ወደ መጋዘኑ እንዲገቡ በማድረግ እህሉ በሲኖትራክ ተጭኖ ሊወጣ ሲል እዛ በነበረ ጥበቃ እና ህበረተሰብ ጥቆማ ፌዴራል ፖሊስ ተቆጣጥሮታል።

ትግራይ ፖሊስ ፥ እህሉን ሊሸጥ የነበረው የትራንስ ኢትዮጵያ ሹፌር ነው ያለ ሲሆን ከሱ ጋር የተባበሩ የሲኖ ትራክ ሹፌሮች እና እህሉን ሲጭኑ የነበሩ 6 ጫኝ እና አውራጆች ነበሩ ብሏል።

ሹፌሩ ያመለጠ ሲሆን ሌሎች የተያዙ አሉ፤ ያልተያዙትን ለመያዝ ክትትል እየተደረገ ነው ተብሏል።

የትግራይ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ከሌሎች አካላት ጋር በመሆን ለእርዳታ በሚውሉ እህሎች ላይ የሚፈፀም ስርቆት እና ማጭበርበር የሚከታተል እና ወደህግ የሚያቀርብ ግብረኃይል ማቋቋሙን ገልጿል።

በተጨማሪ የህዝቡን እህል በመስረቅ ላይ የተሰማሩ ዘራፊዎች ማንም አካል ወንጀል ፈፅሞ መደበቅ እንደማይችል ተገንዝበው ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አስጠንቅቋል።

@tikvahethiopia
አንድ የUNHCR ሰራተኛ ከኢትዮጵያ እንዲወጡ ተወሰነ።

የኢትዮጵያ መንግሥት ቅሬታ ያቀረበባቸው የተባባሩት መንግሥታት የስደተኞች ድርጅት ምክትል ተወካይ የሆኑት ማቲጂስ ሌ ሩቴ ድርጅቱ ከአገሪቱ እንዲወጡ መወሰኑ ተሰማ።

ምክትል ተወካዩ ሩቴ ላለፈው አንድ ዓመት ከሁለት ወር በኢትዮጵያ የድርጅቱ ምክትል ኃላፊ ሆነው በማገልገል ላይ የነበሩ ሲሆን መንግሥት ባቀረበባቸው ቅሬታ ምክንያት ተቋማቸው ከኢትዮጵያ አንስቶ ወደሌላ አገር እንዲዘዋወሩ ማድረጉን ቢቢሲ ከድርጅቱ ሠራተኞችና ከመንግሥት ምንጮች ተረድቻለሁ ብሏል።

የዜና ማሰራጨው ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው የዲፕሎማቲክ ምንጮች ተረዳሁኝ እንዳለው ፥ የመንግሥታቱ ድርጅት የስደተኞች ተቋም ከፍተኛ ኃላፊ የነበሩት ግለሰብን ጨምሮ ሌሎች የተቋሙ ሠራተኞች ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት በትግራይ ክልል ከተከሰተው ቀውስ ጋር በተያያዘ ቅሬታ ማቅረቡን ገልጸዋል።

ከከፍተኛ ባለስልጣኑ በተጨማሪም አንዲት ሴት የተቋሙ ሠራተኛ ሌላዋ ቅሬታ የቀረባበቸው ግለሰብ ሲሆኑ ግለሰቧ በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ድርጅት ውስጥ በከፍተኛ ኃላፊነት ላይ ያሉ መሆናቸው ታውቋል።

ከተቋሙ ሠራተኞችና ከሌሎች ምንጮች ቢቢሲ አደረኩኝ ማጣራት ግለሰቧ ተቋሙ በአገር ውስጥ ተፈናቃዮች ዙሪያ በሚሰራቸው ሥራዎች ላይ ከፍተኛ አስተባባሪ ናቸው። ባላቸው ኃላፊነትም በድርጅቱ አምስተኛ የስልጣን እርከን ላይ ያሉ ሰው ናቸው።

More : https://telegra.ph/BBC-03-31

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#TikvahFamilyBaboGambel

በትላንትና እለት በምዕራብ ወለጋ ዞን ባቦ ጋምቤል ወረዳ፣ ቦኔ ቀበሌ ውስጥ የተፈፀመው ጥቃት የበርካቶችን ህይወት ቀጠፈ።

የ "ሰዴቃ" ቲክቫህ አባላት ትላንት ምሽት 2:00 ላይ በርካታ ንፁሃን በሚያሳዝን ሁኔታ መገደላቸውን አሳውቀዋል።

ታጣቂዎቹ በከባድ እና አውቶማቲክ መሳሪያ ጭምር ነው ግድያ የፈፀሙት።

እስካሁን 28 ሰው የተቀበረ ሲሆን ወደ ጤና ተቋም ወደ 15 የሚደርስ ሰው ተወስዷል፥ የመትረፋቸው ነገር አጠራጣሪ ነው ብለውናል።

በርካቶች ጥቃቱን ሸሽተው ጫካ ውስጥ ተሸሽገው ነው ያደሩት።

የሚሰማን አካል ካለ ከአካባቢው መውጣት ነው የምንፈልገው ብለዋል።

በተጨማሪ አንድ የዛው አካባቢ ተወላጅ የሆነ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል በትላንቱ ጥቃት ሁሉም ጓደኞቹ እንደሞቱበት ተናግሯል።

አካባቢው ላይ እንዲህ አይነት ድርጊት እንደሚፈፀም ይታወቅ ነበር ያሉት አባላቶቻችን ከዚህ በፊት "ታጣቂዎች" አካባቢውን ለ7 ቀን ያህል ይዘውት ነበር ፥ ነገር ግን መንግስት ይሄን እያወቀ ምንም አይነት ጥበቃ ሊያደርግ አልቻለም ብለዋል።

ጉዳዩ ውስብስብ ያለ ሆኖብናል ሲሉ ገልፀዋል።

ከሰዎች ግድያ በተጨማሪ ቤቶችም ስለመቃጠላቸው አባላቶቻችን ገልፀዋል።

ትላንት ጥቃቱ ሲፈፀም ምንም አይነት የፀጥታ ኃይል ያልደረሰ ሲሆን ዛሬ ከነጋ ነው ቦታው ላይ የደረሰው። አሁን ላይ የወረዳው ሚሊሻ፣ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል፣ እና የአካባቢው ፖሊስ ቦታው ላይ ይገኛል።

የክልሉ መንግስት በንጹሃን ዜጎች ላይ ጥቃት መፈፀሙን እና ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ዜጎች መገደላቸውን ዛሬ ባወጣው መግለጫ አረጋግጧል።

ጥቃቱ በፈጸሙ የተወሰኑ ኃይሎች ላይ እርምጃ ወስጃለሁ ብሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#NEAEA

ትላንት የ2012 ዓ/ም ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ መደረጉ ይታወቃል።

የፈተናው ውጤት በተመለከተ አንዳንድ ተማሪዎች እንዲሁም የተማሪ ወላጆች ቅሬታ እንዳላቸው እየገለፁ ሲሆን ይህንን ቅሬታም የሚመለከተው አካላ ምላሽ እንዲሰጥበት ጠይቀዋል።

ቅሬታ ማስተናገጃ መድረክም እንዲፈጠር ጥሪ አቅርበዋል። በተለይም በክልል ያሉ ነዋሪዎች።

የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘና እና የፈተናዎች ኤጀንሲ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ውጤትን አስመልክቶ ቅሬታ ካላቸው/አቤቱታ ካላቸው ከሰኞ መጋቢት 27 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ ማቅረብ እንደሚችሉ አሳውቋል።

በኤጀንሲው ዋና መስሪያ ቤት ደጃፍ ላይ የተለጠፈው ማስታወቂያ ግን በክልል ያሉ ነዋሪዎች እንዴት ቅሬታ እንደሚያቀርቡ ያለው ነገር የለም ፤ ተከታትለን እናሳውቃለን።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#TikvahFamilyBaboGambel በትላንትና እለት በምዕራብ ወለጋ ዞን ባቦ ጋምቤል ወረዳ፣ ቦኔ ቀበሌ ውስጥ የተፈፀመው ጥቃት የበርካቶችን ህይወት ቀጠፈ። የ "ሰዴቃ" ቲክቫህ አባላት ትላንት ምሽት 2:00 ላይ በርካታ ንፁሃን በሚያሳዝን ሁኔታ መገደላቸውን አሳውቀዋል። ታጣቂዎቹ በከባድ እና አውቶማቲክ መሳሪያ ጭምር ነው ግድያ የፈፀሙት። እስካሁን 28 ሰው የተቀበረ ሲሆን ወደ ጤና ተቋም…
የታጠቁ ሰዎች ?

ከጊዜ ወደ ጊዜ የታጠቁ ኃይሎች በንፁሃን ላይ የሚያሰርሱት ጥቃት ይቆማል ተብሎ በትዕግስት ቢታለፍም ሁኔታው ግን እየከፋ እና እየተለመደ መጥቷል ሲሉ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት በላኩት የፅሁፍ እንዲሁም የድምፅ መልዕክት ገልፀዋል።

ለመሆኑ የታጠቁ ኃይሎችን ማነው የሚያስታጥቃቸው ? ከየት ነው ትጥቅ የሚያገኙት ? ማነውስ ቀለብ የሚያቀርበው ? እንዴት ነው በነፃነት ሰላማዊ ሰዎች ያሉበት ቦታ ድረስ ገብተው ንፁሃንን የሚገድሉት የሚለው ጥያቄ መልስ ሊሰጠው ይገባል ብለዋል።

ምን ያህል የበዛ ታጣቂ ቢኖር ነው በየጊዜው የንፁሃን ህይወት የሚያልፈው ? እውነት የመንግስት የፀጥታ መዋቅር ይህን ማስቆም አቅቶት ነው ? የድህንነት ስራውስ ምን ያህል ዝቅተኛ ቢሆን ነው ብሎ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሆነ ዜጋ ሊጠይቅ ይገባል ብለዋል።

ጥቃት በደረሰባቸው የተለያዩ አካባቢዎች ያሉ የቲክቫህ አባላት ፥ መንግስት የዜጎቹ ሰላም ማስከበር ካልቻለ የተሻለ ቦታ እንዲሄዱ ማድረግ አለበት ሲሉ አሳስበዋል።

አብዛኛው ጊዜ የሚገደሉት ንፁሃን ፣ የፖለቲካ ተሳትፎ የሌላቸው ፣ ያልታጠቁ ፣ ሀገሪቱ ስላለችበት የፖለቲካ ሁኔታ በቅጡ የማየውቁ ፣ እራሳቸውን መከላከል የማይችሉ ሴቶች፣ ህፃናት ናቸው ብለዋል።

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ የት ደርሷል ?

By : EPA

- የኮርቻ ግዱቡ 99 በመቶ ደርሷል፤
- የጎርፍ ማስተንፈሻው ወይም ጎርፍ መከላከያ 97 በመቶ፤
- የኃይል ማመንጫዎች ግንባታ 84 በመቶ ተጠናቋል፤
- አጠቃላይ የሲቪል ስራው ዛሬ ላይ 91.4 በመቶ ተጠናቋል፤
- የኤሌክትሮ ሜካኒካልና የብረታ ብረት ስራዎች 54 በመቶ ተሰርቷል
- አጠቃላይ የህዳሴው ግድብ ግንባታው 79 በመቶ ደርሷል፤

ለግድቡ ከ2003 ዓ.ም እስከ መጋቢት/2013 የተሰበሰበ ገንዘብ መጠን ምን ያህል ነው ?

- ከሀገር ውስጥ ቦንድ ግዢና ልገሳ...13,762,030,021.64
- የዲያስፖራ ቦንድና ልገሳ...1,068,349,251.54
ልዩ ልዩ ገቢዎች… 333,454,551.80
- ጠቅላላ ድምር ... 15,163,833,824.98

ከሀምሌ 2012- መጋቢት 2013 የተሰበሰበ ገንዘብ ፦

- የአገር ውስጥ ቦንድ ሽያጭና ስጦታ ….1,322,448,847.53
- የውጭ አገር ዲያስፖራ ቦንድ ሽያጭና ስጦታ… 61,553,943.51
- በኢ/ኤ/ኃይል የስጦታ አካውንት ገቢ የሆነ /GERD LOCAL Grant… 10,750,690.98
- ከፒን ሽያጭ ገቢ የሆነ/… 392,750.00
- ከ8100 አጫጭር የሞባይል መልእክት አገልግሎት...88,764,422.00
- ጠቅላላ ድምር፡- 1,483,910,654.02

Video : Ethiopian Electric Power (Jul 28/2020)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጭር መረጃ ስለመስቀል አደባባይ ፕሮጀክት ፦

- ከ2.5 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት የተመደበለት ነው።

- ሶስት ክፍሎች ያካተተ ሲሆን አንደኛው የሁለት ደረጀ ህንፃ ወለል ግንባታ፣ ስማርት ፓርኪንግ እና የደረጃ ስራ እና 3.5 ኪ/ሜ እስከ ማዘጋጃ ቤት የሚደረስ የመንገድ ማስዋብ ስራ ያካተተ ነው።

- ፕሮጀክቱ ላለፉት 9 ወራት ለ24 ሰዓታት (ቀን እና ለሊት) ሲሰራ ነበር።

- 6 ግዙፍ የማስታወቂያ ስክሪኖች ተገጥመዋል።

- ከ200 በላይ መፀዳጀ፣ መታጠቢያ ቤቶችን አሉት።

- ኢትዮጵያን የሚገልፁ፣ የሚችሉ ቅርሶች እንዲታዩ፣ እንዲሸጡ እና ፣ እንዲታወቁ ለማድረግ ትልልቅ ሱቆች ከላይ በኩል ተገንብተዋል።

- 45 ሱቆች ከታች ተገንብተዋል።

- ከ1 ሺህ 400 በላይ ተሽከርካሪዎችን ማስተናገድ የሚያስችል የመኪና ማቆሚያ አሉት።

- 6 ሊፍቶች እና ቬንትሌተሮች ተገጥመዋል፤ ዘመናዊ የፓርኪንግ ማስተናገጃዎች አሉት።

- WiFI ኢንተርኔት አገልግሎትም በአካባቢው እንዲሰጥ ተደርጎ ነው እየተሰራ ያለው።

- ፕሮጀክቱ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዶ/ር ኬይረዲን በኮቪድ-19 ህይወታቸው አለፈ።

የኢትዮያጵያ መድኃኒት እና ምግብ ቁጥጥር ባለስልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ዶ/ር ኬይረዲን ረዲ ህይወታቸው ማለፉን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

ዶ/ር ኬይረዲን ህይወታቸው ያለፈው በኮቪድ-19 ምክንያት እንደሆነ ተገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የንፁሃንን ህይወት የቀጠፈው የጂግዳ ቀበሌ ጥቃት ፦

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን በንጹሃን ዜጎች ላይ ግድያ ተፈፅሟል።

ጥቃቱ የተፈጸመው በዞኑ ማንዱራ ወረዳ ጂግዳ ቀበሌ መሆኑን ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡

ከቻግኒ ወደ ግልገል በለስ ሲጓዝ በነበረ መለስተኛ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ውስጥ የነበሩ ተጓዦችን በማስወረድ ግድያ ተፈጽሟል፡፡

የቆሰሉት ደግሞ ወደ ፓዊ ሆስፒታል መወሰዳቸውን ለአብመድ አሳውቀዋል።

በጥቃቱ የሞቱ ፣ የቆሰሉ እና ታግተው የተወሰዱትን ሰዎች ቁጥር ግን በትክክል አይታወቅም።

ወደ ቻግኒ እና ወደ ግልገል በለስ የተሽከሪካሪ እንቅስቃሴ ቆሟል።

በገነተ ማርያም ቀበሌ በተመሳሳይ የታጠቁ ቡድኖች በነዋሪዎች ላይ የከፈቱትን ተኩስ የአካባቢው የፌዴራል ፖሊስ እና የመከላከያ ስራዊት መከላከል መቻላቸውን ነዋሪዎች ለአብመድ ገልጸዋል፡፡

የቲክቫህ አባላት ፦

አሁን ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት የቲክቫህ ማንዱራ አባላት እንዳሳወቁት ዛሬ ቀን ላይ በተፈፀመው ጥቃት በርካታ ሰዎች መሞታቸውን ገልፀው አሁንም ወረዳው የስጋት ቀጠና እንደሆነ ተናግረዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ : https://telegra.ph/Metekel-03-31

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#እጅግ_ከፍተኛ_ጥንቃቄ😷

ባለፉት 24 ሰዓት 24 ሰዎች በኮቪድ-19 መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል።

በተመሳሳይ ከተደረገው 8,022 የላብራቶሪ ምርመራ 2,068 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

ትላንት 1,484 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

በአጠቃላይ 206,589 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 2,865 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 158,109 ሰዎች አገግመዋል።

በአሁን ሰዓት 865 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#Purpose
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
የንፁሃንን ህይወት የቀጠፈው የጂግዳ ቀበሌ ጥቃት ፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን በንጹሃን ዜጎች ላይ ግድያ ተፈፅሟል። ጥቃቱ የተፈጸመው በዞኑ ማንዱራ ወረዳ ጂግዳ ቀበሌ መሆኑን ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡ ከቻግኒ ወደ ግልገል በለስ ሲጓዝ በነበረ መለስተኛ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ውስጥ የነበሩ ተጓዦችን በማስወረድ ግድያ ተፈጽሟል፡፡ የቆሰሉት ደግሞ ወደ ፓዊ ሆስፒታል መወሰዳቸውን ለአብመድ…
"10 ንፁሃን ተገድለዋል፤ 2 ህፃናት ታፍነው ተወስደዋል" - ጓንጓ ኮሚኒኬሽን

ዛሬ ከቀኑ 7 ሰዓት አካባቢ ከቻግኒ ወደ ግልገል የሚሄድ የህዝብ ማመላለሻ መኪና ላይ በተፈፀመው ጥቃት 10 ንፁሃን ሰዎች መገደላቸውን 3 ሰዎች መቁሰላቸውን እንዲሁም 2 ህፃናት ታፍነው መወሰዳቸውን የጓንጓ ኮሚኒኬሽን አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia