TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የ3 ሰዎችን ህይወት የቀጠፈው የቦንብ ፍንዳታ !

ጠዋቱ 2፡30 ሠዓት በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው ስልጤ መስኪድ ጀርባ ለልማት በፈረሰ ክፍት ቦታ ላይ ማንነታቸው ባልታወቁ ግለሰቦች ተጥሎ በተገኘ የእጅ ቦንብ የጎዳና ተዳዳሪ የሆኑ የ3 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ በ5 ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

ከፍንዳታው ጋር በተያያዘ ያለው የምርመራ ሂደት እየተጣራ መሆኑ ተገልጿል። የምርመራ ውጤቱ እንደተጠናቀቀ ለህብረተሰቡ ግልጽ ይደረጋል ተብሏል።

በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የልዩ ልዩና የተደራጁ ወንጀሎች ምርመራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮማንደር አለማየሁ አያልቄ ባስተላለፉት በተለያዩ ቦታዎች እንደ አልባሌ በሚጣሉ ቦንቦችና ፈንጂዎች ንፁሀን ሰለባ መሆናቸውን አስታውሰው ህብረተሰቡ ምንነታቸው ያልታወቁ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት ከመነካካት በመቆጠብ ለሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት ጥቆማ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

Via Addis Ababa Police Commission
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#WolaitaSodo

ዛሬ ጥዋት በወላይታ ሶዶ "መርካቶ ገበያ" የደረሰው የእሳት አደጋ ሙሉ በሙሉ ማለት በሚችል ደረጃ ከፍተኛ ውድመት አድርሷል።

አደጋው በበርካታ የንግድ ሱቆች እና ተቋሟት ላይ ውድመት አስከትሏል።

ጥዋት የተነሳውን የእሳት አደጋ መቆጣጠር እንደተቻለ የከተማው አስተዳደር ያሳወቀው ከ6:20 በኃላ ነው።

እሳቱ ወደ ሌሎች አከባቢዎች እንዳይዛመት የወላይታ ሶዶ ህብረተሰብ ከፍተኛ ርብርብ አድርጓል።

የከተማ አስተዳደሩ ህብረተሰቡ ላደረገው ቀና ትብብር ምስጋውን አቅርቧል።

የአደጋውን መንስኤ ፖሊስ እያጣራው ይገኛል።

Via Wolaita Sodo Administration
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#SUDAN #ETHIOPIA

ኢትዮጵያ እና ሱዳን የድንበር ውዝግባቸውን ለመፍታት በሚቀጥለው #ማክሰኞ ድርድር እንደሚጀምሩ የጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

የሱዳን ጠ/ሚ ጽ/ቤት ባወጣው መግለጫ እንዳለው ሐምዶክ እና ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው ዕለት ተገናኝተው በመጪው ማክሰኞ ታኅሳስ 13 ቀን 2013 ዓ.ም የሁለቱን አገሮች ድንበር ለማካለል የተቋቋመው ኮሚቴ በሚያደርገው ድርድር ላይ ተወያይተዋል።

ኢትዮጵያ እና ሱዳን 1,600 ኪሎ ሜትር የሚረዝም ድንበር ይጋራሉ።

ምንጭ፦ AFP / Deutsche welle
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#COVID19Ethiopia

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 5,373
• በበሽታው የተያዙ - 457
• ህይወታቸው ያለፈ - 7
• ከበሽታው ያገገሙ - 827

አጠቃላይ 119,951 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,853 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 102,980 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።

267 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ትላንት የተካሄደው የኢጋድ ስብሰባ ፦

* ዶ/ር አብይ አህመድ በኢትዮጵያ ስለተፈጠረው ሁኔታ 'ስለተወሰደው የህግ ማስከበር' ዘመቻ ሪፖርት አቅርበዋል።

1. የኢትዮጵያ መንግሥት የአገሪቱን አንድነት እና መረጋጋት ለማረጋገጥ የወሰደው እርምጃ ቆራጥነት የተሞላበት መሆኑን የአፍሪከ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋቂ ማሓመት ተናግረዋል።

የፌደራል መንግሥት የወሰደው እርምጃ "የአገሪቱን ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት ለማስከበር" መሆኑን ጠቅሰው፣ ይህም ሁሉም አገራት የሚጠበቅባቸው ሕጋዊ ኃላፊነት ነው ብለዋል።

በትግራይ ክልል የተከሰተው ቀውስ ተከትሎ ከፍተኛ መጠን ያለው መፈናቀል መከሰቱን ተናግረው ፤ በዚህ ረገድ ኢጋድ ለስደተኞችና ለተፈናቀሉ ሰዎች የተለየ ትኩረት በመስጠት ኢትዮጵያ ከምታደርገው የሰብአዊ ድጋፍ ጥረት ከጎኗ እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል።

የኢጋድ አባላት ለኢትዮጵያ መንግሥት ድጋፋቸውን መግለጻቸው ተነግሯል።

2. ዶክተር አብይ አህመድ የኢጋድ አባል ሀገራት መንግስት የወሰደውን የህግ ማስከበር እርምጃ ህጋዊነት በመረዳታቸውና እውቅና በመስጠታቸው እንዲሁም ኢትዮጵያን ለመደገፍ በመግለፃቸው ምስጋና አቅርበዋል።

3. ከኢጋድ ስብሰባ ጎን ለጎን ውይይት ያደረጉት ዶ/ር አብይ እና የሱዳን ጠ/ሚ ዶ/ር አብደላ ሃምዶክ በድንበር አካባቢ ያጋጠመው ችግር እንዲቆም እና ችግሩ በውይይት እንዲፈታ ተስማምተዋል። ሱዳን ውስጥ ስላለው ችግርም የሃሳብ ልውውጥ አድርገዋል፤ ዶ/ር አብይ ለሱደን መንግስት ድጋፋቸውን ሰጥተዋል።

4. የሱማሊያና ኬንያ መሪዎች በዶ/ር አብይ አህመድ አማካኝነት ውይይት አድርገዋል። ችግራቸውን በውይይት ለመፍታት፣ የዴፕሎማሲ ግንኙነታቸውን ዳግም መጀመር መስማማታቸውን ተነግሯል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ፣ ጅቡቲ ቴሌቪዥን፣ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን፣ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#SUDAN #UNHCR #Ethiopia

በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል የነበረውን ግጭት ሸሽተው ወደ ሱዳን የተሰደዱ የሀገራችን ዜጎች ከ50,000 ይበልጣሉ።

#UNHCR እና የሱዳን ባለስልጣናት በመነጋገር 14,000 ስደተኞችን ከሃምደያት እና አብድራፊ ድንበር ሃም ራኩባ ካምፕ አዘዋውረዋቸዋል። ቦታው ከኢትዮጵያ ድንበር 70 KM ይርቃል።

አብዛኞቹ ስደተኞች ሴቶች እና ህፃናት እንደሆኑ የUNHCR መረጃ ያሳያል።

https://www.unhcr.org/news/stories/2020/12/5fd60c0f4/growing-needs-thousands-displaced-ethiopians-sudan.html

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#EASA

የአውሮፓ የአቪየሽን ደኅንነት ኤጀንሲ የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች ከዚህ በኋላ ወደ ሰማይ ለመመለስ ዝግጁ ናቸው ሲል ለBBC አረጋግጧል።

የኤጀንሰው ኃላፊ እንደተናገሩት አውሮፕላኖቹ ከዚህ በኋላ ለመብረር አንዳችም ስጋት እንደሌለባቸው እርግጠኛ ሆነን መናገር እንችላለን ብለዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ኢቀመማ በትግራይ ክልል ውስጥ በግጭት ለተጎዱ ወገኖች የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ መቀጠሉን አሳውቋል !

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር በትግራይ ክልል ተከስቶ በነበረው ግጭት ለተፈናቀሉ እና ጉዳት ለደረሰባቸው 2000 ወገኖች ከብር 3 ሚሊዮን በላይ ወጪ በማድረግ ልዩ ልዩ ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች ድጋፍ አድርጓል፡፡

ማኅበሩ በትግራይ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ካደረገው ድጋፍ መካከል ብርድ ልብስ፣ ምንጣፍ የመመገቢያ እና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች እና መሠረታዊ መድኃኒት ድጋፍ ይገኝበታል፡፡

ኢቀመማ ግጭቱ ከተከሰተ በኋላ ከዓለም ዓቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ እና ከሌሎች ተባባሪ አካላት ጋር በመሆን ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች አስቸኳይ ሠብዓዊ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱ ይታወቃል፡፡

ከዚህም መካከል የመጀመሪያ ደረጃ የህክምና እርዳታ ፣ የአምቡላንስ አገልግሎት፣ የተጠፋፉ ቤተሰቦችን የማገናኘት፣ የተለያዩ የምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች ድጋፍ ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

ማኅበሩ በመቀለ ከተማ ተፈጥሮ የነበረውን የንፁህ መጠጥ ውሀ እጥረትን ተከትሎ ለከተማዋ ነዋሪዎች መጠጥ ውሀ ድጋፍ እንደተደረገ ይታወቃል፡፡

(የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
በአማራ ክልል የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና እየተሰጠ ነው!

በአማራ ክልል የስምንተኛ ክፍል ክልል ዓቀፍ ፈተና መሰጠት ተጀምሯል።

ፈተናው ከዛሬ ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት ይሰጣል፡፡

ፈተናው እየተሰጠ የሚገኘው በ5,162 የፈተና ጣቢያዎች ሲሆን በመደበኛ ፣ የማታ እና የግል ተፈታኞችን ጨምሮ ከ400 ሺህ በላይ ተማሪዎች ፈተናውን ይወስዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ምንጭ፦ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#SurConstruction

የሱር ኮንስትራክሽን ሠራተኞች የሁለት (2) ወር ደምወዝ አልተከፈለንም እንዳልተከፈላቸው ለኢዲስ ማለዳ ጋዜጣ ተናግሩ።

በአዲስ አበባ በሱር ኮንስትራክሽን ዋናው መሥሪያ ቤት የሚሠሩ ሠራተኞች የ2 ወር ደምወዝ እንዳልተከፈላቸው እና ችግር ላይ እንደሆኑ አሳውቀዋል።

በመሥሪያ ቤቱ በተለያየ የኀላፊነት ቦታ የሚሠሩ ሠራተኞች ቅሬታቸውን ሲገልጹ ላለፉት 2 ወራት ምንም ዓይነት ክፍያ ስላልተሰጠን ችግር ውስጥ ወድቀናል ብለዋል።

MORE : https://buff.ly/3mAtTVN

ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ ጋዜጣ
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#Hawassa

የሀዋሳ ከተማ ምክትል ከንቲባ ረ/ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ የቅዱስ ገብርኤል ንግስ በዓል በደማቅ ሁኔታ ሃይማኖታዊ ይዘቱን በጠበቀ መልኩ እንዲከበር አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል።

ምክትል ከንቲባው ከወዲሁ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በዓሉን ለመታደም ወደ ሀዋሳ የሚመጡ እንግዶችን ያለምንም የፀጥታ እና ደህንነት ችግር ከተማዋን ጎብኝተው እንዲሄዱ የማድረግ ስራ እንደተሰራ አሳውቀዋል።

ረ/ፕሮፌሰር ፀጋዬ አሁን ላይ ሀዋሳ እጅግ ሰላማዊ፣ የደህንነትና የፀጥታ ችግር የሌለባት ሁሉም ነገር ሰላማዊ የሆነባት ከተማ መሆኗን ገልፀው ይህም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

እንግዶችም ወደ ሀዋሳ ከተማ ሲመጡ ምንም አይነት የደህንነት እና የፀጥታ ችግር ሳይገጥማቸው በተሻለ ሁኔታ እንደሚስተናገዱ ምክትል ከንቲባው ተናግረዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
ከፍተኛ ስጋትን የደቀነው አዲሱ የኮቪድ ዝርያ !

በርካታ የአውሮፓ አገራት ብሪታኒያ ላይ የጉዞ እቀባ እያደረጉ ነው።

ለዚህ ምክንያቱ በብሪታኒያ አዲስ ዓይነት የኮቪድ ዝርያ መገኘቱ ነው።

አዲሱ ዝርያ ገና በስፋት ያልተጠና ቢሆንም ከቁጥጥር ውጭ በሆነ መንገድ ከሰው ወደ ሰው ይዛመታል የሚለው ፍርሃት በርካታ አገራትን ድንጋጤ ውስጥ ከቷቸዋል።

እስከ አሁን ጀርመን ፣ አየርላንድ፣ ፈረንሳይ፣ ጣሊያንና ኔዘርላንድስ እና ቤልጂየም ሁሉም ወደ ብሪታኒያ የአየር በረራን አቋርጠዋል።

ዛሬ የአውሮፓ ኅብረት መሪዎች ስብሰባ ስለሚቀመጡ ከዚህ የባሰ የእቀባ ውሳኔ ሊኖር እንደሚችል እየተጠበቀ ነው።

አዲሱ ኮቪድ-19 ዝርያ በለንደንና በደቡብ ምሥራቅ ኢንግላንድ በአጭር ጊዜ ውስጥ ነው በስፋት የተሰራጨው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ቅዳሜ በሰጡት አስቸኳይ ትእዛዝ ደረጃ 4 የጥንቃቄ ደንቦች እንዲከበሩ አዘዋል።

ለፈረንጆች ገና እና አዲስ ዓመት የእንቅስቃሴ ገደቦች ይላላሉ ተብሎ ታስቦ የነበረውን ሐሳብ ሰርዘዋል።

የጤና ባለሙያዎች አዲሱ የተህዋሲው ዝርያ ይበልጥ ገዳይ ስለመሆኑ ሆነ ለክትባት እጅ የማይሰጥ ስለመሆኑ ገና እርግጠኛ አልሆኑም።

ሆኖም ግን ከለመድነው የኮሮና ቫይረስ በ70 በመቶ በይበልጥ የመሰራጨት አቅም አለው መባሉ ማን ይተርፋል ? እንዲባል አድርጓል።

የብሪታኒያ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ይህ አዲስ ዝርያ ቫይረስ ከቁጥጥር ውጭ ሆኖብናል ፤ በቁጥጥራችን ልናውለው ይገባል ብለዋል።

የዓለም ጤና ድርጅት አዲሱን የኮሮና ቫይረስ ዝርያ በተመለከተ ከዩኬ (UK) ባለሥልጣናት ጋር በቅርበት እየተነጋገረ እንደሆነ አስታውቋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia