TIKVAH-ETHIOPIA
ከፍተኛ ስጋትን የደቀነው አዲሱ የኮቪድ ዝርያ ! በርካታ የአውሮፓ አገራት ብሪታኒያ ላይ የጉዞ እቀባ እያደረጉ ነው። ለዚህ ምክንያቱ በብሪታኒያ አዲስ ዓይነት የኮቪድ ዝርያ መገኘቱ ነው። አዲሱ ዝርያ ገና በስፋት ያልተጠና ቢሆንም ከቁጥጥር ውጭ በሆነ መንገድ ከሰው ወደ ሰው ይዛመታል የሚለው ፍርሃት በርካታ አገራትን ድንጋጤ ውስጥ ከቷቸዋል። እስከ አሁን ጀርመን ፣ አየርላንድ፣ ፈረንሳይ፣ ጣሊያንና…
#UPDATE
ሳዑዲ አረቢያ በፍጥነት እየተዛመት ነው የተባለውን አዲሱን የኮቪድ ዝርያ በመፍራት ሁሉንም አለም አቀፍ በረራዎች ለጊዜው አግዳለች።
እገዳው ለአንድ (1) ሳምንት ሲሆን ከዚህም ሊራዘም እንደሚችል የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳውቋል።
የካርጎ በረራዎች ይቀጥላሉ።
ይህ እገዳ ስለአዲሱ የኮቪድ ዝርያ ግልፅ የሆነ የህክምና መረጃ እስኪገኝ ሊቀጥል እንደሚችልም ተጠቁሟል።
የሀገሪቱ የመሬት እና ባህር ወደቦችም ለአንድ ሳምንት ይዘጋሉ ተብሏል።
የሳዑዲ መንግሥት ባለፉት ሶስት ወራት ከአውሮፓ ሀገራት የመጣ ወይም በአውሮፓ ሀገራት በኩል ጉዞ ያደረገ ማንኛውም ሰው በአስቸኳይ የኮቪድ-19 ምርመራ እንዲያደርግ አዟል።
በተመሳሳይ ፦
ኩዌት በረራዎችን አግዳለች ፤ የመሬት እና የባህር ድንበሮቿን ከዛሬ ጀምሮ እስከ Jan 1 (ታህሳስ 23) ዘግታለች።
የካርጎ በረራ ይቀጥላል።
እንዲሁም ኦማን የባህር ፣ አየር፣ የመሬት ድንበሮቿን ከነገ ማክሰኞ ጀምሮ ለአንድ (1) ሳምንት ትዘጋለች።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

ወይዘሮ አዜብ መስፍን ልጃቸው ሰመሓል መለስ በመቐለ ከተማ መታሰሯን ተናገሩ !
(በቢቢሲ የአማርኛው አገልግሎት)
የቀድሞው ጠ/ሚር መለስ ዜናዊ ሴት ልጅ ሰመሐል መለስ ትግራይ መቐለ ውስጥ ተይዛ እንደታሰረች እናቷ ወይዘሮ አዜብ መሰፍን ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ወ/ሮ አዜብ ልጃቸው ሰመሐል በምን ምክንያት ለእስር እንደተዳረገች የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ተናገረው ፣ ወደ መቐለ የሄደችው ወታደራዊ ግጭቱ ከመጀመሩ በፊት እንደሆነ ገልጸዋል።
አዲስ አበባ የሚገኙት ወይዘሮ አዜብ ጨምረውም ሰመሐል ወደ መቀለ ያቀናችው በአባቷ የህይወት ታሪክ ላይ የተጻፈ መጽሐፍን ተንተርሶ የተዘጋጀን ቲያትር ለማስመረቅ በርካታ ሰዎች ካሉበት ቡድን ጋር መሆኑን አመልክተዋል።
ሰመሐል "የፖለቲካ አቋም ሊኖራት ይችላል። ነገር ግን የፖለቲካ ፓርቲ አመራርም፣ አባልም፣ ደጋፊም አልነበረችም" ያሉት እናቷ ወ/ሮ አዜብ መስፍን የእስሯ ምክንያት ምን እንደሆነ እንደማያውቁ ተናግረዋል።
ወ/ሮ አዜብ፥ ሰመሐል በየትኛው አካል እንደተያዘችና ምክንያቱ ምን እንደሆነ ከአንዳንድ አካላት ለማወቅ ጥረት ማድረጋቸውን የሚናገሩት ወ/ሮ አዜብ ነገር ግን ምላሽ ለማግኘት እንዳልቻሉ ጠቅሰዋል።
ከሰመሐል በተጨማሪ የጀነራል ኃየሎም አርአያ ልጅ የሆነው ብርሐነመስቀል ኃየሎም በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል።
የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ፕሬስ ሴክሬታሪያት አወል ሱልጣን እና የፌደራል ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ጄይላን አብዲን ስለጉዳዩ ቢጠየቁም የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ተናግረዋል።
MORE : https://telegra.ph/BBC-12-21-3
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

#COVID19Ethiopia
የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :
• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 4,242
• በበሽታው የተያዙ - 397
• ህይወታቸው ያለፈ - 8
• ከበሽታው ያገገሙ - 701
አጠቃላይ 120,348 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,861 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 103,681 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።
265 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

#WolaitaSodo ዛሬ ጥዋት በወላይታ ሶዶ "መርካቶ ገበያ" የደረሰው የእሳት አደጋ ሙሉ በሙሉ ማለት በሚችል ደረጃ ከፍተኛ ውድመት አድርሷል። አደጋው በበርካታ የንግድ ሱቆች እና ተቋሟት ላይ ውድመት አስከትሏል። ጥዋት የተነሳውን የእሳት አደጋ መቆጣጠር እንደተቻለ የከተማው አስተዳደር ያሳወቀው ከ6:20 በኃላ ነው። እሳቱ ወደ ሌሎች አከባቢዎች እንዳይዛመት የወላይታ ሶዶ ህብረተሰብ ከፍተኛ ርብርብ…
#WolaitaSodo
ትላንት በወላይታ ሶዶ ከተማ 'መርካቶ ገበያ' በደረሰው የእሳት አደጋ ጉዳት የደረሰባቸውን ነጋዴዎች የዞኑ አስተዳደር ከመላው የወላይታ ህዝብ ጋር በመሆን ለመደገፍ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት ዶክተር እንድርያስ ጌታ አሳውቀዋል።
በአደጋው የተጎዱ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋምና ዘላቂ መፍትሔ ለመፍጠር አንድ አቢይ እና የተለያዩ ንዑሳን ኮሚቴዎችን ተቋቁሟል ፤ ከነገ ጀምሮ ወደ ሥራ ይገባል።
የመርካቶ ገበያ መቃጠል የንግዱ ማህበረሰብን ብቻ ሳይሆን በአመዛኙ የሶዶ ከተማ ገቢ የሚመነጨው ከገበያ ማዕከሉ በመሆኑ በከተማይቱ ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል።
የትላንቱ የእሳት አደጋ ከባድ በመሆኑ ወደተለያዩ የከተማው ክፍሎች እና አካባቢዎች እንዳይዛመት ፦
- የሐዋሳ ከተማ እሳትና ድንገተኛ አደጋ ማጥፊያ ቡድን፣
- የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር እሳትና ድንገተኛ አደጋ ማጥፊያ ቡድን፣
- የሲዳማ ክልል መንግስት ፣
- የፀጥታ አካላት፣
- የግል ባለሀብቶች እና መላው የወላይታ ሶዶ ነዋሪዎች ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ምስጋና ቀርቧል።
ዛሬ የክልል ፣ የዞን እና የወላይታ ሶዶ ከተማ ከፍተኛ አመራሮች በመርካቶ ገበያ የእሳት አደጋው ያደረሰውን ጉዳት ተመልክተዋል።
ወላይታ ሶዶ ከዚህ በፊት አራት ጊዜ እንዲህ አይነት ተመሳሳይ የእሳት አደጋ አስተናግዳለች። የትላንቱ ለአምስተኛ ጊዜ የተከሰተ አደጋ ነው።
ምንጭ፦ የወላይታ ዞን ኮሚኒኬሽን

#ExitExam
የህግ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና (Exit Exam ) ከዛሬ ጀምሮ መውሰድ ይጀምራሉ።
በኮቪድ ምክንያት የትምህርት ተቋማት ከተዘጉ በኋላ ወደ 2013 የተዛወረው ፈተና ቀጥሎም በሀገሪቱ በተፈጠረው የጸጥታ ስጋት ምክንያት ዳግም ሊራዘም ችሏል።
በዚህ ምክንያት በትግራይ ክልል ውስጥ ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም በትግራይ የሚገኙ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ፈተናውን አይወስዱም።
በአስፈታኝ ዩኒቨርሲቲዎች ለማስፈተን አመቺ ሁኔታዎች ከሌሉ በአጭር ጊዜ የድጋሚ ፈተና በልዩ ሁኔታ በማዘጋጀት እንዲፈተኑ ይደረጋል ተብሏል።
የፍትሕ እና የሕግ ምርምርና ሥልጠና ኢኒስትቲውት ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች በጻፈው ደብዳቤ ፈተናው ከታህሳስ 13-16 ባለው ጊዜ ውስጥ እንዲሰጥ መወሰኑ ይታወሳል።
@tikvahethmagazine

ወይዘሮ አዜብ መስፍን ልጃቸው ሰመሓል መለስ በመቐለ ከተማ መታሰሯን ተናገሩ ! (በቢቢሲ የአማርኛው አገልግሎት) የቀድሞው ጠ/ሚር መለስ ዜናዊ ሴት ልጅ ሰመሐል መለስ ትግራይ መቐለ ውስጥ ተይዛ እንደታሰረች እናቷ ወይዘሮ አዜብ መሰፍን ለቢቢሲ ተናግረዋል። ወ/ሮ አዜብ ልጃቸው ሰመሐል በምን ምክንያት ለእስር እንደተዳረገች የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ተናገረው ፣ ወደ መቐለ የሄደችው ወታደራዊ ግጭቱ ከመጀመሩ…
ሰመሓል መለስ ከእስር ተለቀቀች።
ወ/ሮ አዜብ መስፍን ልጃቸው ሰምሃል ከእሁድ ጀምሮ እስከ ሰኞ ምሽት ድረስ ለ36 ሰዓታት ተይዛ መቆየቷን ገልጸው ፤ ትናንት ምሽት እራሷ ደውላ መለቀቋን እንደገለጸችላቸው ዛሬ [ማክሰኞ] ጠዋት ተናግረዋል።
ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ወ/ሮ አዜብ መስፍን ልጃቸው ሰምሃል ከእሁድ ጀምሮ እስከ ሰኞ ምሽት ድረስ ለ36 ሰዓታት ተይዛ መቆየቷን ገልጸው ፤ ትናንት ምሽት እራሷ ደውላ መለቀቋን እንደገለጸችላቸው ዛሬ [ማክሰኞ] ጠዋት ተናግረዋል።
ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#COVID19 የኤስራኤል ጠ/ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ የኮቪድ-19 ክትባት (Pfizer/BioNTech) ተከተቡ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ክትባቱን ሲወስዱ በቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት ታይተዋል። ኔታንያሁ የኮቪድ-19 ክትባትን የወሰዱ የመጀመሪያው እስራኤላዊ ሲሆኑ በወሩ መጨረሻ በሚሊዮን የሚቆጠር የኮቪድ-19 ክትባት እንደሚደረስ ተነግሯል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዜጎቻቸው ክትባቱን ይወስዱ ዘንድ መልዕክት አስተላልፈዋል።…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ባይደን የኮቪድ-19 ክትባት ተከተቡ።
ተመራጩ የአሜሪካው ፕሬዜዳንት ጆ ባይደን ትላንት ምሽት የኮቪድ-19 ክትባት ተከትበዋል።
ተመራጩ ፕሬዜዳንት ክትባቱን ሲወስዱ በቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት ለህዝብ ተላልፏል።
ከጥቂት ቀናት በፊት የእስራኤሉ ጠ/ሚር ቤኒያሚን ኔታንያሁ በተመሳሳይ የኮቪድ - 19 ክትባት መከተባቸው የሚታወስ ነው።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ተመራጩ የአሜሪካው ፕሬዜዳንት ጆ ባይደን ትላንት ምሽት የኮቪድ-19 ክትባት ተከትበዋል።
ተመራጩ ፕሬዜዳንት ክትባቱን ሲወስዱ በቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት ለህዝብ ተላልፏል።
ከጥቂት ቀናት በፊት የእስራኤሉ ጠ/ሚር ቤኒያሚን ኔታንያሁ በተመሳሳይ የኮቪድ - 19 ክትባት መከተባቸው የሚታወስ ነው።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#UPDATE
አዲስ ተገኘ የተባለው የኮሮና ቫይረስ ዝርያ ለዓለም ሀገራት ስጋት እየሆነ ነው።
ከ40 በላይ አገራት ከUK ወደ አገራቸው የሚደረጉ በረራዎችን አግደዋል።
የአውሮፓ ሕብረት አባል አገራት በዚህ ዙሪያ የጋራ ፖሊሲ ለማውጣት እየተወያዩ ነው።
ዴንማርክ ውስጥ አዲሱ የቫይረስ ዝርያ በመታየቱ ስዊድን ወደ ዴንማርክ የሚደረግ ጉዞ አግዳለች።
ዝርያው በከፍተኛ ሁኔታ የሚሰራጭ ነው። በከፍተኛ ደረጃ ጎጂ ስለመሆኑ ግን እስካሁን የተገኘ መረጃ የለም።
የዓለም ጤና ድርጅቱ ማይክ ራየን ፥ አዲሱ የቫይረስ ዝርያ በወረርሽኙ ዝግመተ ለውጥ ሂደት የሚጠበቅ ነው ብለዋል።
የUK የጤና ሚንስትር ጸሐፊ ማት ሀንኮክ አዲሱ ዝርያ ከቁጥጥር ውጭ ሆኗል ቢሉም ማይክ ራይን አዲሱ ዝርያ "ከቁጥጥር አልወጣም" ብለዋል።
UK ከተገኘው የቫይረስ ዝርያ የተለየ አዲስ ዝርያ በደቡብ አፍሪካም ተገኝቷል። የደቡብ አፍሪካ ተጓዦች ላይ እገዳ እየተጣለም ነው።
እስካሁን የአዲሱ ቫይረስ ዝርያ በዴንማርክ፣ አውስትራሊያ፣ ጣልያን እና ኔዘርላንድስም ተገኝቷል።
አንዳንድ ባለሙያዎች እንደሚሉት ከሆነ ፤ የቫይረሱ ዝርያ ከተገኘባቸው ቦታዎች ውጪ ተሰራጭቶ ሊሆን ይችላል።
UK የዘረ መል ቅንጣት ላይ ጥናት በማድረጓ አዲሱን የቫይረስ ዝርያ እንደደረሰችበት አስረድተዋል።
በቤልጄም የሚሠሩት የቫይረስ አጥኚ ማርክ ቫን፤ "በቀጣይ ቀናት አዲሱ የቫይረሱ ዝርያ በብዙ አገሮች ይገኛል ብለን እንጠብቃለን" ብለዋል። (BBC)

#SUDAN #ETHIOPIA ኢትዮጵያ እና ሱዳን የድንበር ውዝግባቸውን ለመፍታት በሚቀጥለው #ማክሰኞ ድርድር እንደሚጀምሩ የጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ጽህፈት ቤት አስታውቋል። የሱዳን ጠ/ሚ ጽ/ቤት ባወጣው መግለጫ እንዳለው ሐምዶክ እና ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው ዕለት ተገናኝተው በመጪው ማክሰኞ ታኅሳስ 13 ቀን 2013 ዓ.ም የሁለቱን አገሮች ድንበር ለማካለል የተቋቋመው ኮሚቴ በሚያደርገው ድርድር…
#ETHIOPIA #SUDAN
በም/ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የተመራ ልዑክ በኢትዮጵያ እና ሱዳን የጋራ የድንበር ኮሚቴ ውይይት ላይ ለመታደም ዛሬ ሱዳን ካርቱም ገብቷል፡፡
በልዑኩ የመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ቀንዓ ያደታ እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደህንነት አማካሪ ገዱ አንዳርጋቸው መካተታቸውን አል ዓይን (AlAIN) ዘግቧል።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
በም/ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የተመራ ልዑክ በኢትዮጵያ እና ሱዳን የጋራ የድንበር ኮሚቴ ውይይት ላይ ለመታደም ዛሬ ሱዳን ካርቱም ገብቷል፡፡
በልዑኩ የመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ቀንዓ ያደታ እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደህንነት አማካሪ ገዱ አንዳርጋቸው መካተታቸውን አል ዓይን (AlAIN) ዘግቧል።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#MinistryOfEducation
የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን በመከላከል የመማር ማስተማር ስራው ቢጀመርም በርካታ ተማሪዎች በትምህርት ገበታቸው ላይ መገኘት አልቻሉም ተባለ።
በዚህ ጉዳይ ላይ የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና የክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች በበይነ መረብ መክረዋል።
ተቋርጦ የነበረው የመማር ማስተማር ስራ ድጋሚ የተጀመረ ሲሆን አሁንም ወደ ትምህርት ገበታቸው ያልተመለሱ ተማሪዎች እንዳሉ ተነስቷል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢ/ር ጌታሁን መኩሪያ ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት እንዲልኩ አሳስበዋል።
ትምህርት ላይ የሚሰሩ አጋር አካላት እንዲሁም ከትምህርት ዘርፍ ውጭ ያሉ ተቋማትም ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ እየተደረገ ያለውን ጥረት እንዲደግፉ ጠይቀዋል።
ትምህርት ሚኒስቴር "ወደ ትምህርት ቤት እንመለስ" በሚል ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታቸው የመመለስ ዘመቻም እንደሚጀመር አሳውቋል።

#ETHIOPIA #SUDAN በም/ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የተመራ ልዑክ በኢትዮጵያ እና ሱዳን የጋራ የድንበር ኮሚቴ ውይይት ላይ ለመታደም ዛሬ ሱዳን ካርቱም ገብቷል፡፡ በልዑኩ የመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ቀንዓ ያደታ እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደህንነት አማካሪ ገዱ አንዳርጋቸው መካተታቸውን አል ዓይን (AlAIN) ዘግቧል። @tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#UPDATE
ሁለተኛው የኢትዮ - ሱዳን የድንበር ጉዳዮች የከፍተኛ ደረጃ የፖለቲካ ውይይት በካርቱም ሱዳን እየተካሄደ ነው።
2ቱ ወገኖች በጋራ የድንበር አካባቢ ወቅታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ይመክራሉ።
በማስቀጠልም የጋራ ድንበራቸውን በተመለከተ ያሉ ማናቸውንም ዓይነት ልዩነቶች ሁሉንም በሚያስማማ መንገድ ለመፍታት የወደፊት አቅጣጫ ያስቀምጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። (EPA)