TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63K photos
1.61K videos
216 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በአዲስ አበባ ከተማ የተደረገ የዳሰሳ ጥናት!

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአስሩም ክፍለ ከተሞች በተደረገ ከቤት ውጭ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ የመጠቀም የዳሰሳ ጥናት በጥናቱ ከተካተቱት 14,836 ሰዎች ውስጥ 11,119 ሰዎች ይኸውም 74.9% የሚሆኑት ብቻ በአግባቡ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል የተጠቀሙ ናቸው።

በማህበረሰቡ ውስጥ በተለይ አፍ እና አፍንጫን በአግባቡ ከመሸፈን ፣ ርቀትን ከመጠበቅ እንዲሁም እጅን በአግባቡ እና በየጊዜው ከመታጠብ አንፃር ከፍተኛ የሆነ ጥንቃቄ የሚያስፈልግበት ወቅት ላይ መደረሱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በአሥራት ጋዜጠኞች ላይ የቀረበው ይግባኝ ውድቅ ተደረገ!

የልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ይግባኝ የወንጀል ችሎት ፖሊስ በአሥራት ጋዜጠኞች ላይ ያቀረበውን የይግባኝ ጥያቄ ውድቅ አድርጎታል።

ፖሊስ የአሥራት ጋዜጠኞች በዋስትና ከእስር ቢፈቱ መረጃ ያጠፉብኛል ቢልም ፍርድ ቤቱ ይግባኙን አልተቀበለውም።

ፖሊስ ከአራቱ የአሥራት ጋዜጠኞች መካከል በበላይ ማናዬ፣ ሙሉጌታ አንበርብርና ምስጋናው ከፈለኝ ላይ ይግባኝ ጠይቆ የነበር ሲሆን በዋነኛነት ከኢመድኤ / INSA ፣ ከሆስፒታል እና ከብሮድካስት ባለስልጣን መረጃ እንደሚያመጣ ጠቅሶ ከእስር ከወጡ ተፅዕኖ ፈጣሪ ስለሆኑ መረጃ ያጠፉብኛል ብሏል።

ይሁንና ፍርድ ቤቱ መረጃ ይመጣባቸዋል ከሚባሉት ተቋማት መረጃ ማጥፋት ሆነ ማዛባት እንደማይቻል ገልፆ የእስር ፍርድ ቤቱ በተደጋጋሚ ፖሊስ መረጃ እንዲያቀርብ ቀጠሮ ከሰጠ በኋላ ጋዜጠኞቹ በዋስትና እንዲለቀቁ ማድረጉ ትክክለኛ ውሳኔ ነው ብሎታል።

ምንጭ፦ አስራት ቴሌቪዥን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
CONGRATULATIONS!

ዛሬ ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ በሁለተኛ ዲግሪ መርሀ ግብር ያሰለጠናቸውን 659 ተማሪዎችን አስመርቋል። ዩኒቨርሲቲው ያስመረቃቸው ተማሪዎች በእፅዋት ሳይንስ ፤ በኢኮኖሚክስ እና በሌሎች የተለያዩ የትምህርት መሰኮች የሰለጠኑ 515 ወንድ እና 144 ሴቶች በድምሩ 659 ተማሪዎች ናቸው።

በሌላ በኩል ዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በዛሬው ዕለት በተለያዩ መስክ ያስተማራቸውን 3 ስፔሻሊስት ዶክተሮችን ፣ 47 የህክምና ዶክቴሮችን ፣ 486 የድህረ ምረቃ እና 543 ተከታታይ ተማሪዎች በአጠቃላይ 1ሺህ 79 ተማሪዎችን አስመርቃል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
41ኛው የቦረና ጉሚ ጋዮ ጉባዔ በቦረና ዞን በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በጉባዔው ላይ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝደንት የሆኑት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ፣ የጨፌ ኦሮሚያ አፈጉባዔ ወይዘሮ ሎሚ በዶ እና ሌሎችም የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

በጉባዔው ላይ አዳዲስ ህጎች የሚወጡ ሲሆን ከዚህ ቀደም የነበረ መልካም ህጎችም እንዲቀጥሉ፤ ጉድለት ያለባቸውም እንዲስተካከሉ ይደረጋል ተብሏል።

በተጨማሪ በዚህ ጉባዔ ላይ በነበሩ እና ባሉ ችግሮች ዙሪያ ውይይት እንደሚደረግም ነው የተገለፀው።

በቦረና ገዳ ስርዓት ባለፉት ስምንት (8) ዓመታት ያገለገሉ ህጎችን በመገምገም መስተካከል ያለባቸው እንዲስተካከሉ ይደረጋል የተባለ ሲሆን፥ በጉባዔው ላይ የሚተላለፉ ውሳኔዎችም ሙሉ በሙሉ ተፈፃሚ እንደሚደረጉ ከOBN ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኮሮና ቫይረስ ዳግም እያንሰራራባቸው ያሉ ሀገራት!

- በስፔን ኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ከ525 ሺ በልጧል። ይህም የሆነው ትምህርት ቤቶች እንደገና ከመከፈታቸው ጋር በተያያዘ ቫይረሱ ለ2ተኛ ጊዜ በማገርሸት ላይ በመሆኑ ነው፡፡

- ፈረንሳይ ውስጥ በየቀኑ የተጠቂዎች ቁጥር 'አሳሳቢ' በሆነ ደረጃ እየጨመረ መሆኑን ሀገሪቱ አሳውቃለች። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በየዕለቱ በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በአማካይ ከ5,000 በላይ ደርሷል።

- ዩናይትድ ኪንግደም በተመሳሳይ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት እየጨመረ ነው። ትላንት ብቻ 2,948 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። የአገር ውስጥ የቫይረሱ ስርጭት በአብዛኛው ከወጣቶች ጋር የተያያዘ ስለመሆኑ ዘ ናሽናልን ዋቢ በማድረግ አል ዓይን (Al Ain) ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በመንግስት ጥሪ እየተደረገ ሰዎች የሚሰበሰቡባቸው ዝግጅቶች መላ ቢፈለግላቸው መልካም ነው እንላለን።

ፎቶው ዛሬ ጠዋት ሐና አካባቢ የነበረ የፅዳት ዘመቻ ለማድረግ የተሰባሰቡ ሰዎችን የሚያሳይ ነው። ማስክ ያላደረጉ አንዳንድ ሰዎችም ጭምር ነበሩበት።

ከቅርብ ጊዜ ወደህ እያየን ያለነው አንዳንድ እንቅስቃሴ መንግስት ራሱ ለወረርሽኙ እየሰጠ ያለው ትኩረት ከጊዜ ወደጊዜ እየቀነሰ እየመጣ እንደሆነ የሚያሳይ ነው።

ዝግጅቶች መቅረት የለባቸውም ከተባለ በጤና ባለሞያዎች የሚሰጡ ምክሮችን ሳያጓድሉ መፈፀም ይገባል።

የጤና ባለሞያዎችን ምክር መፈፀም የማይቻል ከሆነ ግን ይህ ሁኔታ ሀገርን አደጋ ላይ የሚጥል በመሆኑ ቢቀር የተሻለ ነው።

የጤና ሚኒስቴር፣ ጤና ቢሮዎች እንዲሁም የጤና ባለሞያዎች አሁን ላይ በአንዳንድ ቦታዎች እየታየ ያለው 'ማስክ' ማድረግ ብቻ ሙሉ በሙሉ በሽታውን ይከላከላል የሚለውን የተሳሳተ አመለካከት በተቻለ አቅም በእቸኳይ እንዲታረም ርብርብ ማድረግ ይገባል።

ዛሬ ጥዋት በቲክቫህ ኢትዮጵያ የተጋራውን የአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ ሪፖርት (ከነሃሴ 1 እስከ 30) አንብባችሁታል። ከሪፖርቱ ምን ያህል ይህ ወረርሽኝ በአደገኛ ሁኔታ በፍጥነት እየተዛመተ ፤ የሰዎችንም ህይወት እየቀጠፈ እንደሆነ ተመልክታችኃል፤ ስለዚህ መዘናጋቱ በቃ ሊባል ይገባዋል!

ነገን በህይወት ለመኖር ዛሬን እንጠንቀቅ!
የቲክቫህ አባላት አዲስ አበባ
ጳጉሜ 3/2012 ዓ/ም

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በአሥራት ጋዜጠኞች ላይ የቀረበው ይግባኝ ውድቅ ተደረገ! የልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ይግባኝ የወንጀል ችሎት ፖሊስ በአሥራት ጋዜጠኞች ላይ ያቀረበውን የይግባኝ ጥያቄ ውድቅ አድርጎታል። ፖሊስ የአሥራት ጋዜጠኞች በዋስትና ከእስር ቢፈቱ መረጃ ያጠፉብኛል ቢልም ፍርድ ቤቱ ይግባኙን አልተቀበለውም። ፖሊስ ከአራቱ የአሥራት ጋዜጠኞች መካከል በበላይ ማናዬ፣ ሙሉጌታ አንበርብርና ምስጋናው ከፈለኝ ላይ…
የአሥራት ጋዜጠኞች ወደእስር ቤት እንዲመለሱ ተደረጉ!

የአሥራት ጋዜጠኞች ዛሬ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን (3ኛ) እስር ቤት ከተፈቱ በኋላ 7 ሲቪል የለበሱ ግለሰቦች "ለጥያቄ ትፈለጋላችሁ" በሚል ወደ እስር ቤት እንዲመለሱ መደረጉን ቴሌቪዥን ጣቢያው አሳውቋል።

በትናንትናው ዕለት የአራዳ መጀመርያ ፍርድ ቤት የዋስትና መብት የጠበቀላቸው ሲሆን ፖሊስ ከእስር እንዳይፈቱ አድርጎ ይግባኝ እንደጠየቀባቸው ይታወቃል።

ይሁንና የፈደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ይግባኝ ወንጀል ችሎት የፖሊስን ይግባኝ ውድቅ አድርጎ የዋስትና መብታቸው መከበሩ ትክክል መሆኑ ውሳኔ ሰጥቷል።

የአሥራት ጋዜጠኞች በእያንዳንዳቸው በ10 ሺህ ብር ዋስ እንዲፈቱ በተጠየቀው መሰረት አሥራትን በሕዳር ወር 2012 ዓ/ም የለቀቀው ዮናታን ሙሉጌታ ተፈትቷል።

ይሁንና ሙሉጌታ አንበርብር ፣ በላይ ማናዬ ፣ እና ምስጋናው ከፈለኝ ከእስር ቤት ሲወጡ ሲቪል የለበሱ ግለሰቦች በር ላይ ጠብቀው ወደ እስር ቤት እንዲመለሱ ተደርገዋል።

ምንጭ፦ አስራት ቴሌቪዥን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

በነሐሴ ወር በተደረገ የምርመራና የንቅናቄ ዘመቻ ከ37 ሺህ በላይ ዜጎች የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለጹ።

ዶ/ር ሊያ ታደሰ በዛሬው መግለጫቸው ያነሷቸው #ENA

- በነሐሴ ወር የማኅበረሰብ ንቅናቄ እና የምርመራ ዘመቻው በሁሉም የአገሪቱ ክልሎች ተካሂዷል። 1 ሺህ 95 ወረዳዎችን በማዳረስ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ለቫይረሱ ተጋላጭ የሆኑ የማኅበረሰበ ክፍሎችን ለማግኘት ተችሏል።

- ዘመቻው ከተጀመረ ጀምሮ በድምሩ 575 ሺህ ሰዎችን መመርመር እንደተቻለና በቀን የመመርመር አማካይ አቅም 19 ሺህ ደርሷል።

- በነሐሴ ወር ብቻ 37,748 ሰዎች ቫይረሱ እንዳለባቸው በምርመራ ተረጋግጧል። ይህ እስካሁን በአገሪቱ በአጠቃላይ ከተያዙት ሰዎች ቁጥር 64 በመቶውን ይሸፍናል።

- በኮሮና ቫይረስ በጠና የታመሙ ሰዎች ቁጥር በማሻቀቡ በፊት ከነበረበት 1 በመቶ በአሁኑ ወቅት 4 ነጥብ 5 በመቶ ደርሷል።

- ከንቅናቄው በፊት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት 368 ሰዎች ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን ከንቅናቄው በኋላ ይህ አሀዝ ወደ 550 ከፍ ብሏል። እስከ ነሐሴ መጨረሻ ድረስ በአጠቃላይ ከወረርሽኙ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 21 ሺህ ደርሷል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
👍1
የትግራይ ክልላዊ ምርጫ ነገ ይካሄዳል!

ነገ በትግራይ ይደረጋል ለተባለው ምርጫ 2672 ድምፅ መስጫ ጣብያዎች መዘጋጀታቸው የትግራይ ምርጫ ኮምሽን ማስታውቁን ዶቼ ቨለ (DW) ዘግቧል።

በነገው ድምፅ የመስጠት ስነ ስርዓት 2 ነጥብ 7 ሚልዮን ህዝብ ድምፅ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ከዛሬ ምሽት ጀምሮ የብስክሌቶች ፣ የሞተር ሳይክሎች ፣ ባለሶስት እግር ተሽከርካሪዎች (ባጃጆች) እንቅስቃሴ በጊዜያዊነት መከልከሉ የትግራይ ፀጥታና አስተዳደር ቢሮ አስታውቋል፡፡

ነገ ጳጉሜ 4/2012 ዓ/ም ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ እስከ ማታ 12 ሰዓት መራጮች ድምፅ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጳጉሜ 3/2012 ዓ/ም

የኢትዮጵያ የኮቪድ-19 መረጃዎች #1፦

#Somali

በሱማሌ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 119 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 18 ሰዎች በኮቪድ-19 መያቸው ተረጋግጧል።

#BenishangulGumuz

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 417 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 66 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

በቫይረሱ ከተያዙት መካከል፦
- 2 ከመንጌ ወረዳ
- 41 ከጉባ ወረዳ
- 4 ከማንዱራ ወረዳ
- 1 ከፓዌ ወረዳ
- 8 ከአሶሳ ወረዳ
- 7 ከብልዲግሉ ወረዳ ይገኙበታል።

#Harari

በሀረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 384 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 13 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።

በቫይረሱ የተያዙት፦
- 6 ከአቦከር ወረዳ
- 2 ከሀኪም ወረዳ
- 1 ሽንኮር ወረዳ፣ 1 ሶፊ ወረዳ፣ 1 ኤረር ወረዳ እንዲሁም 1 ከሌላ ክልል የመጣ ነው።

#DireDawa

ድሬዳዋ ከተማ ባለፉት 24 ሰዓት 72 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 8 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል። ሁሉም ግለሰቦች ናሙናቸው ከማህበረሰቡ የተሰበሰበ ነው።

#Tigray

በትግራይ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 1,473 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 208 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። የአንድ ሰው ህይወት አልፏል። በቫይረሱ ከተያዙት 208 ሰዎች መካከል 153 ከማህበረሰቡ የተገኙ ናቸው።

@tikvahethiopiaBOT
በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ከ60 ሺህ አለፉ!

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 14,815 የላብራቶሪ ምርመራ 1,136 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ16 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 888 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 60,784 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 949 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 22,677 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጳጉሜ 3/2012 ዓ/ም

የኢትዮጵያ የኮቪድ-19 መረጃዎች #2፦

#SNNPRS

በደቡብ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 1,528 የላብራቶሪ ምርመራ ስልሳ አንድ (61) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ የአንድ ሰው ህይወት አልፏል (ከቤንች ሸኮ ዞን - የ32 ዓመት ወንድ)

በቫይረሱ የተያዙት፡-
- ከከምባታ ጠምባሮ ዞን 17 (9 ከሺንሺቾ፣ 3 ከዱራሜ ከተማ፣ 2 ከደምቦያ፣ 1 ከቃጫቢራ፣ 1 ከጠምባሮ እና 1 ከዶዮ ገና)
- ከጌዴኦ ዞን 12 ( 8 ከዲላ ከተማ፣ 2 ከረጲ፣ 1 ከዲላ ዙሪያ እና 1 ከይርጋጨፌ)፣
- ከወላይታ ዞን 8 (4 ከአባላ አባያ፣ 2 ከቦዲቲ ከተማ፣ 1 ከሶዶ ከተማ እና 1 ከኪንዶ ኮይሻ፣ )፣
- ከደቡብ ኦሞ ዞን 5 ( 3 ከማሌ እና 2 ከሰሜን አሪ)፣
- ከሃዲያ ዞን 5 (3 ከሾኔ ከተማ እና 2 ከሆሳዕና ከተማ)፣
- ከቤንች ሸኮ ዞን 4 (2 ከሚዛን ከተማ እና 2 ከጉራፈርዳ)፣
- ከካፋ ዞን 3 (3ቱም ከዴቻ)፣
- ከጉራጌ ዞን 2 (2ቱም ከሶዶ)፣
- ከስልጤ ዞን 2 (2ቱም ከአሊቾ ወሪሮ)፣
- ከባስኬቶ ልዩ ወረዳ 1፣
- ከኮንሶ ዞን 1 (ኬና)፣ እንዲሁም 1 ከኦሮሚያ ክልል የመጣ።

#Sidama

በሲዳማ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 244 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 49 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።

በቫይረሱ ከተያዙት መካከል፦
- 23 ከሀዋሳ ከተማ
- 4 ከሀዌላ
- 3 ከሸበዲኖ
- 3 ከወንዶ ገነት
- 2 ከአርቤጎና ይገኙበታል።

አጠቃላይ በሲዳማ ክልል ውስጥ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 1,703 የደረሰ ሲሆን ከነዚህ መካከል የ20 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ 1008 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል።

@tikvahethiopiaBOT
#TikvahFamilyBulen

በቡለን ወረዳ በተፈፀመ ጥቃት የሰዎች ህይወት መጥፋቱን እንዲሁም በሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የቤኒሻነጉል ጉሙዝ ክልል ቡለን ወረዳ ቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት አሳውቀል።

የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የሆኑ የጤና ባለሞያዎች እንደተናገሩት በሚሰሩበት የጤና ተቋም ጉዳት ደርሶባቸው የመጡ የፀጥታ ኃይል አባላት ስምንት (8) የሚደርሱ እና በርካታ ነዋሪዎች አሉ።

ከነዋሪዎች መካከል ህይወታቸው ያለፈ አጠቃላይ ቁጥራቸው እስካሁን ባይታወቅም የ3 ሰዎች ህይወት ማለፉን እንዳረጋገጡ ተናግረዋል ፤ እንዲሁም የሁለት (2) የፀጥታ ኃይሎች ህይወት ማለፉን እንደሰሙ መረጃውን አካፍለዋል።

በዛሬው ዕለት አካባቢው ሙሉ በሙሉ እንዳልተረጋጋ ያሳወቁት አባላቶቻችን ተጨማሪ ህክምና እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ታካሚዎችን ወደ ባህር ዳርና ፓዊ ለመላክ መኪና እየተጠበቀ እንደሆነ አሳውቀዋል።

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መከላከል ዘርፍ ኃላፊ ኮማንደር ነጋ ጃራ ትላንት በወንበራና ቡለን ወረዳዎች ድጋሚ ግጭት መቀስቀሱን ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።

ኃላፊው 'ጸረ ሰላም' ያሏቸው አካላት ወንበራ ወረዳ መልካን በሚባለው ቀበሌ ውስጥ ገብተው ሰዎችን አፍነው ገንዘብ ሲቀነበሉ እንደነበርና በዚህም ሰላሳ (30) የአካባቢውን ነሪዎች አፍነው ገንዘብ በመቀበል መልቀቃቸውን አረጋግጠዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia