👆CMC ሚካኤል አካባቢ የደረሰውን የእሳት አደጋ የሚያሳዩ ፎቶዎች!
በአካባቢው ያሉ የቲክቫህ አባላት እስካሁን በአደጋው በሰው ላይ ስለደረሰ ጉዳት ማረጋገጥ ባይችሉም ፤ በእሳት አደጋው እስካሁን በውል ያልታወቀ ንብረት መውደሙን ገልፀዋል።
PHOTO: DANIEL GETACHEW
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

በአዲስ አበባ ከተማ በደረሰው የእሳት አደጋ 12 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ወደመ፤ የእሳት አደጋ መከላከል ሰራተኞች ጉዳት ደርሶባቸዋል!
ዛሬ 6 ሰዓት ከ25 ደቂቃ ላይ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ሲኤም ሲ በደረሰ የእሳት አደጋ 12 ሚሊዮን 856 ሺ 620 ብር የሚገመት ንብረት መውደሙን የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን ማስታወቁን አል አይን ዘግቧል።
የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ቡድን መሪ አቶ ጉልላት ጌታነህ አደጋው ከዚህ በላይም ጉዳት ሊያደረስ ይችል እንደነበር ተናግረዋል፡፡ በዚህም ከ 48 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረትን ከውድመት መታደግ መቻሉን አስታውቀዋል፡፡
አደጋውን ለመቆጣጠር አራት ሰዓት ከ15 ደቂቃ መፍጀቱን ያነሱት አቶ ጉልላት አምስት የአደጋ ሰራተኞች በሥራ ላይ ሳሉ ቀላል የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል ብለዋል፡፡
ከ70 በላይ የአደጋ መከላከል ሰራተኞችና ከ14 በላይ ከባድ ተሽከርካሪዎች ጥቅም ላይ መዋላቸውም የአል ዓይን መረጃ ይጠቁማል።

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተቋረጠውን ትምህርት ለማስቀጠል ማስታወቂያ አውጥቷል!
በሁሉም ደረጃ ያሉ ተማሪዎች ሳይሆን 'የድህረ ምረቃ ተማሪዎች' ብቻ በ2012 ዓ/ም ያቋረጡትን ትምህርታቸውን ለመቀጠል እንዲመዘገቡ ጥሪ ተደርጎላቸዋል።
1. የመደበኛ ፕሮግራም (Regular) ተማሪዎች መስከረም 4-6/2013 ዓ/ም
2. የእረፍት ቀን ፕሮግራም (Weekend) ተማሪዎች መስከረም 7-8/2013 ዓ/ም
ምዝገባ የሚከናወን ሲሆን የመደበኛ ፕሮግራም ተማሪዎች መስከረም 7 እንዲሁም የእረፍት ቀን ተማሪዎች መስከረም 9/2013 ዓ/ም ትምህርት ይጀምራል።

ነሃሴ 27/2012 ዓ/ም
የኢትዮጵያ የኮቪድ-19 መረጃዎች #1፦
#Somali
በሱማሌ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 585 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 4 ሰዎች በኮቪድ-19 መያቸው ተረጋግጧል።
#Oromia
በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 3,493 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 146 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። የአንድ ሰው ህይወት አልፏል።
በቫይረሱ ከተያዙት መካከል ፦
- 17 ከቄለም ወለጋ
- 16 ከሞጆ ከተማ
- 16 ከቢሾፍቱ ከተማ
- 12 ከፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን
- 10 ከምስራቅ ሀረርጌ
- 9 ከሻሸመኔ
- 9 ከአዳማ ይገኙበታል።
#BenishangulGumuz
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 260 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 5 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።
በቫይረሱ የተያዙት ፦
- 2 ከማኦና ኮሞ ልዩ ወረዳ
- 3 ከኩርሙክ ወረዳ
#Amhara
በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 6,189 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 84 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ የ2 ሰዎች ህይወት አልፏል (ከደ/ብርሃንና ቦሩሜዳ)
በቫይረሱ ከተያዙት መካከል፦
- 23 ከጎንደር ከተማ
- 16 ከሰ/ወሎ ዞን
- 9 ከሰ/ሸዋ ዞን
- 9 ከባህር ዳር ከተማ
- 6 ከምዕ/ጎንደር ዞን
- 5 ከደ/ጎንደር ዞን ይገኙበታል።
#Harari
በሀረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 890 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 80 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል። የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል።
@tikvahethiopiaBot

የአ/አ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ሲ.ኤም.ሲ አሊታድ ሚካኤል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የደረሰው የእሳት አደጋ ተዘዋውረው በመጎብኘት ተጎጂዎችን አጽናንተዋል፡፡
በንብረት ላይ የደረሰው ጉዳት ከባድ ቢሆንም በሰው ሕይወት ላይ ጉዳት አለመድረሱን ገልጸው የከተማ አስተዳደሩ በአደጋው የተጎዱ ወገኖችን ለማቋቋም አስፋላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ አረጋግጠዋል፡፡
#AddisAbabaPressSecretary
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በንብረት ላይ የደረሰው ጉዳት ከባድ ቢሆንም በሰው ሕይወት ላይ ጉዳት አለመድረሱን ገልጸው የከተማ አስተዳደሩ በአደጋው የተጎዱ ወገኖችን ለማቋቋም አስፋላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ አረጋግጠዋል፡፡
#AddisAbabaPressSecretary
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዛሬ CMC አሊታድ ሚካኤል አካባቢ የደረሰው የእሳት አደጋ መንስኤ እየተጣራ መሆኑን የቦሌ ክፍለ ከተማ የሰላም እና ጸጥታ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
በዛሬው አደጋ 12 ሚሊዮን ብር የሚገመት ፦
- 18 የንግድ ሱቆች ፣
- 11 መጋዘኖች እና
- አንድ ባርና ሬስቶራንት ጉዳት ደርሶባቸዋል።
48 ሚሊዮን የሚሆን ንብረት ደግሞ ለማዳን መቻሉ የአዲስ አበባ ከተማ የእሳት እና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የተገኘው መረጃ ያሳያል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በዛሬው አደጋ 12 ሚሊዮን ብር የሚገመት ፦
- 18 የንግድ ሱቆች ፣
- 11 መጋዘኖች እና
- አንድ ባርና ሬስቶራንት ጉዳት ደርሶባቸዋል።
48 ሚሊዮን የሚሆን ንብረት ደግሞ ለማዳን መቻሉ የአዲስ አበባ ከተማ የእሳት እና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የተገኘው መረጃ ያሳያል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 1,105 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ የ18 ሰዎች ህይወት አልፏል!
ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 21,360 የላብራቶሪ ምርመራ 1,105 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ18 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 416 ሰዎች አገግመዋል።
በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 54,409 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 846 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 19,903 ደርሷል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 21,360 የላብራቶሪ ምርመራ 1,105 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ18 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 416 ሰዎች አገግመዋል።
በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 54,409 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 846 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 19,903 ደርሷል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ነሃሴ 27/2012 ዓ/ም
የኢትዮጵያ የኮቪድ-19 መረጃዎች #2፦
#SNNPRS
በደቡብ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 2,616 የላብራቶሪ ምርመራ 56 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ የአንድ ሰው ህይወት አልፏል (ከወላይታ ዞን)
በቫይረሱ የተያዙት፦
- ከጌዴኦ 16 ( 8 ከዲላ ከተማ ፣ 4 ከዲላ ዙሪያ፣ 2 ከቡሌ ፣ 1 ከራጴ አና 1 ከአከሾ) ፣
- ከካፋ 13 ( 13ቱም ከቦንጋ ከተማ)፣
- ከወላይታ 7 (6 ከሶዶ ከተማ እና 1 ከዳሞት ጋሌ) ፣
- ከጉራጌ 5 (3 ከምሁር አክሊል እና 2 ከሶዶ)፣
- ከከንባታ ጠምባሮ 4 (4ቱም ከሺንሺቾ) ፣
- ከዳውሮ 3 (2 ተርጫ ከተማ እና 1 ከዛባ) ፣
- ሀዲያ 3 (1 ከሲራሮ፣ 1 ከሚሻ እና 1 ከጎምቦራ)
- ከሃላባ 1 ፣
- ከቤንች ሸኮ 1 (ሚዛን ከተማ)፣
- ከኮንታ 1 ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች እንዲሁም 2 ከሱማሌ ክልል የተገኙ ናቸው።
#Sidama
በሲዳማ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 696 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 5 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል።
በቫይረሱ የተያዙት፦
- 4 ከሀዋሳ ከተማ
- 1 ከወንዶ ገነት ወረዳ
#DireDawa
ድሬዳዋ ከተማ ባለፉት 24 ሰዓት 168 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 17 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።
#Afar
በአፋር ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 518 የላብራቶሪ ምርምራ የተደረገ ሲሆን 57 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።
@tikvahethiopiaBOT

"...ይህ አይነት ጎርፍ በከተማዋ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ነው" - አቶ ታደለ ዲሪርሳ (የመተሃራ ከተማ ከንቲባ)
የአዋሽ ወንዝ ሞልቶ በዛሬው ዕለት እንደ መተሃራ እና ወንጂ ያሉ የምስራቅ ሸዋ ከተሞች ላይ ጉዳት አድርሷል።
የመተሃራ ከተማ ከንቲባ አቶ ታደለ ዲሪርሳ ፥ ይህ አይነት ጎርፍ በከተማዋ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ነው ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
በሰው ላይ የደረሰው ጉዳት እስካሁን አለመመዝገቡን ይሁን እንጂ በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ከንቲባው አሳውቀዋል።
በጎርፍ በተጥለቀለቀው የከተማዋ አንደኛው ቀበሌ ወደ 20 ሺህ የሚገመቱ ነዋሪዎች መኖራቸውን የገለጹት አቶ ታደለ ተፈናቃዮችን ወደ ሌላኛው ቀበሌ እያሰፈሩ መሆኑን ገልፀዋል።
አሁንም ቢሆን የውሃ መጠኑ እየጨመረ በመሆኑ ተጨማሪ አደጋ እንዳይከሰት ከፍተኛ ስጋት እንዳለባቸው ከንቲባው ለቢቢሲ ተናግረዋል።

በአፋር ክልል አሚባራ ወረዳ ከትናንት ማታ አራት ሰዓት ተኩል ጀምሮ በሰባት (7) ቀበሌዎች ውስጥ ጎርፍ ተከስቷል።
ጎርፉ ከባድ በመሆኑ የከፋ ጉዳት ከማድረሱ በፊት በውሃ የተከበቡ ነዋሪዎችን በማውጣት በሌላ አካባቢ ለማስፈር በሄሊኮፕተር የታገዘ ጥረት እየተደረገ መሆኑን የአሚበራ ወረዳ የአርብቶ አደርና ግብርና ልማት ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
በአሚባራ ወረዳ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት አሁንም ጎርፉ እያስከተለ ያለው ጉዳት ከፍተኛ በመሆኑ ሁሉም አካል እንዲረባረብ / አቅም ተጠናክሮ ነዋሪዎችን እንዲታደግ ጥሪ አቅርበዋል።
PHOTO : SOCIAL MEDIA

"ገንዘቡ የታገደው በፕሬዘዳንት ትራምፕ ትዕዛዝና አመራር ነው" - Associated Press
አሜሪካ ለኢትዮጵያ ልትሰጥ የነበረውን 130 ሚልዮን ዶላር ገደማ በቅርቡ ያገደችው በፕሬዝደንት ትራምፕ ትእዛዝ እና አመራር መሆኑን ስቴት ዲፓርትመንት ያሉ ምንጮቼ ነግረውኛል ሲል AP ዘግቧል።
ይህም ኢትዮጵያ ከግብፅ እና ሱዳን ጋር ስታደርግ የነበረው ውይይት ውጤት አልባ መሆኑን ተከትሎ ኢትዮጵያን ተጠያቂ በማድረግ እንደሆነ ተጠቅሷል። በተጨማሪም "ስምምነት ላይ ሳይደረስ የግድቡን ሙሌት በቅርቡ በማከናወኗ" ነው ተብሏል።
ሙሉ የAP ዘገባ : https://apnews.com/7ce2f23741eed4886a09e39c0064b894
Via Elias Meseret (Associated Press)

በትግራይ ክልል በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ4 ሺህ አለፈ!
ከትግራይ ክልል ጤና ቢሮ የነሃሴ 27/2012 ሪፖርት እንዳገኘነው መረጃ ከ800 የላብራቶሪ ምርመራ 134 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል ፤ 25 ሰዎች አገግመዋል።
በቫይረሱ ከተያዙት 134 ሰዎች መካከል 44 ለይቶ ማቆያ ማዕከል የነበሩ ፣ 2 በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያላቸው ፣ 88 ደግሞ ከማህበረሰቡ የተገኙ ናቸው።
እስከሁን ድረስ በትግራይ ክልል 48,446 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 4,112 ሰዎች ኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፤ ከነዚህ መካከል የ21 ሰዎች ህይወት አልፏል ፣ 2,537 ሰዎች አገግመዋል።

የኬንያው አየር መንገድ ለጤና ባለሙያዎች የአውሮፕላን ቲኬት ቅናሽ ሊያደርግ ነው!
በአለም ዙሪያ የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች ወደ የትኛውም አቅጣጫ በኬንያ አየር መንገድ ሲጓዙ ግማሽ ክፍያውን አየር መንገዱ እንደሚሸፍን አስታወቀ፡፡
በመጪው መስከረም ወር የሚጀምረው ቅናሹ ቢዝነስ ክላስና ኢኮኖሚ ከላሰን እንደሚጨመርም ተጠቅሷል፡፡
እንደ አየር መንገዱ ገለፃ በአውሮፕላን ቲኬት 50 በመቶ ቅናሽ ለማድረግ የወሰነው የኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ ፊትለፊት በመጋፈጥ ህዝቦቻቸው ለሚያገለግሉ የጤና ባለሙያዎች ነው ብሏል፡፡
ወረርሽኝን ተከትሎ መንግስታት አየር መንገዶችን በረራ እንዲያቆሙ ከማስገደዳቸው አስቀድሞ፤ ብሔራዊው አየር መንገዱ ሊደርስ የሚችለውን ኪሳራ ለመቋቋም በመስራት ላይ እንደሆም ነው የተገለፀው።
የኬንያ የፓርላማ አባላት ያለፈው ሐምሌ ወር አየር መንገዱን ከኪሳራ ለመታደግ ድጋፍ ማድረግ እንደሚስፈልግ ድምጽ መስጠታቸውን ከአየር መንገዱ የተገኘው መረጃ ይጠቁማል #ENA

ችሎት!
አቶ ልደቱ አያለው በምስራቅ ሸዋ ዞን ቢሾፍቱ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት በሌላ መዝገብ ቀርበው ጉዳያቸው ታይቷል።
አቃቤ ህግ ፦
- እጃቸው ላይ የተገኘ የሽግግር መንግስት መመስረቻ ሰነድ የሚልና ለውጡን ተቃርኖ “ለውጡ ከድጡ ወደ ማጡ” የሚል ርእስ የተሰጠው የፖለቲካ ይዘት ያለውና ህገ መንግስቱን ለመናድ አልሞ የተዘጋጀ ሰነዶችን ተከትሎ ክስ ለመመስረት እየመረመርኩ ነው ብሏል።
አቶ ልደቱ አያሌው ፦
- የሽግግር መንግስት መመስረቻ ሰነድ በመንግስት ደረጃ አስገብቼው ተቀባይነት የለውም ተብዬ ያስቀመጥኩት ነው፤ ተጠያቂነት ቢኖረው ኖሮ መንግስት ተቀባይነት የለውም ብሎ ዝም አይለኝም ነበረ ብለዋል።
- “ለውጡ ከድጡ ወደ ማጡ” የሚለውም ቢሆን በረቂቅ ላይ ያለ ያልታተመ ነው፤ ልከሰስ የምችለው ሰነዱን አሳትሜ አሰራጭቼ ቢሆን ነበረ ፤ በዚህች ሀገር ላይ ሳንሱር የለም ስለዚህ ሀሳቤን ነው እየገለፅኩ ያለሁት፤ ፍርድ ቤቱ ይህንን ሊረዳልኝ ይገባል ብለዋል።
- ውጭ ሀገር ሄጄ የታከምኩት ሀብታም ነጋዴ ሆኜ ሳይሆን ፤ ህክምናው እዚህ ስለሌለ ነው፤ ይህንን ፍርድ ቤቱ ከግምት ያስገባልኝ” ሲሉ ጠይቀዋል።
የአቶ ልደቱ አያለው ጠበቃ ፦
- ለደንበኛቸው ዋስትና እንዲፈቅድላቸው ለፍርድ ቤቱ አመልክተዋል።
የሁለቱን ክርክር የተከታተለው ፍርድ ቤቱ መዝገቡን መርምሮ ብይን ለመስጠት ለዛሬ ከሰዓት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
Via Tarik Adugna (FBC)