TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#MEKEDONIA

መቄዶኒያ የአረጋውያንና አዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ከሁለት ሺህ በላይ በጎዳና የወደቁ አረጋዊያንን አዕምሮ ህሙማን ለማንሳት ህብረተሰቡ ጥቆማ እንዲሰጠው ጥሪ ማቅረቡን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ማዕከሉ በአዲስ አበባና ሐረር ከተሞች ከሁለት ሺህ በላይ አረጋውያንና አዕምሮ ህሙማንን ከጎዳና ለማንሳት እየሰራ ነው።

በአዲስ አበባ ከሁለት ሺህ በላይ አረጋዊያን እና የአእምሮ ህሙማንን ለማንሳት ማቀዱንና እስካሁን ከአንድ ሺህ በላይ ከጎዳና መነሳታቸውን በተመሳሳይ በሐረር ከተማ ለማንሳት ከታቀደው 110 አረጋውያንንና አዕምሮ ሕሙማን መካከል 60ዎቹን ማንሳቱን አስታውቀዋል።

መጋቢት 6 ቀን 2012 በሚሌኒየም አዳራሽ በተዘጋጀው የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ቃል የገቡ ግለሰቦችና ድርጅቶች ቃላቸውን እንዳልፈጸሙም ተገልጿል፡፡

በወቅቱ ቃል ከተገባው ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ሲሆን እስካሁን የተሰበሰበው ከ15 ሚሊዮን ብር እንደማይበልጥ ነው የተነገረው፡፡

ጥቆማ ለመስጠት ፦

- 094-49-49-49 ወይም
- 09-70-70-70-70 ይጠቀሙ።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ሩሲያ የኮቪድ-19 ክትባት ማምረት ጀመረች!

የሩሲያ ጤና ሚኒስቴር ሀገራቸው ለኮቪድ-19 የተዘጋጀውን ክትባት ማምረት መጀመሯን አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ በሰጠው መግለጫ በብዛት የሚመረተው ክትባት በያዝነው ወር መጨረሻ መከፋፈል እንደሚጀምር ገልጿል።

ነገር ግን የዘርፉ ተመራማሪዎች ሩሲያ በችኮላ ያመረተችው ክትባት ሌላ መዘዝ ይዞ እንዳይመጣ ስጋታቸውን እየገለጹ ነው።

Via BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
መልዕክት!

(ዶክተር ሊያ ታደሰ - የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስትር)

በዓለም ጤና ድርጅት (WHO) የቀረበው ማስክ የማድረግ ጥሪ በመቀላቀል በሀገራችን የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል እንዲሁም ለመቆጣጠር የተጀመረው የማህበረሰብ አቀፍ ንቅናቄና ምርመራ አንዱ አካል የሆነውን የ"ማስክ ኢትዮጵያ" ዘመቻ በትላንትናው እለት ጀምረናል።

ሁላችንም ማስክን በትክክል በማድረግ ራሳችንንም፣ ወገኖቻችንንም፣ ከበሽታ እንጠብቅ!

አንድም ሰው በበሽታ እንዲያዝ፣ ምክንያት አንሁን!!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጋዜጠኞች ስለ ጣና ሀይቅ ጉዳይ ይመክራሉ!

ዳጉ ኮሚንኬሽን ሃላ/የተ/የግ/ማህበር 'ጣና፤ታላቁ የህዳሴ ግድብ ህልውና!" በሚል መሪ ቃል ዛሬ ነሀሴ 09/2012 ዓ/ም 10 ሰዓት በኢትዮጵያ ሆቴል ያዘጋጀውና የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ማህበር አባላት እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች ብቻ የሚገኙበት መድረክ ይካሄዳል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ነሃሴ 9/2012 ዓ/ም

የኢትዮጵያ የኮቪድ-19 መረጃዎች #1 ፦

#Oromia

በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 3448 የላብራቶሪ ምርምራ ተደርጎ 202 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

በቫይረሱ ከተያዙት መካከል ፦

- 32 አ/አ ከተደረገ ምርመራ
- 22 ቡራዩ
- 18 ጉጂ ዞን
- 18 ገላን
- 17 ምዕራብ ሸዋ
- 14 ሞጆ
- 14 ቢሾፍቱ
- 12 ሰበታ ይገኙበታል።

#BenishangulGumuz

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 645 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 3 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

- 1 ከአሶሳ ዞን አሶሳ ወረዳ
- 1 ከመተከል ዞን ግልገል በለስ ከተማ
- 1 ከብልዲግሉ ወረዳ

#Afar

በአፋር ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 453 የላብራቶሪ ምርምራ ተደርጎ 13 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

አጠቃላይ በአፋር ፦

- 409 በቫይረሱ የተያዙ
- ያገገሙ 191

#Tigray

በትግራይ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 1,384 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 196 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል.

አጠቃላይ በትግራይ ፦
- 1,688 በቫይረሱ የተያዙ
- 11 ሞት
- 764 ያገገሙ

#DireDawa

ድሬዳዋ ከተማ ባለፉት 24 ሰዓት 352 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 19 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል። ሁሉም ከማህበረሰቡ በተወሰደ ናሙና የተገኙ ናቸው።

#Sidama

በሲዳማ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 703 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 75 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

#Somali

በሱማሌ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 265 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 12 ሰዎች በኮቪድ-19 ተይዘዋል።

- 6 ጅግጅጋ
- 4 ሞያሌ
- 2 ጎዴ

@tikvahethiopia
በኢትዮጵያ በአንድ ቀን 1,652 ሰዎች በኮቪድ-19 ተያዙ!

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 22,252 የላብራቶሪ ምርመራ 1,652 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ17 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 377 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 28,894 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 509 ደርሷል ፤ እንዲሁም አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 12,037 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ነሃሴ 9/2012 ዓ/ም

የኢትዮጵያ የኮቪድ-19 መረጃዎች #2 ፦

#Amhara

በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 6,011 የላብራቶሪ ምርመራ 90 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። የሁለት (2) ሰዎች ህይወት አልፏል።

ከነዚህ መካከል፦

- 26 ከምዕ/ጎንደር ዞን
- 22 ከባህር ዳር
- 13 ከሰ/ሸዋ ዞን
- 10 ከደ/ወሎ ዞን
- 8 ከደሴ ከተማ ይገኙበታል።

ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ፦

- 1 ከሰ/ሸዋ ዞን
- 1 ከደሴ ከተማ

#Harari

በሐረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 687 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 6 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።

አጠቃላይ በሀረሪ ፦
- 472 በቫይረሱ የተያዙ
- 14 ሞት
- 80 ያገገሙ

#SNNPRS

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በደቡብ ክልል በተደረገው 1053 የላብራቶሪ ምርመራ 48 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል ፤ የሶስት (3) ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ 35 ሰዎች አገግመዋል።

በቫይረሱ ከተያዙት መካከል ፦

- 29 ከወላይታ
- 4 ከኮንሶ
- 3 ከጉራጌ
- 2 ከስልጤ
- 2 ከጎፋ
- 2 ከየም ልዩ ወረዳ
- 2 ከቤንች ሸኮ
- 1 ከጋሞ፣ 1 ከሀላባ፣ 1 ከከምባታ ጠምባሮ፣ 1 ደ/ኦሞ ዞኖች ይገኙበታል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ATTENTION

ይህ የቀብር ስነ ስርዓት ዛሬ በስልጤ ዞን አልቾ ውሪሮ ወረዳ የተፈፀመ ነው፤በቡኔ ቀበሌ የ80 አመት አዛውንት በህክምና ሲረዱ ቆይተው በዛሬው እለት ህይወታቸው አልፏል።

አዛውንቱ ቫይረሱ ከተገኘባቸው ጊዜ ጀምሮ በወራቤ ኢትዮ ቻይና የኮሮና ህክምና ማእከል የህክምና ድጋፍ ሲደረግላቸው ቆይተዋል።

ቀብር ስነ ስርአቱ ወቅት ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ለኮሮና ቫይረስ ተጋላጭ እንዳይሆኑ በጤና ባለሙያዎች ተፈፅሟል። ይህን መረጃ ያገኘነው ከወረዳው ህዝብ ግንኙነት ዩኒት ነው።

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በሀገራችን ከትልልቅ ከተሞች ውጭ ባሉ ወረዳዎች፣ ቀበሌዎች፣ የገጠር አካባቢዎችም ጭምር እየተስፋፋ ይገኛል ፤ ሁኔታው ከቁጥጥር ውጭ እንዳይወጣ ሁላችንም ኃላፊነታችንን እንወጣ።

አንድም ሰው በበሽታው እንዲያዝ፣ምክንያት አንሁን!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በኮሮና የተያዘው ታዋቂው የአፋን ኦሮሞ ድምፃዊ ኢቲቃ! (በቢቢሲ የአማርኛው አገልግሎት የተዘጋጀ) በአፋን ኦሮሞ የፖለቲካ ዘፈኖቹ የሚታወቀው ድምጻዊ ኢቲቃ ተፈሪ በኮሮና ቫይረስ መያዙን ካወቀ/ከተረጋገጠ ሳምንታት መቆጠሩን ለቢቢሲ ተናግሯል። ድምጻዊው "በሽታው እንዲህ አይነት ቦታ ያዘኝ ብዬ መናገር አልችልም" ካለ በኋላ የሚጠረጥረው ስፍራ እንዳለ ግን ገልጿል። ድምጻዊው ሃጫሉ ሁንዴሳ በተገደለበት…
ድምፃዊ ኢቲቃ ተፈሪ ከኮቪድ-19 አገገመ!

ከጥቂት ቀናት በፊት በአፋን ኦሮሞ የትግልና ፖለቲካ ሙዚቃዎቹ የሚታወቀው ድምፃዊ ኢቲቃ ተፈሪ በኮሮና ቫይረስ ተይዞ በሚሊኒየም አዳራሽ ህክምና ማዕከል ከዛም በቤቱ የህክምና ክትትል ሲደረግለት እንደነበረ መገለፁ አይዘነጋም።

ድምፃዊ ኢቲቃ ዛሬ በይፋዊ ፌስ ቡክ ገፁ ከበሽታው #ማገገሙን ያስታወቀ ሲሆን ሁሉም ሰው እራሱን እንዲጠብቅ ፣ የሚተላለፉ የጤና ባለሞያ ምክሮችን እንዲተገብር ፣ አካላዊ ርቀትን እንዲጠብቅ ፣ ማስክ እንዲያደርግ ፣ የእጅን ንፅህና እንዲጠብቅ ምክሩን አስተላልፏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ቴሌግራም 'Video Call' ጀመረ!

ቴሌግራም ትላንት ሰባተኛ ዓመቱን ይዟል፤ ይህ መተግበሪያ አገልግሎት መሰጠት የጀመረበትን ሰባተኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ አዲስ ይዘት ይዞ ቀርቧል ይኸውም 'Video Call' ነው።

ቴሌግራም አሁን ላይ በዓለም '400 ሚሊዮን' ተጠቃሚዎች ያሉት እና ከ10 በብዛት ዳውንሎድ ከተደረጉ መተገበሪያዎች አንዱ መሆን ችሏል።

ቴሌግራም Video Call ለመጠቀም በመጀመሪያ አሁን ላይ እየተጠቀማችሁ የምትገኙትን መተግበሪያ PlayStore ላይ ገብታችሁ #update ልታደርጉት ይገባል።

https://play.google.com/store/apps/details?id=org.telegram.messenger

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የሲዳማ ብሔር ቋንቋ እና ባህል 26ኛ ሲምፖዚየም ዛሬ ነሃሴ 10/2012 በሀዋሳ ከተማ 'ሲዳማ ባህል አዳራሽ' እየተካሄደ ይገኛል።

PHOTO : SMN
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኮቪድ-19 በአዲስ አበባ ከተማ ከነሃሴ 1-7/2012 ዓ/ም ሲቃኝ!

ባለፈው አንድ ሳምንት ከነሃሴ 1 - 7/2012 ዓ/ም በአጠቃላይ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ 3,016 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን የ93 ሰዎች ህይወት አልፏል።

በአጠቃላይ በበሽታው እስከ ነሃሴ 7/2012 ዓ/ም ድረስ በአዲስ አበባ ውስጥ የተያዙት ሰዎች ብዛት 17,335 ሲሆን ባለፈው ሳምንት ብቻ በበሽታው የተያዙት ሰዎች ከአጠቃላዩ 17.4 % መሆኑን ያሳያል።

በአጠቃላይ 377 ሰዎች በአዲስ አበባ በኮቪድ-19 ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን 25 % የሚሆነው የሞት መጠን የተመዘገበው በያዝነው ወር መጀመሪያ በነበሩት ሰባት ቀናት ብቻ ነው።

ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AFAR

በአፋር ክልል በጎርፍ ለተፈናቀሉ ዜጎቻችን የሚደረጉ ድጋፎች ተጠናክረው መቀጠላቸውን የክልሉ የአደጋ መከላከልና መቆጣጠር ምግብ ዋስትና ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።

የክልሉ የአደጋ መከላከል እና መቆጣጠር ምግብ ዋስትና ጽሕፈት ቤት ሀላፊ አቶ መሀመድ ሁሴን እንደገለጹት ፤ በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች በቅርቡ የተከሰተው ድንገተኛ የጎርፍ አደጋ በርካቶችን አፈናቅሏል።

በአደጋው እስከአሁን የሰው ህይወት ባያልፍም ከፍተኛ ቁጥር ባለው አርብቶ አደር ህብረተሰብና በእንስሳቱ ላይ የደረሰው ጉዳት ከፍ ያለ እንደሆነ አብራርተዋል።

አቶ መሀመድ እንደገለጹት በአሁኑ ወቅት ችግሩ ይበልጥ ጉዳት እንዳያደርስ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡

የደረሰውን ጉዳት አስመልክቶ የክልል እና የፌዴራል መንግስትን ጨምሮ የተለያዩ ክልሎች እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጀቶች ድጋፍ እያደረጉ መሆናቸውንም ገልጸዋል።

በሌላ መረጃ የአፋር ሰብዓዊ መብት ድርጅት ከአለም አቀፍ ለአፋር ሰብዓዊ ድጋፍ አስተባባሪ ግብረ ሀይል ጋር በመሆን በመጪው እሁድ August 16/2020 አለም አቀፍ የድጋፍ ማሰባሰብ ዘመቻ ሊያካሂድ እንደሆነ ሰምተናል።

ዘመቻው ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ሲሆን እሁድ ከቀኑ 12pm በዲሲ አካባቢ ሰዓት አቆጣጠር ጀምሮ በቀጥታ ስርጭት ተዋቂ ሰዎች፣ የሀይማኖት የአባቶች ፣ የተለያዩ የማህበረሰብ አካላት እና ተቋማት መሪዎች በሚሳተፉበት የድጋፍ ማሰባሰብ ይካሄዳል ተብሏል።

ምንጭ፦ ኢዜአ፣ አሰመድ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኦሮሚያ ክልል በ24 ሰዓት የ8 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 185 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል!

በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው የ3,537 የላብራቶሪ ምርመራ 185 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጣል።

በቫይረሱ ከተያዙት መካከል ፦

- 68 ሰዎች ከአርሲ
- 21 ሰዎች ከምስራቅ ሀረርጌ
- 18 ሰዎች ከቄለም ወለጋ
- 16 ሰዎች ከቡራዩ ከተማ ይገኙበታል።

በተመሳሳይ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የስምንት (8) ሰዎች ሕይወት ማለፉን የኦሮሚያ ጤና ቢሮ በዕለታዊ ሪፖርቱ አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በጎንደር ከተማ በዛሬዉ ዕለት (10/12/2012 ዓ/ም) በኮቪድ- 19 ወረርሽኝ ምክንያት የመጀመሪያው ሞት ተመዘገበ!

በጎንደር ከተማ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ ሶስት (3) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጎንደር ከተማ አስዳተደር ጤና መምሪያ አስታውቋል።

በከተማይቱ ዛሬ የመጀመሪያው ሞት እንደተመዘገበ እና ህብረተሰቡ ከመቸውም ጊዜ በላይ ጥንቃቄውን #እንዲያጠናክር የከተማ አስተዳደሩ ጤና መምሪያ መልዕክት አስተላልፏል።

ሦስቱም (3) ተኝተው ታካሚዎች ሲሆኑ አንዱ ታካሚ ናሙና ተወስዶ ውጤቱ ሳይታወቅ ህይወቱ ያለፈ ሲሆን የናሙና ውጤቱ ግለሰቡ በኮሮና ቫይረስ የተያዘ እንደሆነ አረጋግጧል።

በአጠቃላይ በከተማዉ ኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ወደ 26 ከፍ ብሏል፡፡ እስካሁን ባለው መረጃ መሠረት በቫይረሱ ተይዘው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 11 ደርሷል።

ምንጭ፦ የጎንደር ከተማ ኮሚኒኬሽን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia