አጫጭር መረጃዎች ፦
- በትግራይ 5ኛው ሞት ተመዝግቧል፤ በሌላ በኩል ባለፉት 24 ሰዓት 59 ሰዎች በኮሮና ተይዘዋል አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 1,016 ደርሰዋል።
- በኦሮሚያ ክልል ባልፉት 24 ሰዓት 85 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል ከነዚህ መካከል 22 ሰዎች ከሻሸመኔ ከተማ፣ 26 ሰዎች ከምሥራቅ ሸዋ ይገኙበታል።
- በአፋር ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 9 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።
- በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ አስር (10) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል ፤ ከአስሩ አራቱ (4) ከባህር ዳር ከተማ ናቸው።
- በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 39 የላብራቶሪ ምርመራ 1 ሰው በቫይረሱ መያዙ ተረጋግጧል።
- በሐረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 24 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ የአንድ ሰው ህይወት አልፏል።
- በደ/ብ/ብ/ሕ/ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 713 የላብራቶሪ ምርመራ 17 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል ፤ 8 ከወላይታ እና 9 ከኮንሶ ዞን ናቸው።
- በድሬዳዋ ከተማ ባለፉት 24 ሰዓት 4 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።
- በአዲስ አበባ ባለፉት 24 ሰዓት 324 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ 15 ሰዎች ሞተዋል (11 ከአስክሬን ምርመራና 4 ከጤና ተቋም)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

#NewsAlert
ንብረትነቱ የኤር ኢንዲያ ኤክስፕረስ (Air India Express) የሆነው የበረራ ቁጥሩ IX-1344 የነበረው አውሮፕላን በሕንድ ደቡባዊ ግዛት ኬራላ በሚገኝ አየር ማረፊያ 191 ሰዎችን አሳፍሮ ለማረፍ ሲንደረደር መከስከሱን ባለሥልጣናት ማስታወቃቸውን ቢቢሲ ዘገበ።
ከዱባይ የተነሳው አውሮፕላኑ በካሊከት ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ለማረፍ በመንደርደር ላይ ሳለ ተንሸራቶ ለሁለት መከፈሉን የሕንድ አቪየሽን ባለሥልጣን ገልጿል።
በስፍራው የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ተሰማርተው ርብርብ እያደረጉ ይገኛሉ።
በአደጋው እስካሁን በትንሹ አብራሪውን ጨምሮ ሁለት (2) ሰዎች መሞታቸውንና በርካታ መንገደኞች መጎዳታቸውን የአየር መንገዱ ቃል አቀባይ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
አውሮፕላኑ 10 ህፃናትን ጨምሮ 184 መንገደኞችን እንዲሁም ሁለት አብራሪዎችን ጨምሮ ስድስት የበረራ ሰራተኞችን አሳፍሮ ነበር።
ምንጭ፦ BBC

#UPDATE
በኤር ኢንዲያ ኤክስፕረስ የአውሮፕላን መከስከስ አደጋ የሞቱ ሰዎች ቁጥር አስራ ስድስት (16) መድረሱን ከኤዢያ ኒውስ ኢንተርናሽናል [ANI] ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
ከዚህ በተጨማሪ በአውሮፕላን መከስከስ አደጋው አንድ መቶ ሃያ ሶስት (123) ሰዎች ተጎድተዋል ፤ አስራ አምስት (15) ሰዎች ደግሞ በፅኑ መጎዳታቸው ተገልጿል።

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በፕሬዘዳንት ክፍት የስራ ቦታ ላይ አመልካቾችን አወዳድሮ ለመሾም ይፈልጋል !
ተፈላጊ ችሎታ ፦
1. ሶስተኛ ዲግሪ (PHD) ወይም ሁለተኛ ዲግሪ (Masters) ትምህርት ዝግጅት ያላት/ያለው እና ፕሮፌሰር ወይም ተባባሪ ፕሮፌሰር ወይም ረዳት ፕሮፌሰር ማዕረግ ያላት/ያለው
2. በከፍተኛ ትምህርት ተቋም ውስጥ በተለያዩ ደረጃዎች በአመራርነት የስራ ልምድ ያላት/ያለው ወይም ከዚህ ውጪ ባለ መስክ በከፍተኛ አመራርነት የተረጋገጠ የስራ ልምድ ያላት/ያለው
3. ከ 5 ገጽ ያልበለጠ እስትራቴጃካዊ እቅድ ከተቋሙ ተልኮ አንፃር በማዘጋጀት ተቋሙ አሁን ከነበረበት ወደከፍታ ለማሸጋገር የሚያስችል ስልት አዘጋጅቶ ለተቋሙ ማህበረሰብ በግንባር ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
ተወዳዳሪዎች የትምህርት ደረጃ ፤ የስራ ልምድ ፤ ሲቪ ፤ እስትራቴጂያዊ እቅድ ፤ እንዲሁም ሌሎች ለዚህ ዉድድር ይጠቅማል የሚሉትን ማስረጃ በታሸገ እንቭሎፕ አድርገዉ ይህ ማስታወቅያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ 10 የስራ ቀናት ዉስጥ ብሎክ 14 ቢሮ ቁጥር F2 ዘወትር በስራ ሰዓት ገቢ ማድረግ ወይም በአማረጭ መወዳደሪያ ሰነዳቸውን እስካን በማድረግ በኢሜል [email protected] OR [email protected] መላክ ይኖርባቸዋል፡፡

የአፍና አፍንጫ መሸፈኛዎን በአግባቡ ያስወግዱ!
የተጠቀሙበትን የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ክዳን ባለው መጣያ ካልጣሉ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) እንዲሰራጭ ምክንያት ይሆናል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የተጠቀሙበትን የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ክዳን ባለው መጣያ ካልጣሉ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) እንዲሰራጭ ምክንያት ይሆናል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Congratulations!
ዛሬ ከወሎ ዩኒቨርሲቲ የድህረ ምረቃ ትምህርታችሁ በስኬት አጠናቃችሁ የተመረቃችሁ ተማሪዎች በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ ፤ እንኳን ለዚህች ቀን አበቃችሁ ለማለት እንወዳለን።

ወሎ ዩኒቨርሲቲ 419 ተማሪዎችን አስመረቀ!
ወሎ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ ፣ በኤክስቴንሽን እና በክረምት መርሃ ግብር ያስተማራቸውን ተማሪዎች በዛሬው ዕለት በኦንላይ አስመርቋል።
ዩኒቨርሲቲው በደሴ እና በኮምቦልቻ ካምፓስ በ49 የድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች በመደበኛ ፣ በኤክስቴንሽንና በክረምት መርሃ ግብር ያስተማራቸውን ተማሪዎች ነው ያስመረቀው።
የወሎ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት ሃምሌ 30/2012 ዓ/ም ባደረገው ስብሰባ በተለያዩ የድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ውጤት መርምሮ ዛሬ እንዲመረቁ ባፀደቀው መሰረት በደሴ እና በኮምቦልቻ ካምፓስ ወንድ 350 ፣ ሴት 69 በድምሩ 419 ተማሪዎች ተመርቀዋል።

ምክንያት አልሆንም!
የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት የኮሮና ቫይረስ በሽታ ለመከላከልና በልዩ ትኩረት በሽታውን ለመቆጣጠር የሚያስችል የማህበረሰብ ንቅናቄ እና ምርመራ (ማንም) ዘመቻ፡ 'ምክንያት አልሆንም' በሚል መሪ ቃል ይፋ አድርገዋል፡፡
የዘመቻው ዋነኛ አላማ ማንኛውም ሰው ለቫይረሱ መስፋፋት ምክንያት ላለመሆን ራሱን የሚከላከልበት ፣ ከራሱ አልፎ ቤተሰቡን እንዲሁም አካባቢውን የሚጠብቅበት እና በተሰማራበት ሙያ ሁሉ ሃላፊነት በመውሰድ በእኔነት ስሜት ለራሱ ቃል የሚገባበት ነው ተብሏል።

ህወሓት ወደ አዲስ አበባ ሽማግሌ ልኳል ?
ከሰሞኑን በአንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በፌደራል መንግስቱና በትግራይ ክልል መንግስት መካከል ያለውን አለመግባባት ለመፍታት ህወሓት ለሽምግልና በዶ/ር አዲስአለም ባሌማ የተመራ ቡድን ወደ አዲስ አበባ ልኳል ተብሎ ሲነገር ነበር።
በዚህ ጉዳይ የቀድሞ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የነበሩት የህወሓት ከፍተኛ አመራር ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም '#አባይ' ከተባለ ሚዲያ ስለጉዳዩ እውነትነት ጥያቄ ቀርቦላቸው 'ሲናፈስ የነበረው ነጭ ውሸት ነው፣ ህወሓት ሽማግሌ አላከም፣ ሊልክም አይችልም' ሲሉ መልስ ሰጥተዋል።
በሌላ በኩል ወ/ሮ ኪሪያ ህወሓት አሁንም ለውይይት ዝግጁ መሆኑን ነገር ግን አሁን ያለው ችግር ሀገራዊ ስለሆነ ጉዳዩን የህወሓት እና የብልፅግና ፓርቲ ብቻ አድርጎ መወሰድ እንደሌለበት ፤ ሁሉንም ወገን ያካተት፣ ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚሳተፉበት የውይይት መድረክ ከተዘጋጀ ፓርቲው እንደማንኛው ፓርቲ ለመሳተፍ ዝግጁ እንደሆነ አሳውቀዋል።
ወ/ሮ ኪሪያ 'በህወሓት እና በብልፅግና ፓርቲ መካከል ብቻ የሚደረግ የውይይት መድረክ ሊሆን አይችልም ፤ ከዚህ ቀደም ወደ መቐለ መጥተው ለነበሩት የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች የተሰጠው ሀሳብም ይኸው ነው ፤ አሁንም የያዝነው አቋም ይህ ነው' ብለዋል።

ጆሃንስበርግ አቅራቢያ የሚገኘው የወል መቃብር!
የኮሮና ቫይረስ በሽታ/ኮቪድ-19 ከተስፋፋባቸው የዓለማችን እንዲሁም የአፍሪካ ሀገራት ውስጥ ደቡብ አፍሪካ አንዷ ናት።
ከቪኦኤ እንደተገኘው መረጃ የሀገሪቱ ባለሥልጣናቱ የወል የቀብር ስፍራ አዘጋጅተዋል። እስካሁን ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በኮቪድ-19 ምክንያት ከ9,900 በላይ ሰዎች ሞተዋል።
ከላይ በፎቶው የምትመለከቱ የወል መቃብር ሥፍራ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ጆሃንስበርግ ከተማ አቅራቢያ የሚገኝ ነው።
በደቡብ አፍሪካ እስከዛሬ 545,476 ሰዎች በኮሮና ቫይስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከ394,000 በላይ ሰዎች አገገመዋል።

በኦሮሚያ ክልል በኮሮና የተያዙ ሰዎች ከ1,900 አለፉ!
በኦሮሚያ ክልል ያለው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ከዕለት ወደ ዕለት በእጅጉ እየጨመረ ነው።
ባለፉት 24 ሰዓት ከተደረገው 2,139 የላብራቶሪ ምርመራ ውስጥ 111 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
ከአንድ መቶ አስራ አንዱ (111) በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ከተረጋገጠ ሰዎች መካከል ሰላሳ ሁለቱ (32) ሰዎች ነቀምቴ ከተማ ናቸው።
በአጠቃላይ በክልሉ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 1,932 የደረሰ ሲሆን ከነዚህ መካከል 25 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

የቲክቫህ የትዊተር ገፅ!
ትዊተር ላይ የምታዘወትሩ የቲክቫህ አባላት የኢትዮጵያን ሀገር አቀፍና የክልል የኮቪድ-19 ሪፖርቶች ከታች ባለውን ሊንክ ማግኘት ትችላላሁ።
TIKVAH-ETHIOPIA https://twitter.com/tikvahethiopia?s=09 (@tikvahethiopia):

በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ከ22 ሺህ አለፉ!
ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 10,919 የላብራቶሪ ምርመራ 801 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ10 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 292 ሰዎች አገግመዋል።
በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 22,253 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 390 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 9,707 ናቸው።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 10,919 የላብራቶሪ ምርመራ 801 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ10 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 292 ሰዎች አገግመዋል።
በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 22,253 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 390 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 9,707 ናቸው።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያና ጎረቤት ሀገራት የኮቪድ-19 ስርጭት!
በኢትዮጵያ ፣ ኬንያ ፣ ሱማሊያ፣ ጅቡቲ፣ ሱዳን ፣ ደቡብ ሱዳን እና ኤርትራ በአጠቃላይ 71,297 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል።
ከኤርትራ ውጭ በስድስቱ ሀገራት የ1,780 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ በአጠቃላይ 36,080 ሰዎች በተደረገላቸው ህክምና ከበሽታው አገግመዋል።
በኢትዮጵያና በጎረቤት ሀገራት ያለውን የኮቪድ-19 ወቅታዊ መረጃ ከ CARD ጋር በመተባበር ባዘጋጀነው ምስል ከላይ መመልከት ትችላላችሁ።

የቲክቫህ ኢትዮጵያ የትዊተር ገፅ አማራጭ!
ምንም እንኳን ከ8 ዓመት በፊት የትዊተር ገፁ የተከፈተ ቢሆንም አክቲቭ ሳይሆን እስከዛሬ ቆይቷል።
ከዛሬ ጀምሮ ለመላው የቲክቫህ አባላት ትዊተር ላይ አማራጭ የመረጃና የሀሳብ መለዋወጫ ሆኖ ቀርቧል።
በተለይ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ሀሳቦቻችሁ ለመስጠትና እርስ በእርስ ፍፁም መከባበር በተሞላበት መልኩ ለመነጋገር የትዊተር ገፁን እንደ አማራጭ ተጠቀሙት።
የትዊተር ተጠቃሚዎች ገፁን TIKVAH-ETHIOPIA https://twitter.com/tikvahethiopia?s=09 (@tikvahethiopia): ታገኛላችሁ!

በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የኮቪድ-19 ምርመራ ተጀመረ!
የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ በሀገር ደረጃ የምርመራ አቅምን ለማሳደግ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ማእከል ከፍቶ ትናንት ስራ ማስጀመሩን ኢዜአ ዘግቧል።
ዩኒቨርሲቲው በጎባ ከተማ የኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ምርመራ ለማስጀመር እንዲቻል የላብራቶሪ መመርመሪያ መሳሪያውን በድጋፍ ያገኘው ከወለጋ ዩኒቨርሲቲ መሆኑም ተመልክቷል፡፡
አገልግሎት መስጠት የጀመረው የምርመራ መሳሪያ በቀን እስከ አራት መቶ ናሙና የመመርመር አቅም አለው ተብሏል።