#TIGRAY
የትግራይ ክልል ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 'አስቸኳይ ጉባኤ' በክልሉ ሕገ-መንግስት ማሻሻያ ማድረጉን ጋዜጠኛ ሚሊዮን ኃይለስላሴ ዘግቧል፡፡
ምክር ቤቱ የሕገ መንግስቱ አንቀፅ 48 ቁጥር ሁለት የቀየረ ሲሆን ፣ በዚህም መሰረት የምርጫ ስርዓቱ ከአብላጫ ድምፅ ወደ ቅይጥ (mixed) ቀይሯል፡፡
Via Million Haileselase /DW
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

#UPDATE
የፈረንሳይ ፕሬዘዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ዛሬ ሊባኖስ (ቤሩት) ገብተዋል ፤ ፕሬዘዳንቱ ከትላንት በስቲያ ከባድ ፍንዳታ የደረሰበትን አካባቢ ጎብኝተዋል፤ ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖችን አፅንናንተዋል።
በአሁን ሰዓት ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ከሊባኖስ ዋነኛ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እንዲሁም ከሲቪክ ማህበራት ተወካዮች ጋር ውይይት እያደረጉ ይገኛሉ።

TIKVAH-ETHIOPIA
አቶ ጀዋር መሐመድ ፣ አቶ በቀለ ገርባና አቶ ሐምዛ አዳነን ጨምሮ 14 ተጠርጣሪዎች ዛሬ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ! በእነ አቶ በቀለ ገርባ እና አቶ ሐምዛ አዳነ የምርመራ መዝገብ ላይ በዋስትና ጥያቄ ጉዳይ እና ዐቃቤ ህግ የጊዜ ቀጠሮ መዝገብ ተዘግቶ ለቀዳሚ ምርመራ ችሎት እንዲመራኝ ብሎ ባቀረበው ጥያቄ ላይ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ከሰዓታት በኃላ ትዕዛዝ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡…
ችሎት!
የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አቶ ጃዋር መሀመድና እና አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ 14 ተጠርጣሪዎች ላይ አቃቤ ህግ የቅደመ ምርመራ ምስክሮችን እንዲያሰማ ብይን ሰጠ።
አቶ ጃዋር መሀመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ እንዲሁም አቶ ሐምዛ አዳነን ጨምሮ 14 ተጠርጣሪዎች በዛሬው እለት በፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ቀርበዋል።
ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ ጃዋር መሃመድን ጨምሮ አጠቃላይ 14 ተጠርጣሪዎች አቶ ጃዋር መሃመድ በሚል መዝገብ በመዝገብ ቁጥር 215585 ላይ የቅድመ ምርመራ መዝገብ ከፍቷል።
በተጨማሪም በዚህ መዝገብ ቁጥር (215585) ሁከት እና ብጥብጥ በማነሳሳት ወንጀል የተጠረጠረ አንድ ጋዜጠኛ ተካቷል #More : https://telegra.ph/fbc-08-06
Via Tarik Adugna (FBC)

በኢትዮጵያ በአንድ ቀን 429 ሰዎች አገገሙ!
ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 9,068 የላብራቶሪ ምርመራ 564 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ9 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 429 ሰዎች አገግመዋል።
በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 20,900 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 365 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 9,027 ናቸው።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 9,068 የላብራቶሪ ምርመራ 564 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ9 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 429 ሰዎች አገግመዋል።
በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 20,900 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 365 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 9,027 ናቸው።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር መረጃዎች ፦
- በትግራይ ክልል 4ኛው የኮሮና ቫይረስ ሞት ተመዝግቧል ከዚህ በተጨማሪ ባለፉት 24 ሰዓት 60 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
- በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 101 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ከነዚህ መካከል ከባሌ 18፣ ምስራቅ ሸዋ 16፣ ጅማ 6 ፣ ነቀምቴ 9 ሰዎች ይገኙበታል።
- በሱማሌ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 27 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል፤ ሁሉም የጅግጅጋ ነዋሪዎች ናቸው።
- በአፋር ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ሁለት (2) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዡ 294 ደርሰዋል።
- በቢኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ከተደረገው 115 የላብራቶሪ ምርመራ 9 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
- በሐረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 41 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል ፤ ከነዚህ መካከል ሃያ አንዱ (21) ከሀኪም ወረዳ ናቸው።
- በድሬዳዋ ከተማ ባለፉት 24 ሰዓት 1 ሰው ሲሞት 3 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። በከተማው የሟቾች ቁጥር 17 የደረሰ ሲሆን 521 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።
- በሲዳማ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ከተደረገው 184 የላብራቶሪ ምርመራ ስድስት (6) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።
- በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 15 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል ፤ ከነዚህ መካከል 5 ከኦሮሞ ብ/ሰብ ዞን ባቲ ከተማ ፣ 4 ከአዊ ብ/ሰብ ዞን ይገኙበታል።

ከሰሞኑን በድሬዳዋ '21 የጤና ባለሞያዎች' በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው በተለያዩ ሚዲዎች ሲገለፅ እንደነበር አይዘነጋም።
የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ በዛሬው ዕለታዊ መግለጫው በኮሮና ቫይረስ የተያዙት 21 ሰዎች የጤና ባለሞያዎች እና በጤና ተቋት የተለያዩ ዘርፎች ሰራተኞች እንደሆኑ አሳውቋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ በዛሬው ዕለታዊ መግለጫው በኮሮና ቫይረስ የተያዙት 21 ሰዎች የጤና ባለሞያዎች እና በጤና ተቋት የተለያዩ ዘርፎች ሰራተኞች እንደሆኑ አሳውቋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE
በሊባኖስ ዋና ከተማ ቤይሩት በነበረው ፍንዳታ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 157 ደርሷል ፤ ከ5,000 በላይ ሰዎች የተጎዱ ሲሆን የሟቾችና ተጎጂዎች ቁጥር እንደሚጨምር ይጠበቃል።
በሌላ በኩል ሊባኖስ ከከባዱ ፍንዳታ በኃላ ባለፉት 24 ሰዓት 255 በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎችን ሪፖርት አድርጋለች ፤ ይህ በሀገሪቱ በአንድ ቀን የተመዘገበ ከፍተኛው የታማሚዎች ቁጥር ነው።

መልዕክት!
"እኛ ወይም የምንወደው ሰው ቀጥሎ በቫይረሱ የሚያዘው ሰው ልንሆን እንደሚችል በመገንዘብ ከመቼውም ግዜ በላይ በመጠንቀቅ ስርጭቱን ማቆም እንችላለን።
በዚህ ወረርሽኝ አንዳችን ለአንዳችን ዘብ በመቆም የኮሮና ቫይረስ የመከላከያ ዘዴዎችን በመተግበር አንዳችን ስንዘናጋ ሌላችን ካስታወስን ህይወት ልናተርፍ እንችላለን።
በመሆኑም የኮሮና ቫይረስ መከላከያ መንገዶችን አንዱን ዘዴ ከሌላው ሳናማርጥ በሙሉ መተግበር ይገባናል።" - ዶክተር ሊያ ታደሰ

የኮቪድ-19 ስርጭት በሀዋሳ!
በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ እስከ ትላንት ድረስ በኮቪድ-19 መያዛቸው ከተረጋገጠው 111 ሰዎች መካከል ስልሳ ሶስቱ (63) የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ሰራተኞች ናቸው።
የሲዳማ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ዶክተር ማቴ መንገሻ ለቪኦኤ እንደተናገሩት ከትላንት በስቲያ በሀዋሳ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው 36 ሰዎች ሁሉም በሚባል ደረጃ የፓርኩ ሰራተኞች ናቸው።
በአብዛኛው ከሶስት ሼድ በተወሰደ ናሙና ነው ሰዎቹ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው በምርመራ የተረጋገጠው።
እነዚህ ሰዎች በሰራተኝነት ፣ በአስተባባሪነት፣ በተለያየ ሞያ ሰልጥነው በኢንዱስትሪ ፓርኩ ውስጥ የሚሰሩ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።
ዶክተር ማቴ ለቪኦኤ እንደገለፁት 'ይህ ሁኔታ በኢንዱስትሪ ፓርኩ አካባቢ ችግር እንዳለ፣ ሰዎቹ ወደ ከተማ ሲወጡ ብዙ ሰዎች በከተማ ውስጥ በቫይረሱ እየተያዙ እንዳለ ማሳያነው' ብለዋል።
የሲዳማ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በሀዋሳ ከተማ ኢንዱስትሪ ፓርክ የተገኘውን ውጤት እንዲሁም ስርጭቱን በተመለከተ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መምከሩን ለቪኦኤ አስታውቋል።

በአፋር የጎርፍ መጥለቅለቅ 49 ሺህ ሰዎች ተፈናቀሉ!
በአፋር ክልል በአዋሽ ወንዝ መሙላት ሳቢያ በደረሰ የጎርፍ መጥለቅለቅ ከ49 ሺህ በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል ፤ 51 ሺህ የሚሆኑት ደግሞ በስጋት ላይ እንደሆኑ የክልሉ መንግሥት ለአብመድ አስታውቋል፡፡
የጎርፍ መጥለቅለቅ በእንዲህ ያለ ዝናብ ወቅት የሚጠበቅ ቢሆንም ዘንድሮ ግን በአዋሽ ዳርቻ በሚገኙ ወረዳዎችም ላይ ጎርፍ እየተከሰተ ነው ተብሏል፡፡
እስካሁን ባለው መረጃ በደረሰው የጎርፍ መጥለቅለቅ የሰው ሕይወት አልጠፋም ነገር ግን ነዋሪዎቹ በብዛት አርብቶ አደር በመሆናቸው በርካታ እንስሳት በጎርፍ ተጎድተውባቸዋል።
አስቀድመው ሰውነታቸው የተዳከመ በርካታ እንስሳት በዝናቡ መክበድ ምክንያት እንደሞቱ የክልሉ መንግስት ገልጿል።
በጎርፍ መጥለቅለቁ አስራ ስድስት (16) ወረዳዎች ሊጠቁ እንደሚችሉ የተገለፅ ሲሆን አሁን ላይ በሰባት (7) ወረዳዎች ጎርፍ መከሰቱን አብመድ የክልሉን መንግስት ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

የሪፐብሊኩ ጥበቃ ልዩ ኃይሎች ተመረቁ!
በውጭ ሀገርና በሀገር ውስጥ የሰለጠኑ የሪፐብሊኩ ጥበቃ ልዩ ኃይሎች መመረቃቸው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዘግቧል።
በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የሪፐብሊኩ ጥበቃ ኃይል ዋና አዛዥ ሜ/ጀነራል ብርሃኑ በቀለ የጥበቃ ኃይሉ እንደማንኛውም የፀጥታ ተቋም ህገ መንግስቱንና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን ማስጠበቅ አላማ ያነገበ ነው ብለዋል።
ሜ/ጀነራል ብርሃኑ አሁን የተመረቁት የሪፐብሊኩ የጥበቃ ልዩ ኃይሎች በውጭ ሀገር ለስድስት (6) እና ሰባት (7) ወራት ስልጠና የወሰዱ ናቸው ሲሉ ተናግረዋል።
በውጭ የወሰዱት ስልጠና በእዛው ሀገር ዶክትሪን፣ መልክአ ምድርና የአየር ፀባይ ሲሆን ወደፊት ከሚገጥማቸው ግዳጅ ሊዛመድ የሚችል በኢትዮጵያ ዶክትሪን ፣ መልክአ ምድርና የአየር ፀባይ ለሁለት ወር 'በወንዶ ጢቃ' የማዛመጃ ስልጠና እንደተሰጣቸው አስታውቀዋል።

በትግራይ ክልል የምርጫ ቅስቀሳ ሊጀመር ነው!
በትግራይ ክልል ለሚደረገው ስድስተኛው ክልላዊ ምርጫ የሚሳተፉ የተፎካካሪ ፓርቲዎች ከነሃሴ 5/2012 ዓ/ም ጀምሮ አጠቃላይ የምርጫ ቅስቀሳ እንደሚጀምሩ ተገልጿል።
በመገናኛ ብዙሃን አጠቃቀም፣ በበጀት ድልድል እና በሌሎች ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ በተፎካካሪ ፓርቲዎችና በምርጫ ኮሚሽን አመራሮች መካከል ለሁለት ቀን ውይይት ሲደረግ ቆይቶ ትላንት መጠናቀቁን ከትግራት ቲቪ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
የትግራይ ክልል ምርጫ ኮሚሽን ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር የጋራ ስምምነት በማድረግ የምርጫው ጊዜ ገደብ ተላይቶ በቀጣይ የውይይት መድረክ ይፋ እንደሚደረግ ገልጿል።
በትግራይ ክልል በሚደረገው ምርጫ 5 ተፎካካሪ ፓርቲዎች (ህወሓት፣ ባየቶና ፣ ሳልሳይ ወያነ ትግራይ ፣ ውድብ ናፅነት ትግራይ ፣ አሲምባ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት) እና 11 የግል እጩዎች ተወዳዳሪዎች መመዝገባቸው ይታወሳል።

የአሥራት ጋዜጠኞች ፍርድ ቤት ቀረቡ!
ሐምሌ 29/2012 ዓ/ም የታሰሩት በላይ ማናዬ፣ ሙሉጌታ አንበርብር ፣ ምስጋናው ከፈለኝ እና ዮናታን ሙሉጌታ በዛሬው ዕለት አራዳ ምድብ ችሎት ቀርበው የአስራ ሶስት (13) ቀን ቀጠሮ እንደተሰጠባቸው አሥራት ቴሌቪዥን (ASRAT MEDIA) አሳውቋል።
ፖሊስ አሥራት ቲቪ ከሕዳር 12/ 2012 እስከ ሰኔ 2012 ዓ/ም የአማራ ሕዝብ በተለየ ሁኔታ እንደተበደለ ፣ መንግስት የአማራ ሕዝብን መከላከል እንዳልቻለ ፕሮግራሞችን በማቅረቡና በመዘገቡ በኦሮሚያ ክልል ደምቢዶሎ እና ኦዳ ቡልቱም የመሳሰሉ ቦታዎች ብጥብጥ እንዲፈጠር በማድረግ የሰው ሕይወትና ንብረት ጠፍቷል ብሏል።
በቁጥጥር ስር የዋሉት ጋዜጠኞች በዚህ ወቅት የአሥራት ሰራተኞች ስለነበሩ እጃቸው አለበት ብሎ እንደጠረጠራቸው ገልጿል።
አሥራት ቴሌቪዥን በሀገር አቀፍ ደረጃ ሲለሚታይ ደንቢዶሎ እና ኦዳ ቡልቱን ጨምሮ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ መርማሪ ስለምልክ በሚል ፖሊስ 14 ቀን እንዲፈቀድለት ሲጠይቅ ፍርድ ቤቱ 13 ቀን የፈቀደለት ሲሆን ለነሃሴ 13/2012 ዓ/ም ተቀጥሮባቸዋል : https://telegra.ph/ATV-08-07

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት በእስር ላይ የሚገኙት የሕወሃት አመራሮች እና አባላት በዋስ እንዲፈቱ በዛሬው ዕለት ብይን እንደሰጠ አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል፡፡
ችሎቱ ፖሊስ የጠየቀው ይግባኝ ውድቅ በማድረግ ታሳሪዎቹ በዋስትና ከእስር እንዲለቀቁ ባለፈው ሳምንት የመጀመሪያ ፍርድ ቤት የወሰነውን ውሳኔ ነው ያጸናው፡፡
በዋስ እንዲወጡ የተወሰነላቸው በአዲስ አበባ የሕወሃት ጽ/ቤት ሃላፊ ተወልደ ገብረ ጻድቃን ፣ በሚንስትር ደዔታ ማዕረግ የሕግ ጥናት እና ምርምር ማዕከል ሃላፊ ተስፋለም ይኸድጎ ፣ የማዕከሉ 2 ሹፌሮች እና የደኅንነት መስሪያ ቤቱ ባልደረባ አጽብሃ አለማየሁ ናቸው፡፡
Via Addis Standard /Wzema Radio/

የአቶ እስክንድር ነጋ የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ተደረገ!
የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አንደኛ የወንጀል ችሎት አቶ እስክንድር ነጋን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ማድረጉን የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዘግቧል።
መርማሪ ፖሊስ ፍርድ ቤቱ በሰጠው ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ያገኘውን የምርመራ ሥራ ለፍርድ ቤቱ አብራርቶ ለቀሪ የምርመራ ሥራዎችም የ14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ጠይቋል።
ጠበቆችም አቶ እስክድር ነጋ የዋስትና መብቱ እንዲጠበቅ የጠየቁ ሲሆን ፣ ፍርድ ቤቱ የዋስትና ጥያቄውን ውድቅ አድርጓል።
ምክንያቱ መርማሪ ቡድኑ አቶ እስክንድር ነጋ የጠረጠረበት ወንጀል ሞት ያስከተለ በመሆኑ ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ ከ15 ዓመት በላይ ሊያስቀጣቸው ስለሚችል ነው ብሏል።
በሌላ በኩል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በአቶ እስክንድር ነጋ ላይ የቀዳሚ ምርመራ ፋይል እንዲከፈት የወሰንኩ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ይስጠኝ በማለት አመልክቷል።
ችሎቱ በሰጠ ትዕዛዝ ዐቃቤ ሕግ ለቀዳሚ ምርመራ ችሎት የሚያቀርበው አቤቱታ እስከነምስክሮች ዝርዝር እንዲያቀርብ ትዕዛዝ በመስጠት ለነሐሴ 5 ቀን 2012 ዓ.ም ዐቃቤ ሕግ በሚያቀርበው አቤቱታ የጠበቆች መቃወሚያ ካለም እሰማለሁ ብሏል። ይህ እስከሚሆን ድረስ ግን ተጠርጣሪው አቶ እስክንድር ነጋ በፖሊስ ማረፊያ ቤት እንዲቆይ አዝዟል።

በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ከ21 ሺህ አለፉ!
ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 9,203 የላብራቶሪ ምርመራ 552 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ15 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 388 ሰዎች አገግመዋል።
በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 21,452 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 380 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 9,415 ናቸው።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 9,203 የላብራቶሪ ምርመራ 552 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ15 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 388 ሰዎች አገግመዋል።
በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 21,452 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 380 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 9,415 ናቸው።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዶ/ር ፍሰሃየ አለምሰገድ ህይወታቸው አለፈ!
በአክሱም ዩኒቨርሲቲ የህብረተሰብ ጤና ትምህርት ቤት በኢፒዲምዮሎጂ ትምህርት ክፍል ባልደረባ የነበሩት ዶ/ር ፍሰሃየ አለምሰገድ (ተባባሪ ፕሮፌሰር) የኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሞያቸው ሕብረተሰባቸውን በማገልገል ላይ እያሉ በኮሮና ቫይረስ በሽታ ታመው የሕክምና እርዳታ ሲደረግላቸው ከቆዩ በኃላ በቀን 01/12/2012 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡
አክሱም ዩኒቨርሲቲ በዶክተር ፍሰሃየ ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ሀዘን የገለፀ ሲሆን ለቤተሰቦቻቸው፣ ለስራ ባልደረቦቻቸዉ፣ ለጓደኞቻቸዉ እንዲሁም ለመላዉ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ መፅናናትን ተመኝቷል።

ዶ/ር ፍሳሃየ አለምሰገድ !
- በ1970 ዓ.ም በትግራይ ክልል ዓድዋ ወረዳ ልዩ ስሙ ይሓ በተባለ ቦታ ነው የተወለዱት።
- ዶክተር ፍሳሃየ በጠቅላላ ሓኪም እና በሕብረተሰብ ጤና የኢፒዶሞሎጂ የማስተርስ ትምህርታቸውን አጠናቅቀዋል።
- በጅማ ዩኒቨርሲቲ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በመምህርነት፣ በተማራማሪነትና በሙያ እማካሪነት ከ1994 ዓ/ም እስከ 2011 ዓ/ም አገልግለዋል።
- ከመስከረም 2012 ዓ.ም ጀምሮ ወደ በአክሱም ዩኒቨርሲቲ የህብረተሰብ ጤና ትምህርት ክፍል ሲያገለግሉ ቆይተዋል።
- በእናቶች እና ህፃናት ህክምና፣ ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች፣ በስነ-ምግብ ፣ በወባ ፣ በኤች አይቪ ኤድስ እና ሌሎች ተላላፊ በሽታዎችን ጨምሮ በሌሎች የሕብረተሰብ ጤና ዘርፎች ከ50 በላይ ችግር ፈቺ ጥናቶችን በታዋቂ ጆርናሎች በማሳተም አዳዲስ እውቀቶች በማፍለቅ ለዓለም አሻራቸውን አሳርፈዋል።
- የኮሮና ወረርሺኝ ለመከላከልና ለመቆጣጠር በአክሱም ዩኒቨርሲቲ የኮሮና ቫይረስ ፈጣን ግብረ መልስ ቡድን መሪ በመሆን ህዝባቸውን ከቫይረሱ ለመታደግ ሌተቀን ሲሰሩ ቆይተዋል።
- የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ባደረገላቸው ጥሪ በኮሮና ቫይረስ መረጃ ትንተና እና ትንበያ ክፍል በመስራት ላይ እያሉ በኮሮና ቫይረስ ተይዘው ህክምና ሲደረግላቸው ቆይቶ ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል።
አክሱም ዩኒቨርሲቲ!
ነፍስ ይማር!