TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.89K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አወጁ ተነስቷል! የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አንስቷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና! እነ ንግስት ይርጋ ታሰሩ። ንግስት ይርጋ፣ አግባው ሰጠኝ፣ አጋዬ አድማሱ፣ አንጋው ተገኘ፣ ዘለቀ አሰማራው፣ አባይ ዘውዱ፣ ተገኘ ሲሳይ፣ ሰጠኝ ቢልልኝ፣ እስክንድር ኬኮ እና ሎሎች በርካታ ሰዎች ዛሬ ግንቦት 28/2010 ዓም አዘዞ መከላከያ ካምፕ ታስዋል።

እነ ንግስት የታሰሩት በቅርቡ ከእስር የተፈታውን አጋዬ አድማሱን ጎንደር አየር ማረፊያ በመቀበል ላይ እያሉ ነው።

አጋዬ አድማሱን ለመቀበል የወጣውን ሕዝብ ያሰረው መከላከያ ሲሆን በአሁኑ ወቅት አዘዞ መከላከያ ካምፕ ይገኛሉ።

የጎቤ መልኬ ምክትል የሆነውን አጋየ አድማሱን ሲቀበሉ ንፁሁን የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ይዘው እንደነበር የገለፁ ሲሆን መከላከያ ሰራዊቱም "ይህን ሰንደቅ አላማ የያዘውን እንጠይቃለን" ማለቱ ታውቋል።

ምንጭ፦ አቶ ጌታቸው ሽፈራው
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና! እነ ንግስት ይርጋ ከእስር ተፈተዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ተቋረጠ! በጅማ ስታዲየም በጅማ አባ ጅፋር እና በቅዱስ ጊዮርጊስ መካከል እየተካሄደ የነበረው ጨዋታ ተቋርጧል። በጨዋታው 69ኛ ደቂቃ ላይ አብዱልከሪም መሃመድ ቅዱስ ጊዮርጊስን ቀዳሚ ያደረገች ጎል ካስቆጠረ በኋላ በደጋፊዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት ጨዋታው ተቋርጧል።

ምንጭ፦ ቤኪ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጅማ ላይ በደጋፊዎች ረብሻ ተቋርጦ የነበረው ጨዋታ ቀጥሏል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፓርላማው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አነሳ! ፓርላማው ማክሰኞ ግንቦት 28 ቀን 2010 ዓ.ም. ባደረገው መደበኛ ስብሰባ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማንሳት የቀረበለትን ረቂቅ አዋጅ በስምንት ድምፀ ተዓቅቦ አጸደቀ፡፡

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ወቅት የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ስለነበሩ፣ ተጣርተው ለፓርላማው እንዲቀርቡ አፈ ጉባዔዋ ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል አሳስበዋል፡፡

ይህ በዚህ እንዳለ፣ ፓርላማው ምሕረትን በሚመለከት የቀረበለትን ረቂቅ አዋጅ ተመልክቶ ለቋሚ ኮሚቴ ዕይታ መርቷል፡፡ አዋጁ የምሕረት ቦርድ የሚያቋቁም ሲሆን፣ ተጠሪነቱም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲሆን ይደነግጋል፡፡

ምንጭ፦ ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Forwarded from Yenesport (Fiker abi)
ዛሬ የተደረጉ የኢ.ት ፕሪሚየር ሊግ ጫወታዎች

FT አዳማ ከተማ 6-1 ኤሌክትሪክ

FT ወልዲያ 0-1 ወልዋሎ

FT ወላይታ ድቻ 0-1 ኢትዮጵያ ቡና

FT ፋሲል ከተማ 0-1 መከላከያ

FT ጅማ አባ ጅፋር 1-1 ጊዮርጊስ

FT ድሬ ደዋ 1-0 መቐለ ከተማ


@yenesport @yenesport
ሰበር ዜና! የኢትዮጵያ መንግሥት የአልጀርሱን ስምምነት ተቀበለ።

ከኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ

(የኢትዮ-ኤርትራ ወቅታዊ ሁኔታን በማስመልከት የተላለፈ ጥሪ)

የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የኢትዮ-ኤርትራ ወቅታዊ ሁኔታን በጥልቀት በመገምገም በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ተፈጥሮ የቆየው አለመግባባት እንዲያበቃና በሁለቱ ወንድማማች ህዝቦች መካከል ዘላቂ ሰላም እንዲፈጠር የሚከተለዉን ጥሪ አስተላልፏል።

ለኢትዮጵያችን እድገትና ለሕዝቦች ተጠቃሚነት ሰላም ከምንም በላይ ትልቅ ዋጋ አለው፡፡

ሰላም የሁሉም ነገር መሰረት ነው፡፡

ከግለሰብ የወደፊት የማደግና መለወጥ ህልም ጀምሮ እስከ ሀገር ድረስ ሰላም ከደፈረሰ የቱንም አይነት የልማትና የዲሞክራሲ አላማዎችን ማሳካት አይቻልም፡፡

በኢትዮጵያና በኤርትራ መሃከል ከ1990 ዓ.ም ጀምሮ የተከሰተውን ጦርነት በአፍሪካ ከተከሰቱ የድንበር ጦርነቶች ሁሉ ደም አፋሳሹ ሲሆን፣ ከሁለቱም ወገን በርካታ ሺህ የሰው ሕይወት ሊጠፋ ችሏል፡፡

ጦርነቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ከኤርትራና ከኢትዮጵያ የድንበር አካባቢ የመኖሪያ ቀዬ አፈናቅሏል፡፡

በሁለቱ ሀገራት መሃከል የተደረገው ጦርነት በሁለቱም ሃገራት ያሉ ቤተሰቦችን አፍርሷል፣

በድንበር አቅራቢያ የሚኖሩ ዜጎች ሁሌም ያለመረጋጋትና የስጋት ስነ-ልቦና ሰለባ አድርጓቸዋል፡፡ በድንበር አካባቢ በንግድ የሚተዳደሩ ሰዎች ላይ ተፅዕኖ ፈጥሯል፡፡

በድምሩ ላለፉት 20 አመታት በሁለቱም ሀገራት ህዝቦች ላይ መጠነ ሰፊ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ቀውስ ፈጥሯል፡፡

በመሆኑም የሁለቱ ሀገራት የወደፊት ግንኙነት ምን ሊሆን ይችላል? የሚለው ጥያቄ የአብዛኛው ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን እንዲሁም የዓለም አቀፉ ኅብረተሰብ ጥያቄ ሆኖ ቆይቷል፡፡

ከጦርነቱ በኋላ በአፍሪካ አንድነት ድርጅትና በተባበሩት መንግስታት አደራዳሪነት የአልጀርሱ ስምምነት ቢደረግም ላለፉት 20 ዓመታት በሁለቱ ወንድማማች ሀገሮች መካከል ጦርነትም ሆነ ሰላም የሌለበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡

የሁለቱን ሀገራት ወዳጅነት ወደነበረበት ለመመለስ ላለፉት ሃያ አመታት የተደረጉ ሙከራዎች በሙሉ ውጤት አላመጡም፡፡

በዚህም ምክንያት በአሁኑ ጊዜ በሁለቱ ሀገራት መካከል የዕውነት ሰላም ለማስፈን ከቀድሞው የተለየ አቋምና አካሄድ ያስፈልጋል፡፡

ሁለቱም መንግሥታት ለህዝባቸው ምርጫና ፍላጎት ቦታ የማይሰጡ ሊሆኑ አይችሉም፡፡

እኔ እበልጥ፣ እኔ እበልጥ የሚል ፉክክር ለሁለቱም ህዝቦች የሚፈይደው ነገር አይኖርም፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ለአፍሪካ ቀንድ ሀገሮችና አካባቢ የፖለቲካ ቀውስ መብረድና መረጋጋት ዘላቂው መፍትሔ የኢትዮጵያና የኤርትራ ጤናማ ግንኙነት መመሥረት ነው፡፡

ይህን ባለማድረጋችን በርካታ ለሁለቱ እህትማማች ሀገሮችም ሆነ ለአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ትልቅ ፋይዳ ያላቸዉ እድሎች አምልጠዉናል፡፡

የኢትዮጵያና የኤርትራ ህዝቦች ቀድሞም ቢሆን ወዳጅ ነን፡፡

በደም፣ በባህል፣ በቋንቋና በረጅም ጊዜ የጋራ ታሪክ የተሳሰርን ሕዝቦች ነን፡፡

በመሆኑም በጥቅም ብቻ ሳይሆን በደም ለተሳሰሩት የሁለቱ ሀገር ሕዝቦች የጋራ ጥቅም ሲባል የኢትዮጵያ መንግስት የአልጀርሱን ስምምነት እና የድንበር ኮሚሽኑን ውሳኔ ሙሉ ለሙሉ ተቀብሎ ተግባራዊ ለማድረግ የወሰነና ለተግባራዊነቱ ያለማመንታት በቁርጠኝነት የሚሰራ መሆኑን ለመግለፅ ይፈልጋል፡፡

ይህንኑ በጋራ ተጠቃሚነትና እኩልነት ላይ የተመሰረተውን የሀገራችን ፖሊሲም አጠናክረን እንደምንቀጥል በዚሁ አጋጣሚ በድጋሚ ለማረጋገጥ እንወዳለን፡፡

የኤርትራ መንግስትም ተመሳሳይ አቋም በመውሰድ ያለምንም ቅድመ-ሁኔታ የሰላም ጥሪያችንን ተቀብሎ በሁለቱም ወንድማማች ህዝቦች መካከል ከዚህ በፊት የነበረውን አብሮነትና ሰላም ወደነበረበት ለመመለስና በቀጣይም ዘላቂነቱን ለመጠበቅ ለተግባራዊነቱ ያለማመንታት በቁርጠኝነት እንዲሰራ እንጠይቃለን፡፡

የኢህአዴግ ም/ቤት ጽ/ቤት
ግንቦት 28/2010 ዓ.ም
አዲስ አበባ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
## ኤርትራ 🤝 ኢትዮጵያ ##

ፕሬዘዳንት ኢሳያስ ሆይ መቼም የዛሬውን ዜና ሰምተዋል። እባኮትን መልካም ምላሾትን መላው ህዝቡ ይጠባበቃልና አፋጥኑት።

ፍቅር ያሸንፋል!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ከእርምጃ ወደ ሩጫ" የተባለው ከሩጫ ወደ እርምጃ ሆኗል።

#ይድረስ_ለኢትዮጵያ_ጠቅላይ_ሚኒስተር_ለክቡር_ዶ/ር #አብይ_አህመድ

ሰላም ሰላም ለዉድ ያገሬ አባቶች እናቶች ወንድሞችና እህቶች እንደ ምን አላችሁ?

ዛሬ አንድ ወሳኝ ጉዳይ ይዠላችሁ መጥቻለሁ።

ጉዳዪ ወደ ህንድ ሀገር የተላኩ ተማሪዎችን በተመለከተ ነው።

እንደምታወቀው በአምና ማለትም በ2009 ዓ.ም ሐምሌ መጨረሻዎቹ አካባቢ አንደኛ አመት የዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡና ጥሩ እንቅስቃሴ ለነበራቸው በተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች የሚሰሩ አባላትን መልምለው በ BETRE SCIENCE ETHIOPIAN SCHOLARSHIP PROGRAM በተሰኘው ስኮላርሽብ መስጠቱና ተማሪዎችን ወደ ህንድ ቻይናና ቱርክ መላኩ ይታወቃል።

ሆኖም ግን እነዚህ ተማሪዎች የምጠይቋቸውን እስከሚያጡ ድረስ ተሰቃይተዋል። ቱርክ የነበሩ ተማሪዎች በተደጋጋሚ ሚድያ ላይ ሀሳባቸውን ገልጸዋል። ህንድ የተላኩ ተማሪዎች ተቀባይ እስከሚያጡ ድረስ የደረሰባቸውን ስቃይ ተቋቁመው እንደነበረና በማያውቁት ሀገር እንደተንከራተቱ ገልጸዋል።

በአሁኑ ሰአት ላይ 44 ተማሪዎች ህገ -ወጥ ቪሳ ይዘው ANDHRA PRADESH STATE VIGNAN UNIVERSITY በሚባል ተቋም ሳይመዘገቡ ዛሬ 7 ወር አልፏቸዋል።

እነዚህ ተማሪዎች በተለያዩ ጊዜያቶች አበቱታቸውን ቢያቀርቡም እስካሁን ድረስ ምላሽ አላገኙም። እንደውም በውሸት እያባበሏቸው እንደነበረና ኢትዮጵያ ትመለሳችሁ ብለው በማስፈራራት ተማሪዎቹ ዝም እንድሉ አድርገዋል። የታመሙም ሆኑ ሌላም ችግር ያለባቸው ተማሪዎች እንኳን መሄድ ቀርቶ መንቀሳቀስ እንዳልቻሉ ገልጸዋል።

ለምሳሌ ያህል አንድ እህታችን ከአቅም በላይ ስላመማት ለመሄድ ከኢምባሲም ሆነ ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስተር ሚኒስተሮች ጋር ያለውን ጉዳይ ጨርሳ የአውሮፕላን ትኬት ተቆርጦላት የመሄጃዋ ቀን መውጣት ስላልቻለች እንዴት ልውጣ ብላ ስትጠይቃቸው አምልጠሽ ዉጪ እንደተባለችና እስካሁን ድረስ በዚህ እንዳለች ተናግራለች። እነዚህ ተማሪዎች አንዳች ነገር ቢደርስባቸው ጠያቂ ተጠያቂም እንደሌለ ግልጽ ነው።

ተማሪዎቹም ምንም መታወቂያ እንኳን የሌለንበት ዩኒቨርሲቲ ዉስጥ መማር አንችልም ቢሉም ጥያቄያቼው ተቀባይነት የማያገኝ ሆኗል። የኢትዮጵያ ኢምባሲ የተቻለዉን ለማድረግ ቢሞክርም ጉዳዩ ከባድ ስለነበረ በቀላሉ ለመፍታት አልተቻለውም።

አጠቃላይ በVIGNAN UNIVERSITY ዉስጥ ያሉ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ቁጥር 90 ሲሆኑ 46ቱ በቀጥታ ወደዛ ተቋም የተመደቡ ናቸው። አሁን ተማሪዎቹ ያሉበት ሁኔታ በጣም የሚያሳዝኑ ሲሆን ተስፋ ቆርጠውና የሚያደርጉትን ስላጡ እየተማሩ ቢገኙም አንዳንዶቹ ግን 1ኛ መንፈቀ ዓመት ጨርሰው 2ኛን መቀጠል አልቻሉም።

ምክንያቱ ከዚህ ተቋም እንቀይራችኋለን ብለው ቃል ስለገቡ ተማሪዎቹ በመሀል ለአንድ ወር ያህል ትምህርቱን አቋርጠል። ሆኖም ግን በዉሸት ስላባበሏቸውና መቀየርስላልቻሉ እዛው እንድቀጥሉ ብያስገድዱም እስካሁን ሳይመዘገቡ ቀርተዋል።

በአሁኑ ሰአት ሁሉም ተማሪዎች ያለ ተስፋ እንደሚማሩና ሙሉ በሙሉ ማቆም እንደሚፈልጉ ገልጸዋል። በተለያዩ ተማሪዎች በኩል በደረሰን መረጃ ተማሪዎቹ በእናንተ ሀገር የትምህርት ተቋም የለም እንደ እንደት እዚህ ተቋም ገባችሁ እስከሚባሉ ድረስ ተተችተዋል።

ከተማሪዎቹ መካከል ወደ አገራቸው መመለስ የፈለጉ እስካሁን ተቀባይነት ሳያገኙ ያለ ምንም ስራ ተቀምጠዋል።

በምኖሩበት ቤት ቁጭ ብሎ ከማልቀስ ዉጪ ምንም አማራጭ ስሌለላቸው ተስፋ ቆርጠው ባይተዋር ሆነዋል። በአሁኑ ሰአት ላይ ተማሪዎቹ አንድ አመት ሙሉ በነጻ ኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ አሳልፈን አሁንም በድጋሚ እዚህ መጥተን አንድ አመት በነጻ መቆየታችን ለችግሩ ፈጣሪ ና ተጠያቂ ኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስተር ሚኒስተሮች መሆኑን በግልጽ እንናገራለን።

ይህም በእንድህ እንዳለ ተማሪዎቹ ወደ ሀገራቸው መመለስ እንደማይችሉ ግልጽ ስለሆነ ተስፋ በመቁረጥና በተለያዩ ስነ-ልቦናዊ ችግሮች ላይ መውደቅ ሆኗል።

የኢትዮጵያ ኢምባሲ ሦስተም አራተም ስለዋሸን አመነታ አተንበታል ስሉ ገልጸዋል። ሀገርን የወከለ ሰው በዜጋው ላይ እንድህ ጨክኖ ስዋሽ ማየቴ ራሱ ግራ ቢገባኝም እንደዚህ አይነት ዉሸት ስለማይጠበቅ ለወደፊት ራሳቸውን ያርሙ ብለናል። የኢትዮጵያ ኢምባሲ መፍትሄ ማግኘት ስላልቻለ ተማሪዎቹን ወደ ሀገር መልሶ ከእንደገና ቪሳ አስተካክሎ መመለስ ወይም ሌላ አማራጭ ይፈልግ ባይ ነኝ። ይህ ድርጊት እንዳይደገም መጠየቅ ያለበት አካል ተጠያቂ ይሁንልን ብለን አቤቱታችንን እናቀርባለን።

አሁን ይህንን የምትሰሙ የኢትዮጵያ ዜጎች በየትኛውም የዓለም ክፍል ያላችሁ ሼር በማድረግ የቀድሞው ኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስተር የበትረ ሳይንስ የኢትዮጵያ ስኮላርሽብ ፕሮግራም ሀሳብ አመንጪና አፍላቂ በአሁኑ ወቅት ኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስተር ሆነው ለተመረጡት ለክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ እንድታደርሱልን በትህትና እናሳስባለን።

@tsegabwode @tikvahethiopia
መንግስት የአልጀርሱን ስምምነት ተግባራዊ ለድረግ መወሰኑ አንዳንዶችን እጅግ አበሳጭቷቸዋል፤ በተቃራኒው ደግሞ አንዳንዶችን አስደስቷቸዋል። ያም ሆነ ይህ መንግስት ስምምነቱ ተግባራዊ እንዲሆን ወስኗል ለሰላም ሲባል።

አስመራ ካሉ ወጣቶች የተላከልኝ ፎቶ ነው...ትኬት መቁረጥ ጀምረናል ወደ አስመራ!
@tsegabwolde
መንግስት የአልጀርሱ ስምምነት መሉ በሙሉ እንዲተገበር መወሰኑን እንዴት አገኛችሁት??

ኤርትራ~ኢትዮጵያ

ትክክል ነው
ትክክል አይደለም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
እጅግ በርካታ የቤተሰባችን አባላት ስለአልጀርሱን ስምምነት ጉዳይ ብዙም መረጃው እንደሌላቸው ስለጉዳዩም ዘርዘር ያለ መረጃ እንዲቀርብላቸው ጠይቀውኛል። ይህን የማደርግ ሲሆን በመንግስት ውሳኔ ዙሪያ በርካታ የቻናላችን ተከታዮች የግል አስተያየታቸውን እየሰጡ ይገኛሉ። አስተያየቶቹንም አለፍ አለፍ እያልኩ ለጥፋለሁ።

ዛሬ ተጠፋፋተን ውለናል ይህም በአንዳንድ ቻናሉን በሚመለከቱ ገዳዮች መሆኑን ለመግለፅ እወዳለሁ!

@tseabwolde @tikvahethiopia
ከኃላፊነታቸው ተነሱ! በምስራቅ ሐረርጌ ዞን የሕዝብ ጥያቄዎችን አልመለሱም የተባሉ 272 አመራሮች ከኃላፊነታቸው ተነሱ::
የልማት፣ የመልካም አስተዳደርና የሕዝብ ጥያቄዎችን አልመለሱም ያላቸውን 272 አመራሮች ከኃላፊነት ማንሳቱን የምስራቅ ሐረርጌ ዞን አስተዳደር አስታወቀ።

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ እንደገለጹት ከኃላፊነት የተነሱት የአመራር አካላት በዞንና በወረዳ ሲሰሩ የነበሩ ናቸው ብለዋል።

የአመራር አካላቱ ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ የተደረገው በዞኑ ለ20 ቀናት በተካሄደ የተሃድሶ ግምገማ መሰረት ሂስና ግለ ሂስ በማድረግ ኃላፊነታቸውን ብበቃት አለመወጣታቸውን ከስምምነት በመድረሱ መሆኑን ተናግረዋል።

በተሃድሶ ግምገማው የአመራር አካላቱ የመልካም አስተዳደር ጥያቄን አለመመለስ፣ በኪራይ ሰብሳቢነት ችግር ውስጥ መዘፈቅ፣ በፕሮጀክት ግንባታ ሥራዎች የአፈጻጸም ጉድለት ማሳየት፣

እንዲሁም የህግ የበላይነትን አለማስከበርን ጨምሮ በሌሎች የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ሥራዎች ላይ ድክመት ማሳየታቸውን አቶ ታረቀኝ ገልጸዋል።

አስተዳዳሪው እንዳሉት የግምገማ ሂደቱን ከዞን እስከ ወረዳና ቀበሌ ድረስ በማውረድ ህዝቡ እንዲወያይበትና ሀሳብ እንዲሰጥበት የተደረገ ሲሆን፥ የአመራሮችን ብቃትና ጥንካሬን የመለየት ስራም ተከናውኗል።

በምትካቸው አዲስ ከተሾሙት አመራሮች መካከል 261ዱ በዞኑ ባሉ 24 ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደር በአመራርነት የሚሰሩ ሲሆን፥ ቀሪዎቹ 11ዱ በዞን ደረጃ የተሾሙ መሆናቸው አመልክተዋል።

ኦህዴድ የህዝቡን የልማት ጥያቄ በሚገባ በመረዳት ጥንካሬዎቹን ለማስቀጠልና ደካማ ጎኖቹን ለማረም እንደሚሰራ ገልጸዋል።

ከልማቱ ጋር እኩል እያደገ የመጣውን የህዝብ ጥያቄ በአግባቡ ለማስተናገድም ድርጅቱ የጀመረውን የአሰራር ስርዓት ለውጥ በቀጣይም አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስረድተዋል።

ድርጅቱ ያደረገው የጥልቅ ተሀድሶ ግምገማ መልካም መሆኑን የገለጹት የሐረማያ ወረዳ ነዋሪ አቶ አብዲ ኢብራሂም በበኩላቸው “እንደዚህ ዓይነት ስር ነቀል ለውጥ ሲደረግ ለመጀመርያ ጊዜ ነው፤ ይህ ደግሞ ለህብረተሰቡ ለውጥ ያመጣል ብዬ አምናለው” ብለዋል።

አዳዲስ የተሾሙትም ሆኑ ነባር አመራሮች የመልካም አስተዳደርና የኪራይ ሰብሳቢነት ችግሮችን ለመፍታት ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ ጠይቀዋል።

ምንጭ፦ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአማራ ተወላጆች! ከቤንሻንጉል እና ከኦሮሚያ ክልሎች የተፈናቀሉ ጥቂት የማይባሉ የአማራ ተወላጆች ዛሬም በተለያዩ መጠለያ ስፍራዎች እንደሚገኙ አመለከቱ። ተፈናቃዮቹን ወደ ነበሩበት አካባቢ ለመመለስ የበኩሉን ጥረት በማድረግ ላይ የሚገኝ ከኅብረተሰቡ የተውጣጣ አንድ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ከቤንሻንጉል ከተፈናቀሉት 50 ገደማውን ወደቦታቸው መመለስ ማስቻሉን ገልጿል።

ምንጭ፦ DWAMHARIC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአልጀርስ ስምምነት! ታህሳስ 3 ቀን 1993 በቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እና የኤርትራው ፕሬዚደንት ኢሳያስ አፈወርቂ የተፈረመው ባለ 6 አንቀጽ ሰነድ አራት መሰረታዊ ግቦች ነበሩት፡፡

እነርሱም፡-

• በሁለቱ ሀገራት መካካል ያለውን የባላንጣነት መንፈስ ማቆም፣ ሀገራቱ ከዛቻ እና የሃይል እርምጃ እንዲቆጠቡ ማድረግ፤

• ቀደም ብሎ በሰኔ 1/1992 የተደረሰውን በባለንጣነት ያለመተያየት ስምምነት እንዲከበር እና እንዲፈጸም ዋስትና መስጠት፤

• በእስር ያሉ የጦር ምርኮኞች እና ግለሰቦች ተለቀው ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ማስቻል፤

• ሁለቱ ሀገራት በግዛቶቻቸው ውስጥ ላሉ የሌላኛው ወገን ዜጎች ሰብአዊ እንክብካቤ እንዲያደርጉ ድልድልይ መሆን ናቸው፡፡

ከላይ የተጠቀሱት ግቦች በየተራ ይሳኩ ዘንድ ሰነዱ ነጻ የድንበር እና የካሳ ኮሚሽኖች እንዲቋቋሙ መሰረት ሆኗል፡፡

5 አባላት ያሉት የኢትዮ ኤርትራ የድንበር ኮሚሽን የራሱን ምርመራ አድርጎ፣ አለመግባባት የፈጠሩ የድንበር ቦታዎች ለየትኛው ሀገር እንደሚገቡ ለመወሰን እንዲችል በወቅቱ ከስምምነት ተደርሷል፡፡

በሰነዱ አንቀፅ አንቀጽ 2 (2) ቀደም ብለው የተገቡ የቅኝ ግዛት ህጎችን እና ዓለም አቀፍ ህግን ተመስርቶ ኮሚሽኑ ውሳኔውን እንደሚያስተላልፍ ተጠቅሷል፡፡

እንዲሁም በአንቀጽ 2 (15) ላይ ኮሚሽኑ የሚሰጠው የወሰን እና ማካለል ውሳኔ የመጨረሻ እና ገዢ እንደሚሆን ተዘርዝሮም ነበር፡፡

ሁለቱ ሀገራት ያላቸውን ማስረጃ በማቅረብ መቀመጫውን ኔዘርላንድ ዘሄግ ባደረገው ኮሚሽን ፊት ተከራክረዋል፡፡ በ1996 ዓመተ ምህረት የኢትዮ ኤርትራ የድንበር ኮሚሽን ውሳኔውን አስተላለፈ፡፡ ሁለቱ ሀገራት ከተፋለሙባቸው ቦታዎች አንደኛዋ የነበረችው ባድመ የኤርትራ ግዛት እንድትሆን ተፈረደ፡፡

ኢትዮጵያ ግን ውሳኔውን ለመቀበል ወታደሮቿን ከባድመ ለማስወጣት አልፈቀደችም፡፡ ኢትዮጵያ የኮሚሽኑን ውሳኔ ተከትሎ የድንበር ማካለሉ ካለ አንዳንድ ቅድመ- እሳቤዎች እንዲሁ ቢተገበር ሊፈጠር የሚችሉ ችግሮችን በመዘርዘር፣ ተጨማሪ ውይይት በሁለቱ ሀገራት መካከል እንዲደረግ ጠይቃለች፡፡

ኤርትራ ግን የኢትዮጵያን ጥያቄ ሳትቀበለው በመቅረቷ፣ የሁለቱ ሀገራት ድንበር ለተጨማሪ 16 ዓመታት የፍጥጫ ስፍራ እንዲሆን ሰበብ ሆነ፡፡

ኤርትራ ባለፉት ዓመታት የአልጀርሱን ስምምነት ተከትሎ የተሰጠው ውሳኔ እንዲከበር ስትጎተጉት ነበር፡፡ ይሄ ባልሆነበት ሁኔታ ሰላም እንደማይኖርም ደጋግማ አሳውቃለች፡፡

የኢትዮጵያ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ መንበረ ሥልጣኑን በተቆናጠጡ ዕለት አጀንዳዬ ብለው ካወጇቸው ጉዳዮች መካከል ከኤርትራ ጋር ሰላም ማውረድ አንዱ ነበር። ነገር ግን ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን አለመግባባት ልትፈታ የምትችለው የአልጀርሱ ስምምነት ተግባራዊ እንዲሆን ስትፈቅድ ብቻ ነው ሲሉ የኤርትራው መረጃ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል ምላሽ መስጠታቸው ይታወሳል።

ትናንት መደበኛ ስብሰባው ላይ ከትሞ የነበረው የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ፤ ኢትዮጰያ ለሁለቱ ሃገራት መፃኢ -ሰላም ሲባል የአልጀርስ ስምምነትን እንደምትቀበል አሳውቋል። ይህም 'ለሃያ ዓመታት ኢትዮጵያና ኤርትራን በጦርነት ውስጥ ተፋጠው እንዲቆዩ ያደረጋቸውን የድንበር ፍጥጫ መፍትሄ ይሰጥ ይሆን?' የሚል ተስፋ አዘል ጥያቄ ጭሯል።

ኤርትራ የኢትዮጵያን የአቋም ለውጥ ተከትላ የምትወስደው ርምጃ የሁለቱን ሀገራት የፍጥጫ ዘመን ለማክተምም ሆነ ለማራዘም ወሳኝነት ይኖረዋል፡፡ ምንም እንኳ ጉዳዩን በተመለከተ እስካሁን ከአስመራ ባለሥልጣናት የተሰማ ድምፅ ባይኖርም።

ይህን ፅሁፍ ያዘጋጀው ቢቢሲ የአማርኛው አገልግሎት ነው።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Forwarded from Yenesport (Fiker abi)
በጋና አስተናጋጅነት በ2018 ለሚካሄደው የቶታል አፍሪካ ሴቶች ዋንጫ ለማለፍ የመጨረሻው የማጣርያ ዙር ላይ የደረሰው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከአልጄርያ ጋር ያደረገውን የመጀመርያ ጨዋታ 3-1 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።

@Yenesport @Yenesport
አፋልጉኝ⬆️ስሙ አለማየሁ አዳፍሬ ይተባለ ወንድሜ ለስራ ወደ ቡሌ ሄራ ዩኒቨርሲቲ ከሄደ በኋላ እስካሁን ወደ ቤቱ አልተመለሰም። አለማየሁ ከሁለት አመት በፊት ከደም ካንሰር የዳነ ቢሆንም በየጊዜው የማገገሚያ መድሀኒት ይወስዳል። ስለዚህ ድንገት በምንም ምክንያት ታሞ ያያችሁት ወይም በየትኛውም ቦታ ያያችሁት እባካችሁ ጠቁሙኝ። ውለታውን ከፋይ ነኝ። ቤተሰቦቹ።

ስልክ፦ 0920 10 40 85