#ItsMyDam
“የኢትዮጵያ ሕዝብ በሀገሩ ሕልውናና ክብር ከመጡበት ሞት የማይፈራ ጀግና ሕዝብ መሆኑን አይደለም ግብጽ ዓለምም ያውቃል” - የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹም ጀነራል ብርሃኑ ጁላ (ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ የተናገሩት)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiapp

#AFRICA
በመላው አፍሪካ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር ከ270,000 አለፈ። ከነዚህ መካከል 7,251 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 125,625 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
3 ከፍተኛ ኬዝ የተመዘገበባቸው የአፍሪካ ሀገራት ፦
- ደቡብ አፍሪካ በቫይረሱ የተያዙ 80,412 ፣ ሞት 1,674፣ ያገገሙ 44,331
- ግብፅ በቫይረሱ የተያዙ 49,219 ፣ ሞት 1,850 ፣ ያገገሙ 13,141
- ናይጄሪያ በቫይረሱ የተያዙ 17,335 ፣ ሞት 468 ፣ ያገገሙ 5,967
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

ኒው ዚላንድ!
ኒው ዚላንድ ሶስተኛውን (3) የኮቪድ-19 ታማሚ ማግኘቷን አስታወቀች። ግለሰቡ ከፓኪስታን ወደ ኒው ዚላንድ የገባ እንደሆነነው የተገለፀው። ሀገሪቷ በዚህ ሳምንት ብቻ የትላንቱን ጨምሮ 3 በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን አግኝታለች።

ኢትዮጵያ 400 መካኒካል ቬንትሌተሮችን ገዝታለች!
የኮሮና ወረርሽኝንና ሌሎች ተጓዳኝ በሽታዎችን ለመከላከል የሚያገለግሉ መድሃኒቶችንና የህከምና መገልገያ ቁሳቁሶችን ለማሟላት የሚያስችል አስቸኳይ ግዢ መፈጸሙን የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ማስታወቁን አል ዓይን አማርኛ ዘግቧል።
ግዢው ከውጭ ሃገራት የተፈጸመ ነው ያሉት የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋአለም አድራሎ 50 የአንስቴዥያ ማሽኖች፣ 400 መካኒካል ቬንትሌተሮች እና 13 ሚሊዬን የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብሎች ወደ ሃገር መግባታቸውን ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪ ተጓዳኝ በሽታዎችን በተመለከተ የወባ ፣ የኤች አይቪ እና የቲቢ መድሃኒቶች የአቅርቦት እና የስርጭት እጥረት እንዳይፈጠር ጥረት እየተደረገ እንደሆነም ነው አቶ ተስፋአለም የገለጹት፡፡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ አባላት በኤጀንሲው ጉብኝት አድርገዋል፡፡

የወባ መድኃኒት ለኮሮና ቫይረስ ህክምና ለማዋል ሲደረግ የነበረው ጥናት ተቋረጠ!
የዓለም ጤና ድርጅት የኮሮና ቫይረስ ታማሚዎችን ለማከም ይረዳል በተባለለት ሃይድሮክሎሮኪን ላይ ያደርግ የነበረውን ጥናት ማቋረጡን #BBC አስነብቧል።
ጸረ-ወባ የሆነው መድኃኒት በሽታውን ቀድሞ ለመከላከልም ሆነ የታመሙትን ለማከም ሊውል ይችላል የሚል ሰፊ ቅድመ ግምት ነበር። ይሁን እንጂ ይህ በጥናት ሳይረጋገጥ ቆይቷል።
ፕሬዝደንት ትራምፕን በተደጋጋሚ መድኃኒቱ ፈዋሽ ስለመሆኑ እና እርሳቸው ይወስዱት እንደነበር መናገራቸው ይታወሳል።
የዓለም ጤና ድርጅት /WHO/ እንዳለው ከሆነ በመድኃኒቱ ላይ የተደረጉ ጥናቶች እንደጠቆሙት "ሃይድሮክሎሮኪን" የኮሮና ቫይረስ ታማሚዎችን አልታደገም። "ሃይድሮክሎሮኪን በሆስፒታል የሚገኙ የኮቪድ-19 ታማሚዎችን የሞት መጠን መቀነስ አልቻለም" ብሏል ጅርጅቱ ባወጣው መግለጫ።

የጤና ሚኒስቴር ማብራሪያ ሊሰጥ ይገባል!
(በዶክተር ኃይለልዑል መኮንን)
ከትላንት በስትያ ይፋ ስለተደረገው 'ዴክሳሜታሶን' መድሃኒት ከልጅ እስከ አዋቂ መድሀኒቱን ለመሸመት በየመድሀኒት መደብሩ ፍለጋ ሲያደርጉ እንደነበር ሰማሁኝ።
እድል የቀናዉ እንደገዛና ፤ ያልቀናዉ ደግሞ አጨብጭቦ እንደተመለሰ ስሰማ ደነገጥኩኝ። 'ነገ ይሄ መድሀኒት ከገበያ ሊጠፋ ይችላል' በሚል ፍራቻ ገዝቶ ለማስቀመጥ ህብረተሰቡ እየተሯሯጠ ይገኛል።
እንደዉ ለመሆኑ ስለመድሀኒቱ የጎንዮሽ ጉዳት እንዲሁም ስለመድሀኒቱ አጠቃላይ መረጃ እና ምንነት ምን ያህል አዉቀናል ? የዚህ መረጃ ክፍት መነሾዉ ደግሞ መጀመሪያ ላይ ስለመድሀኒቱ በተሳሳተ አማርኛ በተረጎሙት የዜና አዉታሮች ችግር ነዉ ብዪ እገምታለሁ።
እባካችሁ ጋዜጠኞች እንደዚህ አይነት መረጃ ለህዝቡ ከማድረሳችሁ በፊት የጤና ባለሙያዎችን ብታሳትፉ መልካም ነዉ።
መድሀኒቱ በሀኪም ትዕዛዝ ብቻ የሚሰጥ እና በከፍተኛ ጥንቃቄ' የሚሰጥ መድኃኒት ሲሆን በርካታ 'የጎንዮሽ ጉዳት' እንዳለዉ መረዳት ይገባናል።
መድሀኒት ቤቶችም (Pharmacy) እባካችሁ ሙያዊ ስነምግባራችሁን ተጠቅማችሁ ከሀኪም ትዕዛዝ ዉጪ ይሄን መድሀኒት አትሽጡ።
ከዚህ መድሀኒት ጋር በተያያዘ ደግሞ 'የጤና ሚኒስቴር' ባፋጣኝ መግለጫ ብትሰጡን ያኔ መጀመሪያ ኮሮና ቫይረስ እንደገባ የፊት ጭምብል እና ሳኒታይዘር ላይ የተፈጠረዉን ክስተት እንዳይደገም ይረዳናል።

#MoHEthiopia
ዴክሳሜታሰን (Dexamethasone) መድሃኒት በኮቪድ-19 በፅኑ የታመሙትን ሰዎች ህይወት ለመታደግ ይረዳል መባሉን ተከትሎ ኢትዮጵያ ተጨማሪ ጥናቶችና ምክሮችን እያሰባሰበች መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ሳህረላ አብዱላሂ ለኤፍ ቢ ሲ /FBC/ እንደተናገሩት ፥ ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተልን ነዉ ብለዋል።
ሚኒስቴሩ ጤናን በሚመለከት የተለያዩ አማካሪ ቡድኖች ጋር ይሰራል ያሉት ሚኒስትር ዴታዋ ፤ ከኮቪድ-19 በሀገሪቱ መከሰት በኋላም ይህ ከሀገር ውስጥና ዲያስፖራን በማካተት የሚሰራው አማካሪ ቡድንም የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን አንስተዋል።
ከዚህ ጋር ተያይዞ የ“ዴክሳሜታሰን” መድሃኒት ጉዳይም መሆኑን በመግለፅ ፤ በጉዳዩ ላይ ሚኒስቴሩን የሚያማክሩ ቡድኖች ክትትል እያደረጉ ነው ብለዋል።
ቡድኑም በመድሃኒቱ ላይ እያደረገ ያለውን የጥናት ውጤት እስከ ዛሬ ምሽት ለሚኒስቴሩ የሚገለጽ መሆኑን በመጥቀስ፤ በቀጣይነት ለህብረተሰቡ ይፋ ይደረጋል ነዉ ያሉት።
እስከዛው ግን ህብረተሰቡ አላስፈላጊ ወጪ ከማውጣት በመቆጠብ የጤና ሚኒስቴር መግለጫን እንዲጠባበቅ ጥሪ አስተላልፈዋል።
ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ

"በኢትዮጵያ ተጨማሪ 195 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ የ2 ሰዎች ህይወት አልፏል።" - ዶክተር ሊያ ታደሰ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 195 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል!
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4,853 የላብራቶሪ ምርመራ 195 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 3,954 ደርሷል።
ቫይረሱ የተገኘባቸው 90 ወንድ እና 105 ሴት ሲሆኑ የዕድሜ ክልላቸው ከ1 እስከ 85 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው።
ቫይረሱ የተገኘባቸው 144 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 12 ሰዎች ከአማራ ክልል፣ 12 ሰዎች ከትግራይ ክልል፣ 7 ሰዎች ከአፋር ክልል፣ ፣ 7 ሰዎች ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ፣ 4 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ 4 ሰዎች ከሱማሌ ክልል፣ 3 ሰዎች ከጋምቤላ ክልል እና 2 ሰዎች ከሐረሪ ክልል ናቸው።
ተጨማሪ መረጃ ፦
በትላንትናው ዕለት ሰማንያ አምስት (85) ሰዎች (73 ከአዲስ አበባ፣ 5 ከኦሮሚያ ክልል፣ 5 ከአማራ ክልል እና 2 ከትግራይ ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 934 ደርሷል።

በኢትዮጵያ የሟቾች ቁጥር 65 ደርሷል!
ከጠቅላላው የላብራቶሪ ምርመራ ውስጥ 44 (19 ከጤና ተቋም እና 25 ከማህበረሰብ በተወሰደ ናሙና) ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ ሲሆን የኮሮና ቫይረስ የተገኘበት ናሙና የለም።
ከዚህ ባለፈ ሁለት (2) በህክምና ማዕከል ውስጥ ህክምና ላይ የነበሩ ሰዎች ህይወት አልፏል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸውና ህይወታቸው የለፈ ሰዎች ቁጥር ስልሳ አምስት (65) ደርሷል።
ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦
1. የ80 ዓመት ወንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ ፤ በህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበሩ።
2. የ60 ዓመት ሴት የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ በህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበሩ።

#AMHARA
በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት የተደረገው ምርመራ 912 ሲሆን ከነዚህ መካከል ነው 12 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው።
- 8 ሰዎች በምዕ/ጎንደር ዞን በሚገኘው መተማ ለይቶ ማቆያ ማዕከል ክትትል ሲደረግላቸው የነበሩ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው
- 1 ሰው ከደሴ ከተማ አስተዳደር
- 3 ሰዎች ኦሮሞ ብ/ሰብ ዞን በሚገኘው ከሚሴ ከተማ በተደረገ የአሰሳ ምርመራ የተገኙ ናቸው።
በፆታ አኳያ 9 ወንዶች እና 3 ሴቶች ናቸው ፤ የእድሜ ክልላቸው ከ15 እስከ 50 ዓመት ውስጥ ይገኛል።
#DireDawa
በድሬዳዋ ባለፉት 24 ሰዓት የተደረገው የላብራቶሪ ምርመራ 155 ሲሆን ከነዚህ መካከል ነው 7 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው።
በቫይረሱ የተያዙት ግለሰቦች 6 ወንዶች እና 1 ሴት ሲሆኑ እድሜያቸው ከ19-70 ዓመት ያሉና ነዋሪነታቸው በድሬዳዋ ከተማ የሆኑ ናቸው።
አራቱ (4) ከዚህ ቀደም በለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበሩ (ሶስቱ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ የነበራቸው አንዱ ከጅቡቲ ተመላሽ) ሲሆኑና ሁለቱ ከማህበረሰቡ ከተወሰደ ናሙና የተገኙ ናቸው። አንደኛዋ ግለሰብ በሆስፒታል በተጓዳኝ ህመም ህክምና ላይ የነበሩ ናቸው።
#TIGRAY
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የተደረገው 283 የላብራቶሪ ምርመራ ሲሆን ከነዚህ መካከል ነው 12 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠው። 11 የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው ናቸው፥ 1 ሰው በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያለው። በአጠቃላይ በትግራይ ክልል በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 179 ደርሷል።

#OROMIA
በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት የተደረገው የላብራቶሪ ምርመራ 292 ሲሆን ከነዚህ መካከል ነው 4 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው።
- 2 ሰዎች ከሰበታ (38 ዓመት ወንድና የ13 ዓመት ሴት) ሲሆኑ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ የላቸውም፤ ሁለቱም በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው ናቸው።
- 1 ሰው ከቡራዩ (የ33 ዓመት ሴት) ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የላትም፤ ከማህበረሰቡ የተገኘች።
- 1 ሰው ከሞጆ (የ39 ዓመት ወንድ) የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የለውም፤ ከማህበረሰቡ የተገኘ።
#AFAR
በአፋር ክልል በኮቪድ-19 መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 60 ደርሷል። ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የተካሄደው የላብራቶሪ ምርመራ 118 ሲሆን ከነዚህ መካከል ነው 7 ሰው በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው።
#HARARI
ባለፉት 24 ሰዓት በሐረሪ ክልል 94 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን ከነዚህ መካከል ነው 2 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው። ሁለቱም በለይቶ ማቆያ ውስጥ የሚገኙ የ38 ዓመት ወንድ (የጂኔላ ወረዳ)ና የ7 ህፃን ሴት (ሽንኮር ወረዳ) ነዋሪዎች ናቸው።

በሐረሪ ክልል 1 ሞት ተመዝግቧል!
የሐረሪ ክልል ጤና ቢሮ በክልሉ ከኮቪድ-19 ጋር በተገናኘ የአንድ (1) ሰው ህይወት ማለፉን በዛሬው ሪፖርት ላይ አሳውቋል።
ሟቹ የአራት (4) ወር ህፃን (የድሬጠያራ ነዋሪ) ሲሆን ሪፖርት ከተደረገበት ቀን ጀምሮ የህክምና እርዳት ሲደረግለት እንደቆየ ቢሮው ገልጿል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ዛሬ በጤና ሚኒስቴር የወጣውን ሪፖርት መልሶ የተመለከተ ሲሆን የ4 ወር ህፃን መሞቱን የሚገልፅ መረጃ አላገኘም።
የሐረሪ ክልል ጤና ቢሮ ሪፖርት ያደረገው ሞት አጠቃላይ የሀገሪቱን የሟቾች ቁጥር ስልሳ ስድስት (66) ያደርሰዋል።