TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በኢትዮጵያ ያገገሙ ሰዎች 849 ደረሱ!

በትላንትናው ዕለት አንድ መቶ አስራ አንድ (111) ሰዎች (109 ከአዲስ አበባ ፣ 2 ከድሬዳዋ) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው (ኮቪድ-19) ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ስምንት መቶ አርባ ዘጠኝ (849) ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
👏የጤና ባለሞያዎቻችን እናመሰግናለን👏

በኢትዮጵያ በሁለት ቀናት ብቻ (ሰኔ 8 እና ሰኔ 9) 229 ሰዎች ከኮቪድ-19 አገግመዋል። የጤና ባለሞያዎቻችን እየሰሩት ላለው ትልቅ ስራ ያለንን ከፍተኛ ክብር ለመግለፅ እንወዳለን!

አሁንም ወረርሽኝኑን ለመከላከል ጥንቃቄ አይለየን። የጤና ባለሞያዎችን ምክር ካዳመጥን ፣ መመሪያዎችን ከተገበርን እና በየዕለቱ በኮሮና ቫይረስ የሚያዙ ሰዎችን ቁጥር መቀነስ ከቻልን ከዚህ ፈተና መውጣታችን አይቀርም ፤ ነገ የተሻለ ቀን ይሆናል!

PHOTO : FILE
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 129 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል! ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5,274 የላብራቶሪ ምርመራ 129 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 3,759 ደርሷል። ቫይረሱ የተገኘባቸው 79 ወንድ እና 50 ሴት ሲሆኑ የዕድሜ ክልላቸው ከ1 እስከ 70 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት ሁሉም ኢትዮጵያውያን…
#OROMIA

በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት የተደረገው የላብራቶሪ ምርመራ 554 ሲሆን ከነዚህ መካከል ነው 5 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው።

- 2 ሰዎች ከቦረና ሲሆኑ አንደኛዋ እድሜዋ የ37 የሆነችና ወደ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ (ኬንያ) ያላት ናት። ሁለተኛው ወንድ ሲሆን እድሜው 21 ነው ፤ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ የለውም ፤ ከማህበረሰቡ የተገኘ ነው።

- 2 ሰዎች ከቡራዩ ሲሆኑ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የላቸውም፤ ከሁለቱ አንደኛው የ3 ዓመት ህፃን ሲሆን በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ አለው። ሌላኛው የእድሜው 26 ሲሆን ከማህበረሰቡ የተገኘ ነው።

- 1 ሰው ከሰሜን ሸዋ እድሜው 20 የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ የሌለው፤ ከማህበረሰቡ የተገኘ።

#SNNPRS

በደቡብ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 456 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን ከነዚህ መካከል 7 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።

ሁሉም የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የሌላቸው ሲሆኑ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ አላቸው።

ቫይረሱ የተገኘባቸው ሁሉም ከሲዳማ ዞን ናቸው። ከሰባቱ መካከል አምስቱ (5) የቦርቻ ወረዳ ነዋሪዎች ሲሆኑ የእድሜ ክልላቸው ከ18 እስከ 24 ነው። ሁለቱ ከቡርሳ ወረዳ እና ዳሌ ወረዳ ሲሆኑ እድሜያቸው 20 እና 21 ነው።

#TIGRAY

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የተደረገው 460 የላብራቶሪ ምርመራ ሲሆን ከነዚህ መካከል ነው 11 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠው። ሁሉም የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው ናቸው። በአጠቃላይ በትግራይ ክልል በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 161 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AMHARA

በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት የተደረገው ምርመራ 667 ሲሆን ከነዚህ መካከል ነው 6 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው።

- 2 ሰዎች በምዕ/ጎንደር ዞን በሚገኙ ለይቶ ማቆያ ማዕከል ክትትል ሲደረግላቸው የነበሩ (1 የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያለው፤ 1 ከታመሙ ሰዎች ጋር ግንኙነት የነበረው)

- 1 ሰው በደ/ወሎ ዞን በሚገኘው ኮምቦልቻ ከተማ

- 3 ሰዎች ከሰ/ወሎ ዞን (2 ከጋዞ ወረዳ እና 1 ከቆቦ ወረዳ) ሲሆን ሁለቱ ከለይቶ ማቆያ እና 1 ከማህበረሰቡ የተደረገ ምርምራ የተገኙ ናቸው።

በፆታ አኳያ ሁሉም ወንዶች ናቸው ፤ የእድሜ ክልላቸው ከ18 እስከ 57 ዓመት ውስጥ ይገኛል።

#AFAR

በአፋር ክልል በኮቪድ-19 መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 53 ደርሷል።ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የተካሄደው የላብራቶሪ ምርመራ 16 ሲሆን ከነዚህ መካከል ነው 1 ሰው በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው።

#DireDawa

በድሬዳዋ ባለፉት 24 ሰዓት የተደረገው የላብራቶሪ ምርመራ 113 ሲሆን ከነዚህ መካከል ነው 4 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው።

በቫይረሱ የተያዙት ግለሰቦች 3 ወንዶች እና 1 ሴት ሲሆኑ እድሜያቸው ከ18-50 ዓመት ያሉና ነዋሪነታቸው በድሬዳዋ ከተማ የሆኑ ናቸው።

ሁለቱ ከዚህ ቀደም በለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበሩና ሁለቱ ከማህበረሰቡ ከተወሰደ ናሙና የተገኙ ናቸው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በአዲስ አበባ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር 2,743 ደርሷል!

ባለፉት 24 ሰዓት በአ/አ ቫይረሱ የተገኘባቸው 85 ሰዎች ሲሆኑ ከነዚህ መካከል 5 ሰዎች የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው ፣ 16 ሰዎች በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን የተቀሩት 64 ሰዎች የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክም ሆነ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት #የሌላቸው ናቸው።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በአዲስ አበባ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰማንያ አምስት (85) ሰዎች ክፍለ ከተማ ፦

• አዲስ ከተማ - 18 ሰዎች
• ቦሌ - 6 ሰዎች
• ጉለሌ - 6 ሰዎች
• ልደታ - 6 ሰዎች
• ኮልፌ ቀራኒዮ - 9 ሰዎች
• ቂርቆስ - 3 ሰዎች
• አራዳ - 12 ሰዎች
• የካ - 4 ሰዎች
• ንፋስ ስልክ ላፍቶ - 6 ሰዎች
• አቃቂ ቃሊት - 9 ሰዎች
* አድራሻቸው በመጣራት ላይ ያለ - 5 ሰዎች

አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ 2,743 ሰዎች ክፍለ ከተማ እንደሚከተለው ቀርቧል ፦

• አዲስ ከተማ - 648 ሰዎች
• ቦሌ - 426 ሰዎች
• ጉለሌ - 295 ሰዎች
• ልደታ - 272 ሰዎች
• ኮልፌ ቀራኒዮ - 263 ሰዎች
• ቂርቆስ - 158 ሰዎች
• አራዳ - 165 ሰዎች
• የካ - 150 ሰዎች
• ንፋስ ስልክ ላፍቶ - 142 ሰዎች
• አቃቂ ቃሊት - 88 ሰዎች
* አድራሻቸው በመጣራት ላይ ያለ - 136 ሰዎች

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Dexamethasone 'ዴክሳሜታሰን' የተባለው መድሃኒት በኮሮና ቫይረስ በሽታ በፅኑ የታመሙትን ሰዎች ህይወት ለመታገድ እንደሚረዳ የብሪታንያ ተመራማሪዎች ገለፁ። ሳይንቲስቶቹ በህክምና ላይ ያሉና በቬንትሌተር የሚተነፍሱት ታማሚዎችን የመሞት እድል በአንድ ሶስተኛ እንደሚቀንስ የገለጹ ሲሆን በኦክስጅን ውስጥ ያሉትን የመሞት ዕድላቸውን በአንድ አምስተኛ እንደሚቀንስ ተናግረዋል፡፡ ይህ መድሃኒት የኮቪድ…
#DrTedrosAdhanom

በዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ 'ዴክሳሜታሶን' በተባለው መድኃኒት ላይ የተደረገው ሙከራና ያስገኘውን ውጤት በበጎ እንደሚመለከተው የዓለም ጤና ድርጅት ማስታወቁን #ቢቢሲ ዘግቧል።

በሙከራው ይህ መድኃኒት በኮቪድ-19 በጽኑ ከታመሙ ሰዎች የአንድ ሦስተኛውን ሕይወት መታደግ እንደሚችል እና በወረርሽኙ ሰበብ ኦክስጂን በሚያስፈልጋቸው ሰዎች ላይ የሚያጋጥምን ሞት በአንድ አምስተኛ ሊቀንስ እንደሚችል ለድርጅቱ የቀረበው የመጀመሪያ ደረጃ ግኝት አመልክቷል።

ድርጅቱ እንዳለው የዴክሳሜታሶን ጠቀሜታ በኮቪድ-19 በጸና በታመሙ ሰዎች ላይ እንጂ ቀለል ያለ ህመም ባለቸው ላይ እንዳልሆነ አመልክቷል https://telegra.ph/T-06-18-2

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የሰኔ 14ቱ ግርዶሽ- የትና መቼ በኢትዮጵያ ?

በአብዛኛው የኢትዮጵያ ክፍል ፀሐይ ከ60 - 80 ፐርሰነት ተሸፍና ከፊል ግርዶሽ ይታያል፡፡ ከ80 ፐርሰነት በላይ ያለውን ዋናውን ግርዶሽ ግን ከምዕራብ ኢትዮጵያ አንሥቶ እስከ ሰሜን ምሥራቅ ኢትዮጵያ በሚገኝ ስፍራ ጎልቶ ይታያል፡፡

ክስተቱ ወለጋ አካባቢ ጀምሮ ከፊል ጎጃምን ፣ ከፊል ጎንደርን አልፎ ወደ ወሎ ላሊበላን አቋርጦ ይሄዳል፡፡ በእነዚህ ቦታዎች ፀሐይ እስክ 99 ፐርሰንት ተሸፍና ቀለበታዊውን ግርዶሽ ማየት ይቻላል፡፡

ቀለበታዊ ግርዶሽ ማየት ከሚችሉ አነስተኛ ከተሞች/ቦታዎች ቤጊ ፣ ሜቲ፣ መንዲ ፣ ጫልቱ ፣ ቡሬ ፣ አገው ግምጃቤት ፣ እንጅባራ ፣ ግሽ አባይ፣ ሞጣ ፣ ዳሞት ፣ ጋይንት ፣ ንፋስ መውጫ ፣ ጋሸና ፣ ሙጃ ፣ ዋጃ ፣ ቆቦ ፣ ኮረም፣ አላማጣ ፣ ጊራራ እና ላሊበላ ይገኙበታል፡፡

በአዲስ አበባ ፤ ሐዋሳ ፤ ድሬደዋ ፤ መቐለ ፤ ደሴ ፤ አዳማ ፤ በመሳሰሉት ከተሞች ቀለበታዊ ግረዶሽ ባይኖርም ከፊል የፀሐይ ግርዶሽ ግን ይኖራቸዋል - #ESSS

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
መኖር መታደል ነዉና ለመኖር እንጠንቀቅ!

(በዶክተር ጋሻው አረጋ)

'የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ምሽት ይጀምራል።' ተብሏል። በኮሮና እየተናጠች ባለችዉ አፍሪቃ የሚገኘዉ ህዝብ በተለይም ወጣቱ ደግሞ ለእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ያለዉ ፍቅር በቃላት የሚገለጥ አይደለም፤ ናፍቆታልም።

ያለንበት ይኽ ወሳኝ ጊዜ ደግሞ 'የሞት ሽረት' ትግል የምናደርግበትና ህይወታችንን የምንታደግበት አስከፊ ወቅት ነዉ። ጨዎታዎች የሚካሄዱት ማታ መሆኑ ደግሞ ሌላዉ ፈታና ነዉ።

ጊዜዉ ጥሩ አይደለምና ወጣቱም ሰሜቱን ገዝቶ ቤቱ ቢቀመጥ መልካም ነዉ፤ የእግር ኳስ ማሳያ ማዕከሎችም ጥብቅ ቁጥጥር ሊደረግባቸዉ ይገባል! ያለ በለዚያ ተያይዘን ማለቃችን ነዉ። መኖር መታደል ነዉና ለመኖር እንጠንቀቅ!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Eritrea

በኤርትራ ተጨማሪ 10 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ ሁሉም በቅርቡ ከሱዳን የተመለሱና በለይቶ ማቆያ ውስጥ የሚገኙ ናቸው። በአጠቃላይ ኤርትራ ውስጥ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 131 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያና ጎረቤት ሀገራት የሟቾች ቁጥር ከ800 አለፈ!

በኢትዮጵያ ፣ ኬንያ ፣ ሱማሊያ፣ ጅቡቲ፣ ሱዳን ፣ ደቡብ ሱዳን እና ኤርትራ በአጠቃላይ 24,691 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል።

ከኤርትራ ውጭ በስድስቱ (6) ሀገራት የ808 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ በአጠቃላይ 9,215 ሰዎች በተደረገላቸው ህክምና ከበሽታው አገግመዋል።

በኢትዮጵያና በጎረቤት ሀገራት ያለውን የኮቪድ-19 ወቅታዊ መረጃ ከ CARD ጋር በመተባበር ባዘጋጀነው ምስል ከላይ መመልከት ትችላላችሁ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

"መከላከል ከመታከም ይቀላል ፣ ቤት መቆየትም ሆስፒታል ከመተኛት ይሻላል ፣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አድርጎ መተንፈስ በማሽን ከመተንፈስ ይልቃል። ስለሆነም እነዚህን እንዲሁም ሌሎችን የቫይረሱን መከላከያ መንገዶች ሳንዘናጋ በመተግበር እራሳችንንና የምንወዳቸውን ከኮሮና ቫይረስ በሽታ እንጠብቅ።" - ዶ/ር ሊያ ታደሰ (የጤና ሚኒስትር)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ደም ይለግሱ!

ደም መንገድ ከየትኛውም ደግነት ሩህሩህነት እንዲሁም ስጦታ ይልቃል!

ሰኔ 13 እና 14 በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል አምስተኛ በር ጎን በማገኘው የቀድሞ ነዳጅ ማደያ ቦታ አጠገብ!

#SHARE #ሼር

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#UPDATE

ሰኔ 14 ቀን 2012 ዓ.ም የሚጠበቀውን 'የፀሐይ ግርዶሽ' በማስመልከት የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲና የኢፌዲሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር በጋራ በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አዳራሽ ዛሬ 8፡00 ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ እና የጥንቃቄ መልዕክቶች ይሰጣሉ፡፡ ተከታትለን እናሳውቃችኃለን!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia