TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#DrLiaTadesse

የጤና ሚኒስቴር ዛሬ በሰጠው መግለጫ የኮቪድ-19 ስርጭት ካለፉት 2 ወራት ይበልጥ ባለፉት 2 ሳምንት ውስጥ የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር 63 በመቶ ድርሻ እንዳለው ገልጿል።

ቫይረሱ ከተገኘባቸው አጠቃላይ ቁጥር 228 የሚሆኑት በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ መሆናቸውን አሳውቋል።

የልደታ ክ/ከተማ 40 በመቶ የሚሆነውን ቫይረሱ ያለባቸውን ሰዎች ቁጥር ሲይዝ አዲስ ከተማ ክፍለከተማ በሁለተኛነት ድርሻውን መያዙን ዶ/ር ሊያ ታደሰ ገልጸዋል፡፡

ይህም ቫይረሱ በአዲስ አበባ በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ መምጣቱን የሚያመላክት እንደሆነ ነው የተገለጸው፡፡

የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የሌላቸው እንዲሁም ቫይረሱ ካለበት ሰው ጋር ግንኙነት ሳይኖራቸው በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር 16 በመቶ መድረሱንም ዶ/ር ሊያ አስታውቀዋል፡፡

ምንጭ፦ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrEbbaAbate

የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር ከቫይረሱ ጋር ንክኪ ያላቸውን ሰዎች ቅኝት የማድረግ ስራ ዋነኛ ተግባር መሆኑን የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት ዳይሬክተር ዶ/ር ኤባ አባተ ገልፀዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 በተደረገ ቅኝት ከቫይረሱ ጋር ንክኪ ከነበረው አንድ ሰው ጋር ንክኪ የነበራቸው 32 ግለሰቦች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡

ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች ውስጥ በወረዳው በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ በተደረገ ድንገተኛ ምርመራ አርባ (40) 'የህግ ታራሚዎች' ይገኙበታል፡፡

ምንጭ፦ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ATTENTION

የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ኤባ አባተ የኮሮና ቫይረስ ከተገኘባቸው 365 ሰዎች 56ቱ የውጭ ሃገር የጉዞ ታሪክም ሆነ ከበሽታው ተጠቂ ግለሰብ ጋር ንክኪ #ያልነበራቸው መሆናቸውን አሳውቀዋል።

ከእነዚህ ውስም 48 በመቶ ' በአዲስ አበባ ከተማ ' ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎች በመሆናቸው ህብረተሰቡ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባው አሳስበዋል።

#FBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#SouthSudan የደቡብ ሱዳን የኢንፎርሜሽን ሚኒስትር ሚካኤል ማኩዪና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ማርቲን ኤሊያ ሎሞሮ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ከተረጋገጠ ከፍተኛ ባለስልጣናት መካከል እንደሚገኙበት #SSNN ይፋ አድርጓል። 2ቱም ሚኒስትሮች ባለፈው ወር ናሙና ለመስጠት ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተው ነበር የተባለ ሲሆን በዚህ ወር ግን ምርመራ ሲደረግላቸው ሁለቱም በቫይረሱ መያዛቸው መረጋገጡን #SSNN ስማቸው…
ሚካኤል ማኩዪ በቫይረሱ መያዛቸውን አረጋግጠዋል!

የደቡብ ሱዳን የኢንፎርሜሽን ሚኒስትር የሆኑት ሚካኤል ማኩዪ በተደረገላቸው የኮሮና ቫይረስ የላብራቶሪ ምርመራ #በቫይረሱ መያዛቸውን በይፋ አሳውቀዋል።

ሚኒስትሩ ለቪኦኤ እንደተናገሩት የቀድሞ 'የኮቪድ-19 ታስክ ፎርስ' አባላት በሙሉ በኮሮና ቫይረስ ስለመያዛቸው መረጃው እንዳላቸው ተናግረዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 24 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል!

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 3,460 የላብራቶሪ ምርመራ ሃያ አራት (24) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 389 ደርሷል፡፡

ቫይረሱ የተገኘባቸው 18 ወንድ እና 6 ሴት ናቸው። በዜግነት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ ከ4 እስከ 57 ዓመት የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ናቸው።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 9 ሰዎች ከአዲስ አበባ (5 ሰዎች በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው እና 4 ሰዎች የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት #የሌላቸው) ፣ 7 ሰዎች ከትግራይ ክልል (4 የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው እና 3 በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው ከነዚህም ውስጥ 1 መቐለ ለይቶ ማቆያ ያለ ሲሆን ስድስቱ (6) ማይካድራ ለይቶ ማቆያ ያሉ ናቸው) ፣ እንዲሁም 8 ሰዎች ከአማራ ክልል (የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው እና መተማ ለይቶ ማቆያ ያሉ) ናቸው።

የዕለቱ ታማሚዎች የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላቸው ግንኙነት ፦

• የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው - 12

• በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው - 8

• የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው - 4

ተጨማሪ መረጃ ፦

በትላትናው ዕለት 2 ሰዎች ከአማራ ክልል ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን አጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር አንድ መቶ ሃያ ሁለት (122) ደርሷል።

@tikvahethmagazine @tikvahethiopia
#MutahiKagwe

በኬንያ በአንድ ቀን 66 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸውን ተረጋገጠ!

በኬንያ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው የላብራቶሪ ምርመራ ስልሳ ስድስት (66) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። እስካሁን ከተመዘገቡት የአንድ ቀን ኬዞች #ከፍተኛው ነው። አጠቃላይ በሀገሪቱ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች 1,029 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
እንኳን አደረሳችሁ!

TIKVAH-ETHIOPIA እንኳን ለሲዳማ የፊቼ ጨምበላላ በዓል በሰላም አደረሰን ፤ አደረሳችሁ ለማለት ይወዳል። በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የደስታ፣ የመተሳሰብ ይሆን ዘንድ እንመኛለን!

ይህን ዓለምን ያስጨነቀ ወረርሽኝን አሸንፈን የዓለም ቅርስ የሆነውን 'ፊቼ ጨምባላላ በዓል' በአደባባይ ተሰባስበን የምናከብርበት ጊዜ ሩቅ እንደማይሆን #ተስፋ እናደርጋለን!!

በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ካምብሪጅ ዩኒቨርስቲ ለ1 አመት ያህል ትምህርት በርቀት እንዲሆን ወሰነ!

(በቢቢሲ የአማርኛው አገልግሎት)

በዓለም ላይ ካሉት እውቅ ዩኒቨርስቲዎች አንዱ የሆነው ካምብሪጅ ዩኒቨርስቲ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ምክንያት ለአንድ (1) አመት ያህል በክፍል ውስጥ የሚኖር ትምህርት #እንደሌለ አስታውቋል።

ሆኖም ከዚህ ቀደም እንደነበረው ሁሉም ትምህርቶች በ 'ኦንላይን' የሚሰጡ ሲሆን " ከተቻለም የተወሰኑ ተማሪዎችን በቡድን አንድ ቦታ ላይ በማድረግ መማር የሚችሉበትን መንገድ ልናመቻች እንችላለን ብሏል።

ዩኒቨርስቲው 'ይህ መሆን የሚችለው ግን ጥቂት ተማሪዎች ቢሆኑም አካላዊ ርቀታቸውን መጠበቅ ሲችሉ ነው' በማለት ባወጣው መግለጫ አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ማዳጋስካር ውስጥ የኮሮና ስርጭት እየጨመረ ነው!

በማዳጋስካር በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር በየዕለቱ እየጨመረ ነው።

ባለፉት 24 ሰዓት ብቻ አርባ አምስት (45) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ ከአርባ አምስቱ መካከል ሶስት (3) ሰዎች ከአንታናናሪቮ እንደሆኑ ተሰምቷል።

አጠቃላይ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች 371 የደረሰ ሲሆን ከነዚህ መካከል 131 ሰዎች በተደርገላቸው ህክምና አገግመዋል፤ የሁለት (2) ሰዎች ህይወት አልፏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#BREAKING

ጅቡቲ ውስጥ በአንድ ቀን 210 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!

ጅቡቲ ውስጥ ባለፉት 24 ሰዓት 1,123 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ሁለት መቶ አስር (210) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 1,828 ደርሰዋል።

ከዚህ በተጨማሪ የሁለት (2) ሰዎች ህይወት ማለፉ ሪፖርት ተደርጓል፤ በዚህም አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር ዘጠኝ (9) ደርሷል።

በሌላ በኩል ትላንት አስራ ዘጠኝ (19) ሰዎች በተደረገላቸው ህክምና ከበሽታው (ኮቪድ-19) ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 1,052 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሱማሊያ በአንድ ቀን 71 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!

ባለፉት 24 ሰዓት በሱማሊያ ተጨማሪ 71 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥርም 1,573 ደርሷል።

በሌላ በኩል በትላንትናው ዕለት አስር (10) ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 188 ደርሷል።

በተጨማሪ የ2 ሰዎች ህይወት ማለፉን ተከትሎ አጠቃላይ በሀገሪቱ በኮቪድ-19 ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ስልሳ አንድ (61) ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#BBC

የቻይና ጤና ባለሙያዎች በሰሜን ምሥራቅ የአገሪቷ ክፍል የተገኘው የኮቪድ-19 ታማሚ ወረርሽኙ በዉሃን ሲጀምር ከታየው በተለየ መልኩ የበሽታ ምልክትና ምልክቱ ለመታየት ረዘም ያለ ጊዜ መውሰዱን መታዘባቸውን ተናገሩ።

በቻይና ብሔራዊ ጤና ኮሚሽን የህክምና ቡድን ከሚገኙ የጽኑ ህሙማን ከፍተኛ የጤና ባለሙያዎች አንዱ የሆኑት ዶክተር ኪው ሃይቦ ፤ ለብሔራዊው ቴሌቪዥን ፤ ቡድኑ ስለታዘበው አዲስ ነገር ተናግረዋል።

ዶ/ር ኪው ቡድናቸው በሰሜን ምሥራቅ ሄሎንግጂያንግና ጂሊን ግዛት በኮቪድ-19 ታማሚዎች ላይ ያልተለመደ ምልክት ማየታቸውንና ምልክቱን ለማየትም ረዥም ጊዜ መውሰዱን ተመልክተዋል።

"ታማሚዎቹ ትኩሳት የላቸውም፤ ነገር ግን የጉሮሮ መከርከር ህመም አሊያም በድካም ይሰቃያሉ። አንዳንዶቹ እንዲያውም ምንም ዓይነት የበሽታው ምልክት የላቸውም" ብለዋል ዶ/ር ኪው። አክለውም ታማሚዎቹ ቫይረሱን ረዘም ላለ ጊዜ ተሸክመው እንደቆዩ አስረድተዋል።

ግሎባል ታይምስ ጋዜጣ በዉሃን አንድ ታማሚ የበሽታውን ምልክቶች ካሳየ በኋላ በሳምንት ግፋ ሲልም በሁለት ሳምንት ከቫይረሱ ነጻ ይሆናል።

ይሁን እንጂ አዲሱ ምልከታ ምንም እንኳን ኮሮና ቫይረስ የሚድን በሽታ ቢሆንም ሰዎች ቫይረሱን ተሸክመው ለረዥም ጊዜ ሊቆዩ እንደሚችሉ የሚያሳይ ነው ተብሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በደቡብ ሱዳን ተጨማሪ 134 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!

የደቡብ ሱዳን ጤና ሚኒስቴር በዛሬው ዕለት እንዳሳወቀው ተጨማሪ አንድ መቶ ሰላሳ አራት (134) ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 481 ደርሰዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ!

በመላው ዓለም በኮቪድ-19 መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ከ5 ሚሊዮን በላይ ሆኗል። ከነዚህ ውስጥ ከ327,000 በላይ ሰዎች ሞተዋል፤ 1.9 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች አገግመዋል።

በአፍሪካ የቫይረሱ ስርጭት እጅግ በፍጥነት እየተስፋፋ ሲሆን እስካሁን ከ96,000 በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ ከ2,900 በላይ ሰዎች ሞተዋል ፤ ከ39,000 በላይ ሰዎች አገግመዋል።

3 ከፍተኛ ኬዝ የተመዘገበባቸው የአፍሪካ ሀገራት ፦

- ደቡብ አፍሪካ በቫይረሱ የተያዙ 18,003 ፣ ሞት 339 ፣ ያገገሙ 8,950

- ግብፅ በቫይረሱ የተያዙ 14,229 ፣ ሞት 680 ፣ ያገገሙ 3,994

- አልጄሪያ በቫይረሱ የተያዙ 7,542 ፣ ሞት 568 ፣ ያገገሙ 3,968

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የዕርቅ ሀሳብ አለኝ!

ቲክቫህ ኢትዮጵያ (Tikvah-Eth) ከእርቀ ሰላም ኮሚሽን ጋር በጋራ በመተባበር ወጣቶች ከያሉበት ሆነው የሚሳተፉበትና የሚወዳደሩበት እንዲሁም ማኅበራዊ አስተዋጿቸውን የሚያበረክቱበት 'የእርቅ ሀሳብ አለኝ' የተሰኘ ንቅናቄ በዛሬው እለት ይፋ አድርጓል፡፡

ይህንን ፕሮጀክት በይፋ ያስጀመሩት የእርቀ ሰላም ኮሚሽን ሰብሳቢ ካርዲናል ብርሃነ ኢየሱስ ሱራፌል በሀገር በቀል የእርቅ ሥርዓት ውስጥ የወጣቱ ተሳትፎ አነስተኛ ነው ያሉ ሲሆን ምንም እንኳን በሚፈጠሩ ግጭቶች ቀዳሚ ተጎጂና ተሳታፊ ወጣቱ ቢሆንም ሰላም ግንባታ ውስጥ እንዲሳተፍ የሚደረገው እንቅስቃሴ አነስተኛ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

ካርዲናል ብርሃነ ኢየሱስ አክለውም ይህ የ'እርቅ ሀሳብ አለኝ' የተሰኘው ፕሮጀክት ወጣቱ የእርቅ እሴቱን እንዲያውቅ፣ እንዲመረምርና በመረጃ የተደገፈ ጥናት እንዲያቀርብ ያስችላል ብለዋል፡፡

በተለይ አሁን ከተከሰተው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ በቤታቸው የሚገኙ ተማሪዎች እንዲሁም በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ወጣቶች በዚህ በጎ ተግባር እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህንን ፕሮጀክት ከኮሚሽኑ ጋር ሲጀምር ወጣቶች ጋር ያለውን የእውቀትና የክህሎት አቅም ለሰላም ፣ ለበጎነትና ለፍቅር መጠቀም እንደሚቻል ለማሳየት በማለም ነው፡፡

ከዚህም ባሻገር ወጣቶች በአከባቢያቸው ያለ የእርቅ ሥርዓቶችን በማጥናት ፣ በመጠየቅ ፣ በማንበብ በሚያቀርቡት ዳሰሳዊ ጹሑፍ በባለሞያዎች አወዳድሮ ለተሳታፊዎች ሰርተፊኬት ለአሸናፊዎች ልዩ ሽልማት የሚያስገኝ ይሆናል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የዕርቅ ሃሳብ አለኝ!

ቲክቫህ ኢትዮጵያ (Tikvah-Ethiopia) ትላንት ከዕርቀ ሰላም ኮሚሽን ጋር በመተባበር በይፋ ያስጀመርነው ንቅናቄ ወጣቶች ከያሉበት ሆነው በአከባቢያቸው ስላለ የዕርቅ ሥርዓት ጥናት በማድረግና በመጠየቅ ከ5-10 ገጽ በሚሆን አጭር የገለጻ ጹሑፍ ውድድር ነው፡፡

በውድድሩ የሚሳተፉ ወጣቶች በቅድሚያ የሚመዘገቡ ሲሆን ከ15-20 ቀናት የመዘጋጃ ጊዜ ይሰጣቸዋል፡፡ ተወዳዳሪዎች ፅሁፋቸውን የሚያቀርቡት #በመረጡት ሀገራዊ ቋንቋ ነው።

በሚያስገቡት ጹሑፍ ስለ አከባቢያቸው አጠቃላይ ገለጻ፣ ማስተዋወቅ ስለሚፈልጉት ባህላዊ የእርቅ ሥርዓት ሥርዓቱ በአሁኑ ወቅት በማህበረሰቡ ዘንድ ያለውን ተቀባይነት በተጨማሪም በሥራው ወቅት የተገነዘቡት እና የታዘቡትን ምልከታ ማካተት የሚጠበቅባቸው ይሆናል፡፡

በመቀጠልም ያስገቡት #ጹሑፍ 'የኢትዮጵያ ዕርቀ ሰላም ኮሚሽን' በሚያዋቅረው ቡድን #ከተገመገመ በኃላ የጹሑፋቸው ይዘት እና አቀራረባቸው በተለያዩ የማወዳደሪያ መስፈርቶች ከተገመገመ በኃላ አሸናፊዎች የሚለዩ ይሆናል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ በውድድሩ የሚሳተፉ እንዲሁም ዋና ዋና መስፈርቶችን ያሟሉ ተሳታፊዎች በሙሉ ሰርተፍኬት ይዘጋጅላቸዋል ፤ #ለአሸናፊዎች ደግሞ 'ልዩ ሽልማት' የሚበረከት ይሆናል።

የምዝገባ ሂደቶችን በቅርቡ የምናሳውቅ ይሆናል!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሱዳን ተጨማሪ 410 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!

(በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ)

የሱዳን ጤና ሚኒስቴር ተጨማሪ 410 ሰዎች ላይ ኮሮና ቫይረስ መገኘቱንና የ10 ሰዎች (5 ከካርቱም ግዛት) ህይወት ሲያልፍ 23 ሰዎች (13 ከካርቱም) በተደረገላቸዉ ህክምና ማገገማቸዉን ገልጿል።

ቫይረሱ የተመዘገበባቸዉ ግዛቶች፦

1. ካርቱም ግዛት 345
2 .ከሰላ 3
3. ጀዚራ 27
4. ገዳሪፍ 10
5. ቀይ ባህር 2
6. ምዕራብ ዳርፉር 3
7. ሰሜን ዳርፉር 4
8. ሰሜን ኮርዶፋን 7
9. ስናር 1
10. ኒል አብያድ 2
11. ናህርኒል 6

ባጠቃላይ በሀገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 3138 (ካርቱም ግዛት 2553) መድረሱንና ከዚህ ዉስጥ 121 ሰዎች ህይወታቸዉ ሲያልፍ 309 ሰዎች በተደረገላቸዉ ህክምና ማገገማቸዉን ታውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በሱዳን ተጨማሪ 410 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ! (በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ) የሱዳን ጤና ሚኒስቴር ተጨማሪ 410 ሰዎች ላይ ኮሮና ቫይረስ መገኘቱንና የ10 ሰዎች (5 ከካርቱም ግዛት) ህይወት ሲያልፍ 23 ሰዎች (13 ከካርቱም) በተደረገላቸዉ ህክምና ማገገማቸዉን ገልጿል። ቫይረሱ የተመዘገበባቸዉ ግዛቶች፦ 1. ካርቱም ግዛት 345 2 .ከሰላ 3 3. ጀዚራ 27 4. ገዳሪፍ 10…
#SUDAN

'በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ' የቀረበው መረጃ ክፍተት አለው ፤ ሪፖርት የተደረገበትን ቀን እንጂ የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገባቸውን ቀናት የሚገልፅ አይደለም።

ከሱዳን ጤና ሚኒስቴር ባገኘነው መረጃ ዛሬ የወጣው ሪፖርት የግንቦት 10፣ 11 እና 12 ድምር ነው።

በአጠቃላይ በሶስቱ ቀናት 410 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። ይህም አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር ወደ 3,138 ከፍ አድርጎታል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

ከስሐራ በታች ባሉ ሀገራት በኮቪድ-19 ምክንያት ከፍተኛ አድሎና መገለል እየደረሰ ነው ተብሏል።

በርካቶች ከቤት ንብረታቸው እየተፈናቀሉ ነው፣ የህክምና ባለሙያዎችም ከፍተኛ መገለል ደርሶባቸዋል፡፡

ሴት ነርሶችም በትዳር አጋሮቻቸው እየተካዱ ፤ ትዳርም እየተበተነ ነው ይላል የአጃንስ ፍራንስ ፕረስ ዘገባ፡፡

ቫይረሱ እንዳለባቸው የተጠረጠሩ ሰዎችም ከፍተኛ እንግልት እየደረሰባቸው መሆኑን ነው ጥናቶች የጠቆሙት፡፡ ጥናቶቹን ያካሄደው የድንበር የለሽ ሀኪሞች የምርመራ ማዕከል ነው።

በመገለል ምክንያትም በርካቶች ለበሽታው ከመጋለጣቸው ባለፈም ተገቢውን የጤና ክትትል እያገኙ አይደለም፤ ይህም ከፍተኛ ስጋትን ጭሯል ብሏል ማዕከሉ፡፡

ምንጭ፦ አሐዱ ሬድዮ ጣቢያ (AFP)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia