“የእንቅስቃሴን ገደብ ማንሳቱ ቀስ በቀስ መሆን አለበት” - የዓለም ጤና ድርጅት
በርካታ አገራት የእንቅስቃሴ ገደባቸውን በግማሽ አሊያም ሙሉ ለሙሉ ማንሳታቸውን ተከትሎ የዓለም ጤና ድርጅት እንዲህ ያሉ ውሳኔዎች ቀስ በቀስ መሆን እንደሚገባቸው አሳሰበ፡፡
ድርጅቱ የአገራት ውሳኔ ወደ ሁለተኛ ዙር የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ ሊያመራ ይችላል ብሏል፡፡
የምዕራብ ፓስፊክ ሪጅናል ዳይሬክተር ታከሺ ካሳይ “ቢያንስ ክትባት አሊያም ውጤታማ የሆነ ህክምና እስከሚገኝ ድረስ እየተከተልነው ያለውን ሂደት አዲሱ የተለመደ ተግባራችን መሆን ይገባዋል” ሲሉ ተናግረዋል፡፡
አክለውም የተጣሉ ገደቦችን ለማለዘብ አሊያም ለማንሳት የሚያስብ ማንኛውም መንግሥት ቀጣይነት ባለው ቁጥጥር እና ደረጃ በደረጃ ማድረግ ይገባቸዋል ብለዋል፡፡
ግለሰብም ሆነ ማህበረሰብ ለአዲሱ የኑሮ ዘይቤም ዝግጁ መሆን አለባቸው ሲሉ ዳይሬክተሩ አሳስበዋል፡፡
እንደ ጃፓንና ሲንጋፖር ያሉ አገራት ወረርሽኙን ተቆጣጠርነው ካሉ በኋላ አዳዲስ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎችን እያገኙ በመሆኑ በሁለተኛ ዙር የኮቪድ- 19 ወረርሽኝ እንዳይጠቁ ስጋት ፈጥሯል፡፡
ምንጭ፡- BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

ሪቻርድ ኩየስት በኮሮና ቫይረስ ተያዘ!
እንግሊዛዊው የኬብል ኒውስ ኔትወርክ (ሲኤንኤን) “ቢዝነስ ሚንስ ኩየስት”ጋዜጠኛ ሪቻርድ ኩየስት በኮሮና ቫይረስ መያዙን ጣቢያው አስታውቋል #AlAin
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
እንግሊዛዊው የኬብል ኒውስ ኔትወርክ (ሲኤንኤን) “ቢዝነስ ሚንስ ኩየስት”ጋዜጠኛ ሪቻርድ ኩየስት በኮሮና ቫይረስ መያዙን ጣቢያው አስታውቋል #AlAin
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19
ብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር ሚያዚያ 10 ቀን 2012 ዓ/ም ይወጣ የነበረው የትንሳኤ ሎተሪ ዕጣ የተራዘመበት ምክንያት በኮሮና ቫይረስ ወረሽኝ ሳቢያ ሎተሪው ባለመሸጡ መሆኑን ገልጿል። የዕጣ መውጫ ቀኑን በቅርቡ አሳውቃለሁ ብሏል፡፡

#Ramaḍān
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጅ ዑመር ኢድሪስ በዚህ ሳምንት የሚጀመረውን የረመዳን ጾም አስመልክተው ጦር ኃይሎች በሚገኘው ቢሯቸው መግለጫ ሰጥተዋል።
ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ኡመር ኢድሪስ በመግለጫቸው መስጅዶች በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ለምዕመናኑ ዝግ ቢሆኑም ህዝበ ሙስሊሙ ወሩን በተለያዩ የአምልኮ ተግበራት በቤቱ ሆኖ ወደ ፈጣሪው የሚቃረብበት ጊዜ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል።
በወሩ ውስጥ መልካም ስራዎችን ማብዛትና የተለመደው መደጋገፍ ለኮሮና ቫይረስ በማያጋልጥ መልኩ መፈፀሙ ወቅቱ የሚጠይቀው መንፈሳዊ ተግባር መሆኑንም አስምረውበታል። የረመዳን ጾም ራስን ከመጣው ወረርሽኝ በመጠበቅ የመጣው ፈተና እንዲነሳ ህዝበ ሙስሊሙ አበክሮ እንድጸልይም ጠይቀዋል።
በዚህ የረመዳን ወር ከቤት ውጭ የተለመደው ዓይነት የህብረት ሶላትም ሆነ መሰል የአምልኮ ተግበራት እንደማይኖሩም አመልክተዋል። የዘንድሮው የረመዳን ጾም ጨረቃ ረቡዕ ምሽት ከታየች ሀሙስ እንደሚጀመርና፣ ይህ ካልሆነ ደግሞ አርብ ዕለት እንደሚጀምር ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ አስታውቀዋል።
(EBC)

#DrLiaTadesse
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 3 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!
በኢትዮጵያ ባለፋት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገ 745 የላብራቶሪ ምርመራ ሶስት (3) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ተረጋግጧል። በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 114 ደርሷል።
የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦
ታማሚ 1 - የ42 ዓመት ቻይናዊ የመኖሪያ ቦታው ሰበታ ዞን ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #የለውም፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያለው ግንኙነት በመጣራት ላይ ነው።
ታማሚ 2 - የ22 ዓመት ኢትዮጵያዊ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #የለውም፤ በስራው ባህሪ ለበሽታው ተጋላጭነት ያለው።
ታማሚ 3 - የ22 ዓመት ኢትዮጵያዊ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ፤ ከሳዑዲ የመጣና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።

ለሕክምና ከሄዱበት ሕንድ መመለስ ያልቻሉ ኢትዮጵያዊያን ችግር ላይ ነን ብለዋል!
በአሁኑ ሰዓት አገሪቱ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኘን ለመከላከል ከአንድ ነጥብ ሦስት ቢሊየን በላይ ሕዝቧ ከቤት እንዳይወጣ እና ማንኛውም እንቅስቃሴ እንዳይደርግ አግዳለች።
ይህን ተከትሎም ለህክምና ወደ አገሪቱ የሄዱ ኢትዮጵያዊያን ወደ አገራቸው መመለስ ባለመቻላቸው ከባድ ችግር ላይ እንደሚገኙ ለቢቢሲ ገልፀዋል።
ዘውዲቱ ንጉሴ የመቅኔ ንቅለ ተከላ ወይም ‘ቦንማሮ ትራንስፕላንት’ የሚባል ህክምና ለማግኘት ነበር ለሁለት ሳምንታት ወደ ሕንዷ ዋና ከተማ ኒው ደልሂ ያቀናችው።
ዘውዲቱ የደርሶ መልስ የአውሮፕላን ትኬት ብትቆርጥም በሕንድ እንቅስቃሴ እንዳይኖር በመታወጁ ካሰበችው በላይ ለተጨማሪ ቀናት እንድትቆይ ተገዳለች።
"የተወሰነ ገንዘብ ብቻ ነበር ይዤ የመጣሁት፤ ግን የእንቅስቃሴ ገደቡ ከታወጀ በኋላ መንቀሳቀስ ስላልተቻለ ካሰብኩት ጊዜ በላይ በቀን 1000 ሩፒ እየከፈልኩኝ እንድቆይ ተደርጌለሁ ፤ እጄ ላይ ያለው ገንዘብ አልቋል። አላስፈላጊ ወጪ እና እንግልት እየደረሰብኝ ነው" ትላለች።
"አጋጣሚ ሆኖ ለትምህርት የመጡ የማውቃቸው ሰዎች በመኖራቸው አገር ቤት ስሄድ የምከፍላቸው ገንዘብ ሰጥተውኛል" በማለት ስላለችበት ሁኔታ ታስረዳለች።
MORE : https://bbc.in/2yudTBu

በኢትዮጵያ ተጨማሪ አስራ ሁለት (12) ላቦራቶሪዎች በዚህ ሳምንት አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ተናገሩ።
ይህን ተከትሎ የላቦራቶሪዎች ቁጥር 20 የደረሰ ሲሆን፤ ተጨማሪ አምስት ላቦራቶሪዎችም በቅርቡ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምሩም ተመልክቷል።
ለላቦራቶሪዎቹ አስፈላጊ ግብዓቶችን በቀጣይ ለማሟላት ከተለያዩ አገራት ጋር ንግግር መጀመሩንም ሚኒስትሯ ገልዋል።
የኮሮና ቫይረስን [ኮቪድ-19] የሚመረምሩ ላቦራቶሪዎች ቁጥር መጨመር ጋር ተያይዞ በጤና ጣቢያዎች ጭምር ከሳንባ በሽታና ሳል ጋር የተያያዙ ምልክቶችን ናሙና ወስዶ መመርመር መጀመሩንም አስረድተዋል።
ምንጭ፦ ኢዜአ

በሱማሊያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች 237 ደርሰዋል!
በሱማሊያ 73 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 237 ደርሰዋል። የሟቾች ቁጥር ስምንት (8) ደርሷል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሱማሊያ 73 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 237 ደርሰዋል። የሟቾች ቁጥር ስምንት (8) ደርሷል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#SUDAN
በሱዳን በኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በየዕለቱ እየጨመረ መጥቷል። በአሁን ሰዓት በሱዳን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች አጠቃላይ ቁጥር 107 የደረሰ ሲሆን፣ 12 ሰዎች ሞተዋል ፤ 8 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል።

#DrMercyMwangangi
በኬንያ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 296 ደረሱ!
የኬንያ ጤና ሚኒስቴር መግለጫ እየሰጠ ይገኛል። ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገ 545 የላብራቶሪ ምርመራ 15 ተጨማሪ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 296 ደርሷል።
ዛሬ በቫይረሱ እንደተያዙ ከተረጋገጠ አስራ አምስት (15) ሰዎች መካከል አስራ አንዱ (11) የኬንያ ዜጎች ሲሆኑ አራቱ (4) ደግሞ የውጭ ሀገር ዜጎች ናቸው።
በሌላ በኩል ባለፉት 24 ሰዓት 5 ተጨማሪ ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ሰባ አራት (74) ደርሰዋል።

#Djibouti
ጅቡቲ ተጨማሪ 99 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ [COVID-19] መያዛቸውን ሪፖርት ማድርጓን #AJArabic ዘግቧል። በአሁን ሰዓት አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 945 ደርሰዋል። በሌላ በኩል ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 112 ደርሰዋል።

TIKVAH-ETHIOPIA
#DrLiaTadesse በኢትዮጵያ ተጨማሪ 3 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ! በኢትዮጵያ ባለፋት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገ 745 የላብራቶሪ ምርመራ ሶስት (3) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ተረጋግጧል። በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 114 ደርሷል። የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦ ታማሚ 1 - የ42 ዓመት ቻይናዊ የመኖሪያ ቦታው ሰበታ ዞን ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ…
ዛሬ ቫይረሱ እንደተገኘበት የተገለጸው ቻይናዊ በሰበታ ከተማ ቀበሌ 8 በሚገኝ "pengifie wood factory" የሚሰራ መሆኑን የከተማው ኮሚውኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል፡፡
ከሰውየው ጋር ግንኙነት ያላቸው ግለሰቦችም ከፌደራል ከክልል እንዲሁም ከከተማው በተወጣጡ የህክምና ባለሞያዎች የመለየት ሥራ አየተሰራ እንደሆነም ተገልጿል፡፡
በዚህም ህብረተሰቡ ሳይሸበር ንጽህናውንና አካላዊ ርቀቱን ጠብቆ አስፈላጊውን መረጃ ለሚመለከተው አካል እንዲሰጥ የከተማ አስተዳደሩ ጥሪ አቅርቧል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከሰውየው ጋር ግንኙነት ያላቸው ግለሰቦችም ከፌደራል ከክልል እንዲሁም ከከተማው በተወጣጡ የህክምና ባለሞያዎች የመለየት ሥራ አየተሰራ እንደሆነም ተገልጿል፡፡
በዚህም ህብረተሰቡ ሳይሸበር ንጽህናውንና አካላዊ ርቀቱን ጠብቆ አስፈላጊውን መረጃ ለሚመለከተው አካል እንዲሰጥ የከተማ አስተዳደሩ ጥሪ አቅርቧል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኢትዮጵያና የአጎራባች ሀገራት የኮሮና ቫይረስ ወቅታዊ መረጃ ፦
(በአል ዓይን የተዘጋጀ)
- ጅቡቲ በቫይረሱ የተያዙ 945፣ ሞት 2፣ ያገገሙ 112፤
- ኬንያ በቫይረሱ የተያዙ 296፣ ሞት 14፣ ያገገሙ 69፤
- ሶማሊያ በቫይረሱ የተያዙ 237፣ ሞት 8፣ ያገገሙ 3፤
- ኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ 114፣ ሞት 3፣ ያገገሙ 16፤
- ሱዳን በቫይረሱ የተያዙ 107፣ ሞት 12፣ ያገገሙ 8፤
- ኤርትራ በቫይረሱ የተያዙ 39፣ ሞት 0፣ ያገገሙ 3፤
- ደቡብ ሱዳን በቫይረሱ የተያዙ 4፣ ሞት 0፣ ያገገሙ 0
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
(በአል ዓይን የተዘጋጀ)
- ጅቡቲ በቫይረሱ የተያዙ 945፣ ሞት 2፣ ያገገሙ 112፤
- ኬንያ በቫይረሱ የተያዙ 296፣ ሞት 14፣ ያገገሙ 69፤
- ሶማሊያ በቫይረሱ የተያዙ 237፣ ሞት 8፣ ያገገሙ 3፤
- ኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ 114፣ ሞት 3፣ ያገገሙ 16፤
- ሱዳን በቫይረሱ የተያዙ 107፣ ሞት 12፣ ያገገሙ 8፤
- ኤርትራ በቫይረሱ የተያዙ 39፣ ሞት 0፣ ያገገሙ 3፤
- ደቡብ ሱዳን በቫይረሱ የተያዙ 4፣ ሞት 0፣ ያገገሙ 0
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከሰበታ ከተማ ከንቲባ የተጠየቀ የትብብር ጥሪ!
(ሰበታ)
የተከበራችሁ ህዝቦቻችን እና ዜጎቻችን፣ አስከፊውን የኮሮና ቫይረስን በተመለከተ መዘናጋት ጎልቶ ይታያል። ስለዚህ ወገኖቻችን የናንተ መኖር የኛ መኖር እንዲሁም የናንተ መኖር የሀገር መኖር መሆኑን በመረዳት ይህንን አስከፊ ግዜ በመደማመጥ እና በተባበረ ክንድ መሻገር የጋራ ሀላፊነታችን ነው።
ስለዚህ የጤና ባለሞያዎች እና የመንግስት መመሪያዎችን ስራ ላይ በማዋል አስከፊውን የኮሮና ቫይረስ እንከላክል።
ህይወታችንን ለማትረፍ ህይወታቸውን ሰጥተው ሌት ከቀን ለሚደክሙልን የጤና ባለሙያዎች ስንል ከአስከፊው የኮሮና በሽታ እራሳችንም ወገኖቻችንን እንጠብቅ ስል በፈጣሪ ስም እጠይቃለሁ።
የኮሮና በሽታ አስክፊነትና መተላለፊያ መንገዶችን ላልገባው በማስገንዘብ የተሰጠንን ሀገራዊ ግዴታ በመተግበር የዜግነት ግዴታችንን እንወጣ መልዕክቴ ነው።
በተባበረ ክንድ የኮሮና በሽታን እናጥፋ፣ፈጣሪ ኢትዮጲያን እና ህዝቦችዋን አብዝቶ ይባርክ። "ከስተታችን መማር ስልጣኔ ነዉ። "
(የሰበታ ከተማ ከንቲባ የተከበሩ አቶ ብርሃኑ በቀለ)
#SHARE #ሼር

አጫጭር መረጃዎች ፦
- በዩናይትድ ኪንግደም ባለፉት 24 ሰዓት 873 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተድርጓል። አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 17,382 ደርሷል።
- በሆንግ ኮንግ የተጣለው የእንቅስቃሴ ገደብ እስከ MAY 7 ተራዝሟል።
- በዓለም ላይ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ 2,500,000 በልጧል።
- በስፔን የሟቾች ቁጥር ከትላንቱ መጨመር አሳይቷል። ባለፉት 24 ሰዓት 430 ሰዎች ሞተዋል። አጠቃላይ በቫይረሱ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 21,282 ደርሷል።
- በሳዑዲ አረቢያ ባለፉት 24 ሰዓት ተጨማሪ 6 ሰዎች መሞታቸውን ተከትሎ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 109 ደርሷል።
- ጀርመን #Oktoberfest2020 ሰርዛለች።
- በዓለም ላይ በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሰዎች ከ171,000 በልጠዋል ፤ ከ659,000 በላይ ሰዎች አገግመዋል።

በየሳምንቱ እሁድ የተቸገሩ ወገኖችን እየመገቡ የሚገኙት ባለሀብት!
ከዚህ ቀደም ስለአቶ ብርሃን ተድላ እንዲሁም ጓደኛቸው ነግረናችሁ ነበር። በየሳምንቱ እሁድ እሁድ ይህ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከሀገራችን እስኪጠፋ ድረስ 250 ለሚሆኑ ወገኖች ምግብ ለማብላት ስራ መጀመራቸው ይታወቃል።
ባለሀብቱ አቶ ብርሃን ተድላ የትንሳኤ በዓልን እንዲሁም የእሁድ የምገባ ፕሮግራማቸውን በሙዳይ በጎ አድራጎት ማህበር ማድረጋቸውን ገልፀውልናል። በዕለቱ የባህልና ቱሪዝም ሚኒትርም ተገኝተው ነበር።
ባለሀብቱ እና የስራ አጋሮቻቸው በሙዳይ የበጎ አድራጎት ማህበር የተገኙበት ዋነኛ ምክንያታቸው ማህበሩ ያለበትን ሁኔታ ለማየት፣ በምን መልኩ መታገዝ እንዳለባት ለማወቅ እንዲሁም በዓሉን በማህበሩ ስር ታቅፈው ካሉት ልጆች ጋር ለማክበር ነበር።
ሙዳይ 600 ልጆችን ነው የምታሳድገው፤ ትልቁ የቤት ችግር ስራዋን ፈታኝ አድርጎባታል። የጠየቀችው የ5000 ካ.ሜ ቦታ እንዲሰጣት በሂደት ላይ ነው ያለው። ቦታው ከተሰጣት በኃላ በቦታው ላይ በአጭር ጊዜ ቤቶችን ለመስራት በሚቻልበት መንገድ ላይ ሚኒስትሯ በተገኙበት አቶ ተድላ ሀሳብ አቅርበዋል።
ከዚህ በተጨማሪ ለሙዳይ የአልጋ ስጦታዎችን ለመስጠት ቃል ተገብቷል። አቶ ብርሃን በእሳቸው በኩል 10 አልጋ ፣ የኢትዮጵያ ሆቴል አሰሪዎች ፌደሬሽን 10 አልጋ፣ የአስጎብኝዎች ድርጅት አሶሴሽን 13 አልጋ እንዲገዛ የማስተባበር ስራ ተሰርቷል። አጠቃላይ በገንዘብ ሲተመን 495,000 ብር ገደማ ይሆናል።
ባለሀብቱ በቀጣይም በሚያስፈልገው ሁሉ ከበጎ አድራጎት ማህበሩ ጋር እንደሚቆሙ ነግረውናል።
ከዚህ በተጨማሪ በየሳምንቱ እሁድ የሚካሄደው የምገባ መርሃ ግብርም እንደሚቀጥል ነግረውናል።

#HAWASSA
አቶ ደረጄ ተካልኝ (የኢንፎሊንክ ኮሌጅ) ባለቤት ለኮኖና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመግታት እየተደረገ የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ እንዲሁም ሀገራዊ ግዴታቸውን ለመወጣር የ100,000 ብር እገዛ ማድረጋቸውን ነግረውናል።

'የፍቅር ማዕድ' በብዙአየሁ ታደለ ፋውንዴሽን!
የብዙአየሁ ታደለ ፋውንዴሽን በድሬዳዋ አስተዳደር ለሚገኙ 700 (ሰባት መቶ) ወገኖች የምገባ መርሀ-ግብር አካሂዷል።
የኢስት አፍሪካን ሆልዲንግ አ.ማ. ግብረ-ሰናይ ድርጅት የሆነው ብዙአየሁ ታደለ ፋውንዴሽን የአክስዮን ማህበሩ አንድ ኩባንያ ከሆነው ናሽናል ሲሚንት አ.ማ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ለ700 (ሰባት መቶ) የድሬዳዋ ነዋሪዎች በአራት የተለያዩ አካባቢዎች በቀን ለሶስት ጊዜ ለሁለት ተከታታይ ወራት የሚቆይ የምግብ ድጋፍ እያደረገ የሚገኝ ሲሆን ወጪው በገንዘብ ብር 5 ሚሊዮን ይተመናል፡፡
ብዙአየሁ ተደለ ፋውንዴሽን ከዚህም በተጨማሪ በአስተዳደሩ በበጎ-ፈቃደኝነት እያገለገሉ ለሚገኙ 150 ወጣቶች የአንፅባራቂ ልብስ ድጋፍ ድጋፍ ያደረገ ሲሆን በተለያዩ የአስተዳደሩ አካባቢዎችም ለእጅ መታጠቢያ የሚሆኑ 50 ማስታጠቢያዎችን ለማሰራጨት በዝግጅት ላይ ይገኛል።
ድጋፉ ፋውንዴሽኑ በአገሪቱ በሚገኙ ስምንት ከተሞች ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የዕለት ጉርሳቸውን ማሟላት የተቸገሩ ወገኖችን ለመርዳት እየሰራ ያለበት 'የፍቅር ማዕድ' የተሰኘ ፕሮጀክት አንድ አካል መሆኑን የፋውንዴሽኑ ተወካይ አቶ ገዛሓኝ ሀምዛ ገልፀዋል፡፡