TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የድጋፍ ሰልፍ...

ዛሬም የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድን የለውጥ አመራር የሚደግፉ ሰልፎች በኦሮማያ ክልል ሲካሄዱ እንደነበር ተመልክተናል።

በዛሬው ዕለት የድጋፍ ሰልፍ ከተደረገባቸው ከተሞች አንዱ ለገጣፎ ለገዳዲ ነው። በድጋፍ ሰልፉ በርካታ ቁጥር ያላቸው የለገጣፎ ለገዳዲ ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።

በተመሳሳይ በመቱ ከተማ የጠቅላይ ሚኒስትሩን የለውጥ አመራር የሚደግፍ የድጋፍ ሰልፍ ተደርጓል። በሰልፉ ላይ የተገኙ የመቱ ነዋሪዎች በስድብ እና በጥላቻ በፍፁም ለውጥ ሊመጣ አይችልም ብለዋል።

#LegetafoLegedadi #FBC #WondeMettu
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሳውዲ አረቢያ 11 ኢትዮጵያውያን ተይዘዋል...

ሳውዲ አረቢያ ከሰሞኑን ሕጋዊ ሆነው በምድሯ እየኖሩ ያልተፈቀደላቸውን ሥራ የሚሠሩ የተለያዩ ሃገራት ዜጎች ማሠር መጀመሯ ተሰማ። በሕጉ መሠረት አንድ የውጭ ዜጋ ወደሳውዲ ሲገባ እንዲሠራ በተፈረደለትን የሥራ መስክ የማይሠራ ከሆነ እንደ ሕገወጥ ይቆጠራል።

በዚሁም መሠረት #ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ አንድ ሺህ ገደማ የሚሆኑ የሌሎች ሃገራት ዜጎች ሕጋዊ ሆነው ሳለ ፈቃድ ከተሰጣቸው የሥራ መስክ ውጭ በመሠማራታቸው በሁለት ሳምንት ውስጥ መታሠራቸውን DW ዘግቧል። በጅዳ ቆንስል ጀነራል አቶ አብዱ ያሲን እንደገለጹት በዚህ የሳውዲ መንግሥት ርምጃ 11 ኢትዮጵያውያን ተይዘዋል።

#DW
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"ትግራይ ላይ ያለው ጥላቻ ይስተካከል፤ ካልሆነ ትግራይ ራስዋን የቻለች አገር ናት ብላችሁ አውጁ" - ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል

''በኢትዮጵያ እየተከሰተ ያለው ጣልቃ ገብነት እንዲሁም በትግራይ ላይ ያለው ጥላቻ የማይስተካከል ከሆነ ትግራይ ራስዋን የቻለች አገር ናት ብላችሁ ልታውጁ ይገባል" ሲሉ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል መልዕክት አስተላለፉ።

ዶክተር ደብረፅዮን ይህንን መልዕክት ያስተላለፉት ህወሓት የተመሰረተበትን 45ኛውን ዓመት አስመልክቶ በዛሬው ዕለት በመቐለ ስታዲየም ለታደሙ ሰዎች ባደረጉት ንግግር ነው።

የትግራይ ምክትል ፕሬዝደንት ዶ/ር ደብረፅዮን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ባስተላለፉት መልዕክት፤ "የስልጣን ጊዜያችሁ [የአባልነት ጊዜ] እያለቀ ስለሚገኝ ከመበታተናችሁ በፊት ታሪክ ስሩ።

በኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው ጣልቃ ገብነት፣ በተለይም ትግራይን በተመለከተ በመሪዎች ደረጃ የተሰጡት የጥላቻና የፀረ ህዝብ ንግግሮችን በይፋ ኮንኑ" ብለዋል። አክለውም "ይህ የማይሆን ከሆነ ትግራይ ራሷን የቻለች አገር መሆኗን ወስኑ፤ አውጁ" ብለዋል።

"አገር በመበተን ሂደት ነበሩ ተብላችሁ በታሪክ እንዳትወቀሱ፤ ግዳጃችሁን ተወጡም" በማለት መልዕክታቸውን በትግራይ ስታዲየም ለተሰበሰበው ህዝብ አስተላልፈዋል።

#BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ፎቶዎች ከትግራይ ስታዲየም መቐለ...

#የካቲት11 - የትግራይ ህዝብ የደርግ ስርዓትን ለመገርሰሰ የትጥቅ ትግል የጀመረበት 45ኛው ዓመት የየካቲት 11 በዓል "በመስመራችን ጸንተን ለመመከት" በሚል መሪ ቃል በትግራይ ስታዲየም በድምቀት ተክብሯል።

#TPLF
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዶ/ር ዐብይን ያበሳጫቸው የማይክ ፓምፒዮ አቀባበል...

[በሪፖርታር ጋዜጣ]

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ ትላንት ማክሰኞ የካቲት 10 ቀን 2012 ዓ.ም. ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ ጋር ለመገናኘት ወደ ጽሕፈት ቤታቸው አምርተው ነበር።

በዕለቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን የጫነው ተሽከርካሪ ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት አካባቢ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት በር ላይ ሲደርስ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የእንኳን ደኅና መጡ አቀባበል ለማድረግ እየጠበቋቸው ነበር፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የፕሮቶኮል ኃላፊዎች የመኪናውን በር ከፍተው ሚኒስትሩ እንዲወጡ ሲጠየቁ የሚጠብቁት ሰው እንዳለ ይገልጻሉ፡፡

ከዚያም ወዲያው ይጠበቁ የነበሩት ግለሰብ የፖምፒዮ ፎቶግራፈር መሆናቸውን የተረዱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ (ዶ/ር) በብስጭት ፊታቸውን አዙረው ወደ ጽሕፈት ቤታቸው ሲያቀኑ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከኋላ ተከትለው ሰላምታ ሲያቀርቡላቸው ከላይ ባለው ምሥል ይታያሉ፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ ያደረጉትን ውይይት ከጨረሱ በኋላ ዓብይ (ዶ/ር) ከፖምፒዮ የፕሮቶኮል ኃላፊዎች ፈቃድ ውጪ መኪና እያሽከረከሩ ምሳ ወደሚበሉበት ቦታ ወስደዋቸው ነበር ሲል ሪፖርተር አስነብቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#NewsAlert

አቶ ሽመልስ አብዲሳ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው መሾማቸውን ከኦሮሚያ ኮሚኒኬሽን ቢሮ የፌስቡክ ገፅ ላይ ተመልክተናል።

ጨፌ ኦሮሚያ እያካሄደ ባለው ጉባኤው ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ክልሉን ሲመሩ የነበሩት አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨፌው በሙሉ ድምፅ ርዕሰ መስተዳደር እንዲሆኑ ሾሟቸዋል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ምስጋና...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በስልጤ ዞን ከሚገኙ ወረዳዎች ከተውጣጡ 1,000 የሚሆኑ የማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር እየተወያዩ ነው።

በውይይቱ መጀመሪያም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በቅርቡ በጅማ፣ ሀረርጌ፣ ሶማሌ እና ሌሎች አካባቢዎች ኅብረተሰቡ ለለውጡ ያለውን ድጋፍ መግለፁን አስታውሰዋል።

ህብረተሰቡ በዚሁ ጊዜ የሀገሪቱን ሰላም የማስቀጠልን አስፈላጊነት የሚያሳስብ መልዕክት ማስተላለፉን እና እርሳቸውም መልዕክቱን መቀበላቸውን ከልብ አረጋግጠዋል።

ምንጭ፡- የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

የአማራ ክልል እና የሱዳን ገዳሪፍ ግዛት ህገ ወጥ ንግድ፣ የሰዎች እና የጦር መሳሪያ ዝውውርን ለመከላከል በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራርመዋል።

#ኤፍቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ እየደረሰ ያለውን ወቅታዊ ችግር አስመልክቶ ከቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ፦ https://telegra.ph/ETH-01-26-3

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#GONDAR

በግንቦት ወር 2010 ዓ/ም አጋማሽ ላይ ከእስር ከተፈቱ ከ110 የፖለቲካ እስረኞች አንዱ የነበረው ወጣት ዘርዓይ አዝመራው፣ ትላንት ማለዳ በሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት ወረዳ ከአንድ ግለሰብ በተተኮሰ ጥይት ተመቶ ህይወቱ አልፏል።

ግድያው ለምን እንደተፈፀመ ምክንያቱ ግልፅ አለመሆኑ ተነግሯል። ወጣት ዘርዓይ ከእስር ከተፈታ በኅላ በጎንደር አካባቢ በሚደረጉ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች ንቁ ተሳታፊ ነበር።

የወጣት ዘራዓይ አዝመራው የቀብር ስነ ስርዓት በዛሬው ዕለት በወልቃይት ዋልድባ ተፈፅሟል። የቀብር ስነ ስርዓቱ በተፈፀመበት በስፍራ ወዳጅ ዘመዶቹ ፣ ፋኖዎች፣ የጎንደር፣ የዳባትና የአካባቢው ህዝብ ተገኝተው ነበር። በነገው እለት በጎንደር ከተማ የለቅሶ ስነ ስርዓት የሚካሄድ መሆኑ ተጠቁሟል።

ምንጭ፦ አማራ ሚዲያ ማዕከል፣ ELU
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሌላ መረጃ የጎንዳር አካባቢ መረጃ ፦

ትናንት የካቲት 10/2012 ዓ/ም ምሽት በጎንደር ከተማ ቀበሌ 18 በታጠቁ ግለሰቦች እና በአማራ ልዩ ሀይል መካከል በተደረገ የተኩስ ልውውጥ የሁለት ሰዎች ሕይዎት ሲያልፍ ፣ 5 ሰዎች ቆስለዋል። ከሟቾቹ መካከል ሻለቃ የኅላሸት የተባለ የልዩ ሀይሉ አባል ይገኝበታል ተብሏል።

ምንጭ፦ አማራ ሚዳያ ማዕከል፣ ELU
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በተለያየ ሃላፊነት ላይ የነበሩ ሰዎችን በዕጩነት አቅርበው አጸድቀዋል። በዚህም ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ ሆነው ተሹመዋል።

አቶ ፍቃዱ ተሰማ የክልሉ መንግስት ተጠሪ ፣ አቶ አዲሱ አረጋ ቂጤሳ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ጉዳዮች ዘርፍ አስተባባሪ፣ አቶ ጀማል ከዲር ገልገዶ የክልሉ ከተማ ልማትና ቤቶች ልማት አስተዳደር ሃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ የክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሀላፊ ሆነው ተሹመዋል።

በተጨማሪ አቶ ጂብሪል መሃመድ ሮባ የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሃላፊ፣ አቶ ቦጋለ ፈለቀ የኦሮሚያ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሀላፊ፣ አቶ ካሳሁን ጎፌ የኦሮሚያ ገቢዎች ባለስልጣን ሀላፊ፣ አቶ ዳንኤል አሰፋ፣ የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ፣ አቶ ከበደ ደሲሳ የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ፣ አቶ ተሾመ ግርማ የኦሮሚያ ክልል ፀረ ሙስናና ስነ ምግባር ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሹመዋል።

https://telegra.ph/ETH-02-19-2

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

በኢትዮጵያ በተከሰከሰው የቦይንግ 737 አውሮፕላን የሟቾች ጠበቆች በቦይንግ ኩባንያ ላይ የመሠረቱት ክስ ዛሬ በቺካጎ ፍርድ ቤት እንደሚታይ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ ኩባንያው ስለ አውሮፕላኑ ስሪት፣ ዲዛይን እና ስለደረሱት አደጋዎች ሙሉ ሰነዶችን እንዲሰጣቸው ነው ጠበቆቹ የከሰሱት፡፡ ጠበቆቹ ኩባንያው ቁልፍ መረጃዎችን ከምርመራው ቡድን እንደደበቀ ያምናሉ፡፡

[ሮይተርስ፣ ዋዜማ ሬድዮ]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia