የኢትዮጵያና ኬንያ አጎራባች ክልሎች የንግድ ባዛር...
የኢትዮጵያና ኬንያ አጎራባች ክልሎች የንግድ ባዛር በኬንያ ሞያሌ ከተማ የካቲት 12 ቀን 2012 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ. ፌብሩዋሪ 20 ቀን 2020) ይካሄዳል። በኬንያ የንግድና ኢንደስትሪ ሚኒስቴር የኬንያ የወጪ ንግድ ፕሮሞሽንና ብራንዲንግ ኤጀንሲ ስራ ኃላፊዎች በኤምባሲው ተገኝተው ከአምባሳደር መለስ ጋር ተወያይተዋል።
[በኬንያ ከኢትዮጵያ ኤምባሲ]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

#ATTENTION
ከ35,000 በላይ ተማሪዎች ቤታቸው ናቸው...
በአንዳንድ የሀገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ምክንያት መደበኛ ትምህርት አቋርጠው ወደ ቤተሰቦቻቸው የተመለሱ ከ35 ሺህ በላይ ተማሪዎች በአስቸኳይ ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ መንግስት ኃላፊነቱን በአግባቡ ሊወጣ ይገባል። ከምንም ነገር በፊት ለነዚህ ተማሪዎች ጉዳይ ቅድሚያ ተሰጥቶ መሰራት ይኖርበታል።

#UPDATE
በጎንደር ባህረ-ጥምቀት ላይ በደረሰው አደጋ ለተጎዱ ወገኖችና ቤተሰቦች ድጋፍ የሚያሰባስብ ኮሚቴ መዋቀሩን የከተማው አስተዳደር አስታውቋል።
የአስተዳደሩ ባህልና ቱሪዝም መምሪያ የማማውን ጥራትና የግንባታ ሁኔታ ሲቆጣጠሩ ከነበሩ የመምሪያው መሐንዲሶች ጋር ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡
የመምሪያው ኃላፊ አቶ አስቻለው ወርቁ እንዳመለከቱት ሰባት አባላትን ይዞ ሥራ የጀመረው ኮሚቴ በአደጋው ለቆሰሉ ህይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦች ድጋፍ የሚያሰባስብ ነው።
በአስተዳደሩ የሰላምና የሕዝብ ደህንነት መምሪያ ሰብሳቢነት የሚመራው ኮሚቴው ፖሊስ፣ ፍትህ፣ ክርስቲያን ኅብረት ጽህፈት ቤት፣ ሰላምና ልማት ሸንጎ፣ የወጣቶች ማህበርና ህንፃ ሹምን ያካተተ ነው።
“በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ህክምና ላይ ላሉ ተጎጂዎች ድጋፍ እያደረግን ነው” ያሉት ኃላፊው፣በቀጣይም አስተዳደሩ ከኮሚቴው ጋር በመቀናጀት ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል፡፡
ኮሚቴው ጉዳት ለደረሰባቸው ግለሰቦች ድጋፍ ከማድረግ ባሻገር፣ የጉዳቱን ሁኔታና መጠን ለማጣራት ኃላፊነት እንደተሰጠውም አቶ አስቻለው ዛሬ በተሰጠው መግለጫ ወቅት አስረድተዋል።
[ENA]

አቶ ማሞ ጌታሁን [የጎንደር ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም መምሪያ የቅርስ ጥገና ባለሙያ] የተናገሩት፦
"አደጋው የደረሰው ከማማው የጥራት ጉድለት ሳይሆን፣ መሸከም ከሚችለው መጠን በላይ በመያዙ ነው። ማማው የሚይዘው ከ460 ያልበለጡ ሰዎችን ቢሆንም ፤ ከዚያ በእጥፍ የሚበልጡ ሰዎች ማማው ላይ በመውጣታቸው አደጋው ተከስቷል። በቀጣይም በብረት ለሚሰራው ማማ ከሚያስፈልገው ከስድስት ሚሊዮን ብር በላይ በጀት የአውሮፓ ኅብረት ሁለት ሚሊዮን ብር ለመስጠት ቃል ገብቷል።"
PHOTO : SAMUEL GETACHEW

ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባና ዙሪያዋ ቤተሰቦች፦
በነገው ዕለት ከቀኑ 7:30 ጀምሮ በጌርጌሴኖን የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማህበር ቆይታ ይኖረናል። በማዕከሉ ከሚገኙ እህት ወንድሞቻችን ጋር ጊዜ እናሳልፋለን። እግረ መንገዳችንንም ለማህበሩ መጠነኛ እገዛ እናደርጋለን።
በዚህ መርሃ ግብራችን ላይ ውድ ከሆነው ጊዜያችሁ ቀንሳችሁ ፣ አንድም በማእከሉን ከሚገኙ ወንድም እና እህቶቻችሁ ጋር ጊዜ እንድታሳልፉ በሌላ በኩል ማዕከሉ በአካል ተገኝታችሁ እንድትጎበኙ ጥሪ እናቀርባለን።
አብራችሁን ለመሆንና ጌርጌሴኖን የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማህበርን ለመጎብኘት የምትፈልጉ ቤተሰቦች በ0913134524 ወይም በ @emush21 አግኙን!
ቦታ፡- ከሽሮ ሜዳ ወደ እንጦጦ በሚወስደው መንገድ ላይ!
"መልካም ማድረግን ለሌሎች ማካፈልን አትርሱ"

#SmartElectronics
- ኦርጅናል እና አዳዲስ ስልኮች እንዲሁም በተለይ ሱቃችን የሚታወቅበት "American slightly used phones" በተለያዩ ሞዴሎች ይዘን ቀርበናል ፤ አዳዲስ ላፕቶፖች በተለያዩ ሞዴሎች ለተማሪዎች ከታላቅ ቅናሽ ጋር።
- የተለያዩ የኢንፎርሜሽን መረጃዎችን፦
• እንዴትስ ኦርጅናል ስልክ መለየት ይችላሉ
• ስለ ላፕቶፖ ስናወራ core i3, core i5, core i7 ስንል ምን ማለታችን ነዉ። ይህን ሊንክ join ብለዉ ቤተሠብ ይሁኑ 👉https://t.iss.one/joinchat/AAAAAEQeR9_lTfIGOZrZxw አድራሻ፦ ቦሌ መድሀኒያለም ቤክ ዝቅ ብሎ ሰላም ሲቲ ሞል 1ፎቅ ላይ ስልክ፦ 0913393937፣ 0921667933

24 የህዝብ የመዝናኛ ፓርኮች ለህዝብ ክፍት ሊሆኑ ነው...
በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ 24 የህዝብ የመዝናኛ ፓርኮች ለህዝብ ክፍት ሊሆኑ ነው። ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ትላንት ለአገልግሎት ክፍት የተደረገውን የፈረንሳይ ፓረክ ጎብኝተዋል፡፡ በከተማዋ የሚገኙ የህዝብ የመዝናኛ ፓርኮች ለአገልግሎት በሚመችና መሰረተልማት ባሟላ መልኩ እድሳት እየተደረገላቸው ሲሆን ጎን ለጎንም ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆኑ ተወስኗል፡፡ ማንኛውም የከተማዋ ነዋሪም እነዚህን መዝናኛ ፓርኮች ያለክፍያ መጠቀም እንደሚችልም ነው የተጠቆመው፡፡

በኢትዮጵያ 8.4 ሚሊዮን ሰዎች ሰብዓዊ ዕርዳታ ይፈልጋሉ...
በተያዘው የፈረንጆች ዐመት በኢትዮጵያ 8.4 ሚሊዮን ሰዎች ሰብዓዊ ዕርዳታ እንደሚፈልጉ ተመድ አስታውቋል፡፡ 6.2 ሚሊዮኖቹ አስቸኳይ ዕርዳታ ይፈልጋሉ፡፡ በኦሮሚያ ክልል 3.3 ሚሊዮን፣ በሱማሌ 2.4 ሚሊዮን፣ በአማራ 1 ሚሊዮን ሕዝብ ሰብዓዊ ዕርዳታ ጠባቂ ይሆናል፡፡ በስሌቱ የአንበጣ መንጋ ሰብል ላይ ያደረሰው ውድመት ታሳቢ ሆኗል፡፡
[ተመድ፣ ዋዜማ ሬድዮ]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በተያዘው የፈረንጆች ዐመት በኢትዮጵያ 8.4 ሚሊዮን ሰዎች ሰብዓዊ ዕርዳታ እንደሚፈልጉ ተመድ አስታውቋል፡፡ 6.2 ሚሊዮኖቹ አስቸኳይ ዕርዳታ ይፈልጋሉ፡፡ በኦሮሚያ ክልል 3.3 ሚሊዮን፣ በሱማሌ 2.4 ሚሊዮን፣ በአማራ 1 ሚሊዮን ሕዝብ ሰብዓዊ ዕርዳታ ጠባቂ ይሆናል፡፡ በስሌቱ የአንበጣ መንጋ ሰብል ላይ ያደረሰው ውድመት ታሳቢ ሆኗል፡፡
[ተመድ፣ ዋዜማ ሬድዮ]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኢቢሲ ጋዜጠኞች ጉዳይ....
በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) ለረዥም ዓመታት ያገለገሉ ከ4 ያላነሱ ነባር ጋዜጠኞች ባለፉት ጥቂት ወራት በተለያዩ አጋጣሚዎች ባቀኑባቸው ምዕራባውያን ሃገራት ጥገኝነት ጠይቀዋል። ከእነዚህም መካከል አንዱ ለ9 ዓመታት በኢቢሲ ከሪፖርተርነት እስከ ዜና ክፍል ምክትል ዋና አዘጋጅነት ያገለገለው ጋዜጠኛ ቢላል ወርቁ ይገኝበታል።
ጋዜጠኛው ቢላል በዚህ ሳምንት ሰኞ የተካሄደውን የዩኬ-አፍሪካ የኢንቨስትመንት ፎረም ለመዘገብ በምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን ከሚመራ ልዑክ ጋር ወደ ለንደን የተጓዘ ሲሆን ጥገኝነት መጠየቁን ለቢቢሲ አረጋግጧል።
ከቢላል በተጨማሪ ሌሎች ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የኢቢሲ ነባር ጋዜጠኞች በተለያዩ አጋጣሚዎች በሄዱባቸው ምዕራባውያን ሃገራት ጥገኝነት ለመጠየቅ የተገደዱት ከጋዜጠኝነት ሥራቸው ጋር በተያያዘ በሚደርሱባቸው ጫናዎች እንደሆነ ተናግረዋል።
የቀድሞ የኢቢሲ ጋዜጠኞች ለቢቢሲ በላኩት የጽሑፍ መልዕክት በጋዜጠኝነት ሥራቸው የኤዲቶሪያ ነጻነት እንደሌላቸው ተናግረዋል። ጉዳዮች እየተመረጡ ነው የሚዘገቡት ያሉት ጋዜጠኞቹ እንደምሳሌ፦
- በጅግጅጋ አብያት ክርስቲያናት ሲቀጣሉ በፍጥነት ሳይዘገብ መቆየቱ
- የሃይማኖት ተቋማት መግለጫዎች ለምሳሌ ሲኖዶሱ የኦሮሚያ ቤተክነት መቋቋምን አወግዛለሁ ማለቱ አለመዘገቡ፣
- በሞጣ የተፈፀመው ጥቃት ሰፊ ሽፋን ሳይሰጠው መቅረቱ፣
- የትግራይ ክልል እና የህውሃት መግለጫዎች አለመዘገባቸው፣
- የደንቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጉዳይ የተዘገበበት መንገድ እና ሌሎችን ጉዳዮችን በመጥቀስ የዜና ሽፋን የሚሰጣቸው ጉዳዮች የተመረጡት ብቻ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
More https://telegra.ph/BBC-01-23
ምንጭ፦ BBC

#NEW
የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ መግለጫ፦
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በኢህአዴግ ውስጥ የተፈጠረው የሃሳብና የመስመር ልዩነት እየሰፋ መጥቶ አሁን ኢህአዴግ በያዘው መስመርና ከነበረው የግንባሩ አደረጃጀት ስርዓትና አሰራር ውጭ ጨርሶ እንዲፈርስ በማድረግ በይዘቱ አዲስ ፓርቲ እንዲመሰረት ተደርጓል፡፡
ህወሓት ይህ ህገ-ወጥና ፀረ-ዴሞክራሲ አካሄድ በተደጋጋሚ እንዲታረም፤ የሀገራችንን ህልውና አደጋ ውስጥ በገባበት ወቅት ቅድሚያ ተሰጥቷቸው ሊታዩ በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ እንድናተኩር በፓርቲው ውስጥም ሆነ ለመላው የሃገራችን ህዝብ በተደጋጋሚ ስንገልፅ ቆይተናል፡፡
ይሁን እንጂ ይህንን ሊቀበል ወይም ሊሰማ ዝግጁ ያልሆነው አመራር ኢህአዴግን በፀረ- ዴሞክራሲያዊ መንገድ እንዲፈርስ እና ህዝብ ያልመረጠው አዲስ ፓርቲ ስልጣን ይዞ እንዲቀጥል አድርጓል፡፡
ከዚህ በኋላ እንደ ድርጅት የነበረን ብቸኛው አማራጭ በጉዳዩ ላይ ህዝባችን በተወካዮቹ በኩል ተወያይቶ እንዲወስን፤ ይህንን ተከትሎም በመጀመሪያው አስቸኳይ ጉባኤያችን ላይ ሂደቱንና ሁኔታዎችን በዝርዝር እንዲወስን ማድረግ ነበር። በዚሁ መሰረት ከተፈጠረው አዲስ ፓርቲ ጋር እንደማንወሃድ መወሰኑ ይታወቃል፡፡
More https://telegra.ph/TPLF-01-23

"... በአሁኑ ጊዜ የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ አመራሮችና አባላት በመሆናቸው ብቻ ከፌዴራል መንግስት እና ከአዲስ አበባ አስተዳደር የኃላፊነት ቦታዎች እንዲነሱ እየተደረገ ነው። ይህ ተግባር በፍፁም ተቀባይነት የለውም። በመሆኑም ይህ ሆነ ተብሎ እየተፈፀመ ያለው እና ከዚህ ቀደም የተፈፀመ መረን የለቀቀ ተግባር ሊታረም ይገባል። ካልሆነ ግን ይህንን ተከትሎ ለሚፈጠር ሁኔታ ሀላፊነት የሚወስደው ይህ ህገ-ወጥ ተግባር እየፈፀመ ያለው አካል መሆኑን ግልፅ ሊሆን ይገባል።" - ህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የክልልነት ጥያቄ ከሚጠይቁ የተለያዩ የደቡብ ክልል ብሔረሰቦች ተወካዮች እና ሽማግሌዎች ጋር ነገ እንደሚወያዩ ይጠበቃል። [ELU] @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚ/ር ዐቢይ አሕመድ ከደቡብ ክልል ከተውጣጡ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር እየተወያዩ ነው። በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት እየተካሄደ ባለው ውይይት ከ2 ሺህ የሚበልጡ ተወካዮች ተሳታፊዎች ናቸው።
ከሁሉም የክልሉ ዞኖች የተውጣጡ ምሁራን፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶች እና የወጣት ተወካዮች እየተሳተፉ ነው። በውይይቱ ላይ ተሳታፊዎቹ ከመሰረተ ልማት እና በክልል መደራጀት ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ።
[ኤፍቢሲ]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚ/ር ዐቢይ አሕመድ ከደቡብ ክልል ከተውጣጡ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር እየተወያዩ ነው። በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት እየተካሄደ ባለው ውይይት ከ2 ሺህ የሚበልጡ ተወካዮች ተሳታፊዎች ናቸው።
ከሁሉም የክልሉ ዞኖች የተውጣጡ ምሁራን፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶች እና የወጣት ተወካዮች እየተሳተፉ ነው። በውይይቱ ላይ ተሳታፊዎቹ ከመሰረተ ልማት እና በክልል መደራጀት ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ።
[ኤፍቢሲ]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE - 2019-nCoV ቫይረስ በቻይና በርካታ ግዛቶች ተከስቷል - እስካሁን ዘጠኝ (9) ሰዎች ሞተዋል - 440 የቫይረሱ ተጠቂዎች አሉ - ቫይረሱ በአሜሪካ፣ ታይላንድና ደቡብ ኮሪያ ተስፋፍቷል 2019 ኤን ሲ ኦ ቪ፦ ይህ ቫይረስ የመተንፈሻ አካላትን የሚያጠቃ ሲሆን አሁን ካለበት በላይ ሊስፋፋ እንደሚችል ማስጠንቀቂያዎች እየተላለፉ ነው። ቫይረሱ በአጭር ጊዜ ውስጥ ያሳየው መስፋፋት በቀጣይ…
#UPDATE
[ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት]
በቻይናዋ ዉሀን ከተማ እንደተነሳ የሚገመተው ቫይረስ በፍጥነት በአለም ዙርያ እየተዛመተ እንደሆነ እየተነገረ ሲሆን እስካሁንም ለ17 ሰዎች ህልፈት ምክንያት ሆኗል። ከ400 በላይ ሰዎች በዚህ ከእንስሳት ወደ ሰው በሚተላለፍ ቫይረስ መጠቃታቸውን ተከትሎ የተለያዩ ሀገራት የአየር ማረፊያዎቻቸው ላይ ቁጥጥር ማድረግ ጀምረዋል።
ደቡብ አፍሪካ፣ ኬንያ፣ ናይጄርያ እና ግብፅ እስካሁን ተጓዦችን መመርመር የጀመሩ የአፍሪካ ሀገራት ሆነዋል። በቦሌ አየር ማረፊያ ይህ እስካሁን እንዳልተጀመረ ለማወቅ ተችሏል።
ኢትዮጵያ በቦሌ አየር ማረፍያ ከፍተኛ መንገደኞችን የምታስተናግድ ከመሆኗ አንፃር እርምጃ በአፋጣኝ መውሰድ እንዳለባት የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰጡ ነው።
ታዋቂዋ የሚቺጋን ዩኒቨርሲቲ ፊዚሽያን ፕሮፌሰር ሰናይት ፍሰሀም በኢትዮጵያ ቁጥጥር ጉዳይ ላይ ትዊተር ላይ አስተያየት ሰጥተዋል። ከዚህ ጋር በተያያዘ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር በሚወሰዱ እርምጃዎች ዙርያ ነገ መግለጫ እንደሚሰጥ ከሚኒስቴር ተሰምቷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት የመሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ክትትል ቋሚ ኮሚቴ አባላት በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች እየተገነቡ ያሉ አምስት የአስፓልት መንገድ ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል፡፡

በጌዴኦ ዞን የተለያዩ አካባቢዎች የአንበጣ መንጋ መከሰቱን የቲክቫህ እትዮጵያ ዲላ ቤተሰቦች አስታውቀዋል። የሚመለከተው አካል ትኩረት እንዲያደርግም አሳስበዋል።

የአዲስ አበባ አስተዳደር ሹምሽር... የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በዚህ ሳምንት ውስጥ የካቢኔ ሹምሽር እንደሚያደርግ የሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል። በምክትል ከንቲባነት አስተዳደሩን እየመሩ የሚገኙት ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) በዚህ ሳምንት የሚያደርጉትን ሹምሽር ለከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት አቅርበው እንደሚያፀድቁ ተሰምቷል። ይነሳሉ ተብለው ከሚጠበቁት ውስጥ ምክትል ከንቲባና የትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊውን…
#UPDATE
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 7ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባዔውን ከነገ ጥር 15-17 ቀን 2012 ዓ.ም እንደሚያካሄድ አስታወቀ።
ጉባዔው ከከተማ አስተዳደሩ የተመረጡ ሁለት ቢሮዎችና ለምክር ቤቱ ተጠሪ የሆኑ ተቋማት የ2012 በጀት ዓመት የስድስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ይወያያል።
የተለያዩ አዋጆችና ልዩ ልዩ ሹመቶች እንደሚቀርቡና ውይይት ተደርጎባቸው እንደሚጸድቁም ይጠበቃል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 7ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባዔውን ከነገ ጥር 15-17 ቀን 2012 ዓ.ም እንደሚያካሄድ አስታወቀ።
ጉባዔው ከከተማ አስተዳደሩ የተመረጡ ሁለት ቢሮዎችና ለምክር ቤቱ ተጠሪ የሆኑ ተቋማት የ2012 በጀት ዓመት የስድስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ይወያያል።
የተለያዩ አዋጆችና ልዩ ልዩ ሹመቶች እንደሚቀርቡና ውይይት ተደርጎባቸው እንደሚጸድቁም ይጠበቃል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚ/ር ዐቢይ አሕመድ ከደቡብ ክልል ከተውጣጡ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር እየተወያዩ ነው። በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት እየተካሄደ ባለው ውይይት ከ2 ሺህ የሚበልጡ ተወካዮች ተሳታፊዎች ናቸው። ከሁሉም የክልሉ ዞኖች የተውጣጡ ምሁራን፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶች እና የወጣት ተወካዮች እየተሳተፉ ነው። በውይይቱ ላይ ተሳታፊዎቹ ከመሰረተ ልማት እና በክልል…
#UPDATE
በደቡብ ብሔር ፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል የሚነሱ አስተዳደራዊ የአደረጃጀት ጥያቄዎችን ለመፍታት የሚሰራ ኮሚቴ መዋቀሩን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ይፋ አድርገዋል። ኮሚቴው በክልሉ ከሚገኙ ሁሉም ዞኖች የተወከሉ ግለሰቦችን ያካተተ ነው።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በደቡብ ብሔር ፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል የሚነሱ አስተዳደራዊ የአደረጃጀት ጥያቄዎችን ለመፍታት የሚሰራ ኮሚቴ መዋቀሩን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ይፋ አድርገዋል። ኮሚቴው በክልሉ ከሚገኙ ሁሉም ዞኖች የተወከሉ ግለሰቦችን ያካተተ ነው።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ የተናገሩት፦
መንግስት የኢትዮጵያን ብልጽግና ለማረጋገጥ በሚያደርገው እንቅስቃሴ የዜጎችን አንገብጋቢ ጥያቄዎች መመለስ ቁልፍ ስራው ነው። በዚህ ሂደት ውስጥ ግን ዜጎች ችግር ተንታኞች ብቻ ሳይሆኑ ለችግሮች የመፍትሄ ቁልፍ መሆን አለባቸው።
የተነሱ አስተዳደራዊ የአደረጃጀት ጥያቄዎችም በእልህ ሳይሆን በሰከነ ውይይት ሊፈቱ እንደሚገባ ይገባል። የአደረጃጀት ጥያቄዎችን ለመፍታት ከክልሉ ሁሉም ዞኖች የተውጣጡ ግለሰቦች ያሉበት ኮሚቴ ተዋቅሯል። ኮሚቴው በቀጣይ ሕዝቡን በማወያየት የመፍትሄ አቅጣጫ ነው ያለውን ሃሳብ ይዞ ይመጣል።
በበጀት ዓመቱ ለመንገድ መሰረተ ልማት 48 ቢሊዮን ብር ተበጅቶ በተለይ ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ፕሮጀክቶችን ለማስፈጸም እየተሰራ ነው። ይህም ክልሉን በስፋት ተጠቃሚ እንደሚያደርገው ነው።
የጤና ሚኒስቴር አዲስ ባዘጋጀው የጤና ሪፎርም የግብዓት እጥረት ያሉባቸውን ሆስፒታሎችና የጤና ተቋማት ለሟሟላት በልዩ ትኩረት ይሰራል። ነገር ግን መንግስት በአጭር ጊዜ ዕቅዱ አዳዲስ የኢንዱስትሪ ፓርኮችና ዩኒቨርሲቲዎችን እንደማይገነባና ነባሮች ይበልጥ እንዲጠናከሩ ይሰራሉ።

ዶ/ር ሰለሞን ኪዳኔ ከኃላፊነታቸው ተነስትዋል...
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተላያዩ ሹምሽሮችን ሊያደርግ በመሆኑ የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ እና የትራንሰፖርት ቢሮ ኃላፊው ዶ/ር ሰለሞን ኪዳኔ ከኃላፊነታቸው መነሳታቸውን አሀዱ ቴሌቪዥን ጣቢያ በዛሬው ዕለት ዘግቧል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተላያዩ ሹምሽሮችን ሊያደርግ በመሆኑ የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ እና የትራንሰፖርት ቢሮ ኃላፊው ዶ/ር ሰለሞን ኪዳኔ ከኃላፊነታቸው መነሳታቸውን አሀዱ ቴሌቪዥን ጣቢያ በዛሬው ዕለት ዘግቧል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ATTENTION
በዲላ ከተማ የታየውን የአንበጣ መንጋ ከጥፋት ለመከላከል የከተማይቱ ነዋሪዎች በጭስና በድምፅ ለማባረር እየሞከሩ እንደሚገኙ ገልፀዋል።