TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
[ብልፅግና ፓርቲ]

የከፍተኛ የመንግስት ስራ ሃላፊዎች ምደባ ከብሄርና ከማግለል ጋር አይገናኝም!

ከሰሞኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በተለያዩ የስራ መደቦች ላይ በሚኒስትር ደረጃ ሽግሽግና አዳዲስ ሹመቶችን የመስጠት ስራ ተካሂደዋል፡፡ ይህም የተለመደና ለስራ ቅልጥፍና የተሸለ አፈጻጸም ለማረጋገጥ ሲባል በየጊዜው የሚከናወን ስራ ነው፡፡

የአሁኑም እንደተለመደው መንግስት የስራ አፈጻጸምን፤ ብቃትንና ሲታዩ የነበሩ ጉድለቶችን ማረም እንዲሁም የስራ አፈጻጸም ጉድለት ያለባቸውን በሌላ መተካትን መሰረት ያደረገ ሽግሽግ አድርገዋል፤ አዳዲስ ሹመቶችንም ሰጥቷል፡፡

በመሆኑም ከዚህ ጋር ተያየዞ አንድን ብሄር ለማግለልና ከስራ ለማፈናቀል የተደረገ አድርጎ የሚያቀርቡ አካላት አለማቸው ለነገሮች የተሳሳተ ትሩጋሜ በመስጠት ህዝብን ማደናገር መሆኑን ማስገንዘብ እንፈልጋለን፡፡

[ብልፅግና ፓርቲ]

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ዶክተር ሰለሞን ኪዳኔ፦

"በአዲስ አበባ እኛ 25 % ቦታ የማግኘት መብት አለን እንደ ኢህአዴግ ነው የተወዳደርነው ፤ ኢህአዴግ ነው ያሸነፈው ስለዚህ ማን ለማን እንደመረጠን አይታወቅም። የተመረጡት 4 ፓርቲዎች ብቻ ናቸው። እኩል ነው የተሳተፉት፣ እኩል ከተሳተፉ እኩል የመምራት ስልጣን አላቸው። ይህን ማፍረስ ማለት መንግስት አጠቃላይ የከተማ አስተዳደሩን መንግስት ማፍረስ ማለት ነው።"

[BBC]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን መቀበል ጀመረ...

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በዛሬው ዕለት ተማሪዎችን መቀበል ጀምሯል። ባቀባበል ስነ-ስርዓቱ ላይ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት እና የሴኔት አባላት፤ የአካባቢው ነዋሪ እናቶች እና አባቶች እንዲሁም ወጣቶች በተገኙበት ለተማሪዎች ደማቅ አቀባበል እየተደረገላቸው ይገኛል።

[ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ]
@tikvhaethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

የሚንስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 78ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል። ምክር ቤቱ ውሳኔ ያሳለፈባቸው ጉዳዮችም እንደሚከተለው ቀርበዋል፦

1. ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትን ህጋዊ ሰውነት ለመስጠት በተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ህጋዊ ሰውነት እንዲኖረው በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ህጋዊ ሰውነት እንዲሰጠው በሙሉ ድምጽ በመወሰን ረቂቅ አዋጁ ይጸድቅ ዘንድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ ወስኗል፡፡

More https://telegra.ph/PMOEthiopia-01-23

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ እርምጃ ወሰደ...

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የመማር ማስተማር ስራውን ሆን ብለው በማወክ የተለዩና ተጨባጭ ማስረጃ የተገኘባቸው 21 ተማሪዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን አስታውቋል። በዩኒቨርሲቲው አንዳንድ የትምህርት ክፍሎች ተቋርጦ የነበረው ትምህርት መጀመሩም ተገልጿል።

[ENA]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ኢንፎርሜሽን ስትራቴጂክ ኮሚኒኬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ዘውዱ እምሩ የተናገሩት፦

ሙሉ በሙሉ የታገዱት አራት ተማሪዎችን ጨምሮ ትምህርት እንዲስተጓጎል ያደረጉ 21 ተማሪዎች ከአንድ ዓመት እገዳ ጀምሮ እርምጃ ተወስዶባቸዋል።

ሌሎች ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ያላቸውን አካላትም በመለየትና በማጣራት በቀጣይ ተመሳሳይ እርምጃ ይወሰዳል።

የዩኒቨርስቲ ምሁራን ከመማር ማስተማር ስራው ጎን ለጎን ተማሪዎችን በስነ ምግባር በማነጽ ችግር ፈቺ ሆነው እንዲወጡ ማድረግ ይገባቸዋል።

ባለፉት ሳምንታት ተማሪዎች በሚያነሷቸው ጥያቄዎች ዙሪያ ተደጋጋሚ ውይይትና ምክክር ቢደረግም ምክንያታዊ ባልሆነ መንገድ በፖሊ ፣ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ፣ ፔዳና ይባብ ካምፓሶች ትምህርት ተቋርጦ ነበር።

ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ትምህርት ያልተቋረጠበት ነው፤ ፋሽንና ዲዛይን እንዲሁም ግብርና ኮሌጅ በከፊል የተቋረጠባቸው ነበሩ።

በውጫዊ ምክንያት ጊቢ ለቀው የወጡ ተማሪዎችም ከጥር 5 እስከ 7/2012 እንዲመዘገቡ የዩኒቨርሲቲው ሴኔት በወሰነው መሰረት ተመልሰው ወደ መማር ማስተማር ገብተዋል። ካለፈው ማከሰኞ ጀምሮ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ የማስተማር ስራው ቀጥሏል።

ትምህርት ተቋርጦ በነበረበት ወቅት የባከነውን ጊዜ ለማካካስ መምህራን ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ በትርፍ ሰዓታቸው እንዲያስተምሩ ስምምነት ላይ ተደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጌርጌሴኖን...

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት በቦታው ከተገኙ ቤተሰቦቹ ጋር የጌርጌሶን የአዕምሮ መርጃ ማህበርን ጎብኝቷል፡፡ በነበረን ቆይታም ህሙማኑን ተዘዋውረን የጎበኘን ሲሆን ይህንን ትልቅ ኃሳብ ይዞ የተነሳ በተለይም የአዕምሮ ህሙማንን በመንከባከብ እንዲያገግሙና ተመልሰው ወደ ማህበረሰቡ እንዲቀላቀሉ እየሰራ ለሚገኘው ለዚህ ማህበር የበኩላችንን አስተዋጽኦ በቤተሰቡ ስም አበርክተናል፡፡

- 10 ደርዘን የገላ ሳሙና፣
- 100 የልብስ ሳሙና፣
- 20 ሊትር ፈሳሽ ሳሙና፣
- 2 ካርቶን እሽግ የአዋቂ ዳይፐርና
- 11 ደርዘን መታሻ እንዲሁም 16,000 ሺ ብር [በአጠቃላይ 25,000 ብር] ለማህበሩ በቲክቫህ ቤተሰብ ስም አበርክተናል፡፡ እገዛችን ትንሽ ብትሆንም ሌሎችን ለማነሳሳት ይረዳል ብለን እናምናለን።

ማህበሩን መጎብኘት ለምትፈልጉ አዲስ አበባ፣ እንጦጦ፣ ቁስቋም ከ17 ቁጥር አውቶብስ ማዞሪያ አለፍ ብሉ ከውሃ ልማት ጎን ይገኛል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጌርጌሴኖን... ቲክቫህ ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት በቦታው ከተገኙ ቤተሰቦቹ ጋር የጌርጌሶን የአዕምሮ መርጃ ማህበርን ጎብኝቷል፡፡ በነበረን ቆይታም ህሙማኑን ተዘዋውረን የጎበኘን ሲሆን ይህንን ትልቅ ኃሳብ ይዞ የተነሳ በተለይም የአዕምሮ ህሙማንን በመንከባከብ እንዲያገግሙና ተመልሰው ወደ ማህበረሰቡ እንዲቀላቀሉ እየሰራ ለሚገኘው ለዚህ ማህበር የበኩላችንን አስተዋጽኦ በቤተሰቡ ስም አበርክተናል፡፡…
ጌርጌሴኖን...

ጌርጌሴኖን የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማህበር አስታዋሽ የሌላቸው ምንም ዓይነት ረዳት ወገን ዘመድ የሌላቸውን የአዕምሮ ሕሙማን ማለትም ፍፁም ራሳቸውን የማያውቁ ልብሳቸውን ጥለው የሚሄዱና ምግቡን እና አፈርን እንኳን ለይተው የማይመገቡ ወገኖቻችንን ለመርዳት አቶ መለሰ አየለ በተባለ በጎፈቃደኛ ተመስርቶ በ2003 ህጋዊ እውቅናን ያገኘ ማህበር ነው፡፡

አቶ መለሰ አየለ ግን ፍቃድ ከማግኘቱም በፊት ይህንን ሥራ በግሉ ሲሰራ መቆየቱን ሰምተናል፡፡ እኛም በቦታው ተገኝተን መመልከት እንደቻልነው ማህበሩ አሁን ላይ 322 የአዕምሮ ህመምተኞችን በተከራየው በጠባብ ቦታ ላይ እርዳታ እየሰጣቸው ይገኛል፡፡

እስካሁን ማህበሩ ከጎዳና አንስቶ እርዳታ ካደረገላቸው ህሙማን 168ቱ ሙሉ ለሙሉ ድነው ቤተሰብ ጭምር መስርተው ማህበሩን በአቅማቸው እየረዱ ያሉ እንደሚገኙበት ተገልጿልናል፡፡ ይሁንና እስካሁን 68 ያክሉ ደግሞ ወደ ማዕከሉ ከገቡ በኀላ ህይወታቸው ቢያልፍም ስርዓተ ቀብራቸው በክብር ተፈጽሞላቸዋል፡፡

ማህበሩ አሁን ላይ ከቦታው መጣበብ የተነሳ በሙሉ አቅሙ እየተንቀሳቀሰ እንዳልሆነ የገለጸልን ሲሆን እኛም በቆይታችን ከማረፊያ ክፍሎቹ ጥበት ባለ ሦስት ተደራራቢ አልጋዎች መገኘታቸው ከጎዳና ይሻላል ይሆናል እንጂ ሥራው ሰፊ ቦታ እና ልዩ እንክብካቤ እንደሚያስፈልገው ተገንዝበናል፡፡

ከማህበሩ እንደሰማነው ቦታ ለማግኘት በሂደት ላይ ቢገኙም እስካሁን በሂደት ላይ እንደሚገኝ ገልጸውልናል፡፡ በቀጣይ ከማህበሩ መስራች አቶ መለሰ አየለ ጋር ሰፊ ቆይታ አድርገን የምንመለስ ይሆናል፡፡

@tikvahethiopia @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 7ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባዔውን ከነገ ጥር 15-17 ቀን 2012 ዓ.ም እንደሚያካሄድ አስታወቀ። ጉባዔው ከከተማ አስተዳደሩ የተመረጡ ሁለት ቢሮዎችና ለምክር ቤቱ ተጠሪ የሆኑ ተቋማት የ2012 በጀት ዓመት የስድስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ይወያያል። የተለያዩ አዋጆችና ልዩ ልዩ ሹመቶች እንደሚቀርቡና ውይይት ተደርጎባቸው እንደሚጸድቁም…
#UPDATE

የአዲስ አበባ ምክር ቤት 7ኛ አመት ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤውን ጀምሯል። ጉባኤው በዛሬው ውሎው የተማሪዎች ምገባ ኤጀንሲ ለማቋቋም፣ የከተማ አስተዳደር ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ለማሻሻል የወጡ አዋጆችን እንዲሁም የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ረቂቅ ደንቦችን ጨምሮ ሌሎች ደንብና አዋጆችን ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል። የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽንን እንደገና ለማቋቋም የተዘጋጀውን ረቂቅ አዋጅ ያሻሽላል ተብሎ ይጠበቃል። ከሰአት በኋላ በሚኖረው ውሎ ደግሞ የተለያዩ ሹመቶችንም ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

[ENA]
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በ22 ዩኒቨርሲቲዎች ባካሄደው ምርመራና ቅኝት መሰረት፦

- በግማሽ ዓመት ውስጥ ብቻ የ12 ተማሪዎች ሕይወት አልፏል።

- በፀጥታ ችግሮች ምክንያት ከ35 ሺሕ ተማሪዎች በላይ ከትምህርት ገበታቸው ላይ አይገኙም። እነዚህንም ለመመለስ መሠራት እንደሚገባው ተገልጿል።

- በመጀመሪያው መንፈቅ ዓመት በተከሰቱ ግጭቶች ላይ ተሳትፎ ነበራቸው የተባሉ 640 ተማሪዎች ላይ ከአንድ ዓመት ትምህርት እገዳ እስከ ትምህርት ገበታ መሰናበት ድረስ የሚደርሱ የተለያዩ ቅጣቶች ተላልፈዋል።

- በ41 መምህራን እና በ240 የአስተዳደር ሠራተኞች ላይ አስተዳደራዊ ቅጣቶች ተጥለዋል።

ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማርያም የተናገሩት፦

"ከ85 በመቶ በላይ የሚሆኑት ዩኒቨርሲቲዎች በተወሰዱ እርምጃዎች አማካኝነት የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማከናወን የሚቻልባቸው ሆነው ተገኝተዋል።"

[ከአዲስ ማለዳ ጋዜጣ]
@tikvahethiopia @tikvahethiopia
የታገቱት ተማሪዎች እስካሁን ድምፃቸው አልተሰማም...

- ህዳር 20/21 የታገቱበት ቀን።

- ህዳር 24 አምልጣ የወጣችው ተማሪ መታገታቸውን የተናገረችበት።

- ታህሳስ 27 የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በጋዜጣዊ መግለጫቸው የታገቱ ተማሪዎች እንዳሉ ቁጥራቸውም እስከ 4 እንደሚደርስ የገለፁበት ቀን።

- ጥር 2 የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የፕሬስ ሴክሬተርያት ኃላፊ ክቡር አቶ ንጉሱ ጥላሁን ስለታገቱት ተማሪዎች በሰጡት መግለጫ 21 ተማሪዎች መለቀቃቸውንና 6 ተማሪዎች ታግተው እንዳሉ የገለፁበት ቀን። [አቶ ንጉሱ ይህ መግለጫ ከሰጡ ዛሬ 13 ቀን ሆኖታል]

- ጥር 8 የኦሮሚያ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ ክቡር አቶ ጌታቸው ባልቻ ታግተው የተለቀቁት ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ተመልሰዋል፤ ተማሪዎቹ ከእገታ ከተለቀቁ በኋላ ከወላጆቻቸው ጋር ያልተገናኙት በአካባቢው የስልክ ግንኙነት አገልግሎት ባለመኖሩ የተነሳ መሆኑን ገለጹበት ቀን።

ይህ ሁሉ ሲሆን ተማሪዎቹ ከመጀመሪያዎቹ ሳምንታት ውጪ ከቤተሰቦቻቸው ጋር አልተገናኙም ተለቀዋል ከተባለ በኃላም ምንም አይነት ማስረጃ ሊገኝ አልቻለም፡፡

ይህ ለምን እነደሚሆንና ቢያንስ የተማሪዎቹ መለቀቅ በግልፅ ታይቶ ነገሮችን ለማብረድ ምንም አልተሰራም፡፡ ይህ ጉዳይ አስቸኳይ ፍትህ የሚፈልግ ነው፡፡ ሁለት ወር ሊሞላቸው የተቃረቡት ለእኚህ ተማሪዎች አስፈላጊው ትኩረት ያለመሰጠቱ ጉዳይ አሳሳቢ ነው፡፡

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE የሚንስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 78ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል። ምክር ቤቱ ውሳኔ ያሳለፈባቸው ጉዳዮችም እንደሚከተለው ቀርበዋል፦ 1. ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትን ህጋዊ ሰውነት ለመስጠት በተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ህጋዊ ሰውነት እንዲኖረው…
ወታደራዊ ኢንዱስትሪዎች ወደ መከላከያ ሚኒስቴር...

በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ስር ይተዳደሩ የነበሩ ወታደራዊ ኢንዱስትሪዎች ወደ መከላከያ ሚኒስቴር እንዲዘዋወሩ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ትናንት ባካሄደው 78ኛ መደበኛ ስብሰባ ተወስኗል። ትላንት ምክር ቤቱ ከተመለከታቸው ጉዳዮች መካከል የመከላከያ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ማቋቋሚያ ረቂቅ ደንብ ነው።

በአገር መከላከያ ሰራዊት ውስጥ የተጀመረው የሪፎርም ስራዎች አንድ አካል የሆነውና በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ አስፈጻሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 1097/2011 መሰረት ወታደራዊ ኢንዱስትሪዎችን ቀደም ሲል ከነበሩበት ከብረታ ብረት እና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ወደ መከላከያ ሚኒስቴር እንዲዛወሩ ተወስኗል፡፡

በዚሁ መሰረት፦

- የደጀን አቪዬሽን ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ፣

- የጋፋት አርማመንት ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ፣

- የሆሚቾ አሚውኒሽን ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪና የፊውል ነዳጅ

- ፕሮፒላንት ንዑስ ኢንዱስትሪ

መዋቅራዊ አደረጃጀቱን በአንድ ኮርፖሬሽን ስር በማደራጀት ብቁና ተወዳዳሪ ወታደራዊ ኢንዱስትሪዎች መገንባት ይቻል ዘንድ የመከላከያ ሚኒስቴር የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ማቋቋሚያ ረቂቅ ደንብ አዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክቤት ውሳኔ አቅርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በቀረበው ረቂቅ ደንብ ላይ ከተወያየ በኋላ ደንቡ በነጋሪት ጋዜጣ እንዲወጣና በስራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡

[ENA]
@tikvahethiopia @tikvahethiopia