TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
56.9K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#NobelPeacePrize #AbiyAhemedAli

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከኦስሎ ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ አቀባበል ሊደረግላቸው ነው። የዘንድሮው የሰላም ኖቤል አሸናፊ የሆኑት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ነገ ወደ አገራቸው ይመለሳሉ።

የአዲስ አበባ ከንቲባ ከደቂቃዎች በፊት በትዊተር ገጻቸው ላይ እንዳሰፈሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ አቀባበል ይደረግላቸዋል።

ኢንጅነር ታከለ እንዳሉትም የአዲስ አበባ ህዝብ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ ተገኝቶ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቀባል እንዲያደርግላቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።

(ETHIO FM 107.8)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Election2012

"ምርጫው በእርግጠኝነት ይካሄዳል!" - ወ/ሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ (የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ)

ከኢቲቪ ጋር ቆይታ ያደረጉት የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ ቀጣዮ ሀገር አቀፍ ምርጫ በተቀመጠለት ጊዜ "በእርግጠኝነት ይካሄዳል" ብለዋል። ምርጫውን ለማከናወን ያለውን አጭር ጊዜ ታሳቢ በማድረግ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በፍጥነት እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል።

ተአማኒነትን የሚያጎድሉ ስህተቶች እንዳይኖሩም ጥንቃቄ እንደሚደረግም ጠቁመዋል። ለምርጫው የሚያስፈልጉ አለም አቀፍ ግዢዎች እየተደረገ መሆኑንም ሰብሳቢዋ ገልፀዋል።

የሲዳማን ክልልነትን ለመወሰን የተደረገው ህዝበ ውሳኔ ለሀገር አቀፍ ምርጫው በርካታ ልምድ የተገኘበት እንደሆነም ጠቁመዋል። ምርጫ 2012 ነፃ፣ ተአማኒና ገለልተኛ እንዲሆን ቦርዱ ከቃል በላይ በተግባር ይሰራል ያሉት ወ/ሪት ብርቱካን ለዚህም ቁርጠኛ መሆኑን ገልፀዋል።

(ኢቲቪ)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ኢትዮጵያዊው የህግ ባለሙያ አቶ አምሃ መኮንን የዘንድሮውን የሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ ሽልማትን አሸነፉ!

ኢትዮጵያዊው የህግ ባለሙያና ጠበቃ አቶ አምሃ መኮንን የዘንድሮውን የፈረንሳይ ጀርመን የሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ ሽልማት አሸንፈዋል። ጠበቃ አምሃ መኮንን በኢትዮጵያ በነበረው አስቸጋሪ ወቅት እና ጊዜያት ሁሉ ለዜጎች ሰብዓዊ መብት እና ነጻነት መከበር ላበረከቱት አስተዋጽኦ ነው ሽልማቱ የተበረከተላቸው።

ሽልማቱን የጀርመንና የፈረንሳይ አምባሳደሮች ያበረከቱት ሲሆን፥ በስነ ስርዓቱ ላይ ቤተሰቦቻቸው፣ ጓደኞቻቸው እና የሙያ ባልደረቦቻቸው ተገኝተዋል። የፈረንሣይ ጀርመን የሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ ሽልማት በየዓመቱ በፈረንጆቹ ታህሳስ 10 የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ በዓለም ዙሪያ ለ15 የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች የሚሰጥ ነው።

(ኤፍ ቢ ሲ)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በጎንደር ከተማ የደረሰ እሳት ቃጠሎ በንብረት ላይ ጉዳት አደረሰ!

- በጎንደር ከተማ አዘዞ ቀበሌ 19 ትናንት ምሽት በደረሰ የእሳት ቃጠሎ በ3 የእህል ወፍጮ ቤቶችና በአራት ጊዚያዊ የእህል መጋዘኖች ላይ ጉዳት መድረሱን ፖሊስ አስታወቀ፡፡ በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ ተመልክቷል።

የከተማው ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግንኙነት አስተባባሪ ምክትል ኮማንደር አበበ አለባቸው እንዳሉት ቃጠሎው የደረሰው  በከተማው የአውቶብስ መናኸሪያ አጠገብ በሚገኙ ጊዚያዊ የገበያ ስፍራ አጠገብ ነው፡፡

ምሽት አራት ሰዓት ተኩል አካባቢ በተነሳው የእሳት ቃጠሎ ሶስት የእህል ወፍጮ ቤቶችና አራት ጊዚያዊ የእህል መጋዘኖች ለጊዜው ግምታቸው ካልታወቁ ንብረቶች ጋር ወድመዋል፡፡ ለአንድ ሰዓት የዘለቀውን የእሳት ቃጠሎ ለመቆጣጠር የአከባቢው ወጣቶችን ሌላም የህብረተሰብ ክፍል ከከተማው እሳት አደጋ መከላከያ ጋር በመሆን  ርብብር ማድረጋቸውን ምክትል ኮማንደሩ ገልጸዋል፡፡

በዚህም ቃጠሎውን መቆጣጠር መቻሉን ጠቁመው እሳቱን ለማጥፋት በተደረገው ርብርብ ላይ ተሳታፊ የነበሩ ሁለት ሰዎች በጭሽ የመታፈን ጉዳት ደርሶባቸው የህክምና እርዳታ እንዲያገኙ መደረጉን አመልክተዋል። ምክትል ኮማንደሩ እንደተናገሩት ቃጠሎው በሰው ሕይወት ላይ ያደረሰው ጉዳት የለም፡፡ ፖሊስ ቃጠሎው ያደረሰውን የንብረት ውድመትና የአደጋውን መንስኤ ለማጣራት የምርመራ ስራ መጀመሩንም አብራርተዋል፡፡

(ENA)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#BetaSamati

በቅድመ ሮም የነበረች ጥንታዊት ከተማ ኢትዮጵያ ውስጥ ተገኘች!

የቅሪተ አካል ተመራማሪዎች ከ1400 ዓመታት በፊት የነበረች ከተማ ኢትዮጵያ ውስጥ በቁፋሮ ማግኘታቸው ታወቀ። ከተማዋ በምሥራቅ አፍሪካ ገናና የነበረው እና እንደ ሮማ ግዛተ አጼ ከመሳሰሉ ኃያላን ጋር የንግድ ግንኙነት የነበረው የጥንታዊ አክሱም ግዛት አካል የነበረች መሆኗም ተጠቅሷል።

በአሜሪካን አገር ሜሪላንድ ግዛት ባልቲሞር በሚገኘው የጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ ባልደረባ የሆኑት ሚካኤል ሃሮወር “ይህ ስፍራ ከቀደምት ሥልጣኔዎች አንዱ ነው፤ ነገር ግን ሰዎች ስለ ስፍራው የሚያውቁት ነገር የለም። ከግብጽ እና ሱዳን ውጭ ይህ ስፍራ ቀደምት የአፍሪካ ታላቅ ሥልጣኔ የነበረበት ኅብረተሰብ መገኛ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

https://www.newscientist.com/article/2226803-lost-ethiopian-town-comes-from-a-forgotten-empire-that-rivalled-rome/

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በትራፊክ አደጋ 2 ሰዎች ሲሞቱ በ17 ሰዎች ላይ ደግሞ የአካል ጉዳት ደረሰ!

በትግራይ ደቡባዊ ዞን ከማይጨው ከተማ ወደ ነቅሰገ ሲጓዝ የነበረው መኪና ተገልብጦ ሁለት ሰዎች ወዲያውኑ ሲሞቱ በ17 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን የዞኑ ፖሊስ ገለፀ።

በዞኑ ፖሊስ መምሪያ የትራፊክ ደህንነት ቁጥጥርና አጣሪ ምክትል ዳይሬክተር ኮማንደር አብረሃ ወረደ እንደገለፁት 19 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ የተገለበጠው ነቅሰገ ከተማ መግቢያ አካባቢ ነው።

ትናንት ከቀኑ 5 ሰዓት ላይ በደረሰው አደጋ 2 ሰዎች ወዲያውኑ ህይወታቸው ሲያልፍ ሾፌሩን ጨምሮ በ17 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን ኮማንደሩ ተናግረዋል። ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው 17 ሰዎች በማይጨው ሆስፒታልና በማይጨው ጤና ጣቢያ በህክምና ላይ ይገኛሉ ተብሏል።

የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 ትግ 06605 የሆነው ሚኒባስ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ 11 ሰዎች መጫን ሲገባው ትርፍ ጭኖ በመጓዝ ላይ እንዳለ መገልበጡን ገልፀዋል። የአደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ ነው ያሉት ኮማንደሩ የትራፊክ አደጋ በየጊዜው እየጨመረ የበርካታ ወገኖች ህይወት እየቀጠፈና የአገርና የህዝብ ንብረት እያወደመ በመሆኑ አሽርካሪዎች በጥንቃቄ እንዲጓዙ አሳስበዋል።

(ኢዜአ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ነገሮችን ማድበስበስ ሊቆም ይገባል...

በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እየታዩ ያሉት እንቅስቃሴዎች እጅግ አደገኛ ለሀገር ህልውናም አስጊ እንደሆኑ ደጋግመን ሳንሰለች እየገለፅን ነው። ሁሉን አሳታፊ ውይይት ተደርጎ፣ ከምንም ነገር የነፃ እውነተኛ እርቅ ወርዶ፣ ተማሪው ይቅርታ ተጠያይቆ፣ ከኃላፊዎች ጀምሮ ጥፋተኞች ካሉ በአግባቡ ተጠይቀው፣ የተጎዱ ተማሪዎች ተክሰው፣ ወደ ቤተሰቦቻቸው የሄዱትም በክብር ተመልሰው፣ ወንድም ወንድሙን አቅፎ ተቀብሎ የትምህርት ስርዓቱ በአስተማማኝ ሁኔታ ውስጥ ማስቀጠል ካልተቻል፤

ተማሪዎች እያነሷቸው ላሉት ጥያቄዎች በክብር አዳምጦ ምላሽ መስጠት የማይቻል ከሆነ፣ ለተማሪ ሞት፣ ለአካል ጉዳት፣ ግቢ ጥሎ መውጣት ፣ መሰቃየት፣ ምክንያት የሆኑ፣ አካላት በግልፅ በህዝብ ፊት እስካልተጠየቁ ድረስ መሰል ችግሮች ዳግም ላለመከሰታቸው አሁንም እየተከሰቱ ያሉ አሳዛኝ ክስተቶች ላለመቀጠላቸው ምንም ዋስትና የለም። የሀገሪቱ መንግስት የሚታዩትን ምልክቶች እንደቀላል ነገር ከመቁጠር፣ እንዲሁም እያድበሰበሰ ከማለፍ ይልቅ ችግሩ ነገ ሀገር ሊያሳጣን የሚችል እንደሆነ ታምኖ ሳይውል ሳያድር መፍትሄ ቢፈልግ መልካም ነው።

አጥፊዎች፣ የግጭት አቀናባሪዎች በግልፅ ታውቀው እስካልተጠየቁ፣ የተማሪዎች ጥያቄ ምንድነው ብሎ በመጠየቅ ለመፍታት ካልተሰራ፣ እውነተኛ እርቅ እና ሰላም እንዲወርድ ከፖለቲካ የነፃ ተግባራዊ ስራ ካልተሰራ፣ ዜጎች በሀገሪቱ መንግስት ላይ ያላቸው እምነት እየተሸረሸረ እየሄደ እንደሆነ እየታዘብን ነው። በ ሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች፣ ልጆቻቸውን በግፍ ያጡ ምስኪን ወላጆች ዛሬም ፍትህ የታለች እያሉ ነው። ግጭት ሸሽተው በየቤታቸው የተቀመጡ ሀገር ተረካቢ ወጣቶች መፍትሄ፣ ሰላም እንደሚገልጉ እየገለፁ ነው።

የሚሰማን መንግስት ካለ አሁንም ጥሪ እናቀርባለን!

@tikvahethiopiaBot
“መፍትሄ የሚገኘው ወንጀለኛን በመቅጣት ብቻ ሳይሆን፣ ህግና ደንብን በማስተማር ጭምር ነው” - ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ (የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት)
.
.
የጠቅላይ ፍርድቤት ፕሬዚዳንት ወይዘሮ መአዛ አሸናፊ በትላንትናው ዕለት ዓለማቀፍ የሰብአዊ መብት ቀንን ምክንያት በማድረግ ከዳግማዊ ምኒሊክ መሰናዶ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ጋር በተደረገው የውይይት መድረክ ላይ እንዳሉት በፍትህ ዘርፉ ስኬት የሚገኘው ወንጀለኛን በመቅጣት ብቻ ሳይሆን ህግና ደንብን በማስተማር በተለይ ደግሞ በታዳጊዎች ላይ መብትና ግዴታቸውን አውቀው እንዲያድጉ በማደረግ ነው።

በመሆኑም ይላሉ ወይዘሮ መዓዛ ጠቅላይ ፍርድቤት የፍትህ ዘርፉ የሚስተዋልበትን ችግሮች መቅረፍ እንዲችል ታዳጊዎች ላይ ትኩረት አድርጎ በመስራት ላይ ነው። መብት እና ግዴታውን ያወቀ ህብረተሰብ ለመገንባት ጠንክሮ መሰራት ያለበት መሰረቱ ላይ እንደሆነ ፕሬዚዳንቷ አጽዕኖት ሰጥተው ተናግረዋል።

መብቱን ብቻ ሳይሆን ግዴታውን ያወቀ ህብረተሰብ መገንባት ካልተቻለ የዳኝነት ስራውን ከባድ ያደርገዋል ያሉት ፕሬዝዳንቷ ትውልድን ለመገንባትም መስርያ ቤታቸው በወጣቶች ላይ በተለይም ተማሪዎች ላይ ትኩረት በመስጠት ይሰራል፡፡ በመድረኩ 500 የዳግማዊ ምኒሊክ መሰናዶ ትምህርትቤት ተማሪዎች ተሳትፎ ያደረጉ ሲሆን ጠቅላይ ፍርድቤት የሰብአዊ መብት ቀንን ምክንያት በማድረግ በተመሳሳይ በሌሎች ሶስት ትምህርት ቤቶች ላይ ቀጣይ መድረክ ይኖረዋል።

(EPA)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሰኔ 15ቱ የባለሥልጣናት ግድያ ተከሳሾች መዝገብ ላይ ብይን ለመስጠት ለታኅሣሥ 21 ቀጠሮ ሰጠ፡፡

ለታኅሣሥ 1 ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረው የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ 4ኛ ወንጀል ችሎት በእነ አስር አለቃ መሳፍንት ጥጋቡ መዝገብ የተከሰሱትን ዘጠኝ ተጠርጣሪዎች የክስ መቃወሚያ ተቀብሏል፡፡

የአብን ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ክርስቲያን ታደለ የሚገኙበት የዚሁ መዝገብ ተከሳሾች በዐቃቤ ሕግ የቀረበባቸውን ክስ መሰረት በማድረግ የክስ መቃወሚያቸውን ለፍርድ ቤቱ አቅርበዋል፡፡

ፍርድ ቤቱም የክስ መቃወሚያቸውን ተቀብሎ ዐቃቤ ሕግ ለቀረበው የክስ መቃወሚያ መልስ እንዲያዘጋጅ ያዘዘ ሲሆን፤ የክስ መዝገቡን እና መቃወሚያውን መርምሮ ብይን ለመስጠት ለታኅሣሥ 21/2012 ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

(AHADUTV)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FakeNewsAlert

(Elias Meseret)

ይህ "ዛሬ ጠዋት ፕሬዝደንት ኢሳያስ ጠ/ሚር አብይ ልዩ ሰው ነው አሉ፣ እሱን በቃላት ለመግለፅ ይከብዳል ብለው ለጋዜጠኞች ተናገሩ" እየተባለ በብዛት ሼር እየተደረገ ያለ ነገር የሀሰት ነው። ብዙ ተከታይ ያላቸው ግለሰቦች፣ የመንግስት ባለስልጣናት እንዲህም የሚድያ ሰዎች የሀሰት መረጃ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ላለማሰራጨት ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

(ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ነገ የሚዘጉ መንገዶች!

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠ/ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አይሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ለሚደረግላቸው የክብር አቀባባል ሥነ-ሥርዓት የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይከሰት አሽከርካሪዎች የተለመደውን ትብብር እንዲያደርጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጥሪውን አስተላለፈ፡፡

ታህሳስ 02/2012 ዓም የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠ/ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የኖርዋይ ኦስሎ ቆይታቸውን አጠናቅቀው አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አይሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በሚደረግላቸው የአቀባበል ሥነ-ሥርዓት ላይ በርካታ የከተማችን ነዋሪዎች እና የውጭ ሀገር ዕንግዶች በተገኙበት የአቀባባል ሥነ-ሥርዓት ስለሚደረግ በመንገዶች ላይ የትራፈክ መጨናነቅ አንዳይከሰትና አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ኮሚሽኑ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

በዚህም መሠረት፡-ነገ ታህሳስ 02 ቀን/2012 ከለሊቱ 11፡00 ሰዓት ጀምሮ የአቀባበል ሥነ ሥርዓቱ እስከ ሚጠናቀቅ ድረስ ከአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አይሮፕላን ማረፊያ ጀምሮ እስከ ብሔራዊ ቤተ-መንግስት ባሉት ግራና ቀኝ መንገዶች ላይ ተሸከርካሪን ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓት ማቆም የተከለከለ ሲሆን ፡-አሽከርካሪዎችም አማራጭ መንገድ እንዲጠቀሙ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

• ከኡራኤል ቤ/ክርስቲያን ወደ መስቀል አደባባይ

• ከቦሌ ዓለም አቀፍ አይሮፕላን ማረፊያ ወደ መስቀል አደባባይ

• ከቦሌ ኤድናሞል ወደ ቦሌ ዓለም አቀፍ አይሮፕላን ማረፊያ

• ከብሔራዊ ቤተ-መንግስት ፤ ከፍል ውኃ ፤ ከለገሀር ፤ከካሳንችስ፤ከሳንጆሴፍ ትምህርት ቤት ፤ከስታዲየምንና ከሃራምቤ ሆቴል አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስዱ መንገዶች ለጊዜው #ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

https://telegra.ph/ETH-12-11-3

@tikvahethiopiaBot
የፀረ ሽብርተኝነት ህጉ አገሪቱ ከጀመረችው ለውጥ ጋር አብሮ የማይሄድና አፋኝ ህግ በመሆኑ ፖሊስ የጊዜ ቀጠሮ መጠየቂያ ሊያደርገው እንደማይገባ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ገለጸ።

በወንጀል የተጠረጠሩ ዜጎችን መደበኛ ህጉ በሚሰጠው የጊዜ ገደብ መሰረት እየተጠቀሙ መመርመር እየተቻለ በፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ “የምርምራ ጊዜ ቀጠሮ መጠየቅ ተገቢ አይደለም” በማለት ነው ኮሚሽኑ የሚገልጸው።

More👇
https://telegra.ph/ETH-12-11-4

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀጣይ የቤት ስራ...

"አሁን በኢትዮጵያ በክልሎች እና በብሄር ግጭት ምክንያት ከ3,000,000 ዜጎች በላይ በውስጥ መፈናቀል ከቄያቸው ተፈናቅለው ቤት አልባ ናቸው፤ እነኚህ ተፈናቃዮች ወደቤታቸው መመለስ አለባቸው። የኢኮኖሚና የስራ አጥነት ሌላ በሀገሪቱ ያለ ችግር ነው፤ በጤና፣ ትምህርት እና መሰረተ ልማትም ብዙ ስራ ይቀራል፤ እነዚህ ሁሉ ለዘላቂ ሰላም መሰረታዊ ጥያቄዎች ናቸው። መሰራትም ይኖርባቸዋል። ዛሬም የኢትዮጵያና ኤርትራ ድንበር እንደተዘጋ ነው፤ በዚህም ሁለቱ ህዝቦች መገናኘት አልቻሉም። የሰላም ስምምነት የሚያካትተው ማህበራዊ፣ ባህላዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት ጭምር ነው። አሁን ግን ይህ ስራ ያልተሰራ ነው። ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ ይካሄዳል ተብሏል፤ ይህም ለዲሞክራሲ መጎልበት ትልቅ ሚና ስላለው መሰራት አለበት። በኢትዮጵያ ያለው መሪነት እና የፖለቲካ ምህዳር በኢትዮጵያውያን ተሳትፎ ብቻ መወሰንም ይኖርበታል።" - ቤሪት ራይስ አንደርሰን (የኖቤል ኮሚቴ ሊቀ መንበር )

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በህገ-ወጥ መንገድ 109 ሰዎችን ወደ ጅቡቲ ሲያጓጉዝ የነበረ አሽከርካሪ ተያዘ!

ከአማራ ክልል ባቲ ከተማ 109 ሰዎችን አሳፍሮ በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ጅቡቲ ድንበር ሲያጓጉዝ የነበረ ከባድ የጭነት መኪና አሽከርካሪን መያዙን የአፋር ክልል ፖሊስ ኮሚሸን አስታወቀ። መኪናዉ የታየዘው ትናንት ከሌሊቱ 10 ሰአት በሰመራ ከተማ ልዩ ስሙ አይሳኢታ መገንጠያ አካባቢ መሆኑ ተገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#WPDF

የዎላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ዎሕዴግ) ለደቡብ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ሄለን ደበበ በፃፈው ደብዳቤ ለዎላይታ ህዝብ ህገ መንግስታዊ ጥያቄ እጅግ አፋጣኝ የሆነ ህገ መንግስታዊ ምላሽ እንዲሰጥ ጠይቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ምርጫ ቦርድ ለተለያዩ ፓርቲዎች የምዝገባ እውቅና ሰጥቷል!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለሚከተሉት በምዝገባ ሂደት ላይ የነበሩ ፓርቲዎች እውቅና መስጠቱን አስታውቋል።

1. አፋር ህዝባዊ ፍትሐዊና ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢህፍዴፓ)

2. አፋር ህዝብ ነጻነት ፓርቲ (አህነፓ)

3. ጋሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ጋዴፓ)

4. ሞቻ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ(ሞዴፓ)

5. ቁማ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቁህዴፓ)

6. ካፋ አረንጓዴ ፓርቲ (ካአፓ)

7. ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ)

8. ዎላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ (ዎብን) እና

9. ሱማሌ አንድነት ፓርቲ (ሱአፓ)

(የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Mogadishu

በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ አንድ ሆቴል በአልሸባብ ታጣቂዎችና በመንግሥት የፀጥታ ሃይሎች መካከል በተከፈተ የተኩስ ልውጥጥ 10 ሰዎች ተገድለዋል። በሶማሊያ ወጣቶች ሊግ ሆቴል በነበረው ተኩስ አምስት የአልሸባብ አባለት፣ ሁለት የመንግሥት የፀጥታ ሃይሎች እና ሦስት ንፁሃን ዜጐች ተገድለዋል። ሆቴሉ ለመንግሥት ባለስልጣናት እና ለባለሃብቶች አገለግሎት የሚሰጥ ነው ተብሏል። ፖሊስ ባወጣው መግለጫ ለሰባት ሰዓታት የቆየው የተኩስ ልውውጥ አሁን የቆመ ሲሆን፥ ቢያንስ 82 ሰዎች ከሆቴሉ እንዲወጡ ተደርገዋል። የተኩስ ልውውጡ የተጀመረው የአልሸባብ ታጣቂዎች ጥቃት መክፈታቸውን ተከትሎ ነው ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የሚሰማን መንግስት ካለ መፍትሄ ይፈልግ...

ትኩረት በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እየተንገላቱ ለሚገኙት ተማሪዎች፣ ትኩረት እናተ ከዚህ አካባቢ ነው የመጣችሁት ውጡልን መማር አትችሉም ለሚባሉት ምስኪን ተማሪዎች፣ ትኩረት በትምህርት ገበታቸው ላይ እንዳይገኙ ማስፈራሪያ የሚደርሳቸው ተማሪዎች፣ ትኩረት የሀገር ህልውናን አደጋ ላይ ለጣለው የሰሞኑን አደገኛ ምልክት፤ ትኩረት ለሀገር ተረካቢ ወጣቶች፣ ተማሪዎች!

መንግስት ነገሮችን ማድበስበስ አቁሞ ችግሮች እንዲፈቱ፣ አጥፊዎች እንዲጠየቁ፣ ተማሪዎችን እያሸበሩ ያሉ አካላት እንዲለዩ፣ እውነተኛ እርቅ እና ሰላም እንዲወርድ፣ ከትምህርት ገበታቸው በማንነታቸው ምክንያት የራቁ ተማሪዎች በሰላም እንዲመለሱ፣ በግፍ የተገደሉ ተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች ፍትህ እንዲያገኙ ይስራ። እያየን ያለነው ምልክት ውሎ አድሮ ሀገር የሚያሳጣን እንደሆነ ታውቆ ሀገሪቱን አደጋ ላይ ለመጣል እጅግ አደገኛውን ካርድ የመዘዙ አካላትን ለይቶ መጠይቅ ይኖርበታል።

የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች መንግስት ምን እየሰራ እንዳለ ጠይቁ፤ የት የት ዩኒቨርሲቲ ችግር እንዳለ አሳውቁን በሏቸው፣ ተማሪዎችን አስታርቁ፣ ጥፋተኞች ለህግ እንዲቀርቡ ጠይቁ፣ በመንግስት እና በሚዲያዎች የለዘበ መረጃ ሀገር ከፍተኛ ችግር ውስጥ እየገባች ነው፤ ለትምህርት ወደ ተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የሄዱ ተማሪዎች እየተጠቁ፣ እየተጎዱ፣ እየትንገላቱ ነው። ችግሩ ሀገራዊ እና ሁሉንም የሚመለከት ነው።

ትኩረት መስቀለኛ መንገድ ላይ ለምትገኘው ሀገራችን!
ትኩረት በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ለሚገኙ ተማሪዎች!

ሰሚ ካለ እንጮሃለን!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ADDISABEBA

ማስታወሻ!

በነገው ዕለት (ታህሳስ 02/2012) ከለሊቱ 11:00 ሰዓት ለጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ የሚደረገው የአቀባበል ሥነ ሥርዓት እስከሚጠናቀቅ ድረስ ከአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አይሮፕላን ማረፊያ ጀምሮ እስከ ብሔራዊ ቤተ-መንግስት ባሉት ግራና ቀኝ መንገዶች ላይ ተሸከርካሪን ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓት ማቆም የተከለከለ ነው።

አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገድ እንድትጠቀሙ፦

• ከኡራኤል ቤ/ክርስቲያን ወደ መስቀል አደባባይ

• ከቦሌ ዓለም አቀፍ አይሮፕላን ማረፊያ ወደ መስቀል አደባባይ

• ከቦሌ ኤድናሞል ወደ ቦሌ ዓለም አቀፍ አይሮፕላን ማረፊያ

• ከብሔራዊ ቤተ-መንግስት፤ ከፍል ውኃ፤ ከለገሀር፤ ከካሳንችስ፤ ከሳንጆሴፍ ትምህርት ቤት፤ ከስታዲየምንና ከሃራምቤ ሆቴል አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስዱ መንገዶች ለጊዜው ዝግ ይሆናሉ።

የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘት እና መረጃ ለመስጠት የምትፈልጉ በስልክ ቁጥሮች ፡-
011-1-11-01-11
011-5-52-40-77
011-5-52-63-02
011-5-52-63-03 ወይም በነጻ ስልክ መስመር 991 እና 987 መጠቀም ይቻላል፡፡

(የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን)

@tikvahethiopiaBot @tikvagethiopia
#EthiopianEpiphany

የጥምቀት በዓል የማይዳሰስ ቅርስ ሆኖ እንዲመዘገብ መወሰኑን በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) አስታወቀ። ዩኔስኮ በኮሎምቢያ-ቦጎታ በቅርስ ጥበቃ ዙሪያ እያካሄደ ባለው ስብሰባ ነው በኢትዮጵያ የጥምቀት በዓል አከባበር የማይዳሰስ ቅርስ ሆኖ እንዲመዘገብ ውሳኔ ያስተላለፈው።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiBot