#NobelPeacePrize #AbiyAhemed
የዓለም የኖቤል የሰላም ሎሬት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ዛሬ ማለዳ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ 2019 የኖቤል የሰላም ተሸላሚ በመሆን ሽልማታቸውን ከትናንት በስቲያ በኖርዌይ ኦስሎ በተካሄደ ደማቅ ስነ ስርዓት መቀበላቸው ይታወሳል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ አዲስ አበባ ሲደርሱም ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ ታዋቂ ግለሰቦች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተወካዮች አቀባበል አድርገውላቸዋል። ለክብራቸውም 21 ጊዜ መድፍ ተተኩሷል።
(ኤፍቢሲ)
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot

#WolaitaSodo
ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የወላይታ ህዝብ የድጋፍ ስልፍ አካሄደ!
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የሰላም የኖቬል ተሸላሚ መሆናቸውን ተከትሎ የወላይታ ህዝብ በሶዶ ከተማ የድጋፍ ስልፍ አካሂዷል፡፡ የወላይታ ህዝብ በክልል የመደራጀት ጥያቄ በህገመንግስትና በሰላማዊ መንገድ እንዲመለስ ሰልፈኞቹ ጠይቀዋል፡፡
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሽልማት ለሀገራችን የኩራት ምንጭ መሆኑን የጠቀሱት ሰልፈኞቹ በዚህም የወላይታ ህዝብ ታላቅ ደስታ እንደተሰማቸው ገልጸው ይህ እድልም ከአድዋ ድል ያልተናነሰና ሀገራቱን ወደ ከፍታ ማማ የሚያሸጋግር ተግባር ነው ብለዋል፡፡
አያይዘውም የወላይታ ህዝብ የጠየቀው በክልል የመደራጀት ጥያቄ ዳር ለማድስ በሰላማዊ መንገድ እንደሚታገሉም ጠቁመዋል፡፡
በእለቱ ተገኝተው ንግግር ያደረጉ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳጋቶ ኩቤ ሽልማቱ ሀገራችንን የመልካም ዝና ባለቤት ያደረገ ነው ብለው ለቀጣይ ትግል ስንቅ ነው ሲሉ አክለዋል፡፡
የወላይታ ህዝብ በክልል የመደራጀት ጥያቄውን ምላሽ ለማግኘት ያሳየውን ትዕግስት አድንቀው ጥያቄው እንዳይቀለበስ በተለይ ወጣቱ በስከነ መንገድ መንቀሳቀስ አለበት ብለዋል፡፡
(SRTA)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

#Hawassa
በሐዋሳ ከተማ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ የደስታ መግለጫ መርሃ ግብር እየተከናወነ ይገኛል!
በሐዋሳ ከተማ የዓለም የሠላም ኖቤል ተሸላሚ ለሆኑት ለጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ የደስታ መግለጫ መርሃ ግብር በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይም የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች የክልሉ የፖሊስ ማርሻ ባንድ እንዲሁም በከተማው የሚገኙ የመንግሥት ሠራተኞችና ነዋሪዎች መሳተፋቸው ታውቋል።
በስነ ስርዐቱ ላይ የተገኙት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ አቶ ጥላሁን ከበደ ሽልማቱ ለአገራችን ሠላም እና የሕዝባችን አንድነትን እንደሚያጠናክርና በመከባበርና በሠላም አብሮ የመኖር እሴቶቻችንን እንደሚያጎለብት ተናግረዋል፡፡

#Jimma
የጅማ ከተማ ነዋሪዎች በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ የኖቤል የሰላም ሽልማት ደስታቸውን ገልጸዋል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
የጅማ ከተማ ነዋሪዎች በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ የኖቤል የሰላም ሽልማት ደስታቸውን ገልጸዋል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ለተደረገላቸው አቀባበል ህዝቡን አመሰገኑ!
ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ በግል የፌስቡክ ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ "ፍቅርና ክብር የገባዉን ሕዝብ ማገልገል ኩራትም ዕድልም ነው" በማለት ስሜታቸውን ገልጸዋል። በዚሁ መልዕክትም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምስጋናቸውን በአማርኛ፣ በአፋን ኦሮሞ እና በእንግሊዘኛ አቅርበዋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ በግል የፌስቡክ ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ "ፍቅርና ክብር የገባዉን ሕዝብ ማገልገል ኩራትም ዕድልም ነው" በማለት ስሜታቸውን ገልጸዋል። በዚሁ መልዕክትም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምስጋናቸውን በአማርኛ፣ በአፋን ኦሮሞ እና በእንግሊዘኛ አቅርበዋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#attention
በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ስለሚገኙት ተማሪዎች እና በስጋት ምክንያት ወደ ቤተሰቦቻቸው ስለሄዱት የነገ ሀገር ተረካቢ ተማሪዎች ትኩረት እንዲሰጥ እንጠይቃለን!
በአንድ በኩል ዩኒቨርሲቲዎች በአስቸኳይ ወደ ትምህርት ገበታችሁ ተመለሱ ካልሆነ ካምፓስ እስከመዝጋት እንደርሳለን እያሉ ማስታወቂያ ሲለጥፉ በሌላ በኩል ያልታወቁ አካላት ጥያቄያችን ምላሽ አላገኘም ክፍል አካባቢ ድርሽ እንዳትሉ፤ ብትሉ ግን ለሚደርስባቹ ጉዳት እራሳቹ ነው የምትጠየቁት የሚሉ ማስፈራሪያዎችን ይለጥፋሉ።
ነገ ተምረን የቤተሰባችን ህይወት እንቀይራለን፣ ለህዝብ እንሰራለን ብለው የሚያስቡ ምስኪን ተማሪዎች ምን ያድርጉ? ትላንት ከትላንት በስቲያ በአንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች በተማሪዎች ላይ ጉዳት እንደደረሰ የሰማችሁት ነው። በያዝነው ሳምንት የተማሪ ህይወት እንደጠፋም ይታወቃል። እከሌ ከዚህ አካባቢ ስለመጣህ ውጣ የሚል መልእክትም ያለ ከልካይ ሲሰራጩ እየተመለከትን ነው።
የተለያዩ ተጠርጣሪዎች እየተያዙ መሆኑ መንግስት እየገለፀ ይገኛል፤ አስተማማኝ ዘላቂ መፍትሄው ምን እንደሆነ ግን እየተነገረ አይደለም። ተማሪዎች በአግባቡ ሳይማሩ ሴሚስተሩ እየተገባደደ ነው። የመንግስት ስራ ምንድነው? ዘላቂ፣ አስተማማኝ፣ መፍትሄ የለውም? ለተማሪዎች ጥያቄ መልስ የለም? ነገም እንዲሁ ነው የሚቀጥለው? የሚከለተከታቸው አካላት ከችግሩ ክብደት አንፃር ማድረግ የሚችሉት ይህን ብቻ ነው? ግለቸቦች፣ ሚዲያዎች ችግሩ እንዲፈታ እያደረጉ ያለው ጥረት ምን ያህል ነው?
ዉሎ አድሮ የሀገር ህልውና አደጋ ላይ የሚጥል አደገኛ ክስተት ነውና ለተፈጠረው ችግር ልዩ ትኩረት ይሰጥ እያልን ደጋግመን እንጮሃለን!
የዩኒቨርሲቲ ጉዳዮች በ @tikvahethmagazine ላይ መከታተል ትችላላችሁ!

#FederalPolice
ዩኒቨርስቲዎች "በፌደራል ፖሊስ" እንዲጠበቁ በተወሰነው መሰረት በፌደራል ጥበቃ ስር የማድረጉ ስራ እየተካሄደ መሆኑን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ዩኒቨርስቲዎች "በፌደራል ፖሊስ" እንዲጠበቁ በተወሰነው መሰረት በፌደራል ጥበቃ ስር የማድረጉ ስራ እየተካሄደ መሆኑን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
የአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪዎች የጠ/ሚንስተር ዶ/ር አብይ የሰላም ኖቤል ሽልማት በመቀበላቸው የተሰማቸውን ደስታ ገለፁ፡፡
"የኖብል ሰላም ሽልማቱ ዓለም ለኢትዮጵያ የሰጠው እውቅና ነው" በሚል መሪ ቃል የአርባምንጭ ከተማ ነዋሪዎች የፓናል ውይይት በማድረግ ደስታቸውን ገልፀዋል፡፡ መርሃ ግብሩን የጋሞ ባይራ በሽማግሌዎች ምርቃት አስጀምረዋል፡፡
የጠ/ሚ ዶ/ር አብይ የአመራር ጥበብ እና ለሰላም ያበረከቱት አሰተዋፅኦ በአለም ውድ የሆነውን የኖቤል ሽልማት በማስገኘቱ የኢትዮጵያ ስም በአለም አደባባይ ከፍ እንዲል እና በወርቅ ቀለም እንዲፃፍ አስችሏታል፡፡
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"የኖብል ሰላም ሽልማቱ ዓለም ለኢትዮጵያ የሰጠው እውቅና ነው" በሚል መሪ ቃል የአርባምንጭ ከተማ ነዋሪዎች የፓናል ውይይት በማድረግ ደስታቸውን ገልፀዋል፡፡ መርሃ ግብሩን የጋሞ ባይራ በሽማግሌዎች ምርቃት አስጀምረዋል፡፡
የጠ/ሚ ዶ/ር አብይ የአመራር ጥበብ እና ለሰላም ያበረከቱት አሰተዋፅኦ በአለም ውድ የሆነውን የኖቤል ሽልማት በማስገኘቱ የኢትዮጵያ ስም በአለም አደባባይ ከፍ እንዲል እና በወርቅ ቀለም እንዲፃፍ አስችሏታል፡፡
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#NobelPeacePrize
‹‹የራስ ሀገር ዜጋ ትልቅ ለሆነ የክብር ሽልማት ሲበቃ ደስ የማይለው ሰው ቢኖር እጅግ በጣም ጥቂት ነው። እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ደስ ብሎኛል። በሥነ ሥርዓቱ ላይ የነበረው ክብርና ዝና የሚያመጣውን ኃላፊነት መሸከም ከባድ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለውጫዊ ሰላም ያደረጉትን ሀገር ውስጥ ያለውን ሰላም ከፍ በማድረግ፣ የህዝቦች ወድማማችነት እንዲጠናከር፣ ሰው በነፃነት ወጥቶ እንዲገባ፣ የህግ የበላይነት እንዲከበር ለማድረግ መስራት ይጠበቅባቸዋል። ከጎረቤት ሀገራትና ከሌላው አለምም ጋር መልካም ግንኙነት ማድረግ አስፈላጊ ቢሆንም አሁን በሀገር ውስጥ ካለው ተጨባጭ ሁኔታ አስተማማኝ የሆነ ዘላቂ ሰላም ያስፈልጋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሽልማቱ ያሸከማቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ፈጣሪ ይርዳቸው።" - አቶ በቀለ ገርባ (የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ /ኦፌኮ/ ፓርቲ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር)

ዩኒቨርስቲዎች ከማንኛውም አይነት ሁከትና ግርግር የፀዱ ሊሆኑ ይገባል!
“ኢትዮጵያ ከድህነት ለመውጣት የተማረ የሰው ኃይል ያስፈልጋታል፡፡ ይሔንን የተማረ ኃይል ለማፍራት ደግሞ ዩኒቨርስቲዎች ሰላማዊ መማር ማስተማር ሂደት ብቻ የሚከናወንባቸው፤ ከማንኛውም አይነት ሁከትና ግርግር የፀዱ ሊሆኑ ይገባል፡፡ የዩኒቨርሲቲዎችን ሰላም አስጠብቆ፣ የተማሪዎችን ደህንነት አስከብሮ ለመቀጠል የሁሉም አካላት የተግባር ቁርጠኝነት ያስፈልጋል።” ፕሮፌሰር ሂሩት ወ/ማርያም(የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር )
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
“ኢትዮጵያ ከድህነት ለመውጣት የተማረ የሰው ኃይል ያስፈልጋታል፡፡ ይሔንን የተማረ ኃይል ለማፍራት ደግሞ ዩኒቨርስቲዎች ሰላማዊ መማር ማስተማር ሂደት ብቻ የሚከናወንባቸው፤ ከማንኛውም አይነት ሁከትና ግርግር የፀዱ ሊሆኑ ይገባል፡፡ የዩኒቨርሲቲዎችን ሰላም አስጠብቆ፣ የተማሪዎችን ደህንነት አስከብሮ ለመቀጠል የሁሉም አካላት የተግባር ቁርጠኝነት ያስፈልጋል።” ፕሮፌሰር ሂሩት ወ/ማርያም(የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር )
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#NobelPeacePrize
ከትናንት በስቲያ በኖርዌይ ኦስሎ በተካሄደ ሥነ-ሥርዓት የ2019 የኖቤል የሰላም ሽልማታቸውን ለተቀበሉት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በአሁኑ ሰዓት በብሔራዊ ቤተመንግስት አቀባበል እና የእራት ግብዣ እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡ በኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ በተዘጋጀው በዚህ አቀባበል እና የእራት ግብዣ ላይ የፌደራል እና የክልል መንግስታት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ ዲፕሎማቶች እና ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
(ኢቢሲ)

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀጣይ የቤት ስራ...
"ጠቅላይ ሚኒስትር በሽልማት ሥነሥርዓቱ ላይ በራስ መተማመንና በብቃት ያደረጉት ንግግር መልዕክት ስቦኝ ነው እንደተከታተሉት፤ ሀገርንም የሚያኮራ መልዕክት አስተላልፈዋል። ሽልማቱ በኢትዮጵያና በኤርትራ ሀገራት መካከል የነበረውን ችግር በመፍታታቸው ብቻ ሳይሆን፣ በሌሎችም አስተዋጽኦዎች ጭምር ነው። ኢትዮጵያ ካፈራቻቸው ባለሙያዎችና መሪዎች አንዱ መሆናቸውና ሽልማቱም በዘፈቀደ የተሰጠ እንዳልሆነ ግንዛቤ ሊያዝ ይገባል። ስሙ እንዲህ ገኖ ሲወጣ የማያስደስተው ኢትዮጵያዊ ሊኖር አይገባም። ይሁን እንጂ በሁለቱ ሀገራት ሰላም ቢሰፍንም በሰነድ የተደገፈ ስምምነት አለመኖሩ ወደፊት የቤት ሥራ እንደሚጠብቃቸው፣ ህዝብን ይዘው ሀገርን ማረጋጋት፣ ዜጎች በሀገራቸው እንዳይፈናቀሉ እነዚህንና ሌሎችንም ተግባራት ለማከናወን ሽልማቱ የሞራል ግንባታ ይሆናቸዋል።" - ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ (የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ ሊቀመንበር)

#ADAMA
ወጣቶች "የሰላም ኃይል" በመሆን በሀገሪቷ ውስጥ የሚስተዋሉ ግጭቶች ለማስቆም የድርሻቸውን እንዲወጡ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠየቀ። “ወጣቶች ለሰላም ”በሚል መሪ ቃል ሀገር አቀፍ የሰላም ኮንፈረንስ ዛሬ አዳማ ከተማ ተጀምሯል።
የጉባኤው ምክትል ፀሐፊ አቶ ሂሉፍ ወልደስላሱ በኮንፍረንሱ መድረክ እንዳሉት በቅርቡ በሀገሪቱ እየተበራከቱ በመጡት ግጭቶች ውስጥ ወጣቶች ተሳታፊና ተጎጂዎችም ናቸው። በተሳሳተ መረጃና በስሜት በመገፋት ግጭቱ የሚያስከትለውን ጉዳትና ቀውስ ካለማመዘን ወጣቶች የሚሳተፉበት እንደሆነ አመላክተዋል።
“ግጭቶች በባህሪያቸው ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል የሚጎዱ በመሆኑ ችግሮቹን ለማከምና ለማስወገድ ሁላችንም አንድ ሆነን መስራት አለብን“ ብለዋል። በተለይም ወጣቶች የሰላም ኃይል መሆናቸውን ተገንዝበው በሀገሪቱ ውስጥ የሚስተዋሉ ግጭቶች ለማስቆምና አለመግባባቶች ለመፍታት በሚደረገው ጥረት የድርሻቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።
https://telegra.ph/ETH-12-12-2
(ENA)
@tikvahethiopia