"የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ትግል ሁሉም እኩል የሆኑባትን ኢትዮጵያን መፍጠር ነው" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የብሔር ብሔረሰቦችን ቀን ለማክበር በተዘጋጀ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ትግል ሁሉም እኩል የሆኑባትን ኢትዮጵያን ለመፍጠር ያለመ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
"ዴሞክራሲን ማስፈን ቀላል ተግባር አይደለም፤ የጅማሮው ሥራ የቱንም ያህል አስቸጋሪ ቢሆን፣ ጉዞን ወደዚያ ማድረግ ለፍሬ የሚያበቃ ነው" ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡
ወደ ብልጽግና በምናደርገው ጉዞ ራሳችንን በመከባበር፣ በመቻቻል እና በትዕግስት መልህቅ ካጠነከርን እነዚህኑ ፍሬዎች እናጭዳለን ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፡፡
ምንጭ፡- የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

#መከላከያሰራዊት
"የመተዳደሪያ ህገ ደንቡ መሻሻል የሰራዊቱን #ኑሮ በመለወጥ ተቋሙ ጠንካራ ሆኖ እንዲቀጥል ይረዳዋል!" - ምክትል ኢታማዦር ሹም ጀነራል ብርሀኑ ጁላ
.
.
የኢፌደሪ መከላከያ ሰራዊት ምክትል ኢታማዦር ሹም ጀነራል ብርሀኑ ጁላ በቅርቡ የፀደቀውን የመከላከያ ሰራዊት መተዳደሪያ ደንብ በመተግበር የሰራዊቱን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ተናገሩ፡፡
ምክትል ኢታማዦር ሹም ጀነራል ብርሃኑ ይህን ያሉት በተሻሻለው የመከላከያ ሰራዊት መተዳደሪያ ደንብ እንዲሁም በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ለሰራዊቱ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ማጠናቀቂያ መርሀ ግብር ላይ ተገኝተው ነው፡፡
ጀነራል ብርሀኑ በዚሁ ወቅት የሰራዊቱ መተዳደሪያ ደንብ መሻሻል ከነባራዊና ወቅታዊ ሁኔታ ጋር የሚራመድ ገለልተኛ መከላከያ ሰራዊት ለመገንባት ታስቦ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በሌላ በኩል የመተዳደሪያ ህገ ደንቡ መሻሻል የሰራዊቱን ኑሮ በመለወጥ ተቋሙ ጠንካራ ሆኖ እንዲቀጥል እንደሚረዳውም ምክትል ኢታማዦር ሹም ጀነራል ብርሀኑ ጁላ ተናግረዋል፡፡
መከላከያ ሰራዊቱ ገለልተኛ እና ስራዎቹን እውቀትን መሰረት በማድረግ የሚሰራ የመከላከያ ሰራዊት መለዮውን እየቀየረ ነው ያሉት ጀነራል ብርሀኑ ከዚህ በኋላ የመከላከያ መለዮ ከተቋሙ አባል ውጪ ሊለበስ እንደማይችል እና በምንም ምክንያት ወደ ውጪ እንደማይወጣ ተናግረዋል፡፡
(የመከላከያ ሚኒስቴር የኢንፎርሜሽን ዳይሬክተር )
@tsegabwolde @tikvahethiopia

በተሽከርካሪ አደጋ የ11 ሰዎች ሕይወት አለፈ!
በኢሉአባቦር ዞን አልጌ ሳቺ ወረዳ በደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ የ 11 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ። የወረዳ ፖሊስ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ተወካይ ዋና ሳጅን ጃፈር ታየ እንደገለፁት አደጋው የደረሰው አይሱዙ የጭነት ተሽከርካሪ ትላንት ምሽት ላይ በወረዳው “ጎቦራ” ተብሎ በሚጠራ ስፍራ ሲደርስ ድንገት በመገልበጡ ነው።
ተሽከርካሪው አደጋው የደረሰበት ገበያ የዋሉ ሰዎችን አሳፍሮ ከአልጌ ከተማ ወደ ዳሪሙ ወረዳ በመጓዝ ላይ ሳለ ነው። በአደጋው የስድስት ሰዎች ህይወት ወድያውኑ ሲያልፍ አምስት ሰዎች ሕክምና ተቋም እንደደረሱ ሕይወታቸው አልፏል።
ህይወታቸው ካለፈው ሰዎች በተጨማሪ 20 ሰዎች ከባድና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸው በመቱ “ካርል ሪፈራል ሆስፒታል” የህክምና ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑን ሳጅን ጃፈር ገልፀዋል። የመኪናው አሽከርካሪም በቁጥጥር ስር መዋሉን ተናግረዋል።
(ENA)

Dr. Amir A man
የጤና ሚኒስትር ዶ/ር አሚር አማን 18 ማዞሪያ አካባቢ የሚገኘውን ለወገን ደራሽ በጎ አድራጎት ማህበር ጎበኙ!
የጤና ሚኒስትር ዶ/ር አሚር አማን በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ኮልፌ 18 ማዞሪያ አካባቢ የሚገኘውን ለወገን ደራሽ በጎ አድራጎት ማህበርን ጎብኝተዋል፡፡
በአካባቢው እድር አባላት ከ7 ዓመታት በፊት የተመሰረተው ይህ ማህበር በአካባቢው ለሚገኙ 132 ቤተሰቦች እና 242 ህፃናት በምግብ እና የትምህርት መሳሪያ አቅርቦት እንዲሁም በክህሎት ስልጠና ድጋፍ እያደረገ ይገኛል፡፡
ከአባላት ከሚሰበስበው መዋጮ በተጨማሪ ማህበሩ በእርዳታ ባገኘው የዳቦ መጋገሪያ ዳቦ አስጋግሮ በመሸጥ ተጨማሪ ገቢ ለማግኘት እየሰራ ይገኛል፡፡
"የአካባቢያችንን ችግር ራሳችን መፍታት አለብን" በሚል ቁርጠኛ አቋም በበጎ ፈቃደኛ አባላት የተመሰረተው ይህ ተቋም ለሌሎች የእድር ማህበራት መልካም አርአያ ሊሆን እንደሚችል ዶ/ር አሚር ተናግረዋል፡፡
(ዶክተር አሚር አማን)
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot

"የመከላከያ ሰራዊት መለዮውን እየቀየረ ነው። ከዚህ በኋላ የመከላከያ መለዮ ከተቋሙ አባል ውጪ ሊለበስ አይችልም እንዲሁም በምንም ምክንያት ወደ ውጪ አይወጣም።" - የኢፌደሪ መከላከያ ሰራዊት ምክትል ኢታማዦር ሹም ጀነራል ብርሀኑ ጁላ
@tikvahethiopia @tsegabwolde
@tikvahethiopia @tsegabwolde
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአዲስ አበባ ጎዳና ላይ...
የጀርመኑ ARD TV ጋዜጠኛ ማርከስ ፕሪብ በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ ቀረፃ እያደረገ ባለበት ወቅት አንድ መኪና አጠገቡ እንደቆመ እና መኪናውን ደግሞ በምሽት እያሽከረከሩ የነበሩት ጠ/ሚር አብይ አህመድ እንደሆኑ ገልፆ ይህንን ቪድዮ የትዊተር ገፁ ላይ አስፍሯል።
(ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የጀርመኑ ARD TV ጋዜጠኛ ማርከስ ፕሪብ በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ ቀረፃ እያደረገ ባለበት ወቅት አንድ መኪና አጠገቡ እንደቆመ እና መኪናውን ደግሞ በምሽት እያሽከረከሩ የነበሩት ጠ/ሚር አብይ አህመድ እንደሆኑ ገልፆ ይህንን ቪድዮ የትዊተር ገፁ ላይ አስፍሯል።
(ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ቂሊንጦ ማረሚያ!
በቂሊንጦ ማርሚያ ቤት በታራሚዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት ስድስት ታራሚዎች ከፍተኛ ጉዳት ደርሰባቸው፡፡ ዛሬ ሕዳር 28 ቀን 2012 ዓ.ም ረፋድ ላይ በአዲስ አበባ በሚገኘው በቂሊንጦ ማረምያ ቤት በእስረኞች መካከል በተፈጠረ ግጭት በስድስት ታራሚዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው የፌደራል ማረሚያ ቤቶች ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 አስታውቋል፡፡
ጉዳት የደረሰባቸው ታራሚዎችም ወደ ፌደራል ማረሚያ ቤቶች ሆስፒታል እንደተወሰዱ የፌደራል ማረምያ ቤቶች የቀጠሮ ማረፊያ ቤት ዋና አስተዳዳሪ ኮማንደር ጫላ ጸጋ ተናግረዋል፡፡
ግጭቱ በታራሚዎች መካከል ከሆነ ፖሊስ ለምን ብዛት ያለው ጥይት ተኮሰ በሚል ለተነሳላቸው ጥያቄም ፖሊስ ጥይት የተኮሰው እስር ቤቱ ጣራ ላይ የተቀመጡትን ታራሚዎች እንዲወርዱ ለማድረግ በማሰብ ነው ብለውናል ኮማንድር ጫላ፡፡ በግጭቱ ሳብያም እስካሁን የሞተ እንድም ታራሚ አለመኖሩን ኮማንደሩ ተናግረዋል፡፡ በጊዜው የደረሰው ግጭት ወዲያውኑ እንደተቆጣጠሩት እና አሁን ላይም ማረሚያ ቤቱ መረጋጋቱን ኮማንደር ጫላ ገልፀዋል፡፡
(ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8)

"ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ዩኒቨርሲቲዎች ወንድም ወንደሙን በጠላትነት የሚያይባቸው እየሆኑ መጥተዋል። እንደ ሀገር የገጠመን ችግር ሊያሳስበንና ዘላቂ መፍትሔ ሊፈለግለት ይገባል።" አስራት አጸደወይን (ዶክተር)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ሰሚ ካለ አሁንም መፍትሄ ይፈለግ!
ዛሬም አሁንም ጥያቄ ያላቸው መፍትሄ የሚፈልጉ በርካታ ተማሪዎች አሉ፤ ያሉበት ሁኔታ የሚያሰጋቸው፣ ለመማር ምቹ ሁኔታ ያልተፈጠረላቸው፣ ከዚህ አካባቢ የመጣችሁ ክፍል እንዳትገቡ ከገባችሁ በህይወታችሁ ፍረዱ የተባሉ፣ በየጊዜው በሚለጠፉ ማስፈራሪያዎች ትምህርት መማር ያልቻሉ፣ ከማደሪያዎቻቸው በስጋት ምክንያት ወጥተው አዳራሽ የሚገኙ፤ በቤተ እምነት የተጠለሉ፣ በስጋት ምክንያት ወደቤተሰቦቻቸው የሄዱ፣ አሁንም እየሄዱ ያሉ፣ የግቢ በር የተዘጋባቸው ተማሪዎች አሉ።
የፌደራል መንግስት ችግር ያለባቸውን ዩኒቨርሲቲዎች ጠንቅቆ እንደሚያውቃቸው አንጠራጠርም አሁንም በድጋሚ የተማሪዎች ድምፅ ተሰምቶ አስቸኳይ መፍትሄ ይፈለግ እንላለን። እያየን ያለነው ምልክት እጅግ አደገኛ ለሀገር ህልውና የሚያሰጋ በመሆኑ ነገ ሳይሆን ዛሬ፤ በኃላ ሳይሆን አሁን መፍትሄ ይፈለግ። የተማሪ ቤተሰቦችና ተማሪዎች ተስፋ ወደ መቁረጥ ውስጥ እንዳይገቡ መጠንቀቅ እና አስፈላጊውን ሁሉ መፍትሄ መፈለግ ይገባል።
የሚሰማን መንግስት ካለ መፍትሄ ይፈልግ!

የኢፌዴሪ መንግስት በጅቡቲ ኮሪደር የሚሰሩ የኢትዮጵያ አሽከርካሪዎችን ደህንነት ለማስጠበቅ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ ገለጸ!
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መንግስት በጅቡቲ ኮሪደር የሚንቀሳቀሱ የኢትዮጵያ ከባድ መኪና አሽከርካሪዎችን ደህንነት ለማስጠበቅ ከመቼውም ጊዜ የበለጠ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ ጅቡቲ በሚገኘው ኤምባሲው በኩል ገልጿል፡፡
በጅቡቲ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር የሆኑት አብዱልአዚዝ መሐመድ ከከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማህበር ተወካዮች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡
በዚህም መንግስት በተለይ በኮሪደሩ የሚስተዋለውን የአሽከርካሪዎች የደህንነት ስጋት በተመለከተ ጥብቅ ቁጥጥሮችን በማድረግ ፍጹም ሰላማዊ ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩን ገልጸዋል። በተጨማሪም የጉምሩክ ፍተሻ ጣቢያ አገልግሎት የተሳለጠ እንዲሆን ተገቢው ስራ እንደሚሰራም አምባሳደሩ ተናግረዋል፡፡
በኢትዮጵያ አሽከርካሪዎችና በጅቡቲ ፖሊስ መካከል ያለው ግንኙነት አግባብነት ያለውና በስራ ላይ የተመሰረተ ይሆን ዘንድ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተቀራርቦ በመስራት አፋጣኝ ምላሽ ይሰጣልም ብለዋል፡፡
(ኢቢሲ)

#ጥያቄ
ውድ ቤተሰቦቻችን እስኪ መለስ ብለን ራሳችን እንፈትሽ ዘንድ ተከታዮቹን ጥያቄዎች ለዕለቱ አቅርበናል። እናንተም የምታውቁት አካፍሉን።
•ዴሞክራሲ ምን ማለት ነው?
•የዴሞክራሲ አስፈላጊነቶች ምን ምንድናቸው?
•የዴሞክራሲ ስርዓት መገለጫ ባህሪያቶች ምንድናቸው?
እስኪ ምላሻችሁን በ @tikvahethiopiaBot ላኩልን!
(ለ @tikvahethiopiaBot አጠቃቀም አዲስ ከሆናችሁ 👆ተጫኑትና "START" የሚለውን ተጭናችሁ መልዕክቶቻችሁን አስቀምጡ)

የሚሰማን መንግስት ካለ...
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የታየውና አሁንም እየታየ ያለው ምልክት እጅግ አደገኛ እና የሀገሪቱ ህዝብ ህልውና ከፍተኛ አደጋ ውስጥ ሊጥል ስለሚችል ሳይውል ሳያድር መንግስት መፍትሄ መፈልግ ይኖርበታል። መውሰድ ያለበትን የመፍትሄ እርምጃም ሊወስድ ይገባል። ዛሬ ላይ እየተመለከትን ያለነው ሁኔታ ከሁለት ዓመት በፊት ከነበረው የተማሪ እንቅስቃሴ ፈፅሞ የተለይ፣ ሁሉንም ዜጋ አደጋ ላይ የሚጥል ነው።
በየትኞቹ ዩኒቨርሲቲዎች ችግሮች እንዳሉና ተማሪዎች የሚያነሷቸው ጥያቄዎች ምን እንደሆኑ ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት፣ የዩኒቨርሲቲ አመራሮች የተደበቀ አይደለምና ሀገሪቱን አስተዳድራለሁ የሚለው መንግስት ነገ ለሀገር አደጋ የሚሆን ትልቅ ችግር ሳይከሰት አሁን በወጣቶች ዘንድ እየታየ ያለውን አደገኛ አዝማሚያ እልባት እንዲያገኝ ትምህርት ያቋረጡ ተማሪዎችም ትምህርት እንዲቀጥሉ ማድረግ፤ ግቢያቸውን፣ ማደሪያቸውን ጥለው በየቦታው ያሉትን እንዲሁም ለመማር ምቹ ነገር ባለመኖሩ ወደ ቤተሰቦቻቸው የሄዱትን ተማሪዎች መሰብሰብ እና መፍትሄ መፈልግ ይኖርበታል።
የተማሪ ቤተሰቦች መንግስት የህግ የበላይነት እያስከበረ ባለመሆኑ በመንግስት ላይ ያላቸው እምነት ከቀን ወደቀን እየተሸረሸር እየመጣ በመሆኑ አስቸኳይ መፍትሄ ተፈልጎ የተማሪዎች ችግር ሊፈታ ይገባል። ጥያቄ እና የደህንነት ስጋት ያለባቸውን ተማሪዎች ችግሮቻቸውን መፍታት ከምንም ነገር ይቀድማል። መስቀለኛ መንገድ ላይ የምትገኘውን ሀገራችንን እጅግ ወደከፋ ሁኔታ የሚወስዱ አደገኛ ድርጊቶችን እና አዝማሚያዎችን በወጣቶች ዘንድ እያየን፣ እየታዘብን ነውና ትኩረት እንዲሰጥ በድጋሚ እንልመናለን፣ እንማፀናለን፣ እናሳስባለን!
ቲክቫህ ቤተሰቦች!

እንኳን ደስ አለን!
ኢትዮጵያዊቷ ፍሬወይኒ መብራህቱ የሲኤንኤን (CNN) ን የዓመቱ ጀግና ሽልማት አሸነፈች፡፡ በኢትዮጵያዊያን ዘንድ እምብዛም በግልፅ ምክክር ስለማይደረግበትና እንደነውርም በሚቆጠረው የወር አበባ ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው የሚነጠሉ አዳጊዎችን መሰረት በማድረግ በሰራችው በጎ ምግባር ነው ፍሬወይኒ የዓመቱ ጀግኒት የተባለችው፡፡
ግለከሰቧ በመቐለ በገነባችው የንፅህና መጠበቂያ ቁሶች ማምረቻ እየታጠበ መልሶ ማገልገል የሚችልን የሴቶች ንፅህና መጠበቂያ በማምረት በወር አበባ ምክንያት ከትምህርታቸው የሚታጎሉትንም ሆነ የሌሎችን ሴቶች ጫና ማቃለሏ ይነገርላታል፡፡
በዚህ ሥራዋ ለሽልማቱ ያጫት ዓለም ዐቀፉ የመገናኛ ብዙኃንም ከ10 እጩዎቹ ፍሬወይኒን ቀዳሚ አድርጎ በመምረጥ ‹‹የ2019 የሲኤንኤን ጀግና›› መሆኗን ይፋ አድርጓል፡፡ በዚህም ፍሬወይኒ ለሥራዋ ማስፋፊያ የሚሆናትን የ100 ሺሕ ዶላር ተሸላሚ እንደምትሆን ተነግሯል፡፡
(AhaduRadio)

ኢትዮጵያዊቷ ፍሬወይኒ መብራሃቱ የሲ ኤን ኤን (CNN) ን የዓመቱ ጀግና ሽልማት አሸናፊ ሆናለች፡፡ #ጀግኒት #CNN

በትራፊክ አደጋ አምስት ሰዎች ሲሞቱ በ28 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት ደርሷል!
በምስራቅ ሸዋ ዞን በደረሰ የትራፊክ አደጋ በአምስት ሰዎች ላይ የሞት በ28 ሰዎች ላይ ደግሞ የአካል ጉዳት ማድረሱን የዞኑ ፖሊስ ገለጸ። የምስራቅ ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር አስቻለው አለሙ እንደገለጹት አደጋው የደረሰው አደአና አዳሚ ቱሉ ወረዳዎች ውስጥ ነው።
ትናንት ከሌሊቱ አስራ አንድ ሰአት ከሩብ አካባቢ ከሻሸመኔ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ ኮድ 3 ኦሮ 54360 ዶልፊን የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ከቢሾፍቱ ወደ አዱላላ ከተማ ሲጓዝ ከነበረ ኮድ 3ኢት 76745 ሲኖትራክ የጭነት ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ የዶልፉኑ ሹፌርን ጨምሮ የሶስት ሰዎች ሕይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ በአምስት ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን ኮማንደሩ ተናግረዋል።
በአሁኑ ወቀት የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በቢሾፍቱ አጠቃላይ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ነው ተብሏል። በተመሳሳይ መልኩ አዳሚ ቱሉ ወረዳ ልዩ ቦታው ጋራወርጂ በተባለው አካባቢ ትናንት ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ላይ 25 ሰዎችን አሳፍሮ ከሻሸመኔ ወደ ባቱ ሲጓዝ የነበረ ኮድ 3 ደቡብ 09326 ዶልፊን ተሽከርካሪ ተገልብጦ ሁለት ሰዎች ወዲያውኑ ሲሞቱ በ23 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን ኮማንደር አስቻለው ገልፀዋል።
ተጎጂዎቹ በኩየራ ሆስፒታል የህክምና ርዳታ እየተደረገላቸው እንደሆነም ጠቅሰዋል። ዶልፊኑ 15 ሰው መጫን ሲገባው 10 ሰዎችን በትርፍነት መጫኑ ለአደጋው እንዳጋለጠው የተናገሩት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው የሁለቱም አደጋዎች መንስዔ ግን በፍጥነት ማሽከርካርና የጥንቃቄ ጉድለት ነው ብለዋል።

በኢትዮጵያ በአሁኑ ሰአት ከመንግስት ይልቅ ቡድኖችና ግለሰቦች አስፈሪ መሆናቸውን የሰብዓዊ መብት ማዕከል አስታወቀ!
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሰብአዊ መብት ማእከል ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ቀንን በአዲስ አበባ እያከበረ ነው። በበዓሉ ላይ የህግ ምሁራን፣የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ተቋማት፣የመንግስት ተቋማት መሪዎችና የተለያዩ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል።
ወጣቶች ሰብአዊ መብትን ለማስከበር ያላቸው ተስፋ እና እንቅፋቶች እንዲሁም ታችኛው የአስተዳደር አካላት ሰብአዊ መብቶች ላይ ያላቸው ሚና በሚሉ ርእሶች ፁሁፎች ቀርበው ውይይት እየተደረገባቸው ነው። ወጣቶች በሚደረግባቸው መገለል እና የስራ አጥነት ችግሮች ምክንያት በሃገራቸው ጉዳይ ተሳታፊ ከመሆን ይልቅ የተለያዩ ቡድኖች መጠቀሚያ ሆነዋል ተብልዋል።
በሌላ በኩል ታችኛው የአስተዳደር አካላትም ሰብአዊ መብትን በመጣስ ተተችተዋል። ለውጥ የመጣው በፌዴራል ደረጃ እንጂ አሁንም ወደ ታችኛው የአስተዳደር መዋቅር አልደረሰም ተብሏል። በተለይም መደበኛ ባልሆኑ አደረጃጀቶች ለሚፈፀሙ ጥሰቶች እነዚሁ የመንግስት አካላት ሽፋን በመስጠት ላይ መሆናቸው በበዓሉ ላይ ተገልጿል።
(ETHIO FM 107.8)

-ወጣቶች ደም ሲቃቡ፣ አንዱ በአንዱ ላይ ሲነሳ፣ የተማሪ ህይወት እንደዋዛ ሲያልፍ፣ ተማሪ በሰቀቀን ሲሰቃይ፣ ተማሪዎች ከግቢ እንዳይወጡ ተቆልፎባቸው ሲቀመጡ መንግስት ምን እየሰራ ነው? የሚለው የሁሉም ተማሪ እና ቤተሰብ ያላቋረጠ ጥያቄ ነው። ዛሬ በአንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች የተመለክታናቸው ምልክቶች ውለው አድረው ሀገር ሊያሳጡ ይችላሉ።
በርካታ ተማሪዎች መንግስት ደህንነታችንን ማስጠበቅ ካቃተው በአስቸኳይ ወደ መጣንበት ይመልሰን ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላኩት የፅሁፍ መልዕክት ጠይቀዋል። እኛ ደክመን፣ ለፍተን እዚህ የበቃነው ለመሞት፣ ለመንገላታት፣ ለመሰቃየት አይደለም፤ ከምንም ነገር በፊት ህይወታችን ስለሚቀድም መንግስት በአስቸኳይ መፍትሄ ይፈልግልን ብለዋል።
ወንድም በወንድሙ ላይ ሲጨክን እየተመለከትን በምን በኩል ነው በተረጋጋ መንፈስ ትምህርት የምንማረው፤ አሁንም ችግሮች ያልረገቡበት ዩኒቨርሲቲዎች እንዳሉ እየታወቀ ዘላቂ መፍትሄ ባለመሰጠቱ ነገሮች እየባሱ እየሄዱ ነውና መንግስት ከምንም በፊት የተማሪውን ደህንነት ማስጠበቅ አለበት ሲሉ ገልፀዋል።
ዛሬ አንድ ሁለት እየተባለ የተጀመረው ድርጊት ሀገሪትን ሊበታትን ምናልባትም ወደለየለት እልቂት ሊከት የሚችል በመሆኑ ሁሉም የሀገሪቱ ዜጎ ቆም ብሎ ማሰብ አለበት፤ ከስሜታዊነት እና የኔ ብቻ ብሎ ከማሰብ መውጣት አለበት ብለዋል ተማሪዎቹ።
የአንዱ ሞት፣ ስቃይ፣ በደል፣ እንግልት፣ መከራ ሁሉም ሰው በእኩል ካላሳዘነ እና ሁሉም የሀገሪቱ ዜጋ እንደራሱ ካልቆጠረ ሀገሪቱ ትልቅ አደጋ ላይ ትወድቃለች ምናልባትም የትምህርት ስርዓቱ ዳግም እንዳያንሰራራ ሆኖ ይወድቃል ሲሉ አሳስበዋል። የሚታዩትን አደገኛ ምልክቶች መንግስትም ሆነ ህዝብ በቸልታ መመልከት የለበትም፤ ነገ ችግር ተባብሶ ከመላቀስ ዛሬ መጠንቀቅ ያስፈልጋል ሲሉ መክረዋል።
@tikvahethiopia

"ዩኒቨርስቲዎች በፌደራል ፖሊስ ሊጠበቁ ነው" - የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር!
በመላው ሀገሪቱ ውስጥ የሚገኙ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በፌደራል ፖሊስ እንዲጠበቁ መወሰኑን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ለቢቢሲ ገልጿል።
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የኮሙኑኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ደቻሳ ጉርሙ ለቢቢሲ የአማርኛው ክፍል እንደተናገሩት ዩኒቨርስቲዎች ወደ ሰላማዊ የመማር ማስተማር መመለስ የሚቻለው ጥበቃዎቹን ማጠናከር ሲቻል መሆኑ በመታመኑና ተቋማቱ የፌደራል ተቋማት በመሆናቸው በፌደራል ፖሊስ እንዲጠበቁ መወሰኑን ተናግረዋል።
አቶ ደቻሳ አክለውም "ከተማሪዎች ጋር በተደጋጋሚ በተደረገ ውይይት የቀረበው ቅሬታ የግቢው የጥበቃ አካላት ላይ መሆኑን በማንሳት በተጨማሪም ተማሪዎች የፌደራል ፖሊስ በገለልተኝነት እያገለገሉን ነው" በማለታቸው እዚህ ውሳኔ ላይ መደረሱን አብራርተዋል።
More👇
https://telegra.ph/BBC-12-09
(BBC)

አሳሳቢው የዩኒቨርሲቲዎች ጉዳይ...
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎችን በፌደራል ፖሊስ ሊያስጠብቅ እንደሆነ ሰምታችኃል።
ከሳምንታት በፊት በአንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች የጀመረው አለመረጋጋት አሁንም ድረስ ሙሉ በሙሉ ያልረገበበት፣ መደበኛው የትምህርት ስርዓትም የተቋረጠበት እንዳለ እየተመለከትን ነው። ቁጥራቸው ቀላል ያልሆኑ ተማሪዎችም ትምህርታችን ከህይወታችን አይበልጥም በማለት ወደቤተሰቦቻቸው እንዳሉ ሁሉም የሚያውቀው ሃቅ ነው።
ማስፈራሪያዎች፣ ተማሪን ማጥቃት፣ እከሌ መማር አትችልም ሂድ ከዚህ ማለት፣ ብዙ ብዙ አደገኛ ምልክቶችን እየታዘብን ነው። ለመሆኑ አሁን ባለው ሁኔታ ዩኒቨርሲቲዎችን በፌደራል ፖሊስ ብቻ ማስጠበቅ ሰላም ሊያመጣ፣ ተማሪዎችን ያለስጋት እንዲማሩ ያደርጋል?
ውድ ቤተሰቦቻችን እየታዩ ያሉት ምልክቶች እጅግ አደገኛ፤ ለሀገር ህልውና የሚያሰጉ ናቸው። ይህን ጉዳይ ሁሉም ያገባኛል የሚል አካል ቀጠሮ ሳይሰጥ፣ ነገ ሳይሆን ዛሬ ለመፍታት ካልተሰራ ሁኔታዎች ወደ ከፋ ደረጃ ሊደርሱ እንደሚችሉ ስጋታችንን እየገለፅን ነው። ከዚህ ቀደም ደግመን ደጋግመን እናተም እስኪሰለቻችሁ ድረስ ለመንግስት መልዕክት ስናስተላልፍ ነበር፤ አሁንም ይህን ከማድረግ ወደኃላ አላልንም።
•እናተስ የመፍትሄ ሃሳብ የምትሉትን አጋሩ?
•ምን ቢደረግ መፍትሄ ይገኛል ብላችሁ ታስባላችሁ?
•በፀጥታ ኃይል ብቻ ዘላቂ ሰላም ማምጣት ይቻላል?
ሀሳባችሁን አጋሩ @tikvahethiopiaBot

በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በፌደራል ፖሊስ እንዲጠበቁ ተወሰ!
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚታዩ ዩኒቨርሲቲዎችን የግጭት ማዕከል ለማድረግ እየተደረገ ያለውን እንቅስቃሴና እየደረሱ ያሉ ጉዳቶችን ምክንያት በማድረግ መንግስት ዛሬ ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት ሁሉም ዩኒቨርሲቲ ከዚህ በኋላ በፌዴራል ፖሊስ እንዲጠበቅ ተብሏል፡፡ ከዚህም አልፎ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚደረግ እንቅስቃሴዎች በደህንነት ካሜራዎችና በር ላይ በሚደረገው ጥብቅ ቁጥጥርና ፍተሸ እንዲታጀብ ይደረጋል፡፡ በተከሰቱ ጥፋቶች እጃቸው ያለበት አካለትን ለህግ የማቅረብ ስራም ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል መንግስት ገልጿል፡፡
(EPRDF)