TIKVAH-ETHIOPIA
ከሀሰተኛ ገፆች ተጠንቀቁ!! 29,000 like ያለው ይህ በEritrean Press ስም መረጃዎችን የሚያሰራጭ ገፅ ሃሰተኛ ነው!! @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FakeNewsAlert
ከቀናት በፊት 29,000 ገደማ Like ያለው በ "Eritrean Press" ስም የተከፈተው የፌስቡክ ገፅ ሀሰተኛ ዜናዎችን እያሰራጨ እንደሚገኝ ገልፀንላችሁ ነበር። ይኸው ገፅ በዛሬው ዕለት "ኢዜማ እና ብልፅግና ፓርቲ" ለመዋሃድ ንግግር ጀምረዋል የሚል ሃሰተኛ ዜና ይዞ ወጥቷል። ትክክለኛው Eritrean Press የፌስቡክ ገፅ ከ250,000 በላይ Like ያለው ነው። ውድ ቤተሰቦቻችን ከሀሰተኛ መረጃዎች እንድትጠነቀቁ እንመክራለን።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

በተመሳሳይ ... Mereja. com የተባለው የፌስቡክ ገፅ ከ3,000,000 በላይ ተከታዮች አሉት ተመሳሳይ ሀሰተኛ መረጃ ለህዝብ አሰራጭቷል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
በየአመቱ 23 ሺህ ሰዎች በኤች አይ ቪ ቫይረስ ይያዛሉ!
በየአመቱ 23 ሺህ ሰዎች በኤች አይቪ ቫይረስ ይያዛሉ” ሲል የኢፌዴሪ የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
የኢፌዴሪ የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ጽህፈት ቤት በሽታውን ለመቆጣጠርና ለመከላከል እየሰራ ያለው ስራ መቀዛቀዝ በማሳየቱ በሽታውን የመቆጣጠሩ ስራ አዝጋሚ እንደሆነ ገልጿል።
በኢትዮጵያ የኤች አይ ቪ የስርጭት ምጣኔ 0 ነጥብ 91 በመቶ ሲሆን ከ649 ሺህ በላይ የሚሆኑ ወገኖች ቫይረሱ በደማቸው እንደሚገኝ የ2019 አገራዊ የኤች አይ ቪ ስርጭት ያሳያል።
(ENA)

(ERDF Official)
የተሳሳተ መረጀ!
የብልጽግና ፓርቲ ከኢዜማ ጋር መደራደር ጀምሯል፤ በሚል በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ እየተሰራጨ ያለው መረጀ የተሳሳተ ነው፡፡ አዲሱ ውህድ ፓርቲ፤ ፕሮግራሙን ይፋ ከደረገ በኋላ ተመሳሳይ አቋም ካላቸው ማናቸውም የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር አብሮ ለመስረት ዝግጁ መሆኑ ተገልጸዋል፡፡ ሆኖም እስከሁን ከየትኛውም ፖለቲካ ፓርቲ ጋር ንግግርና ድርድር አለመጀመሩን መግለጽ እንወዳለን፡፡
(EPRDF Official)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የተሳሳተ መረጀ!
የብልጽግና ፓርቲ ከኢዜማ ጋር መደራደር ጀምሯል፤ በሚል በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ እየተሰራጨ ያለው መረጀ የተሳሳተ ነው፡፡ አዲሱ ውህድ ፓርቲ፤ ፕሮግራሙን ይፋ ከደረገ በኋላ ተመሳሳይ አቋም ካላቸው ማናቸውም የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር አብሮ ለመስረት ዝግጁ መሆኑ ተገልጸዋል፡፡ ሆኖም እስከሁን ከየትኛውም ፖለቲካ ፓርቲ ጋር ንግግርና ድርድር አለመጀመሩን መግለጽ እንወዳለን፡፡
(EPRDF Official)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አቶ ለማ መገርሳ🛬አሜሪካ ገቡ!
በኢፌዴሪ መከላከያ ሚንስትር አቶ ለማ መገርሳ የተመራ ከፍተኛ የመንግስት ልዑክ በአሜሪካ ጉብኝት በማድረግ ላይ ይገኛል።
በመከላከያ ሚኒስትሩ የተመራው ልኡኩ በዛሬው እለት ዋሽንግተን ዲ.ሲ መግባቱን በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍጹም አረጋ አስታውቀዋል።
ጉብኝቱም የኢትዮጵያ እና የአሜሪካን የሁለትዮሽ የመከላከያ ትብብር ለማጠናከር ያለመ መሆኑን አምባሳደር ፍጹም ገልፀዋል።
(አምባሳደር ፍፁም አረጋ - FBC)

#ህዳር29
በትግራይ ክልል የብሄሮች፣ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል በድምቀት ለማክበር ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ገለጹ። አፈ ጉባኤው አቶ ሩፋኤል ሽፈረ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ “በዓሉ በክልሉ ህገ መንግሰታዊ ስርዓታችን ለዘላቂ ሰላምና ጥቅም በሚል መሪ ሀሳብ ህዳር 29 ይከበራል” ብለዋል፡፡ በዓሉ የሚከበረው በክልሉ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ልማት ስራዎች በሚያሳይና በስፖርታዊ ውድድር ነው።

#GERD
በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌትና አለቃቀቅ ጉዳይ ላይ የሚመክረው የኢትዮጵያ፣ የሱዳንና የግብፅ የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች የቴክኒክ ስብሰባ ዛሬ ህዳር 22 ቀን 2012 ዓ.ም. በካይሮ መካሄድ ተጀምሯል።

Audio
#JawarMohammed #DW
የኦሮሞ ፖለቲካ አቀንቃኝ ጀዋር መሐመድ በቅርቡ በሚደረገው ምርጫ እንደ ፖለቲከኛ እንዴት እንደሚወዳደር እስካሁን እንዳልወሰነ አስታወቀ። አቶ ጀዋር ለዶቼ ቨለ በሰጠው ቃለ ምልልስ የራሱን ፓርቲ መስርቶ ወይም ከሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ተጣምሮ መወዳደርን በተመለከተ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች እና ከገዥ ፓርቲ አመራሮች ጋር ተወያይቶ እንደሚወስን ተናግሯል። የኢህአዴግ አባል ድርጅቶችን ውህደትንም የፌደራል ስርዓቱን የሚሸረሽር ሲል ተችቷል።
@tikvahethiopiaBot
@tikvahethiopia

እምቦጭ ከጣና አልፎ ዓባይን እየወረረ ነው!
(የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት)
.
.
.
በዚህ ዓመት እምቦጭ ከጣና አልፎ አባይ ወንዝ ዳርቻዎች በሚገኝ 200 ሄክታር መሬት ላይ ተንሠራፍቷል። ባለፈው ዓመት በ34 ሄክታር መሬት ላይ የተከሰተው የአባይ እምቦጭ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ 166 ሄክታር ጨምሮ ወደ 200 ሄክታር መስፋፋቱ የአደጋውን አሳሳቢነት ቁልጭ አድርጐ የሚያሳይ ነው።
ይሁንና ሀገሪቱን በበላይነት የሚያስተዳድረው የፌዴራል መንግስት፣ ጣና በለስን ጨምሮ በጢስ አባይ ቁጥር አንድ እና ቁጥር ሁለት የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫዎች ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ሀይል የሚሰበስበው የኢትዮጵያ ውሀ፣ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር እና “ህይወታችን የተመሠረተው በአባይ ወንዝ ላይ ነው” የሚሉት ግብጽ እና ሱዳን ሀይቁን ለመታደግ ምንም አይነት ጥረት አለማድረጋቸው እንቆቅልሽ እንደሆነባቸው የባህር ዳርና አካባቢዋ ነዋሪዎች ይናገራሉ።
እንደ ነዋሪዎቹ ገለፃ እምቦጭ ከተከሰተበት ዓመት ጀምሮ በመከላከል ተግባር ደፋ ቀና የሚሉት የሰሜንና ደቡብ ጐንደር አርሶ አደሮች፣ የክልሉ መንግስት፣ የአካባቢው ተቆርቋሪ ግለሰቦችና ሀገር ወዳድ የበጐ አድራጐት ማህበራት ብቻ ናቸው።
(የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት)
More👇
https://telegra.ph/AMMA-12-02
#ሼር_ያድርጉት!
@tikvahethiopia @tikvahethiopia

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"ስብሰባውን ጥለን ወጥተናል!" - የካፋ ተወካዮች
በትላንትናው ዕለት ነው አዲስ አበባ የገባነው፤ ውይይቱ ዛሬ ሁለት ሰዓት ላይ ነበረ፤ ዛሬ እኛ ጠቅላይ ሚኒስትሩን አላገኘንም። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እኔን ወክለውኛልና እኔ ነኝ የማወራችሁ ብለው ክብርት የሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪያት እና የደቡብ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ርስቱ ይርዳው ሊያወያዩን የሰላም ሚኒስቴር ቢሮ ቀጠሩን፤ ትላንት ማታ ነው የተነገረን፤ እኛ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር እንጂ ከናተ ጋር ውይይት አልነበረንም በሚል በጣም ትልቅ ነገር እንደገጠመን እርስ በእርሳችን ተነጋገርንና የግድ እሳቸው ሊመጡ ይችላሉ በሚል ተስፋ 3:00 ላይ የሰላም ሚኒስቴር ቢሮ ሄድን።
ጥቂት ደቂቃ እንደ ጠበቅን ጠቅላይ ሚኒስትሩን አላገኘናቸውም የጠበቅናቸው እሳቸውን ስለነበር፤...ከዚህ ቀደም የካፋን ማህበረሰብ አነጋግራለሁ፤ እጠራችኃለሁ ያለን ጠቅላይ ሚንስትሩ ነው፤ ያን ተከትሎ መጥተናል፤ እርሳቸውን አላገኘናቸውም ውይይታችንም፤ አጀንዳችንም ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ስለነበር ከእናተ ጋር ምንም አይነት ወሬ የምናወራው የለንም። በክልል ጉዳይ ነው፤ አስቸኳይ ጉዳይ ነው፤ ይህ ጉዳይ ከአንድ አመት በላይ ሆኖታል እና እኛ የምንከሰው ደኢህዴንን ነው፤ የደኢህዴን ሊቀመንበር ነዎት እርሶ ሲቀጥል ደግሞ የደቡብ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳደር ነዎት አቶ ርስቱ ከናተ ጋር ምናወራው ምንም አይነት ወሬ የለም አልናቸው። በዚህም ስብሰባውን ጥለን ወጥተናል!
የካፋ ተወካዮች!
(BBC)

በኩሉ ኢቨንት ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር - “መማሬ ለሀገሬ ሠላም” በሚል መሪ ቃል የ4 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫ በትላንትናው ዕለት ተካሂዷል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#ኡቡንቱ #አርባምንጭ
ቲክቫህ ኢትዮጵየ ከፒስ ሞዴል እና ከጋሞ ዞን አስተዳደር ጋር በመተባበር "ኡቡንቱ" በሚል ርዕስ ያዘጋጀው የአንድ ሳምንት የግንዛቤ ማስጨበጫ ከዛሬ ጀምሮ መካሄድ ይጀምራል። በተለያዩ ትምህርት ተቋማት ውስጥ ከጋሞ አባቶች እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን አብሮ ስለመኖር፣ ስለመከባበር፣ የአንዱ ለአንዱ የመኖር ዋስትና ስለመሆኑ የተለያዩ መልዕክቶች ይተላለፋሉ።

የውጫሌ ግሸን ማርያም መንገድ...
በደቡብ ወሎ ዞን አምባሰል ወረዳ ከ227 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ የተሰራው የውጫሌ ግሸን ማሪያም መንገድ ተጠናቅቆ ተመርቋል። መንገዱን መርቀው የከፈቱት የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር የመንገዱ መዳረሻ በሆነችው ግሼን ማርያም አካባቢ የሚስተዋሉ የመሰረተ ልማት ችግሮችን በቅደም ተከተል ለመፍታት እንደሚሰራ ተናግረዋል።

ከግሸን መገንጠያ - ግሸን ማርያም...
ግሸን መገንጠያ እስከ ግሸን ማርያም ድረስ ያለው መንገድ በኮንክሪት አስፓልት በዚህ ዓመት እንደሚሰራ ተገለፀ። ይህ የተባለው ህዳር 21 ቀን 2012 ዓ.ም የጨፌ-ግሸን ማርያም መንገድ በተመረቀበት ወቅት ነው፡፡ በዕለቱም የአማራ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህን ጨምሮ ሌሎች የፌዴራል፤የክልልና የዞን ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
የአካባቢው ነዋሪዎች እና የቤተክርስቲያኗ ካህናት አካባቢው ግማደ መስቀሉ ያረፈበት ታሪካዊ ቦታና ሙዚየም ያለው የቱሪስ መዳረሻ በመሆኑና በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ምዕመናንን የሚያስተናግድ በመሆኑ መንገዱ እንዲሻሻል በተደጋጋሚ መጠየቃቸውን ለእንገዶቹ ገልፀዋል፡፡ በእለቱ የተገኙት የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳሬክተር ኢንጅነር ሀብታሙ ተገኝ ባደረጉት ንግግርም መንገዱ በዚህ ዓመት እንደሚጀመር አረጋግጠዋል፡፡
(የደቡብ ወሎ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን)

አቶ ለማ በVIP ተርሚናል ነው የተስተናገዱት!
(Elias Meseret)
KMN በተባለ የፌስቡክ ገፅ "የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ለማ መገርሳ እና የቦሌው አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ድራማ" ብሎ የወጣው መረጃ የፈጠራ ወሬ እንደሆነ ከኤርፖርት አካባቢ ያገኘሁት መረጃ ያመለክታል ሲል የAssociated Press ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ገልጿል።
ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ዛሬ ጠዋት አገኘሁት ባለው መረጃ መሰረት አቶ ለማ በVIP ተርሚናል የተስተናገዱ ሲሆን "እንደ ክቡር ሚኒስተርነታቸው እና ለሁሉም ሚኒስትሮች እንደሚደረገው በስነስርአት ተስተናግደዋል። ከዛ ውጪ ያለው የፈጠራ ወሬ ነው።" ተብሏል።

የተዘነጋው የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ጉዳይ!
በኢትዮጵያ ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ (HIV/AIDS) መቀነስ ባለበት ደረጃ እየቀነሰ አለመሆኑን ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡ ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ (HIV/AIDS) ስርጭት ከ1 በመቶ በላይ ከሆነ በወረርሽኝ መልኩ የሚገለጽ መሆኑን የፌደራል ኤች አይቪ መከላከልና መቆጣጠሪያ ጽሕፈት ቤት ይገልጻል፡፡ በዚህም መሰረት ስርጭቱ ወረርሽኝ መልክ ያልተከሰተባቸው የሶማሌ፣ የኦሮሚያና የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልሎች ብቻ ናቸው፡፡ ቀደም ብሎ በመጣው ውጤት መርካት፣ በበሽታው የመሞት እና የአልጋ ቁራኛነት መቀነስ፣ በየእርከኑ ያሉ የአመራር አካላት ትኩረት መላላት፣ የበጀት ዕጥረት እንዲሁም በመንግስት የመዋቅር ማስተካከያዎች በቂ ትኩረት ማጣት ኤች.አይ.ቪ ኤድስ ቫይረስ ስርጭት መጨመር በምክንያትነት ይጠቀሳሉ፡፡
(OBN)

ትኩረት...
አሁንም ቢሆን በአንዳንድ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚበተኑት የማስፈራሪያ ወረቀቶች ቀጥለዋል፡፡ ይህ ጉዳይ ተማሪውን ሰላም ከሚነሱ ጉዳዮች ዋነኛውና አንዱ ቢሆንም እነዚህን ወረቀቶች በሚያዘጋጁና በተደራጀ መልኩ በመማሪያ ክፍል በመኝታ አከባቢ እየተንቀሳቀሱ ማስፈራሪያ የሚያደርጉ አካላት ላይ ትኩረት ያለመደረጉ የታሰበውን ሰላማዊ የመማር ማስተማር ስራ እንዳይጀመር ያደርገዋል። በአንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ከዚህ አካባቢ የመጣችሁ አትማሩም፣ ከዚህ ሂዱልን የሚሉ ለሀገር አደጋ የሆነ ድርጊት እየተፈፀመ ይገኛል። ይህ ጉዳይ ከወዲሁ ትኩረት ካልተሰጠው ለዩኒቨርሲቲዎች ብቻ ሳይሆን ለሀገር አደጋ ነው። ተማሪዎች የሀገሪቱ ሚዲያዎች እያቀረቡት ያሉት ዘገባ እውነታውን የደበቀ እንደሆነ ገልፀዋል። ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች የሚላኩትን የስጋት መልዕክቶች እንዲሁም ጥቆማዎች እና ችግሮች ለሚመለከታቸው አካላት ለማድረስ ጥረት እያደረግን እንገኛለን።

በቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ የተገነባዉ የኢፈ ቱላ ሱሮ ብርሀን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታዉ ተጠናቆ ትምህርት እየሰጠ ነው!
በቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸዉ በምእራብ ጉጂ ሱሮ ባርጉዳ የተገነባዉ የኢፈ ቱላ ሱሮ ብርሀን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታዉ ተጠናቆ ትምህርት እየሰጠ እንደሚገኝ የቀዳማዊት እመቤት ፅ/ቤት አስታወቀ፡፡ ፅ/ቤቱ በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች ትምህርት ቤቶችን እያስገነባ መሆኑ ይታወቃል፡፡
(EPA)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸዉ በምእራብ ጉጂ ሱሮ ባርጉዳ የተገነባዉ የኢፈ ቱላ ሱሮ ብርሀን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታዉ ተጠናቆ ትምህርት እየሰጠ እንደሚገኝ የቀዳማዊት እመቤት ፅ/ቤት አስታወቀ፡፡ ፅ/ቤቱ በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች ትምህርት ቤቶችን እያስገነባ መሆኑ ይታወቃል፡፡
(EPA)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ብልፅግናፓርቲ #NEBE
"ብልፅግና ፓርቲ በምርጫ እስካላሸነፈ ድረስ ቀሪውን የስልጣን ዘመን መቆጣጠር አይችልም!" - አቶ ዘራይ ወልደሰንበት (የህግ ባለሞያ)
.
.
"የተለያዩ ሰዎች የፖለቲካ ፓርቲ ሲመሰርቱም ሆነ ስማቸውን ሲቀይሩ እኛ አስተያየት አንሰጥም። ይህም ጉዳይ ከዚህ የተለየ አይደለም። እኛን በቀጥታ የሚመለከተን ምዝገባ ነው። የብልፅግና ፓርቲ ለቦርዱ የምዝገባ ጥያቄ እስካሁን አላቀረበም። ጥያቄውን ካቀረቡ ልክ እንደማንኛውም አሰራር አይተን እንመዘግባለን። ለብልፅግና ፓርቲ ብቻ ሳይሆን ከዚህ በፊት የነበሩ ፓርቲዎች ስማቸውን ሲቀይሩ፣ ሲዋሃዱ ወይም ተለያየን ሲሉ እኛ ጋር በተለያየ መልኩ የመጣ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ምንም አይነት ምላሽም ሆነ አስተያየት አንሠጥም!" - ወ/ሪት ሶሊያና ሽመልስ (በብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር)
(ቢቢሲ)

ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ የመቀዶኒያ የአረጋውያንና የአእምሮ ህሙማን መርጃ መስራችን አነጋገሩ!
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ፕሬዝደንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የመቀዶኒያ የአረጋውያንና የአእምሮ ህሙማን መርጃ መስራችን አቶ ብንያም በለጠን እና የስራ ባልደረቦቻቸውን በብሔራዊ ቤተ መንግስት አነጋግረዋል። ፕሬዘዳንት ሳህለወርቅ የተሰራውን ስራ አድንቀው የመቀዶኒያ ስራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሚቻለውን በማድረግ እንደሚደግፉ በመግለፅ የማበረታቻ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ምንጭ፡- የፕሬዚዳንት ፅ/ቤት