TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ህዳር29

በትግራይ ክልል የብሄሮች፣ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል በድምቀት ለማክበር ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ገለጹ። አፈ ጉባኤው አቶ ሩፋኤል ሽፈረ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ  “በዓሉ በክልሉ ህገ መንግሰታዊ ስርዓታችን ለዘላቂ ሰላምና ጥቅም በሚል መሪ ሀሳብ ህዳር 29 ይከበራል” ብለዋል፡፡ በዓሉ የሚከበረው  በክልሉ  ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ  ልማት ስራዎች በሚያሳይና በስፖርታዊ ውድድር ነው።

(ENA)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ህዳር29

ለ14ኛ ጊዜ በአዲስ አበባ ከተማ የሚከበረው የኢትዮጰያ ብሔር ፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በሰላም እንዲከበር የፀጥታ አካለት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቀው ወደ ስራ መግባታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

“ህገ-መንግስታዊ ቃል ኪዳናችን ለዘላቂ ሰላም” በሚል መሪ ቃል ህዳር 29 ቀን 2012 ዓ/ም በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አዘጋጅነት 14ኛው የኢትዮጰያ ብሔር ፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በአዲስ አበባ ስታዲየም በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ይከበራል፡፡

በበዓሉ ላይ ለመታደም እንግዶች ወደ አዲስ አበባ እየገቡ መሆኑን ኮሚሽኑ ጠቁሞ በብሔራዊ ደረጃ በሚከበረውና በርካታ ህዝብ የሚታደምበት በዓል በሰላም እንዲከበር ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ፣ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ፣ የኦሮሚያና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽኖች እንዲሁም ሌሎች ተቋማትን ያካተተ የፀጥታ ኮማንድ ፖስት ተዋቅሮ ስራ መጀመሩን ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡

More👇
https://telegra.ph/ETH-12-07

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ህዳር29

ዘንድሮ ለ14ኛ ጊዜ በኦሮሚያ ክልል አዘጋጅነት ለሚከበረው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በድምቀትና በሰላም መጠናቀቅ የቡራዩ ከተማ ድርሻ ወስዶ እየሠራ መሆኑ ተገለጸ። እንግዶችን ተቀብሎ ከማስተናገድ ጀምሮ እስከበዓሉ ፍጻሜ የሚያግዙ ከ100 በላይ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች በከተማ አስተዳደሩ መዘጋጀታቸውም ተጠቁሟል።

(EPA)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia