TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከሀሰተኛ ገፆች ተጠንቀቁ!!

29,000 like ያለው ይህ በEritrean Press ስም መረጃዎችን የሚያሰራጭ ገፅ ሃሰተኛ ነው!!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"እንዲህ አዝኜ አላውቅም" - አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ

ሱሌይማን ደደፎ በተባብሩት ዓረብ ኢሚሬቶች ባለ ሙሉ ሥልጣን አምባሳደር፤ የመከላከያ ሚኒስትር ለማ መገርሳ "በመደመር ፍልስፍና አልስማማም፤ የኢሕአዴግንም ውሕደት አላምንበትም" ማለታቸውን አሳዝኝ እንደሆነ አስታወቁ።

አቶ ለማ ለቪኦኤ ኦሮምኛ ቋንቋ ዝግጅት ክፍል በሰጡት ቃለ ምልልስ "ከመጀመሪያው ጀምሮ የፓርቲዎችን መዋሃድ በተመለከተ የማላምንበት መሆኑን ለሥራ አስፈጻሚውና ለሁሉም በስፋት ገልጫለሁ። መዋሃዱ ትክክል አይደለም፤ ከሆነም በችኮላ መሆን የለበትም። ወቅቱ አይደለም" ብለዋል።

አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎም በበኩላቸው አቶ ለማ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ ጋር ያላቸውን ልዩነቶች እንደሰሙበት ወቅት አዝነው አንደማያውቁ በቲዊተርና ፌስቡክ ገጾቻቸው ላይ አኑረዋል።

#SBS

@tikvahethiopia @tsegabwolde
የብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ሃላፊዎች በፓርቲው ወቅታዊ ሁኔታ እና የስራ ዕቅድ ዙሪያ እየተወያዩ ነው!

የብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅህፈት ቤት እና የክልል ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ሃላፊዎች በዛሬው እለት በፓርቲው ዋና ፅህፈት ቤት በወቅታዊ የፓርቲው ሁኔታ ላይ እየመከሩ ይገኛሉ። ሃላፊዎቹ ፓርቲው በመጪው ጊዜያት በሚፈፅማቸው አበይት ተግባራት ዙሪያም ውይይት ያደርጋሉ።

በኢህአዴግ አባል እና አጋር ድርጅቶች ውህደት በተፈጠረው ብልፅግና ፓርቲ የመጀመሪያ ስብሰባ ላይ ሁሉም ህብረ ብሄራዊ ውህድ ፓርቲውን የተቀላቀሉ ፓርቲዎች ፅ/ቤት ሃላፊዎች መገኘታቸውን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

(ኢቢሲ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"በማናቸውም የኦዲፒ እና የኢሕአዴግ ስብሰባዎች ላይ ውህደቱንና የመደመር ዕሳቤን አስመልክቶ ከአቶ ለማ የልዩነት ሃሳብ አልሰማንም፤ የተለየ አማራጭ ሃሳብም አላቀረቡም!" - አቶ ታየ ደንደኣ(የብልፅግና ፓርቲ ኦሮሚያ ቅርንጫፍ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ)

አቶ ታየ ደንደኣ ስለ ብልፅግና ፓርቲ አመሠራረት ሂደት፣ ፋይዳዎቹና የአቶ ለማ መገርሣ በውህደቱ አላምንም ማለትን አስመልክተው ከSBS አማርኛ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፦ "አቶ ለማ በኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዲፒ) ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ውህደቱ አስፈላጊ እንደሆነና የመደመር ዕሳቤ ከኢትዮጵያ ዐልፎ ለምሥራቅ አፍሪካም ጠቃሚ ሃሳብ እንደሆነ ተስማምተው ነው ያጸደቁት፤ የልዩነት ሃሳብ አልሰማንም። ከዚያም ዐልፎ በኦዲፒ ማዕከላዊ ኮሚቴና ጉባኤ፣ በኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚና ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባዎች ላይ ሁሉ የተለየ አቋም አላንጸባረቁም። በዚህ መሄድ አለብን የሚል የተለየ አማራጭ ሃሳብም አላቀረቡም" ብለዋል።

#SBS
@tikvahethiopia @tsegabwolde
ሶዴፓ ድርጅታዊ ጉባዔውን እያካሄደ ይገኛል!

ሶዴፓ ጅግጅጋ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው ጉባዔ የሶዴፓ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ እና ማእከላዊ ኮሚቴ የብልጽግና ፓርቲን ለመዋሃድ ባሳለፈው ውሳኔ ዙሪያ እንደሚመክር ተነግሯል። ሶዴፓ በድርጅታዊ ጉባኤው የብልፅግና ፓርቲን ለመቀላቀል ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል። እስካሁን የኢህአዴግ አባል እና አጋር ድርጅት የሆኑ ሰባት ፓርቲዎች ብልፅግና ፓርቲን ለመቀላቀል በጉባዔያቸው መወሰናቸው ይታወቃል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የወላይታ ዞን ተወካዮች ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ጋር ሊወያዩ ነው!

የወላይታ ዞን በክልል የመደራጀት ጥያቄን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከሕዝብ ተወካዮች ጋር ለመነጋገር ነገ ማለዳ በጽህፈት ቤታቸው እንደጠሯቸው BBC ያነጋገርናቸው የተወካዮች አባላት አረጋግጠዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ የክልሉ ሕዝብ ተወካዮችን በዞኑ አስተዳደር በኩል ለስብሰባ እንደጠሯቸው ቢነገርም በምን ጉዳይ ላይ እንደሚወያዩ ግን የተገለፀ ነገር የለም።

አቶ አሸናፊ ከበደ የወላይታ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ግንባር የወጣቶች ክንፍ አመራር ሲሆኑ፤ በስብሰባው ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ካቀኑት አባላት መካከል ይገኙበታል።

እርሳቸው እንደሚሉት፤የወላይታ ዞን ክልል የመሆን ጥያቄውን ካቀረበ ታሕሳስ 10 አንድ ዓመት የሚሆነው ሲሆን፣ ከዚያ በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በዚሁ ዙሪያ ሊያነጋግሯቸው እንደጠሯቸው እንደሚገምት ተናግረዋል። ጥያቄው ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረበው አርብ ዕለት መሆኑን በመግለጽም በዞኑ አመራሮች በኩል ጥሪው ደርሶናል ብሏል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከዚህ በፊት ወደ ዞኑ በማምራት ከሕዝብ ተወካዮችና ከዞኑ አመራሮች ጋር በተወያዩበት ወቅት የክልል መሆን ጥያቄው መነሳቱን የሚያስታውሱት የሀገር ሽማግሌዎችን ወክለው ስብሰባው ላይ የሚገኙት አቶ ነጋ አንጎሬ በወቅቱ ከሕዝባችሁ ጋር ተወያዩ መባላቸውን በማንሳት፣ እነርሱ ግን ተወያይተው መጨረሳቸውን መናገራቸውን ያስታውሳሉ።

አቶ አሸናፊ ከበደም በበኩላቸው ይህንኑ ስብሰባ በመጥቀስ ይህ የዘመናት የወላይታ ሕዝብ ጥያቄ የሚወሰንበትን ቀን አስታውቁ በተባልነው መሰረት አሳውቀናል ሲሉ ታሕሳስ 10፣ 2011 ዓ. ም. ጥያቄያቸውን ማቅረባቸውን ይናገራሉ።

More👇
https://telegra.ph/BBC-11-30

(BBC አማርኛ አገልግሎት)

@tikvahethiopia
ሶዴፓ ውህደቱን ለመቀላቀል ወሰነ!

የሶማሌ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ሶዴፓ) ድርጅታዊ ጉባዔ ፓርቲው የብልፅግና ፓርቲን እንዲቀላቀል ውሳኔ አሳልፏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ብልፅግና ፓርቲ...

ብልፅግና ፓርቲን ለመቀላቀል በጉባዔያቸው ውሳኔ ያሳለፉ የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲ ግንባር (ኢህአዴግ) አባል እና አጋር ድርጅት የሆኑ ፓርቲዎች ቁጥር ስምንት ደርሷል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ለትግራይና ለሱዳን ነጋዴዎች በዓለም አቀፍ የንግድ እንቅስቃሴ ላይ ያተኮረ ስልጠና ሊሰጥ ነው!

በትግራይ ክልል ንግድ ማህበራት ዘርፍ አስተባበሪነት ቁጥራቸው ከ650 በላይ ለሚሆኑ የትግራይና የሱዳን ነጋዴዎች በዓለም አቀፍ የንግድ እንቅስቃሴ ላይ ያተኮረ ስልጠና ለመስጠት ዝግጅት መደረጉ ተሰምቷል። የትግራይ ክልል ንግድ ማህበራት ዘርፍ ፕሬዚዳንት አቶ አሰፋ ገብረስላሴ በዛሬው ዕለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳሉት ለነጋዴዎቹ ስልጠና የሚሰጡት ከአልጄሪያ፣ ሞሮኮ፣ ግብፅና ቱኒዚያ የመጡ ከፍተኛ የንግድ ባለሙያዎች ሲሆኑ በትናንትናው ዕለትም ባለሙያዎቹ መቐለ ከተማ ገብተዋል ብለዋል። ስልጠናው በዓለም አቀፍ ደረጃ የገበያ ትስስርና ተወዳዳሪነት፣ የምርት ጥራት ውጤት፣ በገበያ ትስስር ላይ የሚታዩ ችግሮችና መፍትሄዎቻቸው የሚሉና ተዛማጅ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ አተኩሮ ለአራት ቀናት እንደሚሰጥ አቶ አሰፋ ገልጸዋል።

(ENA)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኢትዮጵያዊያን ጋዜጠኞች የአፍሪቃ ትልቁን የስፖርት ሚድያ ተቋም ሱፐር ስፖርትን ተቀላቀሉ!

በደቡብ አፍሪካ መቀመጫውን ያደረገው እና የአለም አቀፍ ስፖርታዊ ክንውኖች ለአፍሪካዊያን ተመልካቾች በማስተላለፍ የሚታወቀው ሱፐር ስፖርት የሚድያ ተቋም ለኢትዮጵያ ተመልካቾች በአማርኛ ቋንቋ የተመረጡ ውድድሮችን ለማስተላለፍ ለያዘው እቅድ ይረዳ ዘንድ አራት ስመጥር የስፖርት ጋዜጠኞችን ወደ ኮሜንታተር ፖናሉ በይፋ ቀላቅሏል።

በዚህ መሰረት ሃይለ-እግዚአብሔር አድሃኖም፣ ማርቆስ ኤልያስ ፣ ግርማቸው እንየው እና ዮናስ አዘዘ በዛሬው እለት ወደ ደቡብ አፍሪቃ አምርተዋል።

ቲክቫህ ስፖርት ለነዚህ ኢትዮጵያዊያን ጋዜጠኞች መልካም የስራ ጊዜን እየተመኘ ስለ ሱፐር ስፖርት አዲሱ የኢትዮጵያ ፕሮጀከት ጠለቅ ያለ መረጃ በቅርብ ይዘን እንደምንመለስ ከወዲሁ ለማሳወቅ እንወዳለን።

(Firew Asrat)

Join 👉 @tikvahethsport
በአዲስ አበባ ከተማ የትራፊክ አደጋ እጨመረ መምጣቱ ተጠቆመ!

በአዲስ አበባ ከተማ የትራፊክ አደጋ በአማካኝ በቀን የሁለት ሰዎች ህይወት መቅጠፉንና 12 የአካል ጉዳት ማድርሱን ጥናት አመላከተ። በአዲስ አበባ ከተማ  የትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ ጥናት እንዳመለከተው፤ በሶስት ወር ውስጥ በትራፊክ አደጋ 132 ሰዎች ህይወት መጥፋቱን፣ ከአንድ ሺህ በላይ ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱንና 7 ሺህ 70 ንብረቶች ላይ ጉዳት ደርሷል። አደጋው የደረሰው በአብዛኛ  ህግን በመጣስና  በብቃት ማነስ ችግር እንደሆነ ጥናቱ ጠቁማል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ  ከትምህት ቤት አመራሮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሂዷል።

(ኢዜአ)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
የመከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳና የፓርቲያቸው ምላሽ!

የመደመርን ሐሳብ ከመነሻውም ቢሆን እንዳልተቀበሉት የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበርና የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳ ትላንት ከቪኦኤ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ማስታወቃቸው ይታወቃል። በሌላ በኩል አቶ ለማ መገርሳ በድርጅታዊ አሠራር ልዩነት ላይ ያነሱት ሐሳብ፣ ዲሞክራሲያዊ እና ሐሳቡ ተጠናቆ ያልተዘጋ በመሆኑ አሁንም ቢሆን ለውይይት ክፍት መሆኑን የብልጽግና ፖርቲ ኦሮሚያ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።

(VOA)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Audio
የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳ እና የፓርቲያቸውን ምላሽ ከላይ ባለው የድምፅ ፋይል አዳምጡ።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#LemmaMegersa #PP

"...አይሆንም ያልኩበት ምክንያት አንደኛ እኛ የኦሮሞ አመራር አባላት የኦሮሞ ህዝብ አምኖን ያቀረበልን ትላልቅ ጥያቄዎች አሉ፤ እነዚህ ጥያቄዎችን እንመልስላችኃለን ብለን ቃል ገብተናል። ህዝባችን ይህን ጥያቄ ያቀረበልን የትላንቱን #ኦህዴድ ስም ለውጠንለት #ኦዴፓ ካልን በኃላ ነው። ስለዚህ ህዝቡ ጥያቄውን አንድ፣ ሁለት፣ ሶስት ብሎ የሰጠው ለሀገራዊ ፓርቲ ሳይሆን ለኦዴፓ ነው። ስለዚህ የህዝቡን ጥያቄ ሳንመልስ ይህን ማድረግ ትክክል አይደለም፤ እምነት ማጉደል ይሆናል እናም ጥያቄዎቹን ቆጥሮ እንደሰጠን መመለስ አለብን የሚል እምነት አለኝ።" አቶ ለማ መገርሳ

.
.
"...የመደመር ፍልስፍና የምንለው ለውጡ የሚመራበት ፍኖተ ካርታ፤ እይታ ነው። በበፊቱ አግባብ መሄድ አንችልም። ጠንካራ ጎኖችን ከድሮ እናስቀጥላለን። ደካማ ጎኖችን ማረም አለብን። ይሄ ለውጡ በምን አይነት ፍኖተ ካርታ ይመራ የሚል የህዝብም የሊሂቃንም ጥያቄ ነበር። በምንድነው የምንመራው ? ፍኖተ ካርታ የለም የሚል አንድ አመት፣ አንድ አመት ተኩል ይሆናል ለውጡ ከተጀመረ በኃላ፤ የመደመር ዋነኛው አስፈላጊነት ለውጡ በምን ጎዳና ይመራል? ከዴሞክራሲ አኳያ እንዴት ነው የምንመራው? ከሰላም አኳያ እንዴት ነው የምንመራው? ከኢኮኖሚ አኳያ እንዴት ነው የምንመራው? ከፖለቲካ አኳያ ቀጣይ እይታችን፣ ቀጣይ ሃሳባችን ፍኖተ ካርታው ባጠቃላይ ሚመራበት ምንድነው የሚለውን ሚመልስ ነው።" አቶ ፍቃዱ ተሰማ (የብልፅግና ፓርቲ ኦሮሚያ ፅ/ቤት ኃላፊ)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ውህደቱ ጊዜው አይደለም!

"ይህን ፓርቲ ማዋሃድ ጊዜው አይደለም። ብዙ አደጋ አለው! በሽግግር ውስጥ ነው ያለነው። ይህ ጊዜ የውሰት ነው እንጂ የኛ አይደለም። በዚህ በውሰት እየመራን ባለንበት ጊዜ ውስጥ ደግሞ ከተለያየ ቦታ ብዙ ችግሮች እየገጠሙን ነው። በዚህ በሽግግር ጊዜ አዲስ ነገር ይዞ መውጣት ወይም የሙከራ ጊዜ የምናደርግበት አይደለም። አዲስ ነገር ይዘን የምንወጣበት ጊዜ ስትሆን እነዚያ ችግሮች በተለይ እኛ በጣም ልናተኩርባቸው የሚገቡ ብለን እኔ ካነሳኃቸው ጉዳዮች ውስጥ አንደኛ የሀገሪቷ ሰላም እና መረጋጋት የሌላት ስለሆነ አብዛኛውን ጊዜያችንን ሀገር ማረጋጋት እና ሰላም ማውረድ ላይ መስራት አለብን የሚል ነው። ልእል ምጣኔ ሀብት በተለይ ህዝቡን እያስቸገር የሚገኝውን የኑሮ ውድነት ላይ ማተኮር አለብን፤ ሶስተኛ ከፊታችን ያለው ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ ማድረግ የመንግስት ግዴታ ስለሆነ ሰላማዊ እንዲሆን ለማድረግ ከአሁኑ መስራት አለብም። እኛም እንደ ህዝብ እንደ ፓርቲ አሸንፈን እንድንወጣ ነገ መንግስት መሆን እንድንችል ምን ማድረግ አለብን? የሚለውን ለመመለስ የተለያዩ ስልቶችን ቀይሰን መስራት አለብን። አሁን ስራችን መሆን ያለበት ይህ ነው። ከዚህ አልፈን ሌላ ነገር መስራት አደጋ ሊያማጣብን ስለሚችል ይህ ጉዳይ ይደር፣ ይቆይ የሚን ነው።" አቶ ለማ መገርሳ

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ይደር፤ ይቆይ ብዬ ለምኛለሁ!

"ወደ ህዝባችን እንመለስ፤ ህዝባችንን እናዳምጥ ተባብለናል። ካሁን ወዲያ ህዝባችን የማይፈልገውን አናደርግም ብለን ፊቱ ምለናል። ህዝቡም አመነን። አሁን ብድግ ብለን አዲስ ነገር ይዘን ስንመጣ ህዝቡ ሊያውቅ ይገባል። ምሁራን፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ህዝቡ ይህ ጉዳይ ያዋጣልን? አያዋጣንም? ብሎ መመርመር አለበት እንጂ የተወሰንን ሰዎች በመሰለን ልክ ሰፍተን ማልበሱ ትክክል አይደለም። እኔ እራሴ አልገባኝም ስለዚህ ይህ ጉዳይ ይደር፣ ይቆይ ብዬ በተናጠልም፣ ለብቻዬ ለምኛለሁ። ለምኛለሁ! ይጎዳል ብዬ ለምኛለሁ፤ ያለኝ ተሰሚነት እምብዛም ነው። ተሰሚነት ካጣሁ ውዬ አደርኩ! ተሰሚነት እና ድርሻ ሳይኖርህ እንዲህ አይነት ውሳኔ ላይ መሳተፍ አስፈላጊም አይደለም። አላምንበትም። ስለዚህ ነው ልዩነቴን ይዤ የወጣሁት።" አቶ ለማ መገርሳ

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
"ዛሬ ጠዋት ከወላይታ የሀገር ሽማግሌዎች እና የወላይታ ዞን የማሕበረሰብ ተወካዮች ጋር ፍሬያማ ውይይት አድርገናል::" ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ አሊ

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#FAKE "በአዲስ ዘመን ጋዜጣ" ላይ የወጣ አስመስሎ በተለያዩ አካላት እየተሰራጩ የሚገኙት መረጃዎች ሀሰተኛ ናቸው። ከላይ የምትመለከቱት በፎቶሾፕ የተቀነባበረ ነው።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ትክክለኛው የዛሬው ህዳር 21/2012 ዓ/ም የዕለተ ሰንበት አዲስ ዘመን ጋዜጣ ከላይ በፎቶ የምትመለከቱት ነው!

@tikvahethiopiaBot @tsegabwolde
አሳዛኝ ዜና!

በኦሮሚያ ክልል አርሲ ነገሌ ወረዳ በደረሰ የመኪና አደጋ የ5 ስዎች ህይወት አለፈ!

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን አርሲ ነገሌ ወረዳ ዛሬ ስምንት ስዓት አካባቢ በደረሰ የመኪና አደጋ የአምስት ስዎች ህይወት አለፈ፡፡ እንዲሁም በተሽከርካሪው ላይ በነበሩ ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ማጋጠሙ ነው የተነገረው፡፡ አደጋው ያጋጠመው በተለምዶው ዶልፊን በሚባለው ተሽከርካሪ ላይ ሲሆን የአካል ጉዳት ያጋጠማቸው ሰዎች የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ኦቢኔን ዘግቧል።

(OBN)

#TIKVAH

@tsegabwolde @tikvahethiopia