TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከ20 ሺህ 504 በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ነገ ይጀመራል!

በአዲስ አበባ ከተማ በዘጠኝ ክፍለ ከተሞች በ69 ነጥብ 2 ሄክታር መሬት ከ20 ሺህ 504 በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ በነገው እለት ይጀመራል።

የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር በመዲናዋ ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍኛ ደረጃ እየጨመረ የመጣውን የመኖሪያ ቤት ፍላጎት ለሟሟላት በተለያዩ ሳይቶች ተጀምረው በግንባታ ላይ የሚገኙትን ቤቶች በፍጥነት ለማጠናቀቅ እና በተያዘው በጀት ዓመትም 500 ሺህ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን በተለያዩ አካባቢዎች በተለያዩ የግንባታ አማራጮች ለማስገንባት እየሰራ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡

በተያዘው በጀት ዓመትም በመልሶ ማልማትና በአዳዲስ ፕሮጀክቶች በዘጠኙም ክፍለ ከተሞች በ69 ነጥብ 2 ሄክታር መሬት ከ20 ሺህ 504 በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ግንባታ ለማካሄድ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማን ጨምሮ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በነገው ዕለት የመሰረተ ድንጋይ የማስቀመጥ ስነ ስርዓት ይካሄዳል ተብሏል።

https://telegra.ph/eth-11-01-2

Via waltainfo
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በፀጥታ ስጋት በርካታ ውድድሮች ተሰርዘዋል!

የአዲስ አበባ ዋንጫ፦

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ከመጀመሩ አስቀድሞ በተለያዩ ከተሞች የአቋም መለኪያ ጨዋታዎች የሚካሄዱ መሆኑ ይታወቃል። ከእነዚህ መካከል አንዱ የሆነው አንጋፋው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ መራዘሙን ፌዴሬሽኑ አስታውቋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከመንግስት አካላት ጋር ባደረገው ምክክር ዘንድሮ ለ14ኛ ጊዜ የሚካሄደውን ውድድር ለቀናት ለማራዘም ተችሏል። በመሆኑም ውድድሩ በመጪው ሐሙስ ጥቅምት 27 የሚጀመር ይሆናል፡፡

የደቡብ የሰላም ዋንጫ፦

ከዚህ ቀደም የደቡብ ካስትል ካፕ በመባል በደቡብ ክልል ይካሄድ የነበረው ውድድርም በተመሳሳይ የመካሄዱ ነገር አሳሳቢ መሆኑን ሶከር ኢትዮጵያ ዘግቧል። የደቡብ የሰላም ዋንጫ በሚል ስሙን የቀየረው ውድድር ከጥቅምት 20-ህዳር 01/2012 ዓ.ም ለማካሄድ የተወሰነ ሲሆን፤ የእጣ ማውጣት ስነስርዓቱም ከትናንት በስቲያ ነበር። ነገር ግን ለትናንት የተራዘመ ሲሆን፤ ምክንያቱም የክልሉ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከጸጥታ አካላት ጋር ባደረገው ውይይት መግባባት ላይ አለመድረሱ ነው። ተሳታፊ ክለቦችም በዚህ ምክንያት ወደ የመጡበት መመለስ እንደጀመሩ ተጠቁሟል።

የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ፦

በመጪው እሁድ ሊካሄድ ቀጠሮ ተይዞለት የነበረው የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫም ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን ፌዴሬሽኑ አስታውቋል። የ2011 ዓ.ም የፕሪምየር ሊግ አሸናፊ መቀሌ ሰባ እንደርታ እና የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊው ፋሲል ከነማ መካከል ጥቅምት 23/2012 ዓ.ም ሊካሄድ የነበረው ጨዋታ ለሌላ ጊዜ መሸጋገሩና ወደ ፊት የሚገለጽ መሆኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

More👇
https://telegra.ph/ETH-11-01-3

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በኦሮሚያ ምዕራብ ሸዋ አምስት ሰዎች በታጣቂዎች ተገደሉ!

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ሜታ ወልቂጤ ወረዳ በትላንትናው ዕለት ማንነታቸው ያልታወቀ ታጣቂዎች በከፈቱት ተኩስ አምስት ሰዎች መገደላቸውን የወረዳው አንድ ባለስልጣን ለዶይቼ ቬለ ተናገሩ። በታጣቂዎች ከተገደሉት ውስጥ ሶስቱ ፖሊሶች መሆናቸውንም ገልጸዋል። የሜታ ወልቂጤ ወረዳ አስተዳደር እና ጸጥታ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጋዲሳ ሌንጂሳ ለጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያእንደተናገሩት ጥቃቱ የተፈጸመው በወረዳው ባለ ሚጤሮ በተባለ አካባቢ ትላንት ጠዋት ሁለት ሰዓት ገደማ ነው። አቶ ጋዲሳ “የታጠቁ ኃይሎች” ሲሉ የጠሯቸው ጥቃት ፈጻሚዎች በመጀመሪያ አንድ የሚሊሺያ አባልን ጭንቅላቱን በጥይት በመምታት መግደላቸውን ገልጸዋል።

More👇
https://telegra.ph/ETH-11-01-4

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ ጣቢያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በጭልጋ እና በመተማ ከ40 በላይ ወጣቶች ምሕረት ተደርጎላቸው ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንደተቀላቀሉ ተገለጸ!

የአማራ ክልል መንግስት የምሕረት ጥሪ ማድረጉን ተከትሎ ለወራት ጫካ ገብተው የነበሩ የቅማንት ወጣቶች ከሕዝብ ጋር እየተቀላቀሉ እንደሚገኙ የክልሉ የሰላምና የሕዝብ ደኅንነት ቢሮ አስታውቋል። በጭልጋ እና በመተማ ከ40 በላይ ወጣቶች ምሕረት ተደርጎላቸው ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንደተቀላቀሉ ቢሮው በማኅበራዊ የመረጃ ገጹ አስታውቋል።

የአማራ ብሔራዊ ክልል የደኅንነትና የፀጥታ ካውንስል ጥቅምት 05/2012 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ "በተለያየ ምክንያትና ሰበብ ተደናግሮም ይሁን በንቃት በኃይል ፍላጎትን ለማሳካት በተደረገው እንቅስቃሴ ውስጥ ተሳትፎ የነበረውን ኃይል፣ ቡድንና ግለሰብ እስከ ጥቅምት 20/2012 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ ወደ ሰላማዊ ሁኔታ እንዲመለስ የክልሉ መንግሥት በድጋሜ ይቅርታ አድርጎለታል፤ በሰው ግድያ ቀጥተኛ ተሳትፎ የነበራቸው ግለሰቦች ጉዳያቸው በህግ አግባብ የሚታይ መሆኑ እንደተጠበቀ ይሆናል" በማለት ማስታወቁ ይታወሳል። የአካባቢውን ሰላም የሚፈልግ ማንኛውም ዜጋ ከጸጥታ ሃይሉ ጎን እንዲሆንም ቢሮው ጥሪ አቅርቧል፡፡

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአዳማ ከንቲባ ንግግር የአማርኛ ትርጉም ሲፈተሽ!

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽነር ነው የተባለ እና ሁለት ደቂቃ ከአስራ አምስት ሰከንድ የሚረዝም ንግግር ወደ አማርኛ ተተርጉሞ በማኅበራዊ ድረ-ገፆች በተለይም በፌስቡክ ሲዘዋወር ሰንብቷል። በትንሹ አስራ ስድስት የፌስቡክ ገፆች ላይ የተጫነው ይኸው ንግግር በአፋን ኦሮሞ የተደረገ ሲሆን ወደ አማርኛ የተረጎመው ወገን ማንነት ግን አልተገለጸም።

More👇
https://telegra.ph/Eth-11-01-5
#GONDAR

የጎንደር ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ዛሬ በአስቸኳይ ጉባኤው ከተመለከታቸው ጉዳዮች አንዱ የከተማዋን ማስተር ፕላን ማሻሻያ ማጽደቅ ነበር፡፡

ምክር ቤቱ የቀረበለትን ማሻሻያ ከመረመረ በኋላ በዋና ዋና መንገዶች ሚሠሩት ቤቶች ዝቅተኛ ደረጃ ሁለተኛ ፎቆ እንዲሆኑ የሚያዘውን ሐሳብ እንዲሻሻል በሚል ምክር ቤቱ ሳያጸድቀው ቀርቷል፡፡

የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ አቶ ፀጋው አዘዘ እንዳስታወቁት የከተማ አስተዳደሩ ያቀረበው ማስተካከያ የወደፊት የከተዋን ዕድገት ታሳቢ ማድረግ እንዳለበት በማመላከት በዋና ዋና መንገዶች ዳር የሚገነቡ ቤቶች ከሁለተኛ ፎቅ በላይ በሆነ ደረጃ እንዲገነቡ ማስተካከያ እንዲደረግ በማለት ሳያጸድቀው ቀርቷል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በአፋርና ኢሳ ጎሳ መካከል ተከስቶ የነበረውን ግጭት ለመፍታት የሚያስችል የሰላም ኮንፈረንስ ተካሄደ!

በአፋርና ኢሳ ጎሳ መካከል ተከስቶ በነበረው ለመፍታት የሁለቱ ጎሳ አባላት እና የአካባቢው ነዋሪዎች የተሳተፉበት የሰላም ኮንፈረንስ በሚሌ ወረዳ አዳይቱ ቀበሌ ተካሂዷል፡፡

በኮንፈረንሱ ላይ የተሳተፉ የሁለቱ ጎሳ አባላት በአፋር እና በኢሳ መካከል ችግር እንደሌለ ገልፀው፤ በአካባቢው ባለፉት 11 ወራት የተከሰተው ግጭት ማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም ወጣቶች ወዳልተገባ ግጭት እንዲገቡ በመደረጉ ነው ብለዋል፡፡

የሶስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነት ሁለቱ ጎሳዎች ግጭት ውስጥ እንዲገቡ ያስቻለ መሆኑን ያስታወሱት የጎሳ አባላቱ፤ በቀጣይ ሰላምን በማስጠበቅ ወደ ልማት ፊታቸውን እንደሚያዞሩ በውይይቱ ወቀት አንስተዋል፡፡

ሁለቱንም ጎሳዎች በመሰረተ ልማት ለማስተሳሳር በቀጣይ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ የአፍር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ በዚህ ወቅት ገልፀዋል፡፡ የአርብቶ አደሩን ልጆች በትምህርት ተጠቃሚ የሚያደርግ አዳሪ ትምህርት ቤት ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ በዚሁ ወቅት ተቀምጧል። የክልሎቹ የስራ ኃላፊዎችም ችግሩን ከመሰረቱ በመፍታት በቀጣይ የልማት ስራዎች ላይ ትኩረት ይደረጋል ብለዋል፡፡

ምንጭ፦ ዋልታ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በአበርገሌ ወረዳ ከፍተኛ አመራሮች ላይ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ!

የዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ በዋለው ሶስተኛ የወንጀል ችሎት በአበርገሌ ወረዳ በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩትን ከፍተኛ አመራሮች መርማሪ ፖሊስ የጠየቀውን የአስር ቀን የምርመራ ውጤት ለመስማት ተሰይሟል፡፡

የዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ በዋለው የወንጀል ችሎት በአበርገሌ ወረዳ በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ ከፍተኛ አመራሮች ጉዳይ ለማየት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ።

ፍርድ ቤቱ ተለዋጭ ቀጠሮውን የሰጠው መርማሪ ፖሊስ የጠየቀውን የ10 ቀናት የምርመራ ውጤት ለመስማት ዳኞች ተሟልተው ባለመቅረባቸው ነው።

መርማሪ ፖሊስ ከኢትዮ ቴሌኮምና ከንግድ ባንኮች ላይ የሚሰበስበውን መረጃ እስኪያቀርብ ለዛሬ ቀጠሮ ተይዞ እንደነበርም ተገልጿል።

በተጨማሪም ተጠርጣሪዎች ሲሰሩባቸው ከነበሩት አራት ተቋማት የኦዲት ምርመራ ውጤት እንዲደርሰው ማዘዙም ተወስቷል። ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ጥቅምት 26 ቀን 2012 ለማየት ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#WKU ለወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንትነት ያመለከቱ ተወዳዳሪዎች የመጀመሪያ ዙር የውጤት መግለጫ፦

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ማስቻል

በነገው ዕለት በኢንዶኔዥያ ኤምባሲ "የምናድገው ሌሎችን በመደገፍ ነው!!!" በሚል መሪ ሀሳብ የመጀመሪያው "የማስቻል (enabling)" ዝግጅት ይካሄዳል።

በTIKVAH-ETH (ቲክቫህ ኢትዮጵያ) እና Youth to Youth (ዩዝ ቱ ዩዝ) ከተባባሪ አጋሮች ጋር በተዘጋጀው በዚህ መድረክ ላይ 50 የሚደርሱ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች የሚሳተፉ ይሆናል። 50ዎቹ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ከቀናት በፊት በ @tikvahethmagazine በነበረ ጥሪ መመዝገባቸው አይዘነጋም።

እነማን ይገኛሉ?

° H.E Mr Al Busyra Basnur, Ambassador of Indonesia

° Mr. Kibret Abebe CEO of Tebita Ambulance

° Mr. Kalewongel Tesfaye CEO of youth to youth

° Mr. Evance Rabare, Google Digital Skills Project lead Ethiopia

#enabling #ማስቻል

1. ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዕድሎች እንዴት ይገኛሉ?
2. ክህሎትን ማዳበርና ጠቀሜታው
3. ማህበራዊ ስራ ፈጣሪ ማለት ምንድ ነው?

ከዝግጅቱ መጠናቀቅ በኃላ የሚነሱ አንኳር ሀሳቦችን ሌሎች ይህን እድል ላላገኛችሁ ቤተሰቦቻችን የምናጋራችሁ ይሆናል። በዚሁ አጋጣሚ ውድ ቤተሰቦቻችን በቀጣይም ተመሳሳይ መድረኮችን እያዘጋጀን እንድትሳተፉ ለማድረግ እንደምንሰራ ቃል እንገባለን።

ዕድሉን ያገኛችሁ ቤተሰቦቻችን ኢንዶኔዥያ ኤምባሲ የሚገኘበትን ቦታ በዚህ መመልከት ትችላላችሁ፦ https://maps.app.goo.gl/HHFzaBR9V6SbuSJHA

We Rise By Lifting Others!

@tikvahethiopiaBot👈አስተያየት መቀበያ!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ማስቻል #enabling

በዚህ ፕሮግራም 50 የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የሚሳተፉ ሲሆን በሀገራዊና አለማቀፍ ዕድሎች፣ በማህበራዊ ሥራ ፈጠራና ክህሎትን በማሳደግ ላይ ምክክር ይደረጋል። በፕሮግራሙ በኢትዮጵያ የኢንዶኔዥያ አምባሳደርን ጨምሮ ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች የሚገኙ ሲሆን የGoogle Digital Skill ሥልጠናና ሰርተፊኬት ይሰጣል። ፕሮግራሙን TIKVAH-ETH እና ዩዝ ቱዩዝ ከተባባሪ አጋሮች ጋር በጋራ አዘጋጅተውታል።
.
.
° H.E Mr Al Busyra Basnur, Ambassador of Indonesia

° Mr. Kibret Abebe CEO of Tebita Ambulance

° Mr. Kalewongel Tesfaye CEO of youth to youth

° Mr. Evance Rabare, Google Digital Skill Project lead Ethiopia

ነገ በኢንዶኔዥያ ኤምባሲ ከጥዋቱ 2:00 ጀምሮ!

#enabling #ማስቻል

@tikvahethiopiaBot 👈 አስተያየት መቀበያ!

@tikvahethiopia @Y2123 @tsegabwolde
በአዲስ አበባ ከተማ ማእከላዊ ቦታዎች የሚገነቡ 20ሺ 504 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ በዛሬው ዕለት በይፋ ተጀምሯል!

ኢ/ር ታከለ ኡማ በቂርቆስ ክፍለከተማ በመገኘት በከተማዋ ማእከላዊ ቦታዎች የሚገነቡ 20ሺ 504 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ግንባታ በይፋ አስጀምረዋል፡፡ የጋራ መኖሪያ ቤቶቹ ወጪያቸው በከተማ አስተዳደሩ የሚሸፈን ሲሆን ግንባታው በዘጠኙም ክፍለከተሞች የሚከናወን ይሆናል።

በግንባታ ስራውም ከ1740 በላይ የጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራት የሚሳተፉ ሲሆን ከ52 ሺህ በላይ ለሆኑ ወጣቶች የስራ እድል የሚፈጥር ይሆናል፡፡ የጋራ መኖሪያ ቤቶቹ በ20/80ና በ40/60 የቤት ልማት መርሀግብር የሚከናወኑ ይሆናሉ፡፡

የግንባታ መርሀ ግብሩ በቅርቡ ይፋ ከተደረገውና 500 ሺህ ቤቶች ከሚገነቡበት የቤቶች ግንባታ እቅድ የመጀመሪያው ምእራፍ ነው።

በከተማ አስተዳደሩ በእቅድነት ከተያዙት እነዚህ ቤቶች ውስጥም 120ሺህ ቤቶች በከተማ አስተዳደሩ ወጪ የሚገነቡ ሲሆን ቀሪዎቹ ከ 300ሺህ በላይ የሚሆኑት መኖሪያ ቤቶች ደግሞ ከግል ባለሀብቶች ጋር በጋራ የሚገነቡ ይሆናል። በዛሬው ዕሐት ግንባታቸው የተሚጀመሩት የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ 69 ሄክታር መሬት ተዘጋጅቷል፡፡

ለግንባታ ከተዘጋጁ ቦታዎች ውስጥ በመሀል ከተማ ውስጥ ለረጅም አመታት ያለአግልግሎት ተይዘው የነበሩና ከተማ አስተዳደሩ ወደ መሬት ባንክ ገቢ ካደረጋቸው ቦታዎች መካከል ይገኙበታል፡፡

Via Mayor Office AA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአማራን ሕዝብ ማዕከል አድርገው የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ ለመሥራት ስምምነት ላይ ደረሱ!

አዴፓ፣ አብን እና የአምስቱ ፖለቲካ ፓርቲዎችን ጥምረት የያዘው የአማራ ድርጅት የስምምነቱ አካል ሆነዋል፡፡ የአማራ ሕዝብ መሠረታዊ ጥያቄዎች እና ጥቅሞች ምላሽ እንዲያገኙም ፓርቲዎቹ በጋራ ለመሥራት ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡

በአማራ ምሁራን መማክርት ጉባዔ አዘጋጅነት በአማራ ክልል እና በአገራዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡ በውይይት መድረኩ በምርጫ ቦርድ ተመዝግበው የአማራን ሕዝብ አማክለው የሚቀሳቀሱት አዴፓ፣ አብን እና የአምስቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥምረት የአማራ ድርጅት ከፍተኛ መሪዎች፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶች ተሳትፈውበታል፡፡

ፓርቲዎቹ ከውይይታቸው በኋላ የአማራን ሕዝብ መሠረታዊ ጥያቄዎች እና ጥቅሞች ምላሽ እንዲያገኙም በጋራ ለመሥራት ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡ በአማራ ክልል ብሎም በሀገሪቱ ሠላም፣ አንድነት እና ዴሞክራሲ እንዲሰፍንና የሕግ የበላይነት እንዲከበርም በተባበረ ክንድ ለመሥራት ተስማምተዋል፡፡

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ETHIOPIA

በኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ፌዴራላዊ ስርዐቱ የተተገበረበት መንገድ ዜጎችን ለሰብአዊ መብት ተጋላጭ ማድረጉን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ ተናገሩ። ዶክተር ዳንኤል በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዳብራሩት፤ ዜጎችን ለሰብአዊ መብት ጥሰት ተጋላጭ ያደረገው ፌዴራላዊ ስርዓቱ የተተገበረበት መንገድና የፌዴራል ስርዓቱ የመንግስት አወቃቀር አንዱ ችግር መሆኑን አሰረድተዋል። የፖለቲካ ፓርቲ አወቃቀሩም ሌላው ምክንያት ሊሆን እንደሚችልም ጠቁመው በተለየ ማንነት ላይ ትኩረት ተደርጎ መሰራቱምለግጭት መዳረጉንም ጠቁመዋል፡፡

የፖለቲካ ፓርቲዎች አወቃቀር፣ የመንግስት አወቃቀርና ህገ መንግስታዊ ማዕቀፍ መፈተሽ አለብን፣የፖለቲካ አወቃቀራችን በተፈጥሯቸው የአግላይነት ጸባይ ስላላቸው በውጤታቸው ደግሞ ለግጭት፣ ለብጥብጥና ለእርስ በእርስ አመጽ የሚጋብዙ ሆነው የሚታዩ ስለሚመስሉ ጉዳዩ ሊመረመር፣ ሊጠና እና ሊታይ ይገባዋል ያሉት ኮሚሽነሩ የፖለቲካ መሪዎችም በእዚህ ጉዳይ መወያየት መጀመር የሚገባቸው ይመስለኛል ብለዋል፡፡

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AddisAbeba

በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ አካባቢዎች በአሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ምክንያት የውሃ ስርጭት መቋረጡ ተገለፀ፡፡ በተለያዩ ምክንያቶች በተደጋጋሚ እየተፈጠረ ባለው የኤልክትሪክ ኃይል መቆራረጥ በውኃ ምርት ፣ አቅርቦትና ስርጭት ላይ ከፍተኛ መስተጓጎል እየፈጠረ መሆኑን የአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ ባለስልጣን አስታውቋል፡፡

ትላንት ከምሽቱ 2 ሰዓት ጀምሮ በተፈጠረ የኤሌክትሪክ መቋረጥ ምክንያት በአቃቂ ከርሰ ምድር የተወሰነ ክፍል ውሃ ማምረት አልቻለም ነው የተባለው፡፡

በዚሁ ምክንያት አቃቂ ፣ በቃሊቲ ፣ በሳሪስ አቦ፣ ቦሌ ቡልቡላ፣ ጎተራ፣ ቦሌ ፣ ኦሎምፒያ፣ ስታዲየም፣ ለገሀር፣ ሜክሲኮ፣ ልደታ፣ ጦር ሀይሎች፣ መርካቶ(በከፊል)፣ ቀራኒዮ፣ ቤቴል፣ አለም ባንክ፣ አየር ጤና ፣በዘነበ ወርቅ፣ መከኒሳ ፣ካራ ቆሬ ፣በጀሞ ፣ለቡ፣ሀና ማሪያም፣ጎፋ እና ቄራ አከባቢዎች የውሃ ስርጭት ተቋረጧል፡፡

ችግሩን ለመፍታት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጥረት እያደረገ መሆኑን የአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ ባለስልጣን አስታውቋል፡፡ በተጠቀሱት አከባቢዎች የምትኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች በትዕግስት እንድትጠብቁን ጠይቋል፡፡

Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ውድ ቤተሰቦቻችን ዘውትር ቅዳሜ በዓለም አቀፉ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት የሚያቀርብላችሁ መረጃዎች የዚህ ሳምንቱ ወደሚቀጥለው ሳምንት መሸጋገሩን ከታላቅ ይቅርታ ጋር ለመግለፅ እንወዳለን።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ETHIOPIA

አቶ ኤሊያስ ሽኩር የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ። አቶ ኤሊያስ በቅርቡ የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው የተሾሙትን አቶ ርስቱ ይርዳውን በመተካት ነው የተሾሙት።

ከዚህ ቀደም የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር በመሆን ሲያገለግሉ መቆየታቸውን ከወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። አቶ ጌታቸው ባልቻ በነበሩበት የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነርነት ቦታ ይቀጥላሉ።

Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የካራ ማራ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የምግባ መርሃ ግብር ተቋረጠ!

በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 የሚገኘው ካራ ማራ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተማሪዎች የምገባ መርሃ ግብር መቋረጡ ተገለጸ። በዚህ ትምህርት ቤት የምገባ መርሃ ግብር ሊቋረጥ የቻለው በማህበራቱ የቅድመ ዝግጅት ማነስ መሆኑን የክፍለ ከተማው የትምህርት ጽህፈት ቤት ገልጿል።

ባለፉት ሁለት ቀናት በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 አካባቢ በሚገኘው የካራ ማራ ትምህርት ቤት በመንግስት በኩል የተመቻቸው የቁርስና የምሳ ምገባ በአግባቡ አልተካሄደም።

የካራ ማራ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የአደራጃጀት ርእስ መምህር አቶ ዮናስ ሽኩር እንደገለጹት፤ ምገባው የተቋረጠው ምግቡን እንዲያቀርቡ በማህበር የተደራጁ እናቶች የንግድ ፈቃድ የላቸውም። በመሆኑም ከክፍያ አፈጻጸም ጋር ችግር በማጋጠሙ የተነሳ ምግብ አቅራቢ እናቶች የገንዘብ እጥረት አጋጥሟቸዋል።

Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የእንጨት ስራ የሚሰራው ወጣት የ2,500,000 ብር እድለኛ ሆኖ ሽማቱን ተረከበ!

በደቡብ ክልላዊ ሲዳማ ዞን ይርጋለም ከተማ ነዋሪ የሆነው አቶ አበበ ጌታቸው በእንቁጣጣሽ ሎተሪ 3ኛ ዕጣ 2,500,000 ብር እድለኛ ሆኖ ሽልማቱን ተረከበ፡፡ እድለኛው ባለትዳርና የሁለት ልጆች አባት ሲሆን የእንጨት ሥራ በማስራት ቤተሰቦቹን ያስተዳድር ነበር፡፡ በደረሰው ገንዘብም “ያላሟላኋቸው የእንጨት ማሽኖች ለመግዛትና አሁን የምንኖረው በኪራይ ቤት ስለሆነ የራሴን ቤት ለመስራት እጠቀምበታለሁ'' ብሏል፡፡

ምንጭ፦ ብሄራዊ ሎተሪ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AddisAbeba

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ባሁኑ ሰአት አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ውስጥ እንደሚገኝ ተገለፀ። ጋዜጠኛው በፖሊስ ኮሚሽኑ ውስጥ ለመገኘቱ እንደ ምክንያት የተባለው ደግሞ በምክር ቤቱ ጽህፈት ቤት ስብሰባ አድርጎ ሲወጣ የተሰባሰቡ ቡድኖች ጉዳት ሊያደርሱበት ሲሞክሩ ፖሊስ ደርሶ ወደ ኮሚሽኑ ግቢ እንዳስገባው ነው ጋዜጠኛ በላይ ማናዬ የገለፀው። የሪፖርተሩ ጋዜጠኛ ታምሩ ፅጌ ስለጉዳዩ የማጣራት ወደ ጋዜጠኛ እስክንድር ጋር ደውሎ ያገኘው ምላሽ፦ "አሁን ማናገር ስለማልችል መልሼ እደውልልሀለሁ" የሚል ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia