TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ ጉባዔ ተቀምጧል፡፡ በዛሬው የጉባዔው ውሎ የመንግሥት ሃላፊዎች መገኘታቸው ተሰምቷል፡፡

Via #WAZEMA

•ከሰሞኑን ከሲኖዶሱ ጋር በተገናኘ በፌስቡክ ብዙ #ሀሰተኛ መረጃዎች እየተሰራጨ ስለሆነ TIKVAH-ETH በታማኝ ሚዲያዎች እና ከሚመለከታቸው አካላት ብቻ የሚሰማውን መረጃ ያጋራል!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ይህ ፎቶ ናይጄሪያ -- አቡጃ ውስጥ ነው⬆️

ደቡብ አፍሪካ በናይጄሪያ የሚገኘውን ኤምባሲዋን ዘጋች። ደቡብ አፍሪካ በናይጄሪያ የሚገኘውን ኤምባሲዋን ለመዝጋት የተገደደችው በደቡብ አፍሪካ ናይጄሪያውያን ላይ እየደረሰ ባለው ጥቃት ምክንያት በናይጄሪያ ኤምባሲዋ ላይ የአፀፋ ጥቃት በመሰንዘሩ ነው። ባለፈው ሳምንት እሁድ የጀመረው በሌላ አፍሪካ ሃገራት ዜጎች ላይ ያነጣጠረው ጥቃት እስከ ዛሬዋ እለት ድረስ ቀጥሎ የብዙዎች ንብረት ተዘርፏል፤ ወድሟልም።የናይጀሪያ መንግሥት ጥቃቱን ያወገዘው ሲሆን የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርም በበኩላቸው ድርጊቱ አሳፋሪ እንደሆነ ተናግረዋል።

Via #BBCአማርኛ
📸REUTERS
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የAASTU/ASTU ምዝገባ ተራዝሟል!

በኢትዮጵያ ሣ.ቴ.ዩኒቨርሲቲዎች የ2012 ትምህርት ዘመን ትምህርታችሁን ለመከታተል ለምትፈልጉ፦

በሀገር አቀፍ ደረጃ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያልተቆረጠ በመሆኑ ምዝገባ የተራዘመ መሆኑን እየገለፅን በትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት እንደተቆረጠ ምዝገባ የሚጀመርበትን ቀን የምናሳውቅ መሆኑን እንገላፃለን፡፡

www.aastu.edu.et

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወደ ደቡብ አፍሪካ እንዳትሄዱ!

የናይጄሪያው ፕሬዝዳንት ሞሃመዱ ቡሃሪ ናይጄሪያውያን ወደ ደቡብ አፍሪካ #እንዳይሄዱ በትዊተር ገጻቸው አስጠንቅቀዋል።

#Xenophobia: A travel advisory issued by Ministry of Foreign Affairs. ...”due to the tension created by the attacks, the Government of Nigeria wished to advice Nigerians to avoid travelling to high risk and volatile areas until the situation is brought under control.”

Kindly RT

Via #BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Xenophobia ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ ዜጎቹ ጥቃት የተፈጸመባቸው የናይጀሪያ መንግሥት ከደቡብ አፍሪቃ ወደ ሃገራቸው ለመመለስ ፈቃደኛ የሆኑ ዜጎቿን ለመውሰድ ማቀዱን አስታወቀ።እቅዱን ይፋ የተደረገው የናይጀሪያ የማስታወቂያ ሚኒስትር ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ላይ ነው።ናይጀሪያ ዜጎቿ ላይ በደረሰው ጥቃት ምክንያት የደቡብ አፍሪቃ አምባሰዷሯን ጠርታለች።

ካለፈው ሳምንት መጨረሻ አንስቶ በደቡብ አፍሪቃ ዋና ከተማ ፕሪቶርያ እና በንግድ ማዕከሏ በጆሀንስበርግ ከተማ ናይጀሪያውያንን እና ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ በውጭ ዜጎች ላይ በተፈጸመ ጥቃት 5 ሰዎች መገደላቸው፣በርካታ ንብረት መውደሙ እና መዘረፉ ሌሎች ዜጎቻቸው የተጎዱባቸውን የአፍሪቃ ሃገራትንም አስቆጥቷል።

ለጥቃቱ የአጸፋ እርምጃ ከተወሰደባቸው ሃገራት ውስጥ ዛምቢያ እና ናይጀሪያ ይገኙበታል።በናይጀሪያ የቴሌኮምኒኬሽን አገልግሎት የሚሰጠው የደቡብ አፍሪቃው ኩባንያ MTN እና PEP የተባለው የገበያ ድርጅት ጥቃት ከደረሰባቸው የደቡብ አፍሪቃ ድርጅቶች ውስጥ ይገኙበታል።

Via #DW

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-05-3
ከሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያ ቴዲ አፍሮ የአዲስ አመት ኮንሰርት በመንግስት እንደተሰረዘ በብዛት ሲፃፍ እንደነበር ይታወሳል። ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ጉዳዩን ኣጣርቶ ይህን አሰራጭቷል፦

የአ/አበባ ከተማ ከንቲባ ፅ/ቤት ፕረስ ሰክረታሪ ፌቨን ተሾመ፦

"በፍፁም አልተከለከለም! የሆነው እንዲህ ነው: የቴዲ አፍሮ ፕሮሞተር እና ማናጀሩ መስቀል አደባባይ ኮንሰርት እንዲያቀርቡ ጠየቁን። እኛም ይህንን ለፀጥታ አካላት ስናሳውቅ እነሱ ግን ለምን ግዮን፣ ስታዲየም ወይም ሌላ ቦታ አይሆንም ብለው አስተያየት ሰጡ። ም/ከንቲባው ግን እዛው መስቀል አደባባይ ይሁን፣ ባይሆን አካባቢውን ለፀጥታ ሲባል ማጠር ይቻላል የሚል መልእክት አስተላለፉ። በዚህም መሰረት የፈቃድ ደብዳቤውን ልከናል። ስለዚህ ሙሉ ፈቃድ በከተማው አስተዳደር ተሰጥቷል። አሁን ግን ቴዲ ተከለከለ የሚል ነገር ሰማን።"

በኮንሰርት ዝግጅቱ ውስጥ ተሳታፊ የሆነ ግለሰብ፦

"ስሜን አትጥቀሰው ግን ይህን መረጃ ልስጥህ። አልተከለከልንም። የፈቃድ ደብዳቤውም እጄ ላይ አለ። ኮንሰርቱ ወደፊት ይካሄዳል። ያሰብነው ለአዲስ አመት ነበር ነገር ግን በራሳችን ጉዳይ አልተሳካልንም። በምንፈልገው ደረጃ ሳውንድ ሲስተም ሀገር ውስጥ ሊገኝ አልቻለም። ሀገር ውስጥ ያለው የዋፋ ድርጅት ነበር እርሱ ደግሞ ቀድሞ ተይዟል። ይህ ነገር in advance አራት እና አምስት ወር የሚፈልግ ነገር ነው። ስለዚህ ለዛ አሁን እየተዘጋጀን ነው። የከተማ አስተዳደሩ በፈለግን ግዜ ፍቃድ መጠየቅ እንደምንችል ነግሮናል። ከእነሱ ጋር ጥሩ ግንኙነት ነው ያለን።"

ምንጭ፦ ኤልያስ መሰረት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥንቃቄ ይደረግ!

ከመስከረም እስከ ታህሳስ ያሉት ወራት ዋነኛ የወባ መተላለፊያ ወቅት በመሆናቸው ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ የጤና ሚኒስቴር አሳሰበ። በኢትዮጵያ 75 በመቶ የሚሆነው አካባቢ ለወባ በሽታ ስርጭት አመቺ ሲሆን 60 በመቶ የሚሆነው ህዝብም በነዚህ አካባቢዎች ይኖራል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
VACANCY⬆️

JIMMA UNIVERSITY AGARO CAMPUS

Via #JIMMA_UNIVERSITY
@tsegabwolde @tikvahethiopia
5 በባለቤቶቻቸው እውቅና የሌላቸው ገፆች⬆️

ቴሌግራም፦

1. BBC አማርኛ -- ይህ የቴሌግራም ቻናል የቢቢሲ አይደለም። ቢቢሲ አማርኛ በፌስቡክና በትዊተር ላይ ካለው የመገናኛ አማራጭ ውጪ በቴሌግራም ምንም አይነት ገፅ የለውም!

2. ESAT TV --- የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ምንም አይነት ይፋዊ የሆነ የቴሌግራም ገፅ የለውም።

3. Jawar Mohammed --- የOMN ዋና ዳይሬክተር አቶ ጃዋር መሃመድ በቴልግራም መልዕክት የሚያሰራጭበት ምንም ይፋዊ የቴሌግራም ቻናል የለውም። እንዲሁም በፌስቡክ ላይ ያለው የግል ገፁ በFACEBOOK #verify የተደረገው ብቻ ነው።

ፌስቡክ፦

1. ዲያቆን ዳንኤል ክብረት--19,359 Like ያለው የፌስቡክ ገፅ የዲያቆን ዳንኤል ክብረት አይደለም። በዚህ ገፅ የመሰራጩ መረጃዎችም የዲያቆን ዳንኤል አይደሉም።

2. ጉለሌ ፖስት -- 87 ሺህ Like ያለው ጉለሌ ፖስት በሚል የተከፈተው ገፅ #ሀሰተኛ ነው። የዋናው የጉለሌ ፖስት ትክክለኛ የፌስቡክ ገፅ 47 ሺ Like ያለው ነው። ይገርማል🤔ትክክለኛውን የሚከተለው እና ሀሰተኛውን ገፅ የሚከተለውን የሰው ቁጥር መልስ ብላችሁ ተመልከቱ!

ሌላው...

ከሰሞኑን በወዳጃች እና እጅግ በምናከብረው አለም አቀፉ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ስም ብዙ ሀሰተኛ መረጃዎች እየተሰራጩ እንደሆነ ተመልክተናል ጥንቄቄ ይደረግ!! ያልተናገረውን ተናግሯል፤ ያላለውንም ብሏል በሚል አንዳንድ ገፆች ሀሰተኛ መረጃዎችን እያሰራጩ ነው።

#TIKVAH_ETHIOPIA

በየዕለቱ 5 ሀሰተኛና በባለቤቶቻቸው እውቅና የሌላቸውን ገፆች እናቀርባለን!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በአጥፍቶ መጥፋት ጥቃት 10 ሰዎች ተገደሉ!

ታሊባን ዛሬ በአፍጋኒስታን መዲና ካቡል በመኪና በተጠመደ ፈንጂ የአጥፍቶ መጥፋት ጥቃት በማድረሱ ቢያንስ 10 ሰዎች ተገድለዋል።

Via #VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ም/ዳይሬክተር አቶ መሳይ ደምሴ በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናዎች ላይ የተፈጠረውን ችግር አስመልክቶ የሰጡት ማብራሪያ!

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለመደባ አያገለግሉም የተባሉት ውጤቶች አልተሰረዙም!

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ም/ዳይሬክተር አቶ መሳይ ደምሴ ለተጠየቋቸው ጥያቄዎች የሰጡት ማብራሪያ፦

TIKVAH-ETH ከአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት አዳምጦ ቃል በቃል ያሰፈረው!

የውጤት ግሽበት ምን ማለት ነው??

"ያልተጠበቀ ውጤት እስካሁን ድረስ በሀገሪቱ የፈተና አሰጣጥ በተለይም የ12ኛ ክፍል ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ሲሰጥ የተመዘገቡ ውጤቶች አሉ የ10 ዓመት ሊሆን ይችላል ወይም ከዚያ በላይ ነገር ግን ባልተጠበቀ መልኩ መቶ እና ሁለት መቶ፣ ሶስት መቶ በሁለት ወይም በሶስት የትምህርት አይነት ወይም በአራት የትምህርት አይነት መቶዎች አይመዘገብም። ዘንድሮ ግን በርካታ ውጤት ከ90 በላይ የተመዘገቡት በተለይ በመጨረሻዎቹ ሁለት ቀናትና ይሄ ያልተጠበቀ ነው። 6002 የሚሆኑ ተማሪዎች አጠቃላይ መቶ ሙሉ በሙሉ ያስመዘገቡት ውጤት ከዚህ በፊት ከተለመደው ባለን ሪከርድ የለም።"

ውሳኔው በራሳቸው ሰርተው ውጤት ላመጡ ተማሪዎች ችግር አይፈጥርም?

" ችግር አይፈጥርም፤ 7 የትምህርት አይነቶች ናቸው የተሰጡት የመጀመሪያዎቹ ሰኔ 6-7 የተፈተኑት ፈተናዎች እንግሊዘኛ ለሁሉም፣ ለተፈጥሮ ሳይንስና ለማህበራዊ ሳይንስ፣ ሂሳብ ለተፈጥሮ ሳይንስ እና ማህበራዊ ሳይንስ፤ አፕቲትዩድ ለሁሉም ለማህበራዊ ሳይንስ ጆግራፊ፣ ለተፈጥሮ ሳይንስ ፊዚክስ ተፈትነዋል። የጋሸበ ውጤት አለ የሚል ግምት ሲፈጠር የሰኞና የማክሰኞ፣ የመጀመሪያዎቹ ፈተናዎችም በኮሚቴ ታይቷል። በአንፃራዊነት የተማሪዎች ውጤት ተቀራራቢ ነው የነዚያኛዎቹ ግን የጋሸበ ነው ያልተጠበቀ ነው።"

የጋሸበ ውጤት የታየባቸው አካባቢዎች?

"የቴክኒክ ኮሚቴው ያጠናው አጠቃላይ በሀገሪቱ ነው። በጣም በተወሰኑ ክልሎች በ4 ክልሎች በደቡብ፣ በአማራ፣ በቤኒሻንጉል አንድ ዞን፣ ኦሮሚያ የተወሰኑ ዞኖች የተወሰኑ ቁጥር፣ በርከት የሚለው በአማራ ክልል ሆኖ የጋሸበ ውጤት የተመዘገበበት ሁኔታ አለ። ነገር ግን በአንፃራዊነት ነው ሲታይ ግን በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች የተሰጠው ፈተና ሰኞ እና ማክሰኞ ግሽበት ያሳያል።"

ለምደባ የማያገለግሉት የትምህርት አይነቶች ዕጣ ፋንታቸው ምንድነው?

"ህብረተሰቡንም #የሚያወዛግበው እና ግልፅ ያልሆነላቸው ይሄ ነው። እጣ ፈንታቸው... በልጆቹ ውጤት ሰርተፊኬት ላይ ይመዘገባል። ከዚህ በፊትም ቢሆን መንግስት ባለው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፤ የሳይንስና ከፍተኛ ሚኒስቴር በሚያወጣው መቁረጫ ነጥብ መሰረት ያስገባል። ሲያስገባ የሚወስደው መስፈርት አለ መስፈርቱ እሱ በወሰነው ነው። በዚህ አራቱ ትምህርት ይወሰድ ብለን ወስነናል። መንግስት ነው የወሰነው። የዩኒቨርሲቲ የማቀበል አቅም ...እነዚህ ዩኒቨርሲቲዎች ለመግባት መንግስት ኢንቨስት ለማድረግ አስተምራለሁ፣ በቀጣይ የሃገሪቱን እጣ ፈንታ የሚወስኑ አካላት ናቸው ብሎ የወሰደው compulsory ሶስቱ የትምህርት አይነቶች ናቸው ሂሳብ፣ እንግሊዘኛ እና አፕቲትዩድ ወሳኝ ናቸው እንደገና በፈተና አሰጣጥም የተረጋጋ በውጤትም በተማሪዎች ነካከል የጎላ ልዩነት ስለሌለ ተፅኖ ስለማይፈጥር ነገር ግን ሰኞና ማክሰኞ የተፈተኑት ለመደባ አያገለግሉም የተባሉት ውጤታቸው አልተሰረዙም ህብረተሰቡ ጋር ግን እንደተሰረዘ ተደርጎ ይወራል አልተሰረዙም! በልጆቹ ሰርተፊኬት ላይ ይቀመጣል። ከተቀመጠ በኃላ ለስኮላርሺፕ ይጠቀሙበታል፣ ለግል ዩኒቨርስቲ ተቋማት ይጠቀሙበታል። ሙቁረጫ ነጥብ 4ቱ የተወሰዱት በግልፅ ህብረተሰቡ እንዲያውቀውና እንዲረዳው የምንፈልገው ለመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች #ብቻ ነው፣ ለሌላ ይጠቀሙበታል።"

መቁረጫ ነጥብና ምደባው እንዴት ይከናወናል?

"የመቁረጫ ነጥቡን የሚወስናው የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ነው፤ ከምን ተነስቶ? ከአራቱ ትምህርት ውጤቶች ትምህርት ተነስቶ። ህብረተሰቡ ማወቅ ያለበት ከ400 ታርሟል። ከ400 ከፍተኛ ውጤት ያመጣው በግሌ በማውቀው ወደ 336 ያመጣው ከ400 ከፍተኛው ውጤት ነው 6 መቶ ምናምን የነበረው ሰው። በግምት እኛ ባለን መረጃ አምና እስከ 150,000 ተማሪዎችን ተቀብሏል ዩኒቨርሲቲዎች አሁንም ከዚያ ባነሰ አይቀበልም ከዚያ በተሻለ ሊቀበል ይችላል። ለጊዜው ግን እኔ የማውቀውና የምረዳውም የአምናውን እንኳን ብንወስድ 150,000 ተማሪ የመቀበል አቅም ይኖራቸዋል ዩኒቨርሲቲዎች፣ ከላይ ተነስቶ ወደታች ይሄዳል።"

ማነው ኃላፊነቱን የሚወስደው?

"ሃላፊነቱን የሚወስድ አካል ይኖራል። ይህንንም አጣርቶ የሚያቀርበው አሁን በሃገር አቀፍ ደረጃ የተቋቋመው ኮሚቴ ካጣራ በኃላ ነው። ተጠያቂ የሚሆነው። ኮሚቴው ተዋቅሮ አልቋል ወደስራም ተገብቷል። ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ነው። በየደረጃው ያለ አካል ከላይ እስከታች ኤጀንሲውም ጋር ችግር ካለ፣ ትምህርት ሚኒስቴርም ችግር ካለ፣ ችግር አለ ተብሎ ተዳሶ እርምጃ ይወሰዳል። ወደፊት ለህብረተሰቡ ግልፅ ይሆናል።"

#TIKVAH_ETHIOPIA

TIKVAH-ETH ከአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት አዳምጦ ቃል በቃል ያሰፈረው!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
እየተጫወተ በተቀመጠበት ሸርተት አለ⬆️

/በጋዜጠኛ ጌጡ ተመስገን/

• ባለቤቱ፤ ሦስቱ ሴቶች ልጆች ጩኸት አሰሙ!

የመስከረም ማዞሪያ ሠፈርተኞች ጩኸቱን ሰምተው ለእርዳታ ተሰባሰቡ፡፡ የአራት ልጆች አባት የነበረው አርቲስት ተዘራ ለማ ቤት ውስጥ ጌም እየተጫወተ ፤ ደንገት በተቀመጠበት ሸርተት ያለው፡፡ ባለቤቱ - ፋንቱ እንዲሁም ልጆቹ - ሰላማዊት፣ ሳባ እና ሳምራዊት ተዘራ ቤት ነበሩ፡፡ ወንድ ልጁ ነቢየልዑል ቤት አልነበረም፡፡

የመስከረም ማዞሪያ ሠፈርተኞች ተረባርበው አቅራቢያ ወደ ሚገኘው ቂርቆስ ክፍለ ከተማ መሷለኪያ ጤና ጣቢያ ተወሰደ፡፡ ትንፋሹ ነበረች፡፡

የመስከረም ማዞሪያ ሠፈርተኞች - የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማኅበር ዋና መስሪያ ቤት መንገድ እንደተሰበሰቡ ዜና እረፍቱን ሰሙ!
ዜና እረፍቱ አሁን አትጻፍ! ምክንያቱም ልጁ -ቤተሰቦቹ አልሰሙም! ዜና እረፍቱ በፌስቡክ እንዳይሆን ‹‹መርዶው ይደር!›› በሚል ከንግስት ተክሉ ቃል አስረን ተለያየን፡፡

‹‹አባ›› እያለች መጮህ ቀጠለች፤ አረረች
አርቲስት ተዘራ ለማ - በሠፈሩ ‹‹አባ›› ተብሎ በክብር፤ በፍቅር ይጠራል፡፡

***

አርቲስት ተዘራ ለማ “ከስጋ ቤት እስከ ህብረት ሱቅ ሽያጭነት…… ከተወዛዋዥነት እና ጊታር ተጨዋችነት እስከ ታዋቂ ተዋናይነት” በከፍተኛ18 ኪነት ቡድን ውስጥ አሁን ታዋቂ ከሆኑት ከእነ ፋሲካ ዲሜትሪ እና ዳዊት መለሰ ጋር ተጫውቷል፡፡ በጊዜውም በኪነት ቡድኑ ውስጥ በተወዛዋዥነት እና በጊታር ተጫዋች ነት ያገለግል ነበር፡፡

ከ1983 ዓ.ም በኋላ ኪነት ቡድኑ በመበተኑ እሱም ከጥበቡ አለም ርቆ ወደ ሹፍርና ሙያ ይገባል፡፡ በሹፍርናም ለ20 ዓመታት ያህል ሰርቷል፡፡ በሹፍርና በአገለገለበት ዘመንም የተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎችን የዞረ ሲሆን በርካታ ውጣ ውረዶችን እና ገጠመኞችን አስተናግዷል፡፡

(በመሳሪያ ከማስፈራራት እስከ መደብደብ ድረስ…) ይህ ሰው አርቲስት ተዘራ ለማ ነው፡፡ ለ20 ዓመት የሰራበት የሹፍርና ሙያ ወደ ትወናው አለም እንዲገባ በር ከፍቶለታል፡፡ በቶም ቪዲዮ አማካኝነት ውሳኔ ፊልም ሲሰራ በሹፌርነት ሰርቶ ነበር፡፡ 500 ብር ቢነጋገርም ተባባሪነቱ እና ቅንነቱን ያየችው የቶም ቪዲዮ ባለቤት ገነት ተጨማሪ 500 ብር በማከል 1000ብር ተከፍሎታል፡፡ እሱ ግን በክፍያው ደስተኛ አልነበረም፡፡ ምክንያቱም የትወና ፍላጎቱ እና በካሜራ እይታ ውስጥ ለመግባት መሻቱ ስላልተሳካለት፡፡

ይሁንና በሁለተኛው ቀን ለዚሁ ለውሳኔ ፊልም ቀረፃ አለም ገና በሄደበት ጊዜ አለቃ ሆኖ የሚሰራበት አጭር ሲን (ትዕይንት) ይሰጠዋል፡፡ በዚህ ጊዜ አርቲስት ተዘራ ደስታው ወደር አልነበረውም፡፡ ይህ ነበር እንግዲህ ፊልምን እና አርቲስት ተዘራን ያስተዋወቃቸው፡፡

የልጅነት ሀሳቡ እና ምኞቱ ሰመረ፡፡ “ወሳኔ ፊልም” የበኩር ሥራው ሆነ ማለት ነው፡፡ ከዚያም ከኩርባው በስተጀርባ የተሰኘ ፊልም ላይ ተውኗል፡፡

አርቲስት ተዘራ ለማ እስካሁን ከ20 በላይ ፊልሞች ላይ የተለያዩ ገፀ ባህሪያትን ተጫውቷል፡፡
እነርሱም ፡-
- ውሳኔ
- ከኩርባው በስተጀርባ
- ፍቅር ባጋጣሚ ፣ታሰጨርሺኛለሽ
- ፍቅር በይሉኝታ
- አልወድሽም
- ወንድሜ ያቆብ
- ኢንጂነሩ
- ጥቁር እና ነጭ
- ፍፃሜው
- ሀማርሻ
- ሰውዬው
- የፍቅር ቃል
- ቪዳ
- ባዶ ነበር
- ፀሀይ የወጣች ቀን
- ጣምራ
- የበኩር ልጅ
- እሷን ብዬ
- ጉደኛ ነች
- ሰበበኛ
- ዘውድና ጎፈር ፤ በመሰራት ላይ ያሉ እና በቅርብ የሚወጡ ፡- ታላቁ ሩጫ ፣ ሰንሰለት ፣ እስክትመጪ ልበድ እና ሌሎችም ይተቀሳሉ፡ በአለም ሲኒማ የታየ “የእኔ እውነት” የተሰኘ ትያትር ሰርቷል፡፡ ይህ ትያትር ሀገር ፍቅር ለመታየት ወረፋ እየጠበቀ ነው፡፡ የኩኩ ሰብስቤ ቻልኩበት ክሊፕ ላይም ተሳትፏል፡፡

በ “በኩር ልጅ” ፊልምም ባሳየው የገፀ ባህሪይ አጨዋወት በ9ኛው የኢትዮጵያ ፊልም ፌስቲቫል ላይ “የአመቱ ምርጥ ተዋናይ” ተብሎ ተሸልሟል፡፡ በ”ፍቅር ቃል” ፊልም ላይም እንዲሁ ባሳየው ብቃት ከእነ ቤተሰቡ የዋንጫ ሽልማት ተበርክቶለታል፡፡

የከፍተኛ 18 ኪነት ቡድን ውስጥ ከተዋወቃት ባለቤቱ ተወዛዋዥ ፋንቱ አርጋው በ1977ዓ.ም ጋብቻውን የፈፀመው አርቲስት ተዘራ ለማ አራት ልጆችን አፍርቷል፡፡ ልጆቹም የእሱን ፈለግ የተከተሉ ሲሆን በተለይ ሰላም የተባለችው ልጁ ከ “ኩርባው በስተጀርባ” ፊልም ላይ አብረው ሰርተዋል፡፡

በ1954ዓ.ም ፍቼ የተወለደው አርቲስት ተዘራ ለማ እድገቱ እዚሁ መዲናችን አዲስ አበባ ርቼ አካባቢ ነው፡፡ ይህ አርቲስት ወደ ጥበቡ ከገባበት ጊዜ ጀምሮ በፊልም ፣ በቴሌቪዥን ተከታታይ ድራማ ፣ በትያትር እና በልዩ ልዩ ማስታወቂያዎች ላይ ሰርቷል፡፡

በተወለደ በ57 አመቱ አርቲስት ተዘራ ለማን በድንገተኛ ህመም ከእዚህ አለም በሞት አጥተነዋል፡፡

አርቲስት ተዘራ ለማ
እንግዲህ አመለጠን

/በጋዜጠኛ ጌጡ ተመስገን/

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Breaking የቀድሞው የዚምባብዌው ፕሬዝደንት ሮበርት ሙጋቤ በ95 አመታቸው ማረፋቸው ተሰምቷል። https://www.bbc.co.uk/news/world-africa-49604152
#ZI ፕሬዘዳንት ኤመርሰን ምንጋዋ የቀድሞው የዝምባዌ ፕሬዘዳንት ሮበርት ሙጋቤ ከዚህ አለም በሞት መለየታቸውን አረገግጠዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ፍርድ ቤቱ በአዲስ አበባና በባሕርዳር ከተሞች ከመንግስት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ግድያ ጋር በተያያዘ ሽብር ወንጀል በተጠረጠሩ ግለሰቦች ላይ ፖሊስ የጠየቀውን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ፈቀደ።

ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባና ባሕርዳር ከተሞች ከተፈፀመው የከፍተኛ መንግስት ባለሥልጣናት ግድያ ጋር በተያያዘ በሽብር ወንጀል በተጠረጠሩ ግለሰቦች ላይ ፖሊስ ሰኔ 23 ቀን 2011 ዓ.ም ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ጠይቆ ነበር።

በወቅቱም የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ተረኛ ችሎት ጉዳዩን መርምሮ መልስ ለመስጠት ለነሐሴ 30 ቀን 2011 ዓ.ም ቀጠሮ ይዞ ነበር።

በዚህ የወንጀል ተግባር በሪሁን አዳነ፣ መርከቡ ኃይሌ፣ ስንታየሁ ቸኮል፣ ማስተዋል አረጋ እና ኃየሎም ብርሃኔ በፖሊስ ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ይገኛሉ። ተጠርጣሪዎቹ ፖሊስ የጠየቀውን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ሰኔ 23 ቀን 2011 ዓ.ም በዋለው ችሎት ቀርበው ተቃውመዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-06