TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ጡሎ ወረዳ ሂርና ከተማ ሀሰተኛ የብር ኖቶችን በመጠቀም ለመገበያየት ሞክሯል የተባለው ግለሰብ አንድ ዓመት ከስድስት ወር በሚደርስ ጽኑ እስራት እንዲቀጣ የተወሰነበት መሆኑን ፖሊስ አስታወቀ።

አብረሀም ገብረ መድን ተንሳይ የተባለው ይሄው ግለሰብ ነሐሴ 20/2011ዓ.ም በሂርና ከተማ 15 ሺህ ሀሰተኛ የብር ኖቶች በመያዝ  ለመገበያየት ሲሞክር እጅ ከፍንጅ ተደርሶበታል።

የጡሎ ወረዳ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል መከላከል እና ቁጥጥር የስራ ሂደት መሪ ሳጅን በላይ አስራት ለኢዜአ እንደገለጹት ግለሰቡ የአካባቢው ህብረተሰብ ለፖሊስ በሰጠው ጥቆማ መሰረት ሊይዝ ችሏል።

በተጠርጣሪነት ተይዞ የቆየው ግለሰቡ በአቃቢ ህግ ከሳሽነት ጉዳዩን ሲከታተለው የነበረው የወረዳው የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ነሐሴ 27/2011ዓ.ም  በዋለው ችሎት ጥፋተኝነቱን አረጋግጦ የቅጣት ውሳኔውን አስተላልፎበታል። ህብረተሰቡ መሰል የወንጀል ድርጊቶችን ለፖሊስ በመጠቆም እያደረገ ያለውን ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥል ሳጅን በላይ አሳስበዋል።

Via ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FAKE የ2012 ዓ/ም የተማሪዎች ቅበላ ቀናት በሚል በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች እየተሰራጨ የሚገኘው ይህ መረጀ ሀሰተኛ ነው።

💫እንደ TIKVAH-ETH የሚደርሱንን የጥሪ ቀናት እናቀርባለን!! የሚመለከታችሁ የዩኒቨርሲቲ ክፍሎች እና የተማሪ ህብረቶች ጥሪዎቻችሁን @tsegabwolde ማድረስ እንደምትችሉ በዚህ አጋጣሚ ለማሳወቅ እንወዳለን!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የመግቢያ ቀናት ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች!

©#Habtish
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአፍሪካ ህብረት በደቡብ አፍሪካ እየተፈፀመ ያለውን ጥቃት አወገዘ፡፡ የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀ-መንበር ሙሳ ፋኪ ማሀማት በደቡብ አፍሪካ በሚገኙ የሌላ ሀገራት ዜጎች ላይ እየተወሰደ ያለውን የሀይል እርምጃ ተቀባይነት የሌለው ተግባር ነው ሲሉ አውግዘዋል።

የዜጎችን ንብረት መዝረፍም ሆነ የማጥፋት አካሄድ በህብረቱ የሚወገዝ መሆኑን አንስተዋል፡፡ ሊቀ-መንበሩ እንደተናገሩት ቀደም ሲል በታሰሩት የሀገሪቱ ባለስልጣናት እንዲህ አይነቱ ተግባር ይበረታታ እንደነበር ገልፀዋል፡፡

የሰዎችን ሕይወትና ንብረት ለመጠበቅ ተጨማሪ አፋጣኝ እርምጃዎች መወሰድ አለባቸው ያሉት ሊቀመንበሩ የደቡብ አፍሪካ መንግስት ወንጀለኞች ለፈፀሙት ድርጊት ተጠያቂ መሆናቸውን እንዲያረጋግጭ አሳስበዋል። እንዲሁም ኢኮኖሚያዊና ሌሎች ተጨማሪ ውድመት ላጋጠማቸው ሰዎች ትክክለኛ ፍትህ መሰጠት አለበት ብለዋል፡፡

የህብረቱ ሊቀ-መንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት እነዚህን ወንጀለኞች ለመያዝ በሚደረገው ጥረት ህብረቱ ለደቡብ አፍሪካ መንግስት ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።

Via #EthioFM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሁለት ዜጎቻችን ደ/አፍሪካ ውስጥ ሞቱ!

በደቡብ አፍሪካ ውስጥ ሁለት ኢትዮጵያዊያን ንብረታቸውን ከዘራፊዎች ለማትረፍ በመሸሽ ላይ እያሉ ባጋጠማቸው የመኪና አደጋ መሞታቸው ተነግሯል። ኢትዮጵያዊያኑ የመኪና አደጋው የገጠማቸው ደቡብ አፍሪካ ዋና ከተማ ጆሃንስበርግ አቅራብያ በሚትገኝ ጁሊየስ የምትባል መንደር ውስጥ ወደሚገኝ ንብረታቸው እየነዱ በነበሩበት ወቅት መሆኑ ታውቋል።

ኢትዮጵያዊያኑ ወደ ሱቆቻቸው ለመሄድ የተነሱት የአካባቢው ነዋሪዎች የስደተኞች ሱቆችን እየዘረፉ ነበር በተባለበት ወቅት እንደነበረ በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያዊያን ማኅበረሰብ ምክትል ሰብሳቢ ናህሊ ሙሳ ለቪኦኤ ገልፀዋል።

Via #VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አደንዛዥ ዕፅ ሲያዘዋውሩ የነበሩ 4 ግለሰቦች በፖሊስ ተያዙ!

በኢሉአባቦር ዞን የአሌ ወረዳ ፖሊስ ዘጠኝ ኪሎ ግራም የሚመዝን አደንዛዥ ዕፅ ሲያጓጉዙ ደርሼባቸዋል ያላቸውን አራት ግለሰቦች መያዙን አስታወቀ። ግለሰቦቹ አደንዛዥ ዕጹን በተሽከርካሪ ጭነው ከአዲስ አበባ ወደ ጋምቤላ በማጓጓዝ ለማሳለፍ ሲሞክሩ ነው ትናንት ከረፋዱ አምስት ሰዓት አካባቢ የተያዙት።

የወረዳው ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ክፍል ተወካይ ሳጅን ኦላና መንግስቱ እንደገለጹት ግለሰቦቹ እስከ ጎሬ ከተማ ከመጡበት ተሽከርካሪ በመውረድ የፍተሻ ኬላ በእግራቸው ለማቋረጥ ሲሞክሩ ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መያዝ ተችሏል። በአሁኑ ወቅት በግለሰቦቹ ላይ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን ያመለከቱት ሳጅን ኦላና በእጃቸው የተያዘው አደንዛዥ ዕፅም ለተጨማሪ ምርመራ ወደ አዲስ አበባ እንደሚላክ አስታውቀዋል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ተመልከቱ⬆️

በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ #የናይጄሪያ ዜጎች ንብረታቸው እንዴት እንደወደመባቸው ተመልከቱ። #SOUTHAFRICA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አስቸኳይ ማሳሰቢያ!

በመላው ደቡብ አፍሪካ ለምትኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሙሉ የተላለፈ አስቸኳይ የማሳሰቢያ መልዕክት!

ምክንያቱ በውል ባልታወቀ ሁኔታ ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ በደቡብ አፍሪካ የተለያዩ አካባቢዎች በተለይ በውጭ አገራት ዜጎች በሚንቀሳቀሱ የንግድ ድርጅቶች ላይ ዘረፋዎች እየተፈጸሙ እንደሚገኝ እንዲሁም ግጭቶችና አለመረጋጋቶች እየተፈጠሩ እንደሆነ ከተለያዩ የማህበረሰባችን አባላት እና ከማህበራዊና ሌሎች የሚዲያ ምንጮች እንዲሁም ከተባበሩት መንግስታት ደረጅት የተገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

ስለሆነም በቅድሚያ በእነዚህ ዘረፋዎች፣ ግጭቶችና አለመረጋጋቶች ሰበብ በህይወት እና በአካል ላይ አደጋ ሊያደርሱ ከሚችሉ ማናቸውም አይነት ፍጥጫዎች በማራቅ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንድታደርጉ በጥብቅ እያሳሰብን፣

1. ወቅታዊ ሁኔታው እስኪረጋጋ ድረስ በሱቆች ውስጥ የሚቀመጡ ውድና በቀላሉ ወደ ገንዘብ የሚቀየሩ ንብረቶች እንዳይያዙ ማድረግ፣ ከተቻለም ሁኔታው እስከሚረጋጋ ድረስ ሱቆችን አለመክፈት፣

2. እርስ በእርስ መረጃዎችን በመለዋወጥ ሰላማዊ ያልሆኑ ዝንባሌዎች ሲያጋጥሙ ወዲያውኑ ለአካባቢው ፖሊስ ሪፖርት ማድረግ፣

3. በተደራጀ መንገድ ከአካባቢው የጸጥታ አካላት እና ማህበረሰብ ጋር በቅርበት በመስራት ችግሮች እንዳይከሰቱ ከተከሰቱም በውይይት እንዲፈቱ መስራት፣ እንደሚያስፈልግ እየጠቆምን፣ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ መረጃዎችን ለመስጠትና ድጋፍ ለማግኘት የኤምባሲያችንን ቀጥታ የስልክ ቁጥሮች 0123464257 እና 0123462947 መጠቀም የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡

በሌላ በኩል የደቡብ አፍሪካ የመንግስት አካላት በዘላቂ የመፍትሄ ዕርምጃዎች ላይ የበኩላቸውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ተጨማሪ እንቅስቃሴዎች የተደረጉ ሲሆን፣ በተለይ ሚሲዮናችን የሚያስተባብረው በኢጋድ አምባሳደሮች ፎረም በአፍሪካውያን ዜጎች ላይ የደረሰው ችግር እንደ አንድ አጀንዳ ተወስዶ የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ መ/ቤት ሃላፊዎች በተገኙበት ውይይት ተደርጎበታል፡፡ መ/ቤቱ ለጉዳዩ አጽንዖት ሰጥቶ የፎረሙ አባል አገራት ከክብርት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ጋር መገናኘት እንዲችሉ፣ ተከታታይነት ያለው የጋራ ፕላትፎርም እንዲፈጠርና በአገሪቱ በሚኖሩ የውጭ ዜጎች ጉዳይ ምክክሮችን ለማድረግ ሁኔታዎችን እንዲያመቻችልን ተጠይቋል፡፡

አሁንም በየአካባቢው እያጋጠሙ ያሉ ዘረፋዎች፣ ግጭቶችና አለመረጋጋቶች ዜጎች ላይ የከፋ ጉዳት ሳያስከትሉ መፍትሄ እንዲያገኙ እንዲሰራ መረጃዎችን ለሚመለከታቸው የደቡብ አፍሪካ የመንግስት አካላት አቅረብን በመከታተል ላይ እንገኛለን፡፡
ኤምባሲው ለዜጎች መብትና ደህንነት መጠበቅ የጀመረውን ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥልና በዚህ ረገድ መረጃዎችን ተከታትሎ ለማህበረሰባችን የሚያቀርብ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን፡፡

ከሠላምታ ጋር
የኢትዮጵያ ኤምባሲ
በደ/አፍሪካ የምትገኙ ቤተሰቦቻችን ማንኛውም አይነት ምልዕክታችሁን በ @tsegabwolde @tsegabtikvah እንዲሁም በ0919743630 በመደወል ማስቀመጥ ትችላላችሁ!!

💫በርከት ያሉ የTIKVAH-ETH ቤተሰቦች በደቡብ አፍሪካ የተለያዩ ከተሞች ይገኛሉ የደቡብ አፍሪካን ሁናቴ እየተከታትለን እናደርሳለን!!

በውጭ ዜጎች ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶችን አጥብቀን እናወግዛለን!
የኩላሊት ህሙማን ነፃ የኩላሊት እጥበት አገልግሎት እንዲያገኙ እየተሰራ ነው!

ከአዲሱ ዓመት ጀምሮ በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ የኩላሊት ህሙማን ነፃ የኩላሊት እጥበት አገልግሎት የሚያገኙበትን እድል ለማመቻቸት እየሰራ መሆኑን የኩላሊት ህመምተኞች እጥበት በጎ አድራጎት ድርጅት ገለፀ። የመንግስት፣ የግል ተቋማትና ኩባንያዎች ስራ አስኪያጆች ላይ ያተኮረ የኃብት ማሰባሰብ መርሃ ግብር ከመጪው ዓመት ጀምሮ የሚተገበር መሆኑንም አስታውቋል።

በአሁኑ ወቅት በመላው አገሪቱ 40 ሺህ የሚጠጉ የኩላሊት ህሙማን በየሳምንቱ እስከ 3 ጊዜ የኩላሊት እጥበት ህክምና ያስፈልጋቸዋል። እያንዳንዱ ታካሚም ለኩላሊት እጥበት በየሳምንቱ እስከ ሶስት ሺህ ብር እንደሚያስፈልገው ይነገራል።

Via ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ለነሐሴ 30 አስቸኳይ ምልዓተ ጉባዔ መጥራቱ ተሰምቷል፡፡ ጉባዔው በቤተ ክርስቲያኒቷ ላይ ሲፈጸሙ ለቆዩ ጥቃቶች እና ጥያቄዎች እየሰጠ ባለው ምላሽ እና በቅርቡ ራሱን “የኦሮሚያ ቤተ ክህነት አደራጅ” ሲል የሰየመው ኮሚቴ ባወጣው መግለጫ ላይ ይነጋገራል፡፡ ሲኖዶሱ ምን ያድርግ በሚለው ላይ የተለያዩ አቋሞች እንዳሉ ተሰምቷል፡፡ በየደረጃው ጠንካራ አቋም እንዲወሰድ የሚጠይቁ ድምጾች እየበዙ መምጣታቸው፣ በሌላ በኩል ደሞ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ለቤተ ክርስቲያኗ ሲኖዶስ አንድነት ያደረጉት አስተዋጽዖ የጉባዔውን አቅጣጫ የሚወስኑ እንደሚሆኑ ዋዜማ ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡

Via ዋዜማ ሬድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በደቡብ ክልል ባለፈው አንድ አመት ተከስቶ የነበረው አለመረጋጋት በቱሪዝም ፍሰቱ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ማሳደሩን የክልሉ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ አስታወቀ። ቢሮው የ2011 ዓ.ም አፈጻጸምና 2012 እቅድ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር በዲላ ከተማ እየመከረ ነው፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ ቻይና ከተሞች በሳምንት የሚያደርጋቸውን 35 በረራዎች ወደ 50 ለማሳደግ መዘጋጀቱን አቶ ተወልደ ገብረማርያም ተናግረዋል። ወደ ጃፓንና ኢንዶኔዥያ የሚያደርጋቸውን ለማሳደግ ወደ ቪየትናም ለመጀመር ወጥኗል።

Via #EshetBekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETH /AFAAN OROMOO/👇

የተለያዩ ቋንቋዎችን ለሚናገሩ፣ ለሚያደምጡና ለሚያነቡ የቤተሰባች አባላት በቅርቡ በሌሎችም የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ወደእናተ መድረስ እንጀምራለን!

Join👇
https://t.iss.one/joinchat/AAAAAFEzH7Ywz6n7V8mzcQ
በድሬዳዋ የቺኩንጉንያ መከላከያ የኬሚካል ርጭት ተጀመረ!

በድሬዳዋ ከተማ የተከሰተውን የቺኩንጉንያ ወረርሽኝ በሽታ ለመከላከል የኬሚካል ርጭት መካሄድ ጀመረ። በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ስር ባለው የበሽታ መከላከል ክፍል ባለሙያ የሆኑት አቶ ተፈሪ መንገሻ ለጀርመን ድምፅ ራድዮ እንደተናገሩት ባለፉት ሶስት ቀናት ብቻ በግቢ ደረጃ ያሉ 1,712 ቤቶች ኬሚካል ተረጭቶባቸዋል።

የኬሚካሉ ርጭት የተደረገው በከተማይቱ የበሽታው ስርጭት ከፍ ብሎ በታየባቸው አምስት የተመረጡ ቦታዎች ላይ መሆኑን ባለሙያው ገልጸዋል። የኬሚካል ርጭት ውጤታማነቱን በመገምገም በቀጣይ በሁሉም አካባቢዎች የማዳረስ ስራ ይሰራልም ብለዋል።

ካለፈው ሐምሌ ወር ጀምሮ በድሬዳዋ የተከሰተው የቺኩንጉንያ ወረርሽኝ ሃያ ሺህ ሰዎችን ለህመም መዳረጉን የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ትላንት በሰጠው መግለጫ አስታውቋል። ይህ ቁጥር በግል የህክምና ተቋማት ሄደው የታከሙ ታማሚዎችን እና ወደ መንግስትም ሆነ ወደ ግል ህክምና ተቋም ያልሄዱ እና በቤታቸው ማስታገሻ በመጠቀም የቆዩ ታማሚዎችን ቁጥር አይጨምርም።

የፌደራል ጤና ጥበቃ ሚንስቴርን ጨምሮ የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር እያደረጉ ባለው ወረርሽኙን የመግታት ጥረት የተለያዩ ስራዎችን እያከናወኑ ስለመሆናቸው ይገለፅ እንጂ የችግሩ አሳሳቢነት አሁንም እንደቀጠለ ነው። ካለፉት ቀናት ወዲህ የድሬዳዋ ከተማ የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞች ለወረርሽኙ መተላለፍ መንስኤ የተባለችው ናት የተባለችው ትንኝ መራቢያ ቦታን ውሃ የማፋሰስ ስራ እያከናወኑ መሆኑ ተገልጿል። ለችግሩ ተጋላጭ በተባሉ ቦታዎች መካሄድ የጀመረው የቤት ለቤት ኬሚካል ርጭት ቢዘገይም ለመፍትሄው አንድ አስተዋፅኦ ይኖረዋል የሚል ተስፋ አሳድሯል።

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አገልጋይ ዮናታን አክሊሉ!

• ግጭትን በመሸሽ ወይም በማምለጥ ከቶውንም ለውጥ አናመጣም። የተሻለ አገርና ቤትም አንገነባም።

• ብዙ ጊዜ ግጭትና ግፊት የሚመጣው አለቅጥ ምቾት ከመፈለግና በተቃራኒው በጎረቤታችን ያለው ልዩ ምቾት በሚፈጥርብን ቅንዓት ነው።

• ግጭት ለምን ተነሳ አይባልም ። ጉርብትና በራሱ፣ አብሮ መኖር በራሱ፣ የሚያማዝዘው ቅራኔ አይጠፋምና።

• ግጭት እንዴት ሊነሳ ቻለ ብሎ መፍትሔውን መፈለግና እንዴትነቱን ማጤን ከአስተዋይ ልብ ይጠበቃል። አሁን ከእኛ የሚፈለገው ይህ ነው።

• የሰው ልጅ በራሱ ከራሱ ጋርም ይጋጫል። ሰው በህይወቱ የሚያጋጥመውን ነገር፣ በሥርዓት ማየት ሲያቅተው ከራሱ ጋር ይጋጫል። በአንድ ጊዜ ሁለት ሶስት ነገሮች ተደራርበው ሲገጥሙት ወይም አንዱን ችግር ተጋፍጦ ሳያበቃ ሌላኛው ሲጨመርበትና ለውሳኔ ሲቸገር ከመፍትሔው ይልቅ ችግሩ ላይ ሲያፈጥ በግለ ግጭት ውስጥ ገብቶ ይወጠራል።

• አንደኛው በተፈጠረብን ምቾት ሳቢያ የበለጠና የተሻለ ምቾት ፍለጋ የጎረቤት ድንበር እንገፋለን ፤የጎረቤት ሰው እንጋፋለን፤ ግጭትም ይፈጠራል። በሌላ ወገን ደግሞ፣ ለፍቶ ጥሮ ግሮ ያገኘው ሃብት ዓይኖቻችንን ሲያቀላብን የሌላውን መልካም ቤት ፣ መኪና፣ ሰው እንደፍራለን፣ እናንጓጥጣለን። በሁሉም ረገድ ግን ግጭታችን የፍላጎቶቻችን እስረኞች ከመሆን የሚመነጭ የሰብዕና ግድፈት የሚመነጭ ዋልጌነት ነው።

#አዲስ_ዘመን

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-03-2
#NEW

ማስታወቂያ!

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ በ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በሜዲካል ማይክሮ ባይሎጂ በድህረ ምረቃ መርሃ ግብር መማር የሚፈልጉ ተማሪዎችን ማስተማር ይፈልጋል፡፡

በትምህርት መስኩ ለመማር የሚያስፈልገው መስፈርት፡-

• የመጀመሪያ ዲግሪ በሜዲካል ላብራቶሪ ቴክኖሎጂ ወይም ቨተርነሪ ሜዲስን ወይም በህክምና ዲግሪ ያለው ያላት

ተመዝጋቢዎች በምዝገባ ወቅት የሚከተሉትን ማስረጃ ይዘው መቅረብ አለባቸው፦

• የመጀመሪያ ዲግሪ ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ
• ስቱደንት ኮፒኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ
• አንድ ጉርድ ፎቶ ግራፍ
• ከመንግስት ተቋም ለምትመጡ የስፖንሰር ሺፕ ደብዳቤ
• በግል ለመማር የሚፈልጉ ኮሌጁ የሚጠይቀውን ወጪ መክፈል አለባቸው
የምዝገባ ቀን፡ ከነሐሴ 29 ቀን 2011 እስከ መስከረም 6 ቀን 2012

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ
ሪጅስተራር ጽሕፈት ቤት

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#HAWASSA በሃዋሳ ከተማ አንጻራዊ ሰላም መስፈኑን ተከትሎ የተቀዛቀዘው የቱሪስት ፍሰት እየተነቃቃ መምጣቱን የተለያዩ የከተማዋ ነዋሪዎች ገለጹ። የቱሪስት ፍሰቱን የበለጠ ለማሳደግ የክልሉ መንግስት፣ የከተማ አስተዳደሩና ባህልና ቱሪዝም ቢሮ በትኩረት እንዲሰሩም ነዋሪዎቹ ጠይቀዋል።

Via #ENA

የTIKVAH-ETH ቤተሰብ የሆኑና በሃዋሳ ከተማ የሆቴል ባለቤት የሆኑ አባላቶችም ከላይ ያለውን መረጃ አረጋግጠው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከተማዋ እጅጉን እየተነቃቃች እንደሆነ እና ተቀዛቅዞ የነበረው ገቢያቸውም አሁን ላይ መነቃቃት ማሳየቱን ገልፀዋል። የከተማዋን ሰላም ማስጠበቅ እንዲሁም ለእድገቷ መትጋት የሁሉም ሃላፊነት ነው ብለዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የመጀመሪያው አገር አቀፍ የፍቅርና የሰላም ጉዞ ሊካሄድ ነው!

በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ የፍቅርና የሰላም ጉዞ የፊታችን ጳጉሜ 3/2011‹‹ ጉዞ በአዲስ አመት ለሰላምና ለአንድነት›› በሚል መሪ ቃል ከአዲስ አበባ እስከ ደብረ ዘይት ይካሄዳል፡፡

የሰላም ተጓዥ አገልግሎት ድርጅት በሀገራችን ዘላቂ ሰላምና ፍቅርን ለመፍጠር እና ለማስፈን የተለያዩ የፍቅርና የሰላም ጉዞዎችን ለማካሄድ ማቀዱንና ይህንንም የፊታችን ጳጉሜ 3/2011 በሚያካሄደው የጉዞና የጉብኝት ፕሮግራም እንደሚጀምር የድርጅቱ መስራች አቶ ቸርነት ጥላሁን ተናግረዋል፡፡

አቶ ቸርነት በሰጡት መግለጫ የሰላም ተጓዥ አገልግሎት ድርጅት ወደ ፊት በሀገር ውስጥ በሚፈጠሩ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ችግሮች ሳቢያ በሀገሪቱ የተከሰቱ ግጭቶችን ለመፍታትና ለማረጋጋት ከሃይማኖት አባቶችና ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር በመሆን ለመስራት ማቀዱን አስታውቀዋል፡፡

የሰላም ተጓዥ አገልግሎት ድርጅት ከሰላም ሚኒስቴር ተለይተው በተሠጡት አካባቢዎች ላይ የተለያዩ የሰላምና የእርቅ ስራዎችን በመስራት የሀገሪቱን የቱሪስት መስብነት ለማስተዋወቅና በ2014 ኢትዮጵያ የህዝቦቿ ሰላም ተመልሶ በቱሪዝም መዳረሻነትና በሀገር ውስጥ ቱሪዝም ከአፍሪካ 5 ሀገራት አንዷ እንድትሆን እንደሚሰራ በመግለጫው ተጠቅሷል፡፡

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NEW

ማስታወቂያ!

የ12ኛ ክፍል ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤታችሁ ላይ ቅሬታ ላቀረባችሁ ተፈታኞች፦

"በ2011 ዓ/ም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ተፈትናችሁ በውጤታችችሁ ላይ ቅሬታ ያቀረባችሁ ተፈታኞች #የቅሬታችሁን ፍሬ ሃሳብ አብዛኞቹን አይተናል። ከዚህ በመቀጠልም የምንሰጣችሁን #የቅሬታችሁን ምላሽ በተመለከተ በድረገፃችን www.neaea.gov.et:8080 በኩል የምናሳውቃችሁ ሲሆን እንደተለመደው የመፈተኛ ቁጥራችሁን በማስተገባት ታዩታላችሁ። ይህም ከዛሬ ጀምሮ የሚለቀቅ ስለሆነ በትዕግስት እንድትጠብቁ እንጠይቃለን።"

የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ

ፎቶ: የተማሪዎች
@tsegabwolde @tikvahethiopia