TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የጣና ጉዳይ ይመለከተናል፤ ያሳስበናል!!

#ትኩረት_ለጣና_ሃይቅ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
“የወጣቱ ጥያቄ የዳቦ ጉዳይ ነው የኢኮኖሚ ጉዳይ ነው፡፡ እዚህ ላይ በጋራ መስራት አለብን፡፡ ሁላችንም ተባብረን የኢኮኖሚ ማሻሻያው ተግባራዊ ማድረግ አለብን፡፡ የፖለቲካ ልዩነታችን ይህቺ ሀገር አንገቷን ቀና እንድታደርግ ከማድረግ እና የህዝቡን ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ ሊመልሰን አይገባም፡፡ በሚያለያየን ነገር እንከራከራለን፡፡ አንድ ሀገር አንድ ህዝብ ነው ያለን እና እሱ ላይ በጋራ እንሰራለን፡፡” ዶ/ር እዮብ ተካልኝ የገንዘብ ሚኒስትር ዲኤታ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያን አስመልክቶ በተደረገ ውይይት ላይ ከተናገሩት የተወሰደ፡፡

Via #AMN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የስኳር ኮርፖሬሽን ምንም ያወጣሁት የአክሲዮን ሽያጭ የለም አለ!

የኢፌዲሪ ስኳር ኮርፖሬሽን በመንግሥትም ሆነ በኮርፖሬሽኑ በኩል ምንም አይነት ለሽያጭ የወጣ የፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች የአክስዮን ሽያጭ አለመኖሩን አስታወቀ። ኮርፖሬሽኑ እንዳስታወቀው ‹‹ኢትዮ ስኳር ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማኅበር›› የተባለ ኩባንያ በመገናኛ ብዙኃን ከሚያስነግረው ማስታወቂያ ጋር በተያያዘ በኅብረተሰቡ ዘንድ ኮርፖሬሽኑ አክስዮን እንደሸጠ ተደርጎ ብዥታ በመፈጠሩ እና ይህንም ተከትሎ በርካታ ግለሰቦች ወደ ኮርፖሬሽኑ በመምጣት አላስፈላጊ ጫና እየተፈጠረበት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ይህን መግለጫ ለመስጠት እንደተገደደ አስታውቋል።

Via #AddisMaleda
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#HORRA

በአዳማ ከተማ የሚገኘው ሆራ ትሬድንግ የባጃጅ ሞተር መገጣጠሚያ ፋብሪካ ከ462ሺህ ብር በላይ ግምት ያላቸው የመማሪያ ቁሳቁሶች ለችግረኛ ልጆች እንዲውሉ ድጋፍ አደረገ።

የፋብሪካው ስራ አስኪያጅ  አቶ ጀማል ኢብራሂም ድጋፉን ለከተማው አስተዳደር ባስረከቡበት ወቅት እንዳሉት ድጋፉ በአስተዳደሩ አራት ክፍለ ከተሞች ለተመለመሉ የችግረኛ ቤተሰብ ልጆችን  ለማገዝ የሚውል ነው። ለእነዚህ 2ሺህ 150 ልጆች በ2012 የትምህርት ዘመን  የሚያስፈልጋቸውን  የትምህርት ቁሳቁስ ማበርከታቸውን አመልክተዋል።

ከድጋፉም መካከል  25ሺህ 500 ደብተሮች እና ከ8ሺህ በላይ እስክሪፕቶዎች ይገኙበታል። ያደረጉት ድጋፍ የዜግነት አገልግሎት ግዴታቸው መሆኑን ስራ አስኪያጁ አመልክተው በቀጣይም ለተቸገሩ ወገኖች እገዛቸውን እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቅርቡ ባፀደቀው የምርጫ ፣የፖለቲካ ፓርቲዎች እና የስነ ምግባር ደንብ አዋጅ ላይ እየመከረ ነው። ምክር ቤቱ አዋጁን በተመለከቱ አተያዮች ፣ አረዳድና አመለካከቶች ላይ እመክራለሁ ያለ ሲሆን ከህግና ስርዓት ያፈነገጡ ግንኙነቶችን በማድረግ የህዝብን ሰላምና ደህንነት ለማደፍረስ በሚሞክሩ ፖርቲዎች ዙሪያ ለመምከር የሚያስችል አጀንዳ ስለመያዙም አስታውቋል።

ምንጭ፦ ኢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
animation.gif
345 KB
እንደ አማዞን ደን እሳት ያልተጮኸለት የአንጎላና ኮንጎ የደን እሳት!

ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ብዙውን ትኩረት የሰጡት በብራዚል ለሚገኘው የአማዞን ደን ሰደድ እሳት ቢሆንም፣ በአማዞን የተከሰተው ሰደድ እሳት በአንጎላም ሆነ በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ከተከሰተው የደን ሰደድ እሳት እንደማይበልጥ የናሳ መረጃ አመልክቷል፡፡

አልጀዚራና ቢቢሲ እንደዘገቡትም፣ በማዕከላዊ አፍሪካ በሚገኙት በሁለቱ አገሮች ደኖች የተከሰተው እሳት በአማዞን ከተከሰተው በሦስት እጥፍ ያየለ ነው፡፡

በቅርቡ በአማዞንም ሆነ በማዕከላዊ አፍሪካ ደኖች ላይ የተነሳው ሰደድ እሳት መጠን ሲታይ ከአንጎላና ከኮንጎ በመቀጠል የብራዚሉ አማዞን በሦስተኛ ደረጃ ሲገኝ ከብራዚል በመለጠቅ የዛምቢያ የደን ሰደድ እሳት አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡ የብራዚል ጎረቤት ቦሊቪያ ደግሞ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ የፖለቲካ ሚዛኑ ያደላውና የመገናኛ ብዙኃንን የላቀ ዘገባ ያገኘው ግን የአማዞኑ ነው፡፡

ከትላንት በስቲያ የተለቀቀውና መረጃው ከመለቀቁ በፊት በነበሩ 48 ሰዓታት ውስጥ የተከሰተውን ሰደድ እሳት አስመልክቶ ሁለት ሳተላይቶችን በመጠቀም የምድር የአየር ንብረት መረጃን የሚለቀው ሞዲስ (ኤምኦዲአይኤስ) እንዳስታወቀው፣ በአንጎላ 6,902፣ በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ከንጎ 3,395 እንዲሁም በብራዚል 2,127 ሥፍራዎች ላይ የደን እሳቶች ተከስተዋል፡፡

በማዕከላዊ አፍሪካ ደን የተከሰተው ሰደድ እሳት፣ በብራዚል አማዞን ቀይ መቀነስ ሠርቶ እንደሚንቦገቦገው እሳት ሁሉ ከጋቦን አንጎላ ድረስ ቀይ ሰንሰለት ሠርቶ ይታያል ሲል የናሳ ሳተላይት ምስልን ጠቅሶ ፍራንስ 24 ዘግቧል፡፡

Via #Reporter
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአለም የጤና ድርጅት ማስጠንቀቂያ ሰጠ!

በምስራቅ አፍሪካ ተመሳስለው የተሰሩ ጸረ- ባክቴርያ (አንቲባዮቲክስ) መድሃኒቶች በመሰራጨታቸው ጥንቃቄ እንዲደረግ የአለም የጤና ድርጅት አሳሰበ፡፡ በኬንያ ተመሳስሎ የተሰራ ጸረ ባክቴርያ መድሃኒት በመድሃኒት ቤቶች በመሰራጨቱ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የአለም የጤና ድርጅት አሳስቧል፡፡

ድርጅቱ እንዳለው ተመሳስሎ የተሰራ “ኦግመንቲን” የተባለ ጸረ ባክቴርያ መድሃኒት በኬንያ በተለያዩ መድሃኒት ቤቶች በብዛት የተገኘ በመሆኑ ኡጋንዳን ጨምሮ ሌሎች ምስራቅ አፍሪካ ሃገራት ሊገባ እንደሚችል ተገምቷል፡፡

“ኦግመንቲን” የተባለውና በብዛት የሚታወቀው ጸረ ባክቴርያ መድሃኒት በባክቴርያ አማካኝነት የሚከሰቱ በርካታ ህመሞችን እንደሚያክም ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ የአለም የጤና ድርጅት ባወጣው መግለጫም ተመሳስሎ የተሰራው የዚህ መድሃኒት አስተሻሸግ ከትክክለኛው ጋር እንዲመሳሰል ተደርጎ የተሰራ ነው ብሏል፡፡

የመድሃኒቱ ትክክለኛ አምራች ተመሳስሎ ስለተሰራው መድሃኒት የሚያውቀው ነገር እንደሌለ የተናገረ ሲሆን መድሃኒቱን የወሰዱ ሰዎች ወደ ህክምና ተቋማት በመሄድ ባለሙያ እንዲያማክሩም ጥሪ ቀርቧል፡፡

የኬንያ የመንግስት ባለስልጣናትም ኬንያውያን በአለም የጤና ድርጅት መልዕክት መሰረት ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መግለጫ አውጥቷል፡፡ በአፍሪካ ተመሳስሎ በተሰራ “ኦግመንቲን” በተባለው መድሃኒት ላይ የአለም የጤና ድርጅት ማስጠንቀቂያ ሲሰጥ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው፡፡

ምንጭ፦ቢቢሲ/AMN/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢትዮ ቴሌኮም የቀጣይ ሶስት አመት ስትራቴጂውን ይፋ አደረገ። የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት፥ ስትራቴጂው ተቋሙን ተወዳዳሪ፣ ብቁና ተመራጭ ለማድረግ የተዘጋጀ ነው።

ስትራቴጂው ከሃምሌ 2011 እስከ ሰኔ 2014 ዓ.ም ድረስ ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን፥ በዘርፉ ሊፈጠር የሚችለውን ውድድር ለመምራት የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ስራ ያካተተ መሆኑም ተጠቁሟል። በቀጣዮ አመትም የተቋሙን የደንበኞች ቁጥር ወደ 50 ነጥብ 4 ሚሊየን በማሳደግ ገቢውን 45 ነጥብ 4 ቢሊየን ለማድረስ መታቀዱንም ገልፀዋል።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
የሰላም ሚኒስቴር ለወጣቶች ቅዳሜ ነሐሴ 25 ቀን ጠዋት 3 ሰዓት ጀምሮ የስነ ጽሑፍ ወርክሾፕ ያዘጋጀ ሲሆን፣ የስነ ጽሑፍ ችሎታና ፍላጎት ያላችሁ በ0912632913 ደውላችሁ እንድትመዘገቡ እንጋብዛለን።

የሰላም ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
የሰላም ሚኒስቴር ለወጣቶች ቅዳሜ ነሐሴ 25 ቀን ጠዋት 3 ሰዓት ጀምሮ የቪዲዮግራፊና ፎቶግራፊ ወርክሾፕ ያዘጋጀ ሲሆን፣ የችሎታውና ለቪዲዮ/ፎቶ የተሟላ መሣሪያ ያላችሁ በ0929009002 ደውላችሁ እንድትመዘገቡ እንጋብዛለን።

የሰላም ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አረንጎዴው ጎርፍ በድጋሚ በራባት የሴቶች ግማሽ ማራቶን!!

እንኳን ደስ አለን!

ከደቂቃዎች በፊት በተካሄደው የግማሽ ማራቶን የሴቶች ውድድር ኢትዮጵያን አትሌቶች ከ 1-3 በመውጣት አስደሳች ድልን በሞሮኮ ራባት አስመዝግበዋል፡፡

🥇 ያለምዘር የኋላ
🥈 ደጊቱ አዝመራው
🥉 መሰረት በለጠ

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

እንኳን ደስ አለን!!!

Via Mekonen Hailu

TIKVAH-SPORT👇
https://t.iss.one/joinchat/AAAAAFb8M0pNEZTiGM68rg

@tsegabwolde @tikvahethiopia
0940101010 0940050505

"ውዳሴ ዳያግኖስቲክ ማዕከል የ10 ዓመት የስኬት ጉዟችንን ለ10 ተከታታይ ቀናት መልካም ነገሮችን በማድረግ ለመዘከር ተሰናድተናል፡፡ የዚሁ አካል ሆኖ ባለፉት 10 ዓመታት ያከናወነውን የጳጉሜ ለጤና መርሃግብር በዚህም ዓመት ከጳጉሜ 1-6 ይከናወናል፡፡ በማዕከላችን በሚሰጡት የሕክምና ምርመራ አገልግሎቶች ከፍላችሁ መመርመር የማትችሉ እና ለምርመራው የሐኪም ማዘዣ ያላችሁ ወገኖቻችን በስልክ ቁጥሮች 0940050505 እና 0940101010 በመደወልና በመመዝገብ ተጠቃሚ እንድትሆኑ እናሳውቃለን፡፡"

#ሼር #share
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኤጀንሲው ከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ የ174.6 ሚሊዮን ብር ክስ ቀረበባቸው!

ኤቢኤች ሰርቪስስ ኃ/የተ/የግል ማህበር የተባለው የማማከርና የምርምር ተቋም በከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ እና በኤጀንሲው አምስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ የብር 174.6 ሚሊዮን የካሣ ክስ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 241863 ከሰውና ከሰነድ ማስረጃዎች ጋር አቅርቧል፡፡

ካሣውን ከኤጀንሲው ጋር በአንድነትና በነጠላ ይከፍሉ ዘንድ የተከሰሱት ባለስልጣናት የቀድሞው የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ የነበሩትና አሁን የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር አንዱአለም አድማሴ፤ የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ታምራት ሞታ፤ የኤጀንሲው የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ታረቀኝ ገረሱ፤ የኤጀንሲው የእውቅና አሰጣጥ ዳይሬክተር አቶ አብይ ደባይ እና የኤጀንሲው የህግ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ታደሰ ናቸው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ABH-08-30
#update የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ብርቅዬ የዱር እንስሳት በሆኑት ዋልያ፣ ቀይ ቀበሮና ጭላዳ ዝንጀሮዎች ላይ በመጪው መስከረም ወር ወቅታዊ የቆጠራ ሥራ እንደሚካሄድ የፓርኩ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡ የፓርኩ ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀው በመጪው መስከረም ወር ላይ የሚካሄደው ወቅታዊ ቆጠራ ሁለተኛ ዙር ነው።

Via ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለመጀመሪያ ግዜ የከንቲባዎች ፎረም ሊካሄድ ነው!

በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ግዜ የከንቲባዎች ፎረም ሊካሄድ መሆኑን የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው የፎረሙ አላማ በዋናነት ቀጣይነት ካለው የከተሞች እድገት ጋር በተያያዘ ከተሞችን በእውቀት መምራት የሚችሉ ከንቲባዎችን ማፍራት ሲሆን ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገብ ለቻሉ ከንቲባዎች እውቅና ለመስጠትም ያለመ ነው።

በተጨማሪም ፎረሙ አሁን ያለውን ሀገር አቀፍ ብሎም አለም አቀፍ የከተሞቻችንን የልማት ትስስር ያጠናክራል ተብሏል።

በከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የከተሞች መልካም አስተዳደር እና አቅም ግንባታ ቢሮ ሃላፊ አቶ ብርሀኑ ተሾመ እንዳሉት ፎረሙ የሀገራችንን ጨምሮ የእህት ከተሞች ከንቲባዎችን ተሳታፊ በማድረግ ሰፊ ልምድ መቅሰም የሚያስችል መድረክ ይፈጥራል፡፡

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጠ/ሚር አብይ ነገ ጠዋት🛫እስራኤል ያመራሉ!

የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለጋዜጠኞች በላከው መረጃ የኢትዮጵያው መሪ ከእስራኤሉ ጠ/ሚር ቤንጃሚን ኔታናያሁ እና ከፕሬዝደንቱ ሬኡቨን ሬቭሊን ጋር ሰኞ ይገናኛሉ።

Via #EliasMeseret
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በደቡብ ክልል ጌዴኦ ዞን በጸጥታ ችግር ምክንያት ትምህርታቸውን መከታተል ላልቻሉ 14 ሺህ 500 ተማሪዎች ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ መሆኑን የዞኑ ትምህርት መምሪያ ገለጸ፡፡

የመምሪያው ኃላፊ አቶ መስፍን ደምሴ እንደገለጹት በ2010 ዓ.ም በጌዴኦ ዞን አጎራባች አከባቢዎች ተከስቶ በነበረው የጸጥታ ችግር 34 ትምህርት ቤቶች ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የተማሪዎችን የሣይንስና ሂሣብ ትምህርቶች ውጤት ለማሻሻል በትኩረት ሊሠራ እንደሚገባ ተገለጸ!

ሁሉም ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች የትምህርት ቢሮ አመራሮችና ባለሙያዎች የሚሣተፉበት 29ኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባኤ እንደቀጠለ ነው።

በጉባኤውም ትምህርት ቤቶች ለመማር ማስተማር ምቹ እንዲሆኑ በተለይም የመማሪያ ግብአቶችን በማሟላትና የመምህራንን አቅም በሚገነቡ ጉዳዮች ላይ በትኩረት ሊሠራ ይገባል ተብሏል።

Via #AMN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ወደ ሀዋሳ መግቢያ ሀበሻ ባስ ተገልብጦ ሰው ላይ ቀላል ጉዳት ደርሷል። የአደጋው መንስኤ መኪና መንገድ ላይ ላም ገብቶ ነው።" #DOLO_LEMMA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሃይማኖታዊ አስተምህሮዎች ከወዴት አሉ? ግጭቶችን መከላከል ለምን ተሳናቸው? ሐዋሳ ላይ ከተሰበሰቡት የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች አንዱ የደቡብ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት መሀመድ ሙስጠፋ ለዚህ ምክንያት ነው የሚሉትን ይናገራሉ ።

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia