TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#HORRA

በአዳማ ከተማ የሚገኘው ሆራ ትሬድንግ የባጃጅ ሞተር መገጣጠሚያ ፋብሪካ ከ462ሺህ ብር በላይ ግምት ያላቸው የመማሪያ ቁሳቁሶች ለችግረኛ ልጆች እንዲውሉ ድጋፍ አደረገ።

የፋብሪካው ስራ አስኪያጅ  አቶ ጀማል ኢብራሂም ድጋፉን ለከተማው አስተዳደር ባስረከቡበት ወቅት እንዳሉት ድጋፉ በአስተዳደሩ አራት ክፍለ ከተሞች ለተመለመሉ የችግረኛ ቤተሰብ ልጆችን  ለማገዝ የሚውል ነው። ለእነዚህ 2ሺህ 150 ልጆች በ2012 የትምህርት ዘመን  የሚያስፈልጋቸውን  የትምህርት ቁሳቁስ ማበርከታቸውን አመልክተዋል።

ከድጋፉም መካከል  25ሺህ 500 ደብተሮች እና ከ8ሺህ በላይ እስክሪፕቶዎች ይገኙበታል። ያደረጉት ድጋፍ የዜግነት አገልግሎት ግዴታቸው መሆኑን ስራ አስኪያጁ አመልክተው በቀጣይም ለተቸገሩ ወገኖች እገዛቸውን እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia