TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-EDU ላለፉት ወራት ተቋርጦ የነበረው የቋንቋ ትምህርት ቀጥሏል። ዛሬ የአፋን ኦሮሞ ቋንቋ 6ኛው ቀን ትምህርት ይቀጥላል።

√የትግርኛ
√ግዕዝ ትምህርቶችም እንዲቀጥሉ ይደረጋል!

በቋንቋ ትምህርት ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ የቤተሰባችን አባላት መድረኩ ክፍት ነው። የኢትዮጵያን ቋንቋዎችና ባህሎች ለወንድሞቻችን እናስተምራለን፤ እንማማራለን ለምትሉ ሁሉ መድረኩ ክፍት ነው።

ሀገርን መውደድ የኛ የኢትዮጵያውያን ዜጎች የሆኑ ነገሮችን ከማክበርና ከመውደድ ይጀምራል!!

TIKVAH-EDU👇
https://t.iss.one/joinchat/AAAAAEWA_-Jt2zIM5COJqw
#ETHIOPIA

የሻደይ፣ አሸንድየ እና ሶለል በዓል በክልል ደረጃ ለሁለተኛ ጊዜ በባህርዳር ከተማ የፊታችን እሁድ እና ሰኞ ይከበራል። በዓሉ ከወዲሁ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ከነሃሴ 16 እስከ 18 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ የሚከበር ሲሆን፥ በደማቅ ሁኔታ ለማክበር የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ማጠናቀቁን የአማራ ክልል ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ አስታውቋል።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ABH ምላሽ ሰጠ!

“ኤጀንሲው ሕግን መሰረት ሳያደርግ ለፈጸመው ስህተት #ይቅርታ ይጠይቀን”–ዶ/ር ማርቆስ ፈለቀ/የኤቢኤች ዋና ሥራ አስፈጻሚ
.
.
ሰኞ ነሐሴ 13/2011 ዓ.ም. ቦሌ በሚገኘው የጅማ የኒቨርሲቲ የአዲስ አበባ ካምፓስ በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የኤቢኤች ፓርትነርስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት ዶ/ር ማርቆስ ፈለቀ እንደተናገሩት “እኛ ሕግን ተከትለን እየሰራን ነው፤ ኤጀንሲውም በአዋጅ የተሰጠንን ስልጣን በፌስቡክ አይሽርም፤“ ብለዋል፡፡ “በመገናኛ ብዙሃን የተገለፀው ጉዳይም፣ የጅማ ዩኒቨርሲቲን ስም የሚያጎድፍና የተሳሳተ እንደሆነም” ዋና ሥራ አስፈጻሚው ይፋ አድርገዋል፡፡

የጅማ ዩኒቨርሲቲን እንደገና ለማቋቋም በወጣው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ አዋጅ 240/2003 አንቀጽ ሶስትን ጠቅሰው የተናገሩት ዶ/ር ማርቆስ፣ “የዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢ ጅማ ሆኖ በሌሎች ቦታዎች ላይ የትምህርት ክፍሎችና የምርምርና የሕብረተሰብ አገልግሎት ሊያቋቁም እንደሚችል” አብራርተዋል፡፡

Via #MollaMultimedia

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ABH-08-19
የሶማሌ ክልል ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባዔ ያካሂዳል!

የሶማሌ ክልል ምክር ቤት አራተኛ አስቸኳይ ጉባዔውን ነገ እንደሚያካሂድ የክልሉ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት አስታወቀ። የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ አብዱረሺድ ዓሊ እንደገለጹት ምክር ቤቱ ለአንድ ቀን በሚቆየው ጉባዔ በሁለት ረቂቅ ዓዋጆች ላይ ተወያይቶ ያጸድቃቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።

ምክር ቤቱ ከሚመለከታቸው ረቂቅ ዓዋጆች አንደኛው የክልሉን አስፈጻሚ አካላት እንደገና ለማደራጀት፣ተግባርና ኃላፊነታቸውን መወሰንን የሚመለከተው ነው። በተጨማሪም የሸሪዓ ፍርድ ቤቶችን እንደገና ለማቋቋም የተዘጋጀውን ረቂቅ ዓዋጅም መርምሮ ያጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ኃላፊው አመልክተዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ በስሩ ካሉ ኩባንያዎች ጋር በመተባበር ለ500 ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ። የቁሳቁስ ድጋፍ የተደረገላቸው የልማት ተነሺ ቤተሰብ ልጆች ሲሆኑ በእዚህም ቦርሳ፣ ደብተር እና የጽህፈት መሳሪያዎች ተበርክቶላቸዋል። ለወላጆችም ለትምህርት ቤት ማስመዝገቢያና ለተጓዳኝ ወጪዎች የሚሆን የገንዘብ ስጦታ መሰጠቱን ነው የገለጸው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ቻይና እንደ ቢትኮይን ያለ ዲጂታል የኢንተርኔት የመገበያያ ገንዘብ ወይም ክሪፕቶከረንሲ ስራ ላይ ልታውል መሆኗን አስታወቀች፡፡ ለ5 ዓመታት ጥናት ሲደረግበት መቆቱንና ወደ ስራ ለማስገባት ዝግጅት መደረጉን ነው የሀገሪቱ ብሔረዊ ባንኩ ያስታወቀው፡፡ ስልክን በመጠቀም ያላንዳች ባንክ ገንዘብ ዲጂታል በሆነ መልኩ ለማንቀሳቀስ የሚያገለግለው ክሪፕቶከረንሲ በዓለም አቀፍ ደረጃ በስፋት ትኩረት እያገኘ መጥቷል፡፡

ምንጭ፡-ኢንዲፔንደንት/etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
መተማ ስለተያዙት ተሳቢዎች በአካባቢው የሚገኙ የፀጥታ አካላት ምንም እንደማያውቁ ገለፁ!
መተማ ስለተያዙት ተሳቢዎች በአካባቢው የሚገኙ የፀጥታ አካላት ምንም እንደማያውቁ ገለፁ!

የመተማ አካባቢ የመከላከያ አዣዥ ሳያውቅ ጥይት ጭነው ወደ ሱዳን ሊሻገሩ የነበሩ “የሠራዊቱ ንብረት ናቸው” የተባሉ አምስት የጭነት ተሽከርካሪዎች በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን የአማራ ክልል ልዩ ሃይል - ምዕራብ ጎንደር ብርጌድ አዣዥ ኮለኔል ሰለሞን አሻግሬ አስታወቁ።

መነሻና መድረሻቸው የት እንደሆነ ለጊዜው ያልተገለፀው አምስቱ ባለተሳቢ የጭነት ተሽከርካሪዎች ድንበሩን ከማለፋቸው በፊት መተማ ዮሃንስ ላይ የተያዙት የአካባቢው ወጣቶች መንገድ ዘግተው ካስቆሟቸው በኋላ መሆኑ ታውቋል።

ማንኛውም ድንበር የሚያቋርጥ የመከላከያም ሆነ ሌላ ማጓጓዣ እንቅስቃሴ መረጃ ወትሮ ቀድሞ እንደሚደርሳቸው ለቪኦኤ የገለፁት በአካባቢው የሚገኘው መከላከያ ሠራዊት የ33ኛ ክፍለ ጦር አንደኛ ብርጌድ፣ አንደኛ ሻለቃ አዛዥ ኮለኔል ሸዋገኝ አብዬ አሁን ስለተያዙት አምስት ተሽከርካሪዎች ግን የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ተናግረዋል። ጉዳዩ በፖሊስና በመከላከያ ኃይሉና አጠቃላይ አካባቢው ላይ ባለ የፀጥታ ኃይል በጥምር እየተመረመረ መሆኑንም ሁለቱም አዛዦች ገልፀዋል።

Via #VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የ2019 የጤና እና ሥነ ህዝብ ዳሰሳ ቅድመ - ውጤት ይፋ ሆነ!

የ2019 የጤና እና ሥነ ህዝብ ዳሰሳ ቅድመ - ውጤት ይፋ ሆነ። በዚህም መሰረት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር (እ. ኤ.አ) የ2019 ከ2016 የዳሰሳ ውጤት ጋር ሲነፃፀር አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል።

🔷የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ሽፋን ከ35% ወደ 41%
🔷አራተኛው የቅድመ ወሊድ ክትትል ሽፋን ከ32% ወደ 43%
🔷እናቶች በሰለጠኑ ጤና ባለሙያዎች የመውለድ ሽፋን ከ28%ወደ 50%
🔷የፔንታ ሶስት ክትባት አገልግሎት ሽፋን ከ53% ወደ 61%
🔷ከአምስት አመት በታች የህፃናት ሞት ቅነሳ ከ67 ወደ 55 ከ1000 ህፃናት
🔷ከአምስት አመት በታች የህፃናት የመቀጨጭ ምጣኔ ከ10% ወደ 7% የቀነሰ ሲሆን

ከላይ ለተገለጹት ውጤቶች መመዝገብ የጤና ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት የጥረት ውጤት ሲሆን መሻሻል ባላሳዩት የጨቅላ ህፃናት ሞት ቅነሳ፣የሁሉንም አይነት ክትባት አገልግሎት ሽፋንና ከስነ - ምግብ ጋር የተያያዙ መለኪያዎች ላይ ትኩረት ሰጥተን በጋራ በመስራት የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ ይገባል ሲል ጤና ሚኒስቴር ገልጻል።

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#uodate የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር አቶ መለስ ዜናዊን 7ኛ ዓመት መታሰቢያ አስመልክቶ ጉለሌ በሚገኘው መለስ ዜናዊ መታሰቢያ ፓርክ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ተከናውኗል፡፡

በመታሰቢያ ስነ-ስርዓቱ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የመለስ ዜናዊ ፋውንዴሽን ቦርድ ፕሬዝዳንት ወ/ሮ አዜብ መስፍን የቀድሞው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር የአቶ መለስ ዜናዊን አጭር የህይወት ታሪክ አቅርበዋል፡፡

አቶ መለስ ዜናዊ በህይወት በነበሩበት ጊዜ ዓለም በአረንጓዴ ኢኮኖሚ መመራት እንዳለባት ያደረጉት ንግግር በተንቀሳቃሽ ምስል በመታሰቢያ ስነ-ስርዓቱ ላይ ቀርቧል፡፡

አቶ መለስ በዚህ ንግግራቸው ያደጉ አገራት ለምድሪቱ ስጋት የጋረጠውን የዓለም ሙቀት መጠን መጨመርን እንደ አፍሪካ ካሉ ታዳጊ አገራት ጋር በመሆን እንዲዋጉ ጠይቀው ነበር፡፡

በመቐለ ከተማም ለቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር አቶ መለስ ዜናዊ 7ኛ ዓመት መታሰቢያ ዛሬ ከሰዓት በኋላ የሻማ ማብራት ስነ-ስርዓት እንደሚካሄድ ይጠበቃል፡፡

Via #ETV
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት ለመፍጠር በየተቋማቱ የአካዳሚክ ነፃነት ሊኖር እንደሚገባ ምሁራን አሳሰቡ። የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በበኩሉ ከዚህ በኋላ ሁሉም አካላት ተጠያቂ የሚሆኑበት አሰራር ተግባራዊ አደርጋለሁ ብሏል።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህርና የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የቦርድ አባል ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ እንዳሉት፤ መንግስት በተማሪዎች ህብረት ስም ለፖለቲካ ጥቅም የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ማቆም አለበት።

በዩኒቨርሲቲዎች ያሉ የተማሪዎች ህብረት የሚባሉ ማህበራት በቡድን ተድራጅተው ተማሪዎችን እርስ በእርስ ሲያጋጩ እንጂ መፍትሄ ሲያመጡ አላየንም ብለዋል ፕሮፌሰሩ። “በዩኒቨርሲቲዎች ሰላም ስለመደፍረሱ መስማት ያሳፍራል” ያሉት ፕሮፌሰር በየነ፤ መንግስትም ለተማሪዎች የአካዳሚክ ነጻነት ሊሰጣቸው ይገባል ነው ያሉት።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በአልሸባብ ላይ ጥቃት መፈፀሟን አሜሪካ ገለፀች!

ዛሬ በተካሄደ ድንገተኛ የአየር ላይ ጥቃት የአልሸባብ ታጣቂ ህይወት ማለፉን አሜሪካ ገልፃለች። በአፍሪካ የአሜሪካ የጦር አዛዥ ሜጀር ጀነራል ዊሊያም ጌለር እንዳስታወቁት ጥቃቱ የተፈፀመው ከሶማሊያ የመንግስት ወታደሮች ጋር በጥምረት ነው። በጥቃቱ በንፁሀን ዜጎች ላይ ጉዳት አለመድረሱንም የጦር አዛዡ አስታውቀዋል። በተከታታይ እየተፈፀመበት ባለው ጥቃት የተነሳ የአልሸባብ ነፃ እንቅስቃሴ መገታቱንም ተናግረዋል።

ዛሬ በሶማሊያ ቁንያ ባሮው በተባለ አካባቢ በተፈፀመ የአየር ላይ ጥቃት የአልሸባብ ታጣቂ ህይወት ማለፉንም ገልፀዋል። አሁን ላይ ከአል ቃይዳ ጋር ትሥሥር ያለው አልሸባብም ሆነ ሌሎች የታጠቁ ኃይሎች አቅም እየተዳከመ እንደሆነም ነው የተዘገበው። ባለፈው ሳምንት በሶማሊያ ታችኛው የሸበሌ ቀጣና አልሸባብ በመንግስት ወታደሮች መጠለያ ላይ በወሰደው እርምጃ 50 የመንግስት ወታደሮች መገደላቸውን፤ ለዚህም ኃላፊነት እንደሚወስድ መግለፁ ይታወሳል።

አልሸባብ ከ2007 (እ.አ.አ) ጀምሮ የሀገሪቱን #ያልተረጋጋ መንግስት ለመጣል እየተዋጋ የሚገኝ ታጣቂ ቡድን ነው። ለምስራቅ አፍሪካ ቀጣና ሥጋት ተደርጎ የተፈረጀውን ታጣቂ ቡድን ለማጥፋትም 20 ሺህ የሚሆኑ የአፍሪካ ኅብረት አባል ሀገራት ወታደሮች እና የተባበሩት መንግስታት ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ።

ምንጭ፦ አልጀዚራ/AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በተሽከርካሪ የጦር መሳሪያ ሲያዘዋውር የተያዘው ተከሳሽ በእስራት ተቀጣ!

ተከሳሽ አብዱራህማን ዩኑስ ከሚመከለተው የመንግስት ፈቃድ ውጪ ወደ ሀገር እንዳይገቡ ገደብ የተደረገባቸው የጦር መሳሪያዎችን በተሸከርካሪ ደብቆ ወደ ሀገር ሊያስገባ ሲል ተይዞ ዐቃቤ ሕግ በመሰረተው ክስ በእስራት ተቀጥቷል፡፡

ተከሳሽ 53 ቱርክ ስሪት ሽጉጦችንና 35 ሺህ 766 ጥይቶችን የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-A50931 አ.አ በሆነ ላንድክሩዘር መኪና ደብቆ ወደ ሀገር ሊያስገባ ሲሞከር በተደረገው ክትትል በአዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ክልል ልዩ ቦታው ጣፎ አደባባይ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በተሸከርካሪው ላይ በተደረገ ፍተሻ ተይዟል፡፡

ተከሳሽ ክሱ በችሎት ተነቦለት እንዲረዳ ከተደረገ በኃላ ድርጊቱን ክዶ በመከራከሩ ዐቃቤ ሕግ እንደ ክሱ አቀራረብ ምስክሮች አሰምቷል፡፡ ፍርድ ቤቱም መዝገቡን መርምሮ ተከሳሽ ሽጉጥና ጥይት በመኪና ደብቆ በፍተሻ ስለመያዙ በመረጋገጡና መከላከልም ባለመቻሉ በተከሰሰበት ድንጋጌ ጥፋተኛ መሆኑን በይኗል፡፡

የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 8ኛ ወንጀል ችሎት መዝገቡን መርምሮ የግራ ቀኙን የቅጣት አስተያየት በመመልከት ተከሳሽ በ2 ዓመት ጽኑ እስራት እና በ5 ሺህ ብር መቀጮ እንዲቀጣ ወስኗል፡፡

ምንጭ፡- ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
እገዳ የተጣለባቸው የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው የተላለፈውን ውሳኔ እንደሚቃወሙትና ተገቢ አለመሆኑን ገልፀዋል። የበላይ አካል ጉዳዩን ይወቅል፤ ችግራችንን ይረዳልን ሲሉም መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፦

"ደብተር ይዞ ግቢውስጥ መንቀሳቀስ ለህይወት አስጊ ነበር፤ በለሊት በተኛንበት ፌደራል ፖሊስ ምንም መረጃ ሳይኖራቸው የዶርማችንን በር ሰብረው ተቀጥቅጠናል ይሄም ተማሪው ለብዙ ቀናት ከግቢ ውጪ እንዲያድር እና እስኪረጋጋ ሲጠብቅ ነበር፤ በጊዜው ኢንተርኔት ተዘግቶ ስለነበር ጩኸታችንን የሚሰማን አካል አላገኘንም። ከአንዴም ሁለቴም የተማሪውን የተስማማበትን ፊርማ አስገብተናል ግን ቀና ምላሽ አልተሰጠንም። በአጠቃላይ ውሳኔውን እንቃወማለን የበላይ አካል አቤት ይበለን።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኦሮሚያና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች አጎራባች ዞኖችና ወረዳዎች የጋራ የሰላምና የልማት ስምምነት ፈጽመዋል፡፡ ዞኖቹና ወረዳዎቹ ስምምነቱን የፈጸሙት ላለፉት ሁለት ቀናት በአሶሳ ሲካሄድ የቆየው የምዕራብ ኢትዮጵያ ክልሎች የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት መድረክ ዛሬ ማጠቃለያ ላይ ነው፡፡ ከኦሮሚያ በኩል ስምምነቱን የፈጸሙት የምዕራብ ወለጋ እና የምስራቅ ወለጋ ዞኖች እና በዞኖቹ ውስጥ የሚገኙ ጎራባች ወረዳዎች ሲሆኑ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በኩል የካማሽ ዞንና አሶሳ ዞኖች በየዞኖቹ ውስጥ የሚገኙ አጎራባች ወረዳዎች ናቸው፡፡

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአውሮፕላኖች በረራ አስተማማኝና ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን በመላ አገሪቱ በሚገኙ 12 ኤርፖርቶች ላይ ፍላይት ካሊብሬሽን እየተካሄደ መሆኑን የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን አስታውቋል። ከሐምሌ 26 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ እየተካሄደ ያለው የበረራ አጋዥ መሳሪያዎች ፍተሻ በአዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ፣ ባህርዳር፣ መቀሌ፣ ጅግጅጋ፣ ጎንደር፣ ላሊበላ፣ አክሱም፣ ሰመራ፣ አዋሳ፣ ጅማናና አርባ ምንጭ ኤርፖርቶች ነው።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መንግሥት ችላ ያለው የኑሮ ውድነት!

መንግሥት በገበያ ንረት ላይ አጥኚ ቡድኖችን አሰማርቻለሁ ቢልም የኑሮ ውድነት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ያሉ የኅረተሰብ ክፍሎችን ሕልውና ፈተና ውስጥ እያስገባ ነው፡፡ ባለፉት ሦስትና አራት ወራት የኑሮ ውድነት እየተባባሰ መምጣቱንና ባላቸው ገቢ መጠን ለመኖር መቸገራቸውን ነዋሪዎች እየገለፁ ነው፡፡ በተለይ ጤፍ መቶ ኪሎ 3500 ብር፣ስንዴ 2000 ብር፣በቆሎ 1500 ብር፣ቀይ ሽንኩርት አንድ ኪሎ 30 ብር፣ነጭ ሽንኩርት 160 ብር፣ቲማቲም 25 ብር፣አንድ ሊትር ዘይት 100 ብር፣አንድ ኪሎ ሙዝ 30 ብር…እየተሸጠ ነው፡፡ መንግሥት ጣልቃ በመግባት ሕገ ወጦችን አደብ አስገዝቶ ገበያውን ማረጋጋትም አልቻለም፡፡

Via Yegize Welafen

እናተስ ስለጉዳዩ ምን ትላላችሁ?

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ አውሮፕላን ኪስማዮ ውስጥ እንዳያርፍ ተከለከለ!

ወታደሮችን አሳፍሮ ደቡብ ሶማሊያ ኪስማዮ ውስጥ ሊያርፍ ነበር የተባለ የኢትዮጵያ አውሮፕላን በኬንያ ኃይሎች በሚደገፉት የጁባላንድ ክልላዊ ወታደሮች መከልከሉን የዓይን ምስክሮች ገለጹ።

ወደ ኪስማዮ ያቀናው አውሮፕላን 'ከ90 በላይ ኮማንዶዎችን አሳፍሮ ነበር' የተባለ ሲሆን ተገቢውን መረጃ ቀድሞ አልሰጠም በሚል ምክንያት ነው እንዳያርፍ የተከለከለው ተብሏል።

ከምሥራቃዊ ኢትዮጵያ የሶማሌ ክልል ጎዴ ከተማ ተነስቶ ወደ ሶማሊያ እንደበረረ የሚነገርለት ይህ አውሮፕላን ኪስማዮ እንዳያርፍ በመከልከሉ ወደ ደቡብ ምዕራብ ሶማሊያ በማቅናት ባይዶዋ ውስጥ እንዳረፈም ተነግሯል።

በኪስማዮ አየር ማረፊያ ሰራተኛ የሆነ ግለሰብ አውሮፕላኑ ከኢትዮጵያ መነሳቱንና በኋላም ወደ ባይዶዋ መሄዱን ለሮይተርስ አረጋግጧል። ነገር ግን አውሮፕላኑ የሲቪል ይሁን ወታደራዊ የታወቀ ነገር የለም።

#ቢቢሲአማርኛ

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-08-20
#update ቅራኔዎችን በመፍታት የሀገሪቱን አንድነት ለማስቀጠል የተቋቋመው የማህበራዊ እሴቶች አፈላላጊ ኮሚቴ ስራ ጀመረ። በእረቅ ሰላም ኮሚሽን የተቋቋመው የማህበራዊ እሴቶች አፈላላጊ ኮሚቴ በዛሬው ዕለት በቀጣይ ሊሰራቸዉ በሚገቡ ጉዳዮች ዙሪያ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር እየተወያየ ነው። በውይይት መድረኩ ላይ ከመንግሥት ተቋማት ፣ ከሰላም ሚኒስቴር እና ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት የመጡ ሰዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ። በኢትዮጵያ የሚታዩ የሰላም መደፍረስ እና ቁርሾ አዘል ግጭቶች በእውነተኛ ዕርቅ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ተፈተው በህዝቦች መካከል መልካም ግንኙነት መፍጠር አስፈላጊ መሆኑ በመድረኩ ተጠቁሟል።

Via #ኢፕድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢትዮጵያውያኑ ከከፋፋይ ሀሳቦች ይልቅ በአንድነት ላይ እንዲያተኩሩ ተጠየቁ!

በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍፁም አረጋ #በዴንቨር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን ትናንት አወያይተዋል። በውይይቱም በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በመተባበር ለሀገራቸው የሚያደርጉትን ድጋፍ እንዲያጠናክሩ አምባሳደሩ ጠይቀዋል።

#ጥላቻ እና #ከፋፋይ ሀሳቦችን በመተው ወደ አንድነትና የሚያስማሙ ሀሳቦች ላይ እንዲያተኩሩም ነው መልዕክት የተላለፈው። ለዚህም በአንድነት መሥራት እንደሚገባቸው አምባሳደር ፍፁም ጠይቀዋል። #በዴንቨር የሚኖሩ የዳያስፖራ ማኅበረሰብ አባላትም ኢትዮጵያዊነትን መሠረት ያደረገ ውይይት መዘጋጀቱ ተገቢ መሆኑን መናገራቸውን በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያሳያል።

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia