TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update "ኢትዮጵያ ወደ ፍቅር" ለተሰኘው የድምፃዊ #ቴዎድሮስ_ካሳሁን(ቴዲ አፍሮ) ኮንሰርት የተዘጋጁ 20,000 የመግቢያ ትኬቶች ሁሉም ተሽጠው ማለቃቸውን ለመስማት ችለናል። ይሄን ኮንሰርት ለየት የሚያደርገው ደግሞ አጠቃላይ ትኬቶች ተሽጠው ያለቁት ኮንሰርቱ ይደረጋል ተብሎ ከነበረበት(ከዛሬ) ሁለት ቀን ቀደም ብሎ ነው።
.
.
ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቀረበ ጥያቄ መሰረት የቴዲ አፍሮ ኮንሰርት #በሚቀጥለው ሳምንት ይካሄዳል።

ምንጭ፦ አዘጋጅ ኮሚቴው
#TIKVAHETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አርቲስት #ቴዎድሮስ_ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) በአዲስ አበባ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ቡራዩና አካባቢው በተፈጸመ ጥቃት ሳቢያ ለተፈናቀሉ ሰዎች ሐሙስ መስከረም 10 ቀን 2011 ዓ.ም. የአንድ ሚሊዮን ብር እርዳታ አደረገ፡፡ ‹‹እርስ በርሳችን ተዋደንና ተፋቅረን መኖር ሲገባን በአገራችን እንዲህ ዓይነት ድርጊት መፈጸሙ ሊኮነን ይገባል፤›› ሲል ለሪፖርተር የተናገረው ቴዲ አፍሮ፣ ‹‹ባላሰቡትና ባልገመቱት ሁኔታ በተፈጸመ ጥቃት ሕይወታቸውን ላጡት ነፍሳቸውን በአጸደ ገነት ያኑርልን፣ ቤተሰቦቻቸውንም ያጽናልን፣ እንዲህ ዓይነት ነገር ድጋሚ እንዳይከሰት ለፍቅር ተግተን መሥራት ይገባናል፤›› በማለት መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

©ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የድምፃዊ #ቴዎድሮስ_ካሳሁን "ኢትዮጵያ ወደ ፍቅር" የተሰኘው የሙዚቃ ኮንሰርት ከታማኝ ምንጮች እንዳገኘሁት መረጃ ኮንሰርቱ ጥቅምት 03 ይካሄዳል ሲል ዘሀበሻ ድረገፅ ዘግቧል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጋሞ ጎፋ ዞን⬇️

በአዲስ አበባ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ቡራያና አካባቢው ለተፈናቀሉ ዜጎች የሀገራችን ታዋቂ አርቲስቶች ስላደረጉት ድጋፍ የጋሞ ጎፋ ዞን አስተዳደር ምስጋና አቀረበ፡፡ አርቲስት #ቴዎድሮስ_ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/፣ አርቲስት #ታማኝ_በየነ እና አርቲስት #አስገኘው_አሽኮ/አስጌ ደንዳሾ/ በአዲስ አበባ ዙሪያ ኦሮሚያ
ልዩ ዞን ቡራያና አካባቢው ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ተጎጂዎችን በመጠለያ ተገኝተው ስላጽናኑና ስለረዷቸው በጋሞ ጎፋ ዞን ሕዝብ
ስም አቶ ኢሳያስ እንድሪያስ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በሌላ በኩል...

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የጋሞ ጎፋ ሀገረ ስብከት በአርባምንጭ ከተማ እና አርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ከሚገኙ አድባራት እንዲሁም ከማህበረ ቅዱሳን በአዲስ አበባ ዙሪያ እና ኦሮሚያ ልዩ ዞን ቡራያና አካባቢው ለተፈናቀሉ ወገኖች 200 ሺህ ብር በማሰባሰብ #ድጋፍ አድርጋለች፡፡

ምንጭ፦ የጋሞ ጎፋ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮ-ኤርትራ ሩጫ‼️

ድምጻዊ #ቴዎድሮስ_ካሳሁን በመጪው እሁድ በአዲስ አበባ በሚካሄደው የኢትዮ-ኤርትራ የፍቅር ሩጫ ላይ በክብር እንግድነት ይገኛል።

የውድድሩ ዋና አስተባባሪ አቶ ሰለሞን ታፈረ እንደገለጹት 20 ሺህ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን የሚሳተፉበትን የፍቅር ሩጫ ቴዲ አፍሮ ያስጀምረዋል።

የሩጫው ዓላማ የኢትዮጵያንና የኤርትራን ወንድማማችነት ማጠናከር ሲሆን ተሳታፊዎች ይህን የሚያሳዩ መልዕክቶችን እንደሚያስተላልፍ
ይጠበቃል።

ከከተማዋ ፖሊስ ጋር በመተባበር በፀጥታ በኩል ችግሮች እንዳይኖሩ በቂ ዝግጅት እንደተደረገም ተገልጿል።

ኢዜአ እንደዘገበው ሩጫው መነሻውን መስቀል አደባባይ ያደርግና በመሿለኪያ-አጎና ሲኒማ -ጎተራ ማሳለጫ-ወሎ ሰፈር-አሎምፒያ- መስቀል አዳባባይ የሚጠናቀቅና የ10 ኪሎ ሜትር ርዝመት የሚሸፍን ነው።

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀዋሳ እና አዲስ አበባ!!

ድምፃዊ #ቴዎድሮስ_ካሳሁን በአዲስ አበባ ስታዲየም #በነፃ የሙዚቃ ዝግጅቱን ለማቅረብ እየተዘጋጀ እንደሆነ ተሰምቷል። ለአዲስ አበባው ኮንሰርት ምንም አይነት ክፍያ እንደማይቀበል የተነገረ ሲሆን ለሙዚቃው ዝግጅት ከአዘጋጆቹ በተጨማሪ የተወሰነውን ወጪ እራሱ ይሸፍናልም ተብሏል። ህዝቡም ኮንሰርቱን በነፃ እንደሚታደምበት ነው የተገለፀው። ከአዲስ አበባው በአይነቱ የተለየ የሙዚቃ ዝግጅት በተጨማሪ ድምፃዊው #በሀዋሳ ከተማ የሙዚቃ ዝግጅት ለማቅረብ እቅድ እንዳለው ለመስማት ተችሏል። የሙዚቃ ዝግጅቶቹ መቼ ይካሄዳሉ?? የሚለው ግን የታወቀ ነገር የለም።

ምንጭ፦ ኢትዮፒካሊንክ የሬድዮ ዝግጅት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ደራርቱ_ቱሉ #ቴዎድሮስ_ካሳሁን

ትናንት ምሽት ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የአፍሪካ ኅብረት ጽ/ቤት ልዩ የዕውቅና ሥነ ሥርዓት ተካሂዷል፦

• ፍልቅልቋ ዝምተኛ ጀግና አትሌት ደራርቱ ቱሉ የመጀመሪያዋ አፍሪካዊት የኦሎምፒክ የወርቅ መዳልያ አሸናፊ በመሆኗ ከአፍሪካ ኅብረት ጽ/ቤት ልዩ ሽልማት አበርክቶላታል፡፡ እንዲሁም የዲሲ ከንቲባ ጽ/ቤት በክብር ሠርተፍኬት አበርክቶላታል፤

• ተወዳጁ አርቲስት ቴዲ አፍሮ ደግሞ በምሽቱ ሦስት ሽልማቶችን ተሽልሟል፡፡ በሙዚቃ ሥራው ለአፍሪካውያን ወጣቶች አርአያ በመሆኑ ከአፍሪካ ኅብረት ልዩ ዋንጫ ሲሸለም፤ የዲሲ ከተማ ከንቲባም የእውቅና ሠርተፍኬት አበርክቶለታል፡፡

የሜሪላንድ ኢትዮጵያውያንም ለቴዲ አፍሮ ልዩ ስጦታ ሰጥተውታል፤ ቴዲ አፍሮ (ድምጻዊ ቴድሮስ ካሳሁን) ባደረገው ንግግር፤ ሽልማቱን ላበረከቱለት ሁሉ አመስግኖ ሽልማቱን ለአፍሪካውያን ወጣቶች መታሰቢያ እንዲሆን አበርክቷል፤

Via #GETU_TEMSEGEN
@tsegabwolde @tikvahethiopia