የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ ከድንበር ተሻጋሪ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትና ከ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ጋር በትብብር ማስተማር እንደማይቻል የመጨረሻ ያለውን ማሳሰቢያ ለመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ሰጥቷል፡፡ ኤጀንሲው በ2000ዓ.ም እና በ2007ዓ.ም በትብብር ማስተማር እንደማይቻል ደብዳቤ ለዩኒቨርሲቲዎች መጻፉን አስታውሶ ‹‹አሁንም የተሰጠውን መመሪያ በመተላለፍ በመገናኛ ብዙኃን ማስታወቂያ የሚያስነግሩ መኖራቸውን ለማረጋገጥ ችለናል›› በማለት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ አሳስቧል፡፡ ከድርጊታቸው በማይቆጠቡ ዩኒቨርሲቲዎች ላይ በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በኩል እርምጃ እንደሚወሰድም አስታውቋል፡፡
ዝርዝሩን ይመልከቱ👇
https://telegra.ph/MSHEE-07-20
ዝርዝሩን ይመልከቱ👇
https://telegra.ph/MSHEE-07-20
#Congratulations
የመቐለ ዩኒቨርስቲ በዛሬው ዕለት በተለያዩ መርሃ ግብሮች ያሰለጠናቸውን 7 ሺህ 425 ተማሪዎች ማስመረቁ ይታወቃል። ዩኒቨርስቲው ካስመረቃቸው ተማሪዎች መካከል 2 ሺህ 418 የሚሆኑት ሴቶች ናቸው። የዛሬው ምረቃ ለዩኒቨርስቲው 27ተኛ ጊዜ ነው። ዩኒቨርስቲው በአሁኑ ሰአት ከ33 ሺህ በላይ ተማሪዎችን እያስተማረ ይገኛል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia

ሁላችሁም ሀምሌ 21 በክብር ተጋብዛችኃል!
/የTIKVAH-ETH ሁለተኛው አመት ምስረታ ክብረ በኣል~በአበበች ጎበና የህፃናት እንክብካቤና ልማት ድርጅት/
ፒያሳ ከአቡነ ጴጥሮስ አደባባይ(1) ወደ ዮሐንስ(2) ወልደ ነጎድጓድ ቤተክርስቲያን የሚወስደውን መንገድ ይዘው ቤተ ክርስቲያኑ ጋር እንደደረሱ ከመጡበት አቅጣጫ በስተግራ ታጥፈው ትንሽ እንደተጓዙ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጎጃም በረንዳ ቅርንጫፍን(3) ያገኛሉ ከዛም ከባንኩ በስተቀኝ በኩል ወደላይ የምትወስድ መንገድ ያገኛሉ ከዛም በየቦታው የምንሰቅላቸውን ባነሮች እየተመለከቱ ከቦታው ይደርሳሉ፡፡ አልያም የአከባቢውን ሰዎች ብጠይቋቸው ይጠቁሟችኀል፡፡
ለበለጠ መረጃ በእጆት ላይ ባለው ስልክ Google map መሰረት ወደ Abebech Gobena Children's Care and Development Association (AGOHELMA) ምራኝ ብትሉት ይመራዎትና ከቦታው ያደርሶታል፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopi

Abebech Gobena Children's Care and Development Association (AGOHELMA)
Dej. Nesibu St, Addis Ababa
011 155 3622
https://maps.google.com/?cid=14408072496157346285

★★★★☆ · Non-profit organisation · Dej. Nesibu St
TIKVAH-ETHIOPIA pinned «Abebech Gobena Children's Care and Development Association (AGOHELMA) Dej. Nesibu St, Addis Ababa 011 155 3622 https://maps.google.com/?cid=14408072496157346285»
#ወንዶ_ገነት
ትናንት በወንዶ ገነት ከተማ በተነሳ ተቃውሞ ላይ በፀጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት የሦስት ወጣቶች ሕይወት ማለፉን የአካባቢው ባለስልጣናት ለቢቢሲ ገልፀዋል።
ተጨማሪ የንብቡ👇
https://telegra.ph/WG-07-20

#update የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በአዲስ አበባ ሰሚት አካባቢ ያስገነባቸውን 112 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዛሬ በዕጣ ለሠራዊት አባላትና ለተቋሙ ሲቪል ሠራተኞች አስረከበ። በዕጣው በቅርቡ ህይወታቸው ያለፈው የጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን ቤተሰቦች ያለ ዕጣ የመኖሪያ ቤት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓል። በዕጣው ከተሳተፉት መካከል 20 ከመቶ የቆጠቡ የሠራዊቱ አባላት፣ የመስሪያ ቤቱ ሲቪል ሰራተኞች እንዲሁም ጡረታ የወጡና በዝውውር በሌላ ተቋም የሚሰሩ ይገኙባቸዋል። የጋራ መኖሪያ ቤቶቹ ርክክብ ሴቶችን ልዩ ተጠቃሚ ያደረገ፣ የሠራዊቱን የአገልግሎት ዘመን መሰረት ያደረገና የጠቅላይ ኢታማዦር አለቆችንም ያካተተ ነው ተብሏል። 112ቱ የጋራ መኖሪያ ቤቶች 27 ባለ አራት፣ 34 ባለ ሶስት፣ 19 ባለ ሁለት መኝታ ክፍልና 18 ባለ አንድ መኝታ ናቸው።
Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FDRE_DEFENCE_FORCE በቅርቡ ህይወታቸው ያለፈው የጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን ቤተሰቦች ያለ ዕጣ የመኖሪያ ቤት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Congratulations የኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርስቲ #የገዳ ስርዓትን ለአለም ማህበረስብ በማስተዋወቅ ረገድ ከፍተኛ ሚና ለነበራቸው ፕሮፌሰር አስመሮም ለገሰ እውቅና ሰጠ። ለፕሮፌሰር አስመሮም እውቅና የተሰጣቸው ዩኒቨርስቲው ለዘጠነኛ ጊዜ በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ በተለያዩ ሙያዎች ያሰለጠናቸውን 5 ሺህ 200 ተማሪዎችን ዛሬ በስመረቀበት ወቅት ነው።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ባህር_ዳር
"የሕዝብ ለሕዝብ #ትስስሩ የተዘራውን #የውሸት ትርክት ማርከሻ መድኃኒት ነው!" አቶ ሙስጠፌ ሙሐመድ ዑመር
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/BC-07-20

#የትግራይ_ህዝብ_ፍቅር_ነው!
"ወደ ትግራይ እንዳትሄድ ብለው አስጠንቅቀውኝ ነበር! የመጣነው ከአዳማ፣ ኦሮሚያ ነው። ልጆቻችን ለማስመረቅ ወደ መቐለ እንሄዳለን ብለን ስንናገር #ይቅርባችሁ ተብለናል። እንሄዳለን ብለን ስንወስንም በሉ አፋን ኦሮሞ እንዳትናገሩ ብለው መክረው ስለ ላኩን አሁን ግን የቴሌቪኑ የስርጭት ቋንቋ አማርኛ ቢሆንም ደስታዬ እና መልእክቴን በአፋን ኦሮሞ ነው ማስተላልፈው!" ብለው በኣፋን ኦሮሞ ደስታቸውን መልዕክታቸውን ተናገሩ። (ከትግራይ ህዝብ ጋር 'በ በሬ ወለደ ውሸታቸው ሊለያዩን የሚያስቡ ሰዎች ጤነኛ ናቸውን?) በማለት በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው በአፋን ኦሮሞ ሐሳባቸውን ገለፁ።
የትግራይ ቴሌቪዥን ጋዜጠኛም ጎበዝ ነበር እንደ እሳቸው በአፋን ኦሮሞ ጥያቄውን አስከተለ (አንድ ቋንቋ የሚናገር አንድ ሰው ነው:ሁለት የሚናገር ሁለት ሰው ነው ይባል የለ?) ጋዜጠኛው ብዙ ሰው ነበረ፡፡ እንግዳውም ቀጥለው... በአማርኛ ቋንቋ የትግራይ ህዝብ በሄዱበት መስጊድ፣ ምግብ ቤትና መኝታ ቤት በታላቅ ክብር እንዳስተናገዷቸው ገልፀው አመሰገኑ፡፡"
ፍቅር፤ ሰላም፤ አንድነት!

#ባህር_ዳር /ጣና/
በሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር #ሙስጠፌ ሙሐመድ ዑመር የተመራው የክልሉ የልዑክ ቡድን አባላት የጣና ላይ ታሪካዊ ሥፍራዎችን ጎብኝተዋል፡፡ #ባህርዳር #ጣና

የሲዳማ ዞን ከተሞች እንዴት ዋሉ? የዛሬው ሁኔታ ምን ይመስል ነበር? #ሀዋሳ #ይርጋለም #ወንዶገነት #ለኩ #ሀገረሰላም
ከ20 ደቂቃ በኃላ እመለሳለሁ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከ20 ደቂቃ በኃላ እመለሳለሁ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሀዋሳ
ካለፉት ሁለት ቀናት የተሻለ ሰላም እና መረጋጋት በዛሬው ዕለት ነበር። ከተማዋ ወደቀደመው እንቅስቃሴዋ እየገባች ነው። የተወሰኑ ባጃጆች እና ታክሲዎች ሲንቀሳቀሱ ነበር/ከመናኸሪያ ሞቢል-ፒያሳ የታክሲ እንቅስቃሴ ነበር/። ብዙሃኑ የንግድ ቤቶች ተዘግተው ነው የዋሉት። አብዛኞቹ ባንክ ቤቶችም ዝግ ነው የዋሉት። በየሰፈሩ ያሉ ሱቆች ተከፍተው ደምበኞቻቸው ሲያስተናግዱ ነበር። እንደሰማሁት ከሆነ በሸቀጦች ላይ መጠነኛ የዋጋ ጭማሪ ታይቷል። ከሁከቱ ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ ተጠርጣሪዎችን አሁንም የፀጥታ አካላት እያሰሩ እንደሆነ ከከተማው ነዋሪዎች ሰምቻለሁ። ከትላንት ምሽት ጀምሮ የመጠጥ ውሃ ተመረዘ ተብሎ ሲናፈስ የነበረው ወሬም ሀሰትና ህዝቡን ለማሸበር የተደረገ እንደሆነ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች በሚዲያ ገልፀዋል።
#ይርጋለም
ባለፉት ሁለት ቀና ከፍተኛ የፀጥታ ችግር የነበረባት እድሜ ጠገቧ ይርጋለም ከተማ ዛሬ ፀጥ ረጭ ብላ ውላለች። በከተማው ምንም አይነት እንቅስቃሴ አልነበረም። ሱቆች፣ ባንኮች፣ ሆቴሎች ዝግ ነው የዋሉት። በከተማይቱ ውስጥ የመከላከያ እና የፌዳራል የፀጥታ ሃይላት በመኪና ሲዘዋወሩ እንደነበር የከተማው ነዋሪዎች ተናግረዋል።
#አለታወንዶ
ባለፉት ሁለት ቀናት በአለታ ወንዶ የነበረው የፀጥታ ችግር ዛሬ መጠነኛ መሻሻል አሳይቷል። ከተማዋ ሙሉ በሙሉ ከእንቅስቃሴ ውጭ ሆናለች። ሰዎች አልፎ አልፎ ካልሆነ አይንቀሳቀሱም። አንዳንድ ሱቆች ተከፍተው ነበር። ልክ እንደሀዋሳ በአለታ ወንዶ ከተማ የዋጋ ጭማሪ ነበር። ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች እንደገለፁልን ከተማውን ወደቀደመው ሰላማዊ እንቅስቃሴ ስራዎች እየተሰሩ ነው። ካለፉት ሁለት ቀናት ዛሬ ከተማዋ ትሻላለች።
ይቀጥላል👇

#ለኩ
የቀድሞ እንቅስቃሴዋ ባይኖርም የፀጥታው ሁኔታ መሻሻል አሳይቷል። አልፎ አልፎ ከሚታዩ የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ውጭ ከተማዋ ጭር ብላ ውላለች። የፀጥታ አስከባሪዎች ከተማውን ሲቃኙ ነበር።
#ሀገረሰላም
ከትላንት በስቲያ እና ትላንት ከፍተኝ ውጥረት እና የሰላም መደፍረስ የነበር ሲሆን ዛሬ አንፃራዊ መረጋጋት እና ሰላም ታይቷል። የተኩስ ድምፅም ሳይሰማ እንደዋለ ነዋሪዎች ነግረውናል።
🏷በአጠቃላል በሁሉም ከተሞች ካለፉት ቀናት የተሻለ መረጋጋት እየታየ መጥቷል። ውሃ ተመረዘ የተባለውም በሁሉም ከተሞች የሚገኙ ዜጎችን ለማሸበር ነበር። ወሬም ውሸት ሆኖ ነው የተገኘው።
📎በየከተሞቹ በተፈጠረው ግጭት ስለጠፋው የሰው ህይወት ቁጥር እና ስለደረሱት ጉዳቶች በዞኑ ከሚንቀሳቀሱ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች፣ ከመንግስት ሰዎችን እንዲሁም ከተለያዩ የዜና አውታሮች የምናገኘውን መረጃ በቀጣይ እናቀርባለን።

#ሲአን #ሲዳማ_ዞን #ሞረቾ #ወተረሬሳ #ሀገረሰላም
በደቡብ ክልል በሐዋሳ ከተማ እና በሲዳማ ዞን የገጠር ከተሞች በተከሰቱ ግጭቶች የሞቱት ሰዎች ቁጥር 21 መድረሱን የሲዳማ አርነት ንቅናቄ አስታወቀ። የሲዳማ አርነት ንቅናቄ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ኔሳ ዛሬ ለጀርመን ራድዮ እንደተናገሩት በሲዳማ ዞን ከፀጥታ አስከባሪዎች ጋር በነበረ ግጭት 21 ሰዎች መሞታቸው ተናግረዋል። በሲዳማ ዞን ስር ባለው ወተረሬሳ 12 ሰዎች መሞታቸውን የሚናገሩት አቶ ደሳለኝ በሞሮቾ ሶስት እና በሀገረሰላም ደግሞ ሁለት ሰዎች በግጭቱ ህይወታቸው እንዳለፈ አስረድተዋል።
በሐዋሳ በነበረው ግጭት አራት ሰዎች መሞታቸውን እና ሌሎች ሰባት ሰዎች በፅኑ መቁሰላቸውን የከተማይቱ ከንቲባ አቶ ስኳሬ ሾዳ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል። በግጭቱ የተጠረጠሩ 150 ሰዎች በህግ ቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ከንቲባው ጠቁመዋል። ግጭቱን ተከትሎ የክልል እና የፌደራል አካላት ባደረጉት የማረጋጋት ስራ በሐዋሳ ከተማ እና በአካባቢው ያለው የፀጥታ ሁኔታ መሻሻሉን አቶ ስኳሬ ገልፀዋል። በሐዋሳ በዛሬው ዕለት የትራንስፖርት እንቅስቃሴ እንደታየና የማህበራዊ አገልግሎት መስጫዎች ተከፍተው ስራ መጀመራቸው ተሰምቷል። የኢንተርኔት አገልግሎት እና የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ግን አሁንም ዝግ ናቸው።
ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ

#አዲስ_አበባ
የአዲስ አበባ ከተማ የ2012 በጀት 47 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር እንዲሆን ተወሰነ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የከተማዋን የሆቴል ኢንቨስትመንት የሚያሳድግ ውሳኔም አሳልፏል።
ካቢኔው ዛሬ ሐምሌ 13 /2011 ባደረገው መደበኛ ስብሰባ የኢትዮጵያና የአፍሪካ መዲና በሆነችው አዲስ አበባ የሆቴል ኢንቨስትመንትን ለማሳደግ እና ከተማዋን ግዙፍ የኮንፈረንስና የልዩልዩ ሁነቶች መስተናገጃ ወይም የማይስ(MICE) ማዕከል ለማድረግ የኮንቬንሽን ቢሮ እንዲከፈት ውሳኔ አሳልፉል፡፡ የኮንፈረንስ ቱሪዝምን ማሳደግ ፣ ኤግዚቢሽኖች መስፋት ፣ የንግድ ለንግድ ትስስሮች እና ኩነቶችን መጠናከር እና ወደ ከተማዋ የሚመጡ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት ደረጃውን በጠበቀ ፕሮቶኮል እንዲስተናገዱ ማስቻል መዲናዋ የማይስ ማዕከል በመሆኗ የምታገኛቸው ዋና ዋና ጥቅሞች ናቸው።
በከተማው ካቢኔ የተቋቋመውን ይህን ማዕከል አቶ ቁምነገር ተከተል በዳይሬክተርነት እንዲመሩም ተሹመዋል። አቶ ቁምነገር የMICE East Africa ዋና አዘጋጅ ፣ የOZZIE ቢዝነስ አማካሪዎች ድርጅት ኃላፊ እና የኢትዮጵያ ቱሪዝም ልማት አማካሪ ቡድን ምክትል ሰብሳቢ ናቸው። 50ሺ ብር የሚገመት ወርሃዊ የስራ ጊዜያቸውን ለከተማ አስተዳደሩ በነፃ ለማገልገልም አቶ ቁምነገር ቃል ገብተዋል፡፡
በሌላ በኩል ካቢኔው የ2012 በጀት ዓመት የአስተዳደሩ በጀት 47.6 ቢሊየን ብር እንዲሆን ወሰኗል። ረቂቅ በጀቱ በአስተዳደሩ ምክር ቤት ቀርቦ ሲፀድቅ ወደ ስራ የሚገባ ይሆናል።
እንዲሁም ካቢኔው ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ የእዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅትን በከፊል ወይም ሙሉለሙሉ ወደ ግል ለማዛወር ጥናት ተደርጎ እንዲቀርብም ውሳኔ አሳልፎዋል።

TIKVAH-ETHIOPIA via @vote