TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update በቅርቡ የመከስከስ አደጋ በደረሰበት የበረራ ቁጥር 302 የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ባለቤታቸውን በሞት የተነጠቁ አንዲት ፈረንሳዊት የቦይንግ ኩባንያ በትንሹ የ276 ሚሊዮን ዶላር ካሳ ይከፍላቸው ዘንድ ክስ መስርተዋል።

Nadege Dubois-Seex የተባሉት ወይዘሮ ክሱን የመሰረቱት በአሜሪካዊው የሕግ ጠበቃቸው ኖማን ሁሴን በኩል ነው። ጠበቃ ሁሴን እንደሚሉት በኢንዶኔዢያና የኢትዮጵያ አየር መንገዶች ላይ የደረሰው አደጋ ሙሉ በሙሉ በቦይንግ ሶፍትዌር ችግር ጋይ የተያያዘ መሆኑን የአሜሪካ አቪዬሺን ባለስልጣንና በመጨረሻም የቦይንግ ኩባንያ ያረጋገጡትና ያመኑበት ጉዳይ በመሆኑ ፤ ባልተሟላ ሶፍትዌርና የበረራ ማኑዋል ምክንያት ለደረሰው አደጋ ኩባንያው ለደንበኛዬ የተጠቀሰውን የገንዘብ መጠን በካሳ መልክ መክፈል አለበት ሲሉ ፓሪስ ላይ ለተሰበሰቡ ጋዜጠኞች ተናግረዋል።

√በተመሳሳይም #በኢንዶኔዥያ አየር መንገድ አደጋ ቤተሰቦቻቸው ሕይወታቸውን ያጡባቸው የቦይንግ ኩባንያን #በመክሰስ የካሳ ጥያቄ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ።

Via #PetrosAshenafi
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በስዊዘርላንድ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሆነው የተሾሙት አምባሳደር #ዘነበ_ከበደ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለስዊዝ ኮንፌዴሬሽንፕሬዚዳንትና የገንዘብ ሚንስትር ኡልሪች ማውረር አቅርበዋል።

Via #PetrosAshenafi
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ዶ/ር ኢንጂነር" ሳሙኤል ዘሚካኤል ከእስር ቤት መልስ ያሳተሙት መፅሀፍ ገበያ ላይ ውሏል።

ፎቶ: Anania Sorri
Via #PetrosAshenafi
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሩዋንዳና የፈረንሳይኛ ቋንቋ ተለያዩ‼️

የሩዋንዳ ፓርላማ በፈረንሳይኛ ቋንቋ ምትክ ስዋሂሊ የሃገሪቱ ኦፊሴላዊ ቋንቋ እንዲሆን በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል።

እኤአ እስከ 1962 ድረስ በቤልጂግ ቅኝ ግዛት ስር የነበረችው ሩዋንዳ ቀደም ብሎም የፈረንሳይኛ ቋንቋ በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መሰጠት እንዲያቆምና በምትኩ የእንግሊዝኛ ቋንቋ እንዲሰጥ ወስና የነበረ ቢሆንም፤ የአሁኑ የፓርላማው ውሳኔ ሁለቱንም ቋንቋዎች የገፋ ነው።

በሩዋንዳ ፓርላማ ውሳኔ ያልተደሰቱት የቀድሞዋ ገዢ ቤልጅዬምና ፈረንሳይ የካጋሜ መንግሥት ላይ የተለያዩ ማዕቀቦችን ሊጥሉና በተለይም ፈረንሳይ የካጋሜን ተቃዋሚ ኃይሎች ልትደግፍ እንደምትችል ፍንጭ እየሰጠች ነው።

በርካታ ጥቁር ፓን አፍሪካኒስቶች የሩዋንዳን ውሳኔ እያደነቁና እያወደሱ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራትም የሩዋንዳን ፈለግ በመከተል የቀኝ ገዢዎች ቋንቋን በመተው በሀገር በቀል ቋንቋዎች ይተኩ ዘንድ በተለይ የአፍሪካ ኅብረት ትኩረት ሊሰጠው ይገባል እያሉ ነው።

Via #PetrosAshenafi
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጋዜጠኛ ጀማል ....

አንጋፋው ጋዜጠኛ በኢትዮጰያ በድሮው ETV የቴሌቪዥን የመዝናኛ ክፍል 120 ፕሮግራም አዘጋጅና አቅራቢ በጀይሉ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ተዘጋጅቶ በኢቢ ኤስ ቴሌቪዘዥን ይቀርብ የነበረው ቢላል ሾው የተሰኘ ፕሮግራም አዘጋጅ እንዲሁም በአሁኑ ሰአት በአፍሪካ ቲቪ የሚቀርቡ የተለያዩ ኢስላማዊ ኘሮግራም የሚያዘጋጀው የጀይሉ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ባለቤት እና ማናጀር ጋዜጠኛ ጀማል አህመድ ባጋጠመው የልብ ህመም ምክንያት በሆስፒታል ህክምና እየተደረለት ይገኛል። ጀማል አህመድ አመለ ሸጋ፣ ትሁት ፣አይናፋር ፣እዩኝ እዩኝ የማይወድ ስትር ያለ ስብእና ያለው ድምፁ የማይሰማ የልዩ ባህሪ ባለቤት ነው።

በዚህ የሮመዳን ወር በያላችሁበት በዱአችሁ አትርሱት!

Via #PetrosAshenafi
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ግንቦት 20, 1983 ዓ/ም👆

ከላይ ባለው ፎቶ የሕወሓት ሊቀመንበር #መለስ_ዜናዊ እና የደኅንነቱ ሹም #ክንፈ_ገብረ_መድኅን ወደ ግዮን ሆቴል ሲገቡ ይታያሉ።

የሚሊተሪ ለብሶ የሚታየው የቀድሞው ጦር (ደርግ) መኮንን የነበረው ኮሎኔል አስራት ነው። ኮሎኔል አስራት በሕወሓት ከተማረከ በኋላ ከኢህአዴግ ጋር ተሰልፎ በብሔራዊ መረጃና ደህንነት መምሪያ ሀላፊነት ደረጃ ድረስ ሲሰራ የነበረ፤ በኋላም የግርማዊ ዐፄ ኃይለሥላሴ አስከሬን ከኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ጽ/ቤት ለማውጣት የተዋቀረውን ግብረ ኃይል ያስተባበረ ነው።

አብዮት ልጇን ትበላለችና ኮሎኔል አስራት የቀይ ሽብር ተዋናይ ነበር ተብሎ ወደ ወህኒ ቤት የወረደ ሲሆን፤ በወህኒ ቤትም እያለ "በህመም" ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት የተለየ መሆኑ ታውቋል።

ግንቦት 20 ዛሬ 28ኛ አመቱ ሲታሰብ በፎቶው ላይ የምናያቸው ሶስቱም አመራሮች በሕይወት የሉም።

Via #PetrosAshenafi
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የሊቨርፑል እና የቶተናም ደጋፊዎች በኢትዮጵያ አየር መንገድ...

በነገው ዕለት በእንግሊዞቹ ሊቨርፑልና ቶተንሃም ክለቦች መካከል በስፔኗ መዲና ማድሪድ ለሚካሄደው የአውሮፓ ቻምፒዬንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ላይ ለመታደም የሁለቱ ክለቦች ደጋፊዎች በኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ሲጓዙ የኢትዮጵያ አየር መንገድ

UEFA Champions League
Liverpool FC Totenham #UCLfinal #Madrid #UCL #ChampionsLeague #LIVTOT

Via #PetrosAshenafi
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የ2019 የዩኔስኮ ፌሊክስ ሁፉዌ ብዋኚ (Félix Houphouët-Boigny) የሰላም ሽልማት አሸናፊ መሆናቸው ይታወቃል። ጠቅላይ ሚንስትሩ በተለይ በኢትዮ ኤርትራ የሰላም ስምምነት ላይ በነበራቸው ከፍተኛ ሚና ለሽልማቱ የታጩ መሆናቸውንም ዩኔስኮ አሳውቋል።

መቀመጫውን ፈረንሳይ ፓሪ ያደረገው የመንግስታቱ ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና ባህል ተቋም ዩኔስኮ አስቀድሞ ሽልማቱን ለመስጠት የፊታችን ጁላይ 9 ቀን መርሐ ግብር ተይዞለት የነበረ ቢሆንም ተቋሙ የሽልማቱን መስጫ ቀን ላልተወሰነ ቀን ማራዘሙን አሳውቋል። https://en.unesco.org/news/ceremony-award-felix-houphouet-boigny-unesco-peace-prize-ethiopian-pm-abiy-ahmed-ali

Via #PetrosAshenafi
🗞ቀን ሰኔ 24/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዶ/ር አርከበ ሆስፒታል ናቸው...

"በሚንስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚንስትሩ ልዩ አማካሪ የሆኑት ዶ/ር #አርከበ_እቁባይ ታመው ቤልጅዬም በሚገኝ ሆስፒታል ህክምና በመከታተል ላይ ይገኛሉ።" ይህ መረጃ #PetrosAshenafi እና ethiopiaobserver.com ናቸው ያወጡት።

🗞ቀን ሰኔ 26/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጋዜጦች በዚህ ሳምንት፦

የኬንያው ዘ ኢስት አፍሪካን ጋዜጣ በፊት ገፁ "የዐቢይ አህመድ የጫጉላ ሽርሽር አበቃ" በሚል ሰፊ ዘገባ ይዞ ወጥቷል። ኢስት አፍሪካን በኬንያ፣ ኡጋንዳ፣ ታንዛኒያና ሩዋንዳ የሚሰራጭ በምስራቅ አፍሪካ ብዙ አንባብያን ያለው ጋዜጣ ነው። ቢሆንም አንዳንድ ጊዜ የዞኑን መንግሥታት ጠንከር ባለ ሁኔታም ስለሚተች በቅርቡ ታንዛኒያ ወደ ሃገሬ አይግባብኝ እያለች ነው። #PetrosAshenafi

🗞ቀን ሰኔ 29/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia