TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update በኢንዱስትሪ ፓርኮች ሰራተኞች የሚከፈላቸው ደሞዝ ዝቅተኛ በመሆኑ ከስራ የሚለቁት ቁጥር እየተበራከተ መምጣቱ ተገለጸ። በበጀት ዓመቱ በመንግስት ከሚለሙ ሰባት ኢንዱስትሪ ፓርኮች 110 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ መገኘቱም ተገልጾል።

https://telegra.ph/በኢንዱስትሪ-ፓርኮች-የሰራተኞች-ፍልሰት-እየተባባሰ-መጥቷል-07-04
#update በቢጂአይ ኢትዮጵያ ለረዥም ጊዜ ያገለገሉት አቶ ኢሳያስ ሃደራ ከኩባንያው መልቀቃቸው ተሰምቷል።

https://telegra.ph/በቢጂአይ-ኢትዮጵያ-ለረዥም-ጊዜ-ያገለገሉት-አቶ-ኢሳያስ-ከኩባንያው-መልቀቃቸው-ተሰማ-07-04
የግብረሰዶማውያኑ ጉዞ ተሰርዟል...

“ቶቶ ቱር” የግብረሰዶማውያን አስጎብኝ ድርጅት በጥቅምት ወር በኢትዮጵያ ሊያደርግ የነበረውን የ16 ቀን ጉብኝቱን “ለደንበኞቻችን ህይወት ስጋት…” በሚል #ለመሰረዝ መወሰኑ ተገልጿል።

https://telegra.ph/Tour-cancels-Ethiopia-trip-after-hearing-LGBTI-tourists-will-be-buried-alive-07-04

Via GSNews
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አዲስ የኢንቨስትመንት አዋጅ በማዘጋጀት የህግ ማሻሻያ ሊያደርግ መሆኑን አስታወቀ፡፡ ኮሚሽኑ ባለፉት አምስት ወራት ግብረ ሀይል በማቋቋም አዲስና ዘመናዊ ህግ ለማሻሻል ሲሰራ መቆየቱን አመልክቷል፡፡ የኢንቨስትመንት ህግ ማሻሻያ አላማው የሀገሪቱን የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ለማሳደግ እና አዲስ እውቀት እና ቴክኖሎጅን መሳብ የሚያስችል አሰራርን ለመዘርጋት መሆኑን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ አበበ አበባየሁ ገልፀዋል፡፡ የኢንቨስትመንት ህጉ መሻሻል መንግስት እየተገበረ ያለውን የኢኮኖሚ ማሻሻያ የሚያግዝ እና የተቀላጠፈ አሰራርን ለማምጣት እና ለባለሀብቶች ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር እንደሚያግዝም ተገልጿል፡፡ አዲሱ የኢንቨስትመንት አዋጅ በሀገሪቱ የሚገኘዉን ከፍተኛ የሆነ የስራ አጥ ቁጥር የሚቀንስ እንደሆነም ኮሚሽነሩ ጨምረው ገልፀዋል፡፡

Via walta
🗞ቀን ሰኔ 28/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቢልለኔ ስዩም የፌስቡክ ገፅ የላትም!

#Billene_Seyoum ይህ የfacebook page #ሀሰተኛ ነው። ይህንን ጉዳይ የAPው ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ከዚህ ቀደም ከራሳቸው አንደበት አረጋግጧል። ዋልታና የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትን ጨምሮ በርካቶች የቢልለኔ ስዩምን ፌስቡክ በመጥቀስ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ የፊታችን ማክሰኞ የዩኔስኮን ፌሊ ሁፉዌ ብዋኚን የሰላም ሽልማት እንደሚቀበሉ እየገለፁ ነው።

ለመረጃ ያህል...

የፊታችን ማክሰኞ ጁላይ 9 የሽልማት ስነስርዓት #አይካሄድም። ጠቅላይ ሚንስትሩም ወደ ፈረንሳይ ፓሪ አይጓዙም። እርግጥ ነው ሜይ 2 ቀን 2019 ዩኔስኮ ጠቅላይ ሚንስትሩ የሰላም ሽልማቱን ማሸነፋቸውንና ጁላይ 9 ቀን ሽልማቱን እንደሚቀበሉ ገልፆ የነበረ ቢሆንም፤ አሁን ግን ለጊዜው የሽልማቱን መስጫ ቀን "ላልተወሰነ" ጊዜ ማራዘሙን ለማረጋገጥ ተችሏል። /#Petros_Ashenafi/

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢትዮጵያዊቷ አትሌት #ገንዘቤ_ዲባባ እና ሙዚቀኛው #ሮፍናን በታዋቂው የአሜሪካ 'ፎርብስ' መጽሔት የ2019 እድሜያቸው ከ30 ዓመት በታች የሆኑ 30 አፍሪካውያን ተጽእኖ ፈጣሪዎች ውስጥ ተካተዋል። የአሜሪካው ታዋቂ የቢዝነስ መጽሔት ፎርብስ በቢዝነስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራ እና ስፖርት ዘርፎች በ2019 በአፍሪካ እድሜያቸው ከ30 ዓመት በታች የሆኑ 30 ተጽእኖ ፈጣሪ ግለሰቦችን ይፋ አድርጓል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/አትሌት-ገንዘቤ-ዲባባ-እና-ሙዚቀኛው-ሮፍናን-በፎርብስ-መጽሔት-እድሜያቸው-ከ30-ዓመት-በታች-የሆኑ-30-አፍሪካውያን-ተጽእኖ-ፈጣሪዎች-ውስጥ-ተካተቱ-07-05
#UpdateSport የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ላቀረባቸው ጥያቄዎች ምላሽ እስከሚያገኝ ድረስ ከኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድሮቸ ራሱን ማግለሉን አስታወቀ፡፡

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር በትናንትናው ዕለት ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሊግ ኮሚቴ የቅዱስ ጊዮርጊስን የሜዳ ተጠቃሚነት ለማሳጣት ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ጋር ሊያደርገው የነበረን ጨዋታ በዝግ ወይም አዳማ ተጫወቱ በማለት ሁለት ጊዜ እንዲቋረጥ አድርጎል ብሏል፡፡

ይህን ጨዋታ ከዚህ በፊት የተቋረጡ የሌሎች ክለቦች ጨዋታወችን ባስተናገደበት ሁኔታ የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብን አላስተናገደም ሲል በፌዴሬሽኑ ላይ ቅሬታውን አቅርቧል፡፡

እንዲሁም በ29ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ለፋሲል ከነማ የተሰጠው ፎርፌ አግባብነት የሌለውና አድሏዊ መሆኑንም ነው በመግለጫው ያመላከተው፡፡

አዲስ ከመጡት የፌዴሬሽኑ አመራሮች ጋር በመተባበር፣ በመቻቻል እና በመተጋገዝ ለመስራት የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር የበኩሉን ድርሻ ሲወጣ ቆይቷልም ነው ያለው፡፡

በመሆኑም ፌዴሬሽኑ የወሰናቸውን ኢ – ፍትሃዊ እርምጃዎችን እንዲመረምር እና ያላአግባብ የተወሰነበትን ፎርፌ እንዲያነሳ የጠየቀ ሲሆን ያቀረባቸው ቅሬታዎች ምላሽ እስከሚያገኙ ከኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድሮች ራሱን ማግለሉን አስታውቋል፡፡

Via #fbc
🗞ቀን ሰኔ 28/2011 ዓ/ም
@tikvahethsport
#update በአዲስ አበባ ቦሌ አካባቢ ሆቴል ላይ በተነሳ እሳት ከ5 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ወደመ፡፡ የእሳት አደጋው የተከሰተው ዛሬ ንጋት 11፡30 ቦሌ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ቦራ የህጻናት መዝናኛ አካባቢ በሚገኘው ኦሬንጅ ሪቨር በተባለ ባለ ሶስት ኮከብ ሆቴል ላይ ነው፡፡

የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን እንዳስታወቀው የእሳት አደጋውን ለመቆጣጠር ሶስት ሰዓት ፈጅቷል 35 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ማዳን ተችሏል፡፡

በተያያዘ ዜና በትናንትናው ዕለት በኮልፌ ቀራንዮ ወረዳ 13 በተለምዶ ጊዮን በረኪና ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በደራሽ ጎርፍ አደጋ አንድ የ33 አመት ጎልማሳ ህይወት ማለፉ ታውቋል፡፡

ጎልማሳው በአካባቢው የሚገኝን አነስተኛ ወንዝ ለማቋረጥ ሲሞክር በደራሸ ጎርፍ መወሰዱ የተገለጸ ሲሆን፣ አስከሬኑን የኮሚሽኑ ጥልቅ ዋናተኛ ባለሙያዎች ፈልገው ማውጣታቸው ነው የተገለጸው፡፡

Via አሀዱ ራድዮ እና ቴሌቪዥን
🗞ቀን ሰኔ 28/2011 ዓ/ም
@tsegwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#update ኢትዮ ስኳር ኢንዱስትሪ አክስዮን ማህበር ሁለት የመንግሥት የስኳር ፋብሪካዎችን ለመግዛት እየተዘጋጀሁ ነው ብሏል። #ሸገርFM102.1

🗞ቀን ሰኔ 28/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢ/ር ታከለ ኡማ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጂራ ጋር ምክክር አድርገዋል፡፡ በሃገራችን እግር ኳስ ላይ እየታየ ባለው የስፖርታዊ ጨዋነት እና ሌሎች የስፖርት አጀንዳዎች ዙሪያ ከፌደሬሽኑ ስራ አስፈፃሚ አካላት ጋር ምክክር አድርገዋል፡፡ ኢ/ር ታከለ ኡማ የአዲስ አበባ ክለቦች በተለይም የኢትዮጵያ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ በሚያነሷቸው ችግሮች ዙሪያ ምክክል አድርገዋል፡፡ መጪው የውድድር ዘመን ከመጀመሩ በፊት መደረግ በሚገባቸው ቅድመ-ዝግጅቶች ዙሪያም ተነጋግረዋል፡፡

Via @mayorofficeAA
🗞ቀን ሰኔ 28/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሱዳን ወታደራዊ ሽግግር ምክር ቤት እና ተቃዋሚዎች የሰብዓዊ መብት ጥሰትን እንዳይኖር እንደሚሰሩም አስታውቀዋል፡፡

ሁለቱ አካላት ምርጫ እስከሚካሄድ ድረስ በሽግግር ወቅት ሥልጣንን ለመጋራት እንደተስማሙ የአፍሪካ ኅብረት አስታውቋል፡፡ በስምምነቱም ለቀጣዮቹ ሦስት ዓመታት በጣምራ ነፃ ወታደራዊ ምክር ቤት በመመስረት ሀገሪቱን ይመራሉ ነው የተባለው፡፡

አምስት ከወታደራዊ ኃይሎች እና አምስት ከሲቪል ተቃዋሚ ኃይሎች የሚመረጡ የሥራ ኃላፊዎች እንደሚኖሩት የተነገረለት ጥምር ኃይሉ ባለፉት ጊዜያት የተፈጠሩትን ግጭቶች የሚያጣራ ነፃ እና ገለልተኛ ቡድን እንደሚኖረውም ተዘግቧል፡፡ ሱዳን ፕሬዝዳንት አልበሽር ከሥልጣን ከተነሱበት ያሳለፍነው ሚያዝያ ጀምሮ በአለመረጋጋት ውስጥ ትገኛለች፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ እና አልጀዚራ/AMMA/
🗞ቀን ሰኔ 28/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update መንግሥት ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም ባህር ዳር ከተማ ለተፈፀመው የአማራ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት ግድያና የመፈንቅለ-መንግሥት ሙከራ ዋነኛ ተጠያቂ ናቸው ያላቸው የብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ፅጌ ባለቤት ወይዘሮ ደስታ አሰፋ በፖሊስ መያዛቸውን ልጃቸው ማኅሌት አሳምነው ለቢቢሲ ገለፀች። የቡራዩ ከተማ የጸጥታና አስተዳደር ኃላፊ አቶ ሰለሞን ታደሰ ወ/ሮ ደስታ በሕግ አግባብ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ለቢቢሲ ያረጋገጡ ሲሆን፤ ተሞክሯል ከተባለው መፈንቅለ መንግሥት ጋር የተያያዙ መረጃዎችን ለማግኘት ከሚደረገው ምርመራ ጋር በተያያዘ እንደሆነም ተናግረዋል። ማኅሌት እንደተናገረችው እናቷ በፖሊስ ከቤታቸው የተወሰዱት ትናንት ሐሙስ ዕለት ቡራዩ ውስጥ በተለምዶ አሸዋ ሜዳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ነው።

https://telegra.ph/የብጄነራል-አሳምነው-ፅጌ-ሚስት-መታሰራቸውን-ልጃቸው-ገለጸች-07-05-4

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን እና የአማራ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት በክልሉ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በመግለጫው ወቅት አማራ ክልል ፖሊስ ከሚሽን እንዳስታወቀው በኦፕሬሽን እና በሕዝብ ትብብር 218 የሚሆኑ ‹‹የብርጋዲዬር ጄኔራል አሳምነው ጽጌ ጥቃት ተባባሪዎች ናቸው›› የተባሉ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡

ከእነዚህ ተጠርጣሪዎች ውስጥ 113 ያህሉ በቀላል ደረጃ የተጠረጠሩ በመሆኑ በቅርቡ ውሳኔ እንደሚሰጣቸው የገለጹት የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ከሚሽነር አበረ አዳሙ ናቸው፡፡

ቀሪዎቹ 105 ተጠርጣሪዎች ግን ተጨማሪ ማጣራት የሚያስፈልጋቸው በመሆኑ የማጣራት ሥራው እየተከናወነ እንደሆነ ነው ኮሚሽነሩ ያስታወቁት፡፡ ጉዳያቸውን በዋናነት ይዞ እያጣራ የሚገኘው የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን መሆኑንም አመላክተዋል፡፡

እንደ ኮሚሽነር አዳሙ መግለጫ በአርሶ አደሮች በቁጥጥር ሥር የዋሉት ተጠርጣሪዎች ከሌሎች ተጠርጣሪዎች ጋር ሳይቀላቀሉ ለብቻ በማረፊያ ቤት ይገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በጥቃቱ የተጓደሉ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችን ለማሟላት እየተሠራ መሆኑን የአማራ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር አቶ አሰማኸኝ አስረስ ተናግረዋል፡፡ የሚሟሉት የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ዝርዝር ጉዳይ በቅርቡ ለሕዝብ ይፋ እንደሚሆንም አስታውቀዋል፡፡

Via #አብመድ
🗞ቀን ሰኔ 28/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ፍፁም #ሃሰት ነው" አቶ አሰመኸኝ

የአማራ ክልል የኮሚኒኬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ አሰመኸኝ አስረስ በቀጣይ ሳምንት አዳዲስ አመራሮች ምደባ ይካሄዳል ብለዋል። የሚሟሉት የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ዝርዝር ጉዳይ በቅርቡ ለሕዝብ ይፋ እንደሚሆንም አስታውቀዋል፡፡ ክልሉን #ፌደራል_መንግስት እያስተዳደረው አይደለም ወይ? ተብለው ተጠይቀው "ፍፁም ሐሰት ነው" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

Via #DW
🗞ቀን ሰኔ 28/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክሪያሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) ማዕከላዊ ኮሚቴ ልዩ ስብሰባውን ማካሄድ ጀመረ፡፡ የንቅናቄው ሊቀ መንበርና የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈርያት ካሚል በልዩ ስብሰባው ሀገራዊና ክልላዊ የጸጥታና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚካሄድ ገልጸዋል፡፡ በማዕከላዊ ኮሚቴው ልዩ ስብሰባ የተለያዩ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት እንደሚካሄድባቸውም ተጠቁሟል፡፡ ልዩ ስብሰባው በአዲስ አበባ የሚካሄድ ሲሆን ለሶስት ቀናት ይቆያል፡፡

Via #fbc
🗞ቀን ሰኔ 28/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
“የቻላችሁትን ያህል ክፍሉ…”

“በዚህች ምድር ለብቻችን አይደለም የምንኖረው፤ አንዳችን ለሌላችን እንደምንኖር ነው የማምነው፡፡ ስለዚህም ማንም ቢሆን… የገቢ መጠኑ የቱንም ያህል ይሁን መሰረታዊ የሕክምና አገልግሎት ማግኘት አለበት ብዬ ነው የማምነው” ዶ/ር ፓውሎ ዴ ቫልዶሌሮስ…

“10 ራንድም የሚከፍል አለ፤ 500 ራንድም የሚከፍል እንደዛው፡፡ ሁሉም ሕክምናውን ካገኘ በኋላ የቻለውን ይከፍላል” ይላል ደቡብ አፍሪካዊው ዶ/ር ፓውሎ ዴ ቫልዶሌሮስ፡፡

ዶ/ሩ የዛሬ አራት ሳምንታት ግድም፣ በደቡብ አፍሪካዋ ብሎምፎንቲየን ከተማ የከፈተው የቀዶ ሕክምና አገልግሎት የሚሰጥ ክሊኒኩ መነጋገሪያ ሆኗል፡፡

የዚህ ምክንያቱ ደግሞ … ወደ ክሊኒኳ ያለ ቀጠሮ ዘው ብለው ገብተው፣ ሕክምናዎትን አግኝተው ሲያበቁ የሚከፍሉት “የቻሉትን ያህል” ብቻ በመሆኑ ነው፡፡ በቀን 20 ያህል በሽተኞችን የሚያክመው ዶ/ሩ የታካሚ ቁጥር እንደጨመረ ይገልፃል፡፡ዶክተሩ፣ የሕክምና አገልግሎቱን እና መሰረታዊ የሚባሉ መድሃኒቶችን ለሕመምተኛው ከሰጠ በኋላ ታካሚው የሚችለውን ከፍሎ ይሄዳል፡፡

“ይህ አሰራር ያዋጣሃል ወይ” ተብሎ የተጠየቀው ዶ/ር ፓውሎ ዴ ቫልዶሌሮስ፣ “ኑሮዬን በገቢዬ መጠን አደርገዋለሁ፡፡ ደግሞም … እኔ ዶክተር ነኝ፤ የእኔ ሃላፊነት የሕክምና አገልግሎት መስጠት ነው፡፡ ሃላፊው እግዚአብሄር ነው” ብሏል፡፡ ቢቢሲ እንደዘገባው … ዶ/ሩን ለመርዳት ገንዘብ የሚያሰባስቡ ሰዎች እየመጡ ነው፡፡

ምንጭ - ቢቢሲ/#ሸገርFM
🗞ቀን ሰኔ 28/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
38 ጋዜጠኞች ተገድለዋል...

እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከጥር 2019 እስከ ሰኔ ባለው ግዜ በ20 የኣለም አገራት የሚገኙ 38 ጋዜጠኞች መገደላቸው ተገልጿል፡፡

Press Emblem Campaign (PEC) የተባለው ተቋም ያወጣው ሪፖርት እንደሚያሳየው በዚህ ስድስት ወራት የሞቱት የጋዜጠኞች ቁጥር ከላፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻፀር በ42 ከመቶ ቀንሷል፡፡ ሆኖም ከሞቱት ጋዜጠኞች መካካል 9 በሜክሲኮ እና 6 ደግሞ በአፍጋኒስታን ብቻ መሆኑ አሳሳቢ ነው ተብሏል፡፡

በአፍጋኒስታን አሸባሪ ቡድኖች እንዲሁም በሜክሲኮ የተደራጁ ወንጀሎች ለሞቱት ጋዜጠኞች ምክንያት መሆናቸው ነው በሪፖርቱ የተጠቀሰው፡፡

የላቲን አሜሪካ አገራት ከሟቾች ቁጥር 15 በመያዝ ችግሩ በስፋት የሚታይባቸው አገራት መሆናቸው ተገልጿል፡፡

በመካከለኛው ምስራቅ የሶርያና በኢራቅ የግጭት ሁኔታ መቀነስ ማሳየቱን ተከትሎ የጋዜጠኞች ሞት ቀንሷል ተብሏል፡፡

አገራት የጋዜጠኞች ጥቃትና መብት ማስከበር የማይችሉ ከሆነ የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ጋዜጠኞች መብታቸው የሚከበርበት እና ከጥቃት የሚታደግበት መላ ሊዘይድ ይገባል ብለዋል Press Emblem Campaign (PEC) ዋና ጸሃፊ ብሌዝ ለምፔን።

Via #ዥንዋ/ENA
🗞ቀን ሰኔ 28/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮ-ቴሌኮም እና የስኳር ፋብሪካዎች ፕራይቬታይዜሽን ሂደትን በተመለከተ የኢፌዴሪ የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ኢዮብ ተካልኝ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫው ላይ እንዳመለከቱትም የቴሌኮም ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ የፓይቬታይዜሽን ሂደቱን በተመለከተ መንግሥት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ከኢትዮ ቴሌኮም በተጨማሪ ሌሎች ሁለት ዓለም አቀፍ የቴሌኮም ኦፕሬተሮች ወደ ገበያ እንዲገቡ ያደርጋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ኢትዮጵያ-ሁለት-ዓለም-አቀፍ-የቴሌኮም-ኦፕሬተሮችን-በጨረታ-ወደ-ቴሌኮም-ገበያ-ልታስገባ-ነው-07-05
#update በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን 4 ሺህ ሄክታር በሚጠጋ የበቆሎና የማሽላ ማሳ ላይ ፈጣንና ሁሉን አውዳሚ #ተምች መከሰቱ ታውቋል፡፡

የዞኑ ግብርና መምሪያ የሰብል ልማት ባለሙያ አቶ #ገበየሁ_ሽፈራው እንደገለፁት ተምቹ 3ሺህ 587 ሄክታር መሬት ላይ በተዘራ በቆሎና ማሽላ ሰብል ላይ ጉዳት እያደረሰ ነው፡፡ በዚህም ከ9 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች ተጎጅ እንደሆኑ ነው ባለሙያው ያስታወቁት፡፡

ችግሩ በኤፍራታና ግድም፣ በአንፆኪያና ገምዛ፣ በሸዋሮቢት፣ በአንኮበርና በጣርማ በር ወረዳዎች በስፋት መከሰቱም ተነግሯል፡፡

ተምቹ በመስኖ በሚለሙ ሰብሎች ላይ ዓመቱን ሙሉ እንደቆዬና ከያዝነው ሰኔ ጀምሮም በበቆሎና በማሽላ ሰብሎች ላይ እየጨመረ መምጣቱን ባለሙያው ተናግረዋል፡፡

ከግብርና ሚኒስቴር 1ሺህ 600 ሊትር ፀረ ተምች ኬሚካል ቀርቦ ለመከላከል ሥራው እየተሰራጨ እንደሆነም ታውቋል፡፡

የሰሜን ሸዋ ዞን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ያጠናቀረው መረጃ እንዳመላከተው አሁን ላይ ተምቹን በኬሚካልና በባህላዊ መንገዶች ለመከላከል ጥረት እየተደረገ ነው፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
🗞ቀን ሰኔ 28/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ስምምነት ላይ ለደረሱት ለሱዳን ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤት ፣ለተቃዋሚ ሀይሎች እና ለሀገሪቱ ህዝቦች የደስታ መልክት አስተላለፉ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስምምነቱ በሱዳን ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን የሚያሰችል ነው ብላዋል ባስተላለፉት መልዕክት፡፡

የሀገሪቱ የፓለቲካ ሀይሎች ስምምነት ላይ እንዲደርሱ ከፍተኛ ሚና ለነበራቸው አምሳደር መሀመድ ድሪር እና መሀመድ ሀኬን አል ላባትም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀጣይ ጊዜ ለሱዳን የሰላምና የብልፅግና እንዲሆን ምኞታቸው አስተላልፈዋል፡፡

🗞ቀን ሰኔ 28/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia