TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለሁለት የስራ ኃላፊዎች ሹመት ሰጥተዋል። በሚኒስትር ማዕረግ ሹመት የተሰጣቸው ዶክተር ሹምቴ ግዛው የጠቅላይ ሚኒስትር ልዪ ፅ/ቤት ኃላፊ በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ አቶ ጌታቸው ኃይለምርያም በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ኮንስትራክሽን ዘርፍ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል።

ምንጭ:-ጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የደቡብ ክልል መስተዳድር በሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎች ተቀጥረው ሲያገለገሉ የተደረሰባቸዉ ከሶስት ሺህ በላይ የመንግስት ስራተኞች ማጋለጡን የክልሉ የሲቪል ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ። የቢሮዉ ኃላፊዎች እንዳሉት ሠራተኞቹ በሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎች መቀጠራቸው የተደረሰባቸዉ በክልል፣ በዞኖችና ወረዳዎች በሚገኙ የአስተዳደር መዋቀሮች ውስጥ በተደረገ ማጣራት ነው። አጭበርባሪዎቹ ከዲፐሎማ እስከ መጀመሪያ ዲግሪ የሚደርሱ የሐሰት የትምህርት መረጃዎችን ለየመስሪያ ቤቱ አቅርበዉ ተቀጥረዉ ሲሰሩ እንደነበር የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ መኮንን ደስታ ለዶቸ ቬለ አስታዉቀዋል። አቶ መኮንን እንዳሉት የሐሰት ማስረጃዎችን በተጠቀሙ ሰራተኞችና አመራሮች ላይ የተለያዩ አስተዳደራዊና ህጋዊ እርምጃዎች ተወስደዋል። ቀጠሪዎቹ መስሪያ ቤቶች ወይም የየመስሪያ ቤቶቹ ኃላፊዎች የሐሰት መረጃዎቹን ሳያጣሩና ሳያረጋግጡ አጭበርባሪዎቹን የቀጠሩበት ምክንያት በዉል አልታወቀም።

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#update የአሰላውን ግጭት #አባብሰዋል ተብለው የተጠረጠሩ 20 ሰዎች በፖሊስ ተይዘዋል ተባለ፡፡

Via #ShegerFM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የፊታችን አርብ ሰልፍ ሊደረግ ነው...

/Wolaita zone administration public relation office/

በወላይታ ዞን የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች #ሰላማዊ_ሰልፍ ለማድረግ ሲያቀርቡት የነበረው ጥያቄ ይሁንታ አግኝቷል።

ከዚህ ቀደም የህብረተሰቡን ሠላምና ፀጥታ ለማስጠበቅ ሲባል ሰልፉ ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙ ይታወሳል።

የወላይታ ሀገር ሽማግሌዎች፣ ምሁራን፣ ዬላጋ አደረጃጀት፣ የክብር ተሰናባች የሠራዊተ አባላት እና የንግድ ማህበራት ምክር ቤቶች ሠላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ በግንቦት 5/2011 ዓ ም በጠየቁት መሠረት ሰላማዊ ሰልፉ መፈቀዱ ታውቋል።

ሰልፉ በግንቦት 9/2011 ዓም ከጧቱ 12:00 ሰዓት እስከ 4:00 ሰዓት ድረስ የሚካሄድ መነሻው አዲሱ የወላይታ ዞን አስተዳደር ሆኖ በፍሬው አልታዬ ጎዳና የወላይታ ጉታራ አዳራሽን አቋርጦ በወላይታ ሶዶ ሁለገብ ስታዲየም የሚዘልቅ መሆኑ ታውቋል።

ከነዚህ ከተፈቀዱ ቦታዎች ውጪ ሰላማዊ ሰልፍ ባለማድረግ እና ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ህብረተሰቡ የተለመደውን ትብብር እንዲያደርግ የዞኑ አስተዳደሩ አሳስቧል።

/Wolaita zone administration public relation office/

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአማራ ክልል መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ በህዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የታሪፍ ማሻሻያ ማድረጉን አስታወቀ።

በቢሮው የትራንስፖርት ዘርፍ ምክትል ሃላፊ አቶ ውቤ አጥናፉ እንደገለጹት፥የታሪፍ ማሻሻያ የተደረገው የተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎች እና የነዳጅ ዋጋ በመጨመሩ ምክንያት መሆኑን ተናግረዋል።

እንዲሁም በክልሉ ያለው የትራንስፖርት ታሪፍ ከአጎራባች ክልሎች ጋር ሲነፃፀር አነስተኛ በመሆኑ ነው ብለዋል።

ማሻሻያውን ለማድረግ ጥናት መደረጉን የገለጹት ሃላፊው፥ አዲሱ ታሪፍ የፌዴራል የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያሻሻለውን የነዳጅ ዋጋ መሰረት ያደረገ ነው ብለዋል።

በዚህ መሰረትም በጠጠር መንገድ ለአነስተኛ ተሸከርካሪዎች ደረጃ አንድ ከዚህ በፊት በኪሎ ሜትር 0.565 ሳንቲም የነበረው ወደ 0.6 ሳንቲም ፡-ደረጃ ሁለት 0.535 ሳንቲም የነበረው ወደ 0.567ሳንቲም፡-ደረጃ ሶስት 0.5 ሳንቲም የነበረው ወደ 0.53 ሳንቲም ከፍ ብሏል።

በአስፋልት መንገድ ለአነስተኛ ተሸከርካሪዎች ደረጃ አንድ በኪሎ ሜትር 0.45 ሳንቲም የነበረው ወደ 0.5 ሳንቲም፡-ደረጃ ሁለት 0.42 ሳንቲም የነበረው ወደ 0.457 ሳንቲም፡-ደረጃ ሶስት 0.38 ሳንቲም የነበረው ወደ 0.415 ከፍ ብሏል።

ለመለስተኛ ተሸከርካሪዎች በጠጠር መንገድ ለደረጃ አንድ 0.52 ሳንቲም የነበረው ወደ 0.59 ሳንቲም፡-ደረጃ ሁለት 0.495 ሳንቲም የነበረው ወደ 0.539 ሳንቲም ፡-ደረጃ ሶስት 0.46 ሳንቲም የነበረው ወደ 0.498 ሳንቲም ከፍ ብሏል።

ለመለስተኛ ተሽከርካሪዎች በአስፋልት መንገድ ደግሞ ለደረጃ አንድ በኪሎ ሜትር 0.399 ሳንቲም የነበረው ወደ 0.48 ሳንቲም፡-ደረጃ ሁለት 0.368 የነበረው ወደ 0.43 ሳንቲም፡-ደረጃ ሶስት 0.336 ሳንቲም የነበረው ወደ 0.396 ሳንቲም ከፍ ማለቱን የትራንስፖርት ዘርፍ ምክትል ሃላፊው አቶ ውቤ አጥናፉ ተናግረዋል።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በፌዴራል ሆስፒታሎች #የትርፍ ሰዓት እና የጥቅማ ጥቅም ክፍያ ታክስ በፌዴራል መንግስት እንዲሸፈን ተወሰነ። በፌደራል ሆስፒታሎች ከዚህ በፊት ሲቆረጥ የነበረው የትርፍ ሰዓት እና የጥቅማ ጥቅም ክፍያ ታክስ ከግንቦት ወር 2011 ዓ.ም.ጀምሮ በፌደራል መንግስት እንዲሸፈን ተወስኗል። ይህም ማለት ግብሩ ይቀነሳል ማለት ሳይሆን ለግብሩ ይከፈል የነበርን ያክል ተመጣጣኝ ክፍያ የፌዴራል መንግስት እንዲከፍል እና ከባለሙያዉ ላይ ይቆረጥ የነበረው እንዲካካስ ይደረጋል፡፡ በተመሳሳይ እስከ አሁን ይሄንን ተግባራዊ ያላደረጉ ክልሎች በአጭር ጊዜ ጉዳዩን ወደ ክልል ካቢኔ አቅርበው እንዲያስወስኑ ስምምነት ላይ ተደርሷል።

Via ጤና ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የመብራት ነገር...

ቦሌ ቡልቡላ እና አካባቢው የመብራት መጥፋት እና መቆራረጥ እጅጉን እንዳማረራቸው የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ገለፁ። እየሆነ ስላለው ነገርም ማብራሪያ የሚሰጥ አካል የለም፤ የሚመለከተው አካል ጋር ስልክ ብንደውልም ስልክ የሚያነሳልን እና ምላሽ የሚሰጠን አካል ጠፍቷል ሲሉ ምሬታቸውን ገልፀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የመብራት ነገር ብሶበታል...

#የቢሾፍቱ እና #የጎንደር የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት በመብራት መቆራረጥ እና መጥፋት ምክንያት ስራቸውን በአግባቡ መስራት እንዳልቻሉ ተናግረዋል። በተመሳሳይ በቢሾፍቱ የውሀ ችግር ብዙ ጊዜ ያስቆጠረ እንደሆነና የሚመለከተው አካል ለችግሩ መፍትሄ እንዲፈልግ እና አስፈላጊውን ማብራሪያም እንዲሰጥ ጠይቀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት በሐገሪቱ ዉስጥ ለሚሰሩ የዉጪ ሐገር ባለሙያዎችና ባለወረቶች ቋሚ የመኖሪያ ፍቃድ (ሒቃማ) ሊሰጥ ነዉ። እስካሁን ድረስ ሳዑዲ አረቢያ ዉስጥ የሚሰራ የዉጪ ሐገር ባለሙያም ሆነ ባለሐብት መኖሪያ ፍቃድ የሚያገኘዉ የሳዑዲ አረቢያ ዜጋ ከሆነ ቀጣሪዉ ወይም የሐብት ተሻራኪዉ ግለሰብ ወይም ኩባንያ ነዉ። የሳዑዲ አረቢያ ምክር ቤት (ሹራ) ባለፈዉ ሳምንት ባፀደቀዉ ደንብ መሠረት ለዉጪ ሐገር ዜጎች የመኖሪያ ፈቃድ የሚሰጠዉ የሐገሪቱ መንግስት ነዉ።ዩናይትድ ስቴትስ «ግሪን ካርድ» በምትለዉ የመኖሪያ ፈቃድ አምሳያ ይዘጋጃል የተባለዉ ፈቃድ «ጎልደን ካርድ» የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል። ፈቃዱ በተለይ በተለያዩ ሙያዎች የሰለጠኑ የዉጪ ሐገር ሠራተኞችና ባለሐብቶች ሳዑዲ አረቢያ ዉስጥ እንዲሠሩና እንዲወርቱ ለማማለል ያለመ ነዉ። ፍቃዱን ለማግኘት ግን ባለሙያዉ ቀጣሪ፤ ባለሐብቱ ደግሞ የሚሰራበት የሥራ መስክ ማግኘት ይኖርባቸዋል። በንጉሳዊቱ አረባዊት ሐገር አሰራር መሰረት የሐገሪቱ ምክር ቤት ያፀደቀዉ ረቂቅ የሚፀናዉ የሐገሪቱን ንጉስ ይሁንታና ፅዲቂያ ሲያገኝ ነዉ። የሳዑዲ አረቢያ ነገስታት ባለፉት ሰወስት ዓመታት «ሕገ-ወጥ» ያሏቸዉን የዉጪ ሐገር ዜጎች በጅምላ ሲያባርሩ ነበር። ሕጋዊ መኖሪያ ፈቃድ ያላቸዉ የዉጪ ሐገር ተወላጆች ደግሞ ለራሳቸዉና ለየቤተሰቦቻቸዉ አባላት በነብስ ወከፍ ግብር ተጥሎባቸዋል።

Via DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የተፈጠረውን ችግር ከደቂቃዎች በኃላ በዝርዝር አቀርባለሁ!! #ድሬዳዋ_ዩኒቨርሲቲ
አሁንም አድማ ላይ ናቸው...

ጠቅላይ ሚንስትር #አብይ_አህመድና የህክምና ባለሙያዎች ያሏቸውን ቅሬታዎችና የመብት ጥያቄዎች በተመለከተ ሀገር አቀፍ ውይይት ቢያደርጉም አንዳንድ የጤና ባለሙያዎቹ አሁንም ድረስ አድማ ላይ መሆናቸውን ፎርቹን አስነብቧል። ውይይቱ ውጤታማ እንዳልነበረም ዘገባው አብራርቷል። የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የጤና ባለሙያዎችና ኢንተር ሀኪሞች አሁንም አድማ ላይ ናቸው።

Via #ፎርቹን/በዋዜማ/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ከትናንት በስቲያ ጀምሮ ተፈጥሮ የነበረው ረብሻ እየተረጋጋ መሆኑን ዩኒቨርስቲው ለሸገር ራድዮ ተናገረ፡፡ ችግሩን በእርቅና በመግባባት ለመፍታትም ከተማሪዎች ጋር ንግግር ማድረግ መጀመሩን ሰምተናል፡፡

ሸገር ራድዮ ከዩኒቨርስቲ ተማሪዎቹ እንደሰማው ከዚህ ቀደም የተለያዩ የቀድሞ የአገር መሪዎችን፣ የአክቲቪስቶችን እና ምንም ዓይነት የባንዲራ ምስል የታተመበትን ቲሸርት በግቢው ውስጥ ለብሶ መንቀሳቀስ ተከልክሏል፡፡ ይህም የሆነው ምስሎቹ በታተሙባቸው ቲሸርቶች መነሻነት ፀብ ይነሳ ስለነበር ነው ብለዋል ተማሪዎቹ፡፡

ከትናንት በስቲያ ግን እንዳይለብሱ የተከለከለውን የባንዲራ ምስል ያለበትን ቲሸርት ለብሰው ወደ ግቢ እንገባለን ያሉ የተወሰኑ ተማሪዎች ከግቢው የፀጥታ አካላት ጋር ተጋጭተዋል፡፡በዚሀም መነሻ ረብሻ ተነስቶ በድንጋይ የመፈንከት አደጋ የደረሰባቸውና ሆስፒታል የገቡ ተማሪዎች እንዳሉ ሰምተናል፡፡

የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተሯ ወ/ሮ መቅደስ ካሳሁን በበኩላቸው የፀቡ መነሻ ተማሪዎች ያሉት መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡ተማሪዎች እርስ በርስ እንዳይጋጩ መሰረታዊ ችግሩን ለማወቅና እርቅ ለማውረድ ዛሬ ከተማሪዎቹ ጋር ዩኒቨርስቲው እየመከረ መሆኑን ነግረውናል፡፡በድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ የተቋረጠው የመማር ማስተማር ሂደት ዛሬ የመግባባት ንግግር ከተደረገ በኋላ ይጀመራል ተብሎ እንደሚጠበቅም ወይዘሮ መቅደስ ለሸገር ተናግረዋል፡፡

Via Sheger Radio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ...

#ድሬዳዋ_ዩኒቨርሲቲን በተመለከተ ከTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት የተገኘውን የተጣራ እና ትክክለኛ የግቢውን ሁኔታ የሚያስረዳ መረጃ አዘጋጅቼ እንደጨረስኩ አቀርብላችኃለሁ!!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የስራ ማቆም አድማ ሊመቱ ነው...

/የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ድህረ ምረቃ ተማሪዎች/

"...መንግስት ጥያቄዎቻችን ለመመለስ ዝግጁ
አለመሆኑን ተረድተናል፡፡ በዚህም ምክንያት ዛሬ ግንቦት 06 ቀን 2011 ዓ.ም ሁላችንም ተገናኝተን በካሄድነው ውይይት ላይ ሰላማዊ ጥያቄወቻችን ተገቢው ትኩረት ተሰጠቷቸው እንዲመለሱልን እያሳሰብን ከግንቦት 07 ቀን 2011 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ ጥያቄዎቻችን እስከሚመለሱበት ዕለት ድረስ በስራ ቦታ ላይ ላለመገኘት የወሰንን ሲሆን፡ ሆስፒታሉ በቂ ዝግጅት እስኪያደርግ ድረስም(ለሁለት ሳምንታት) የጽኑ ህሙማነን (ICU) የማዋለጃ ክፍል (labor ward) እና ድንገተኛ ክፍሌ( EOPD)ን ብቻ በduty መርሃ ግብር መሰረት የምንሸፍን ይሆናል፡፡ በመሆኑም የሁሉም የትምህርት ክፍል ሀላፊዎች፣ የሆስፒታላችን የአስተዳደርር ሰራተኞች፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አመራሮች እና ሎሎች ችግሩ የሚመለከታችሁ አካላት ድምጻችንን ለማሰማት የሄዴንበትን ውጣ ውረድ ግምት ውስጥ በማስገባት ከጎናችን ትቆሙ ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን ከፍተኛ ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ ኢትዮጵያ ለስደተኞች የምታደርገውን ድጋፍ በተመለከተ በተመድ የኢትዮጵያ የስራ ሃላፊዎች ጋር ተወያዩ።

ኮሚሽነሩ ኢትዮጵያ ስደተኞችን ተጠቃሚ ለማድረግ እየወሰደቻቸው የሚገኙ እርምጃዎችን በተመለከተ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተወያይተዋል።

ኢትዮጵያ ከተለያዩ ሀገራት የመጡ ስደተኞች በሀገሪቱ በሚኖራቸው ቆይታ በተለያዩ ዘርፎች ተጠቃሚ መሆን እንዲችሉ ስራዎችን እየሰራች መሆኗ የሚታወቅ ነው።

ከእነዚህ መካከል በቅርቡ የፀደቀው የስደተኞች አዋጅ አንዱ ሲሆን፥ አዋጁ ስደተኞች ወይም ጥገኝነት ጠያቂዎች በመረጡት የሀገሪቷ አካባቢ የመዘዋወርና የመኖሪያ ቦታ የመመስረት እንዲሁም በፈለጉት ጊዜ ከሀገር የመውጣት ነጻነት እንዲያገኙ ያስቻለ ነው።

ኢትዮጵያ አሁን ላይ ከ920 ሺህ በላይ የሶማሊያ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን እና ኤርትራ ስደተኞችን አስጠልላ ትገኛለች።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከአዲስ አበባ...

"አረ የመንግስት ያለህ በልልን አልያስ ከጥር ወር ጀምሮ ውሐ አጣን በ0112770754በ0112771127 በየቀኑ እየደወልን ብናሳውቅ የሚሰማን አጣን በአንድ ትልቅ መስመር(ቱቦ) የሚመጣ ውሐ ወደ ግማሽ ቤት ይገባል ወደ ግማሹ አይገባም ኮልፌ መናፈሻ ፖርክ አካባቢ የድሮ ከፍተኛ 27 ቀበሌ 07"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምርመራ እየተደረገባቸው ነው...

በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በድጋሚ በተነሳው የእሳት ቃጠሎ እጃቸው እንዳለበት የተጠረጠሩ 2 ግለሰቦች በቁጥጥጠር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው ነው ተባለ፡፡

የደባርቅ ወረዳ የወንጀል ምርመራ የስራ ሂደት ሀላፊ ኢንስፔክተር ደጉ ብርሃኑ ለሸገር እንደተናገሩት ሁለቱ ተጠርጣሪዎች ፓርኩን እናቃጥለዋለን በሚል ሲዝቱ የነበሩ ናቸው፡፡

ተጠርጣሪዎቹ በፓርኩ ላይ ጥፋት ለመፈፀም ሲዝቱ እንደነበር የሚያሳዩ መረጃዎች መኖራቸውንም ኢንስፔክተር ደጉ ለሸገር ራድዮ ተናግረዋል፡፡

የስራ ግዴታዎቻቸውን በተገቢው ሁኔታ አልተወጡም የተባሉ 6 ስካውቶች ወይም የጥበቃ ሰራተኞችም በጥርጣሬ ተይዘው በገንዘብ ዋስትና ጉዳያቸውን ውጪ ሆነው እንዲከታተሉ ተፈቅዶላቸዋል ተብሏል፡፡ ሌሎች በቃጠሎው እንደተሳተፉ የሚጠረጠሩ ሰዎች የእስር ማዘዣ ወጥቶባቸው በፖሊስ እየተፈለጉ መሆኑን ኢንስፔክተር ደጉ ተናግረዋል፡፡

Via #ShegerFM
@tsegabwolde @tikvahethiopia