TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
214 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update በአሜሪካ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው የተሾሙት አምባሳደር #ፍፁም_አረጋ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አቅርበዋል።

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Breaking

በቻይና በእስር ላይ ለምትገኘው ናዝራዊት አበራ ኮኬን የተሰኘውን አደንዛዥ እፅ ሰጥታለች በሚል ወንጀል የተጠረጠረችው ስምረት ካህሳይ ከጓደኛዋ #ሰለሞን_ፀጋዬ ጋር በቁጥጥር ስር ዋለች፡፡

Via EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ናዝራዊት አበራ...

በቻይና በእስር ላይ ለምትገኘው ናዝራዊት አበራ ኮኬን የተሰኘውን አደንዛዥ እፅ ሰጥታለች በሚል ወንጀል የተጠረጠረችው ሳምራዊት ካህሳይ ከጓደኛዋ ሰለሞን ፀጋዬ ጋር በቁጥጥር ስር ውላለች፡፡

የናዝራዊት አበራ አብሮ አደግ ጓደኛ እንደሆነች የሚነገርላት ስምረት ካህሳይ በ5 የሻምፖ እቃዎች ኮኬን የተሰኘው አደንዛዥ ዕጽ አታላት ቻይና እንድታደርስላት በማድረጓ ተጠርጥራ ነው በትናንትናው እለት #የፌዴራል_ፖሊስ በቁጥጥር ስር ያዋላት፡፡

ከብራዚል ወደ ኢትዮጵያ በማምጣት ቻይና እንዲላክ የተደረገው አደንዛዥ ዕጽ ከመኖሪያ ቤቱ በመገኘቱ የስምረት ጓደኛ ሰለሞን ፀጋዬ የተባለው ግለሰብም በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

በጠቅላይ አቃቢ ህግ የተቋቋመው የምርመራ ቡድን ከብራዚል በኢትዮጵያ ወደ ቻይና ስለተጓጓዘው ዕጽና ከሽያጩ የሚገኘውን የገንዘብ ዝውውርን ጨምሮ ሌሎች ወንጀሎችን የማጣራት ስራ መጀመሩ ታውቋል፡፡

የምርመራ ቡድኑ በቻይና በዕስር ላይ የምትገኝ ናዝራዊት አበራ ወደ ኢትዮጵያ ተላልፋ እንድትሰጥ ጭምር እንደሚሰራ ከጠቅላይ አቃቢህግ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ሳምራዊት ካህሳይ ከዚህ ወንጀል ጋር በተያያዘ ቀደም ሲል በቁጥጥር ስር ዉላ በዋስ የተለቀቀች መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን በድጋሚ በቁጥጥር ስር ልትውል የቻለችው ፖሊስ አዲስ መረጃ ማግኘቱን ተከትሎ ፍርድ ቤት እንድትያዝ በመፍቀዱ ነው፡፡

Via #ebc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰላም...

ግጭት ተከስቶባቸው የነበሩት አካባቢዎች በዛሬው ዕለት ወደሠላማዊ እንቅስቃሴያቸው እየተመለሱ ይገኛሉ:: የተዘጉ መንገዶችም በመከፈት ላይ ናቸው::

@tsegabwolde @tikvahethiopia
“ጥቃት በፈፀሙ #ታጣቂ ሃይሎች ላይ የማያዳግም እርምጃ ይወሰዳል”- የጠቅላይ ሚንስትር ጽ/ቤት

በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር እና በሰሜን ሸዋ ዞኖች ጥቃት በፈፀሙ ታጣቂ ሃይሎች ላይ መንግስት የማያዳግም እርምጃ እንደሚወስድ የጠቅላይ ሚንስትር ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡

አካባቢዎቹን ለማረጋጋት የፌዴራልና የክልል የፀጥታ አካላት ተመጣጣኝ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰዱ ትዕዛዝ መተላለፉንም የጽህፈት ቤቱ ፕሬስ ሴክሬታሪ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ተናግረዋል፡፡

እሁድ ከፍተኛ ረብሻ ተስተውሎባቸው የነበሩት ኬሚሲ፣አጣዬ እና ማጀቴ አካባቢዎች ትናንት አንጻራዊ መረጋጋት እንደታየባቸው አቶ ንጉሱ አስረድተዋል፡፡

በሰላማዊ ዜጎች ላይ ጥቃት በፈፀሙ ፣ ባቀናበሩ እና ባስተባበሩ አካላት ላይ መንግሰት የማያዳግም እርምጃ ይወስዳል ያሉት አቶ ንጉሱ ለዚህም ህብረተሰቡ በድርጊቱ የተሳተፉ ሰዎችን ለህግ አሳልፎ በመስጠት እንዲተባበር ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ምንጭ - ፋና
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከሚሴ🔝

የከሚሴ የፀጥታ ሁኔታ በፌደራል ፖሊስ እና በሀገር መከላከያ ሰራዊት ታጅቦ ሰላም ሰፍናል:: ዘላቂ ሰላም እንዲኖር ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል በተለይም የከሚሴ ወጣቶች በጋራ #ለሰላም መስራት አለባቸው::

#king ከከሚሴ(Tikvah-Ethiopia)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሰላም ኮንፈረንስ....

የኦሮሚያና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት የጋራ መድረክ በዛሬው እለት በአሶሳ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል:: የሁለቱ ክልሎች የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት የጋራ መድረክ ለመሳተፍም የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎችን ጨምሮ የሁለቱም ክልሎች ተወካዮች ወደ አሶሳ ከተማ ገብተዋል። በዛሬው እለተም የኢፌዲሪ የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል እና የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ አሶሳ ከተማ ገብተዋል።

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰላም እና መረጋጋት እየታየ ነው...

በአማራ ክልል የፀጥታ ችግር ተፈጥሮባቸው የነበሩ የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር እና በሰሜን ሸዋ ዞኖች #መረጋጋትና #ሰላማዊ ሁኔታ እንደሚታይ ተገለፀ።

የአማራ ክልል ሰላም እና ደህንነት ግንባታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኮሎኔል አለበል አማረ እንደተናገሩት፥ የፀጥታ ችግሩ ተከስቶባቸው በነበሩ በሁሉም አካባቢዎች መረጋጋት እና ሰላማዊ ሁኔታ ታይቶባቸዋል።

የአካባቢውን ሰላማዊ እንቅስቃሴ ወደ ነበረበት ለመመለስ የፀጥታ አካላት ከህብረተሰቡ ጋር እየሠሩ እንደሚገኙ የገለፁት ኮሎኔል አለበል፥ አጥፊዎችን በሕግ ተጠያቂ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተነግሯል።

አሁንም ቢሆን ግጭቱን ወደ ሌሎች አካባቢዎች ለማዛመት እና ችግሩን ለማባባስ የተለያዩ ያልተጣሩ መረጃዎችን የሚያሰራጩ ግለሰቦች በመኖራቸው ህዝቡ ከወዲሁ መጠንቀቅ እንዳለበት መልዕክት አስተላልፈዋል።

ግጭቶቹ የተከሰቱባቸው አካባቢ ነዋሪዎች በበኩላቸው፥ ችግር ተፈጥሮባቸው የነበሩ አብዛኛዎቹ አካባቢዎች የተሻለ መረጋጋት ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

እንደ አስተያት ሰጭዎቹ፥ ተፈጥሮ በነበረው ችግር ምክንያት ተደናግጠው አካባቢያቸውን ለቀው ወደ ፈረዶ ውኃ እና መሀል ሜዳ ሸሽተው የነበሩ የአጣየ ከተማ ቀበሌ 01፣ 02 እና 03 ነዋሪዎች ወደ ቀያቸው እየተመለሱ ነው፡፡

በማጀቴም ከትናንት የተሻለ ሰላማዊ ሁኔታ እንደሚታይ ተጠቁሟል።

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰልፉ በሰላም ተጠናቀል...

#በሀዋሳ_ከተማ ህገ መንግስታዊ #መብታችን ይከበር በሚል ሲደረግ የነበረው ሴቶች ብቻ የተሳተፉበት ሰላማዊ ሰልፍ #በሰላም ተጠናቀዋል::

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በድጋሜ ቃጠሎ ተነስቷል። እሳቱ #ግጭ ከሚባለው የፓርኩ አካባቢ መነሳቱን ከታማኝ ምንጮች አብመድ መረጃ አግኝቷል፡፡ የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ከመጋቢት 19 ቀን 2011ዓ.ም ምሽት ጀምሮ ባጋጠመው የእሳት አደጋ በሳንቃ በር እና እሜት ጎጎ አካባቢ በርካታ ሄክታር ደን መውደሙ የሚታወስ ነው፡፡

Via አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia