#update ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የስዊዲን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማርጎት ቫለርስትሮም ጋር ዛሬ አገኝተው አነጋገሩ። በዚሁ ወቅትም በኢትዮ ስዊዲን ትብብር ዙሪያ የተወያዩ ሲሆን፥ ቫለርስትሮም ስዊዲን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል በድጋሜ ማረጋጣቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት አስታውቋል።
#PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀገር ማለት ሰው ነው፤ ሰው ማለት ሀገር ነው፡፡ አባቶች በደም ዋጋ በአደራ የሰጡኝን ምድር በንፅህና ጠብቃለው፡፡ ነገ በገርጂ ታክሲ ተራ ልዩ አረንጓዴ አድዋ ፅዳት ዘመቻ በሴፍ ላይት የወጣቶች ንቅናቄ ከዓለም ጋለሪና ከወረዳ 13 ፅህፈት ቤት ጋር በመተባበር ያደርጋል፡፡ ልክ ጠዋት 1:00 በአለም ጋለሪ እንገናኝ፡፡ አደዋ የእኔ የስራ ወኔ ነው፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአዲስ አበበ የስራ ፍቃዳቸዉን ባላሳደሱ የንግድ ተቋማት ላይ ህጋዊ #እርምጃ እየወሰደ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ የንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡ በአዲስ አበበ ከተማ ዉስጥ በ2011 የንግድ ፍቃዳቸዉን ማሳደስ የሚጠበቅባቸው 251 ሺ 6 መቶ የንግድ ተቋማት ቢኖሩም፣ ፍቃዳቸዉን እስከ ታህሳስ 30፣2011 ዓ.ም ድረስ ማደስ የቻሉት ግን ከ218ሺ አይበልጡም ተብሏል፡፡
Via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዜና እረፍት‼️
ሁለት ታዋቂ የኪነ ጥበብ ባለሞያዎች ትናንት ምሽት ከዚህ አለም በሞት ተለዩ፡፡ ትናንት ምሽት በሞት የተለዩት የኪነ ጥበብ ባለሞያዎቹ #ጌታቸው_ደባልቄ እና #አሚር_ዳውድ ናቸው፡፡
አቶ ጌታቸው ደባልቄ ለረጅም ዓመታት በጸሐፊ ተውኔት እና በአዘጋጅነት ሰርተዋል፡፡ በ83 አመታቸው ያረፉት የአንጋፋው የኪነ ጥበብ ባለሞያ የቀብር ስነ ስርአት ነገ ይፈጸማል ተብሏል፡፡
በትግርኛ ዘፈኖቹ የሚታወቀው አርቲስት አሚር ዳውድ ትናንት ምሽት በመቐለ አይደር ሆስፒታል ነው ያረፈው፡፡ አርቲስቱ የግጥምና የዜማ ደራሲ ሲሆን፥ በተለይም አይሞቱም ጀጋኑና በሚለው ሙዚቃው ይታወቃል። በአርቲስቱ ህልፈት የትግራይ ክልል መንግስት የተሰማውን ሐዘን ገልጿል።
Via fbc

#update የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ አዲስ አበባ ገብተዋል። ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አቀባበል አድርገውላቸዋል። ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በኢትዮጵያ ለሁለት ቀናት ቆይታ ያደርጋሉ። ፕሬዚዳንቱ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ባለው የኢትዮ ኬንያ ንግድና ኢንቨስትመንት ፎረም ላይ እየተሳተፉ ይገኛል።
Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ጥንቃቄ አድርጉ‼️ #ከኢትዮጵያ ወደ #ቻይና የምትሄዱ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ሰዎች ይህን እቃ እዛ ላለ ሰው አድርስልኝ/አድርሺልኝ ሲሏችሁ በደንብ የሚላከውን ነገር ፈትሹ። ቻይና ከሚገኙ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ለመረዳት እንደቻልነው አንዳንዶች በሚላከው እቃ ውስጥ አደንዛዥ እፆችን በመጨመር እንደሚልኩ ጠቁመዋል። በተለይ ምግብ ነክ ነገሮች ውስጥ የአደንዛዥ እፆችን በመክተት ይልካሉ።…
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር‼️
በህገ ወጥ ደላሎች #ነፃ የትምህርት አግኝታችኋል ተብለው ወደ ቻይና የሚጓዙ ዜጎች ለከፍተኛ እንግልት እየተዳረጉ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አቶ #ነብያት_ጌታቸው ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ በሁለቱ ሀገራት በሚገኙ ህገ ወጥ ደላሎች ነጻ የትምህርት እድል አግኝታችኋል ተብለው ወደ ቻይና የሚጓዙ ዜጎች ቁጥር እየተበራከተ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡
ወጣቶቹ አግኝታችሁታል የተባለው ነፃ የትምህርት እድል #ሀሰተኛ በመሆኑ ቻይና ሲደርሱ ለከፍተኛ ችግር እየተጋለጡ መሆኑንም ነው የተናገሩት።
ከዚህ ባለፈም በቻይና አደገኛ እፅ #በማዘዋወር እና #ጫትን ከኢትዮጵያ ወደ ቻይና በማስገባት በህገ ወጥ ስራ ላይ እየተሳተፉ መሆኑን ቃል አቀባዩ አብራርተዋል፡፡
ቃል አቀባዩ በቻይና በዚህ አይነት ወንጀል መሳተፍ ከእድሜ ልክ እስራት እስከ #ሞት ቅጣት በሚደረስ ፍርድ የሚያስቀጣ መሆኑንም ገልጸዋል።
በአሁኑ ወቅትም በዚህ ህገ ወጥ ተግባር ላይ ተሰማርተዋል የተባሉ 47 ኢትዮጵያውያን በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተጠቁሟል፡፡
ከእነዚህ ውስጥ የተወሰኑት በፍርድ ቤት #ጥፋተኛ ተብለው የእርምት ጊዜያቸውን እየተከታተሉ የሚገኙ ሲሆን የቀሪዎቹ ደግሞ ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ዜጎች ከተመሳሳይ ችግር ለመውጣት የትምህርት እድል አግኝታችኋል ሲባሉ ከተቋማቱ በቂ መረጃ መሰብሰብ እንደሚገባቸውም ቃል አቀባዩ አሳስበዋል፡፡
በሌላ በኩል ወደ ቻይና ለተለያዩ ጉዳዮች የሚጓዙ ኢትዮጵያውያን የታሸጉ ነገሮችን ወደ ቻይና አድርሱልን ተብለው ሲጠየቁ ስለእቃዎቹ ትክክለኛ መረጃ ማግኘት ይገባቸዋልም ነው ያሉት።
እነዚህ ወንጀሎች የሁለቱን ሀገራት ጠንካራ ግንኙነት እንዳያበላሹም መንግስታቱ እርስ በርስ የተሳሰሩ ደላሎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል እየሰሩ ነው ብለዋል፡፡
በሌላ በኩል በህገ ወጥ መንገድ ወደ ሌሎች ሀገራት የሄዱ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም ቃለ አቀባዩ አስታውቀዋል፡፡
በዚህም በተያዘው ሳምንት 1 ሺህ 40 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ እና 1 ሺህ 15 ኢትዮጵያውያን ከፑንትላንድ መመለሳቸውን ጠቅሰው፥ በቀጣይ ሳምንት ደግሞ 500 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ እንዲሁም ከፑንትላንድ 517 ዜጎች እንደሚመለሱ አውስተዋል።
እነዚህን ዜጎች ከሀገራት ለማስመለስ ከአለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ጋር በትብብር እየተሰራ ነው።
ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር‼️
የአዲስ አበባ ከተማ የፀጥታ ም/ቤት የዓድዋ ፌስቲቫል እና የዓድዋ በዓል አከባበርን በተመለከተ ከተወያየ በኃላ የሚከተለውን መግለጫ ሰጥቷል፡፡
በዘንድሮው የዓድዋ ድል በዓል ከ500ሺ በላይ ተሳታፊዎች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል፡፡
ለዚህም የከተማ አስተዳደሩ በዓሉን በደመቀ ሁኔታ ለማክበር እና የህብረተሰቡን ደህንነት ለመጠበቅ አስፈላጊው ዝግጅት በሙሉ ማጠናቀቁንም አስታውቋል፡፡
በዕለቱ በዓሉን ለሚያከብሩ የከተማችን ነዋሪዎች የሸገር የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት በነፃ የሚሰጥ ሲሆን በዚህም የከተማ አስተዳደሩ ለትራንስፖርት ዝግ የተደረጉ መንገዶችንም ይፋ አድርጓል፡፡
በዚህም ፦
- ከቂርቆስ እና ቦሌ ለሚመጡ የበዓሉ ታዳሚዎች የደንበል መንገድን እንዲጠቀሙ፤
- ከነፋስስልክ እና አቃቂ ለሚመጡ የበዓሉ ታዳሚዎች በጎተራ-ሪቼ መንገድ እንዲጠቀሙ፤
- ከኮልፌ እና ልደታ ለሚመጡ የበዓሉ ታዳሚዎች የለገሃር መንገድ እንዲጠቀሙ፤
- ከአዲስከተማ እና ጉለሌ ለሚመጡ የበዓሉ ታዳሚዎች የፒያሳ-ጊዮን መንገድ እንዲጠቀሙ፤
- ከኮልፌ ፣ አራዳ ፣ የካ እና ጉለሌ የሚመጡ የበዓሉ ታዳሚዎች በጊቢ ገብርኤል-ECA መንገድ እንዲጠቀሙ እና ለበዓሉ ታዳሚዎች ሲባል ከላይ የተገለፁት መንገዶች ለትራፊክ ዝግ የሆኑ ሲሆን የከተማችን ነዋሪዎች ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙም ገልፀዋል፡፡
በተጨማሪም የበዓሉ ታዳሚዎች በተገለፁት መንገዶች ብቻ እንዲጠቀሙ ም/ቤቱ ጥሪ አቅርቧል፡፡
በመጨረሻም በዓሉ ተጀምሮ እስኪያልቅ የህብረተሰቡን ደህንነት ለመጠበቅ አስፈላጊውን ዝግጅት በሙሉ ማድረጉንም የፀጥታ ም/ቤት በዛሬው ዕለት አስታውቋል፡፡
Via @mayorofficeAA