TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ...

"ፀግሽ እባክህ #ሚዛን_ቴፒ_ዩኒቨርሲቲ የቴፒ ግቢ የክረምት ተማሪዎች የርቀት ኮርስ ሞጁልና አሳይንመንት አልተሰጠንም፤ የሚንማር መሆኑ ራሱ ያጠራጥራል፤ የሚመለከተው አካል የክልልም ሆነ የፌደራል መንግስት ትኩረት ሰጥቶ መፍትሔ ቢፈልግ መልካም ነው።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የቴፒ ነገር...

"እንደምን አለህ ፀጋአብ ወልዴ? በቴፒ ከተማ በተፈጠረው ግጭት የቴፒ ዩኒቨርስቲ መማር ማስተማር ተግባር የተጓተተ መሆኑ ይታወቃል፤ እንዲሁም አሁንም ድረስ አልተረጋጋም። የመደበኛ ተማሪዎች ትምህርት እስከ ነሐሴ 21 2011 ዓም ድረስ ነበር የወጣው። ነገር ግን እኛ የክረምት የመንግሥትም ሆነ የግል ተማሪዎች ዕጣ ፈንታችን ምንድን ነው? መንግስት ወደ ሌላ ዩኒቨርሲቲ #ለማዛወር አቅዷል ወይስ ሁለቱንም መደበኛና የክረምት ተማሪዎችን እንድ ላይ ለማስከድ አስቧል? የማይቻል ከሆነ ከወዲሁ ወደሌላ ዩኒቨርሲቲ የማዛወር ፕሮሰስ እንዲመቻች የሚመለከተው አካል ድርሻውን እነዲወጣ መረጃውን አድርሱልን። አመሰግናለሁ!!"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"አድዋ ላይ #የወደቅነው፤ ሶማሊያን ስንዋጋ #ደማችንን ያፈሰስነው ተከፍሎን አይደለም፤ ቅጥረኞች ሆነን አይደለም። የሞትነው ለአገራችን ነው፤ የሞትነው ለኢትዮጵያ ነው።" ኦቦ #ለማ_መገርሳ (የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በለገጣፎ ለገዳዲ ሲከናወን የነበረው ቤት ማፍረስ ተጠናቋል። በለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ አስተዳደር የከተማውን ፕላን የማስጠበቅ ሥራ በከተማው ከዚህ በፊት በአረንጓዴ ቦታዎች /green area /:ወንዝ ዳርቻዎችን: አስተዳደሩ ካሳ ከፍሎባቸው ቤት የተሰራባቸውን ቦታዎች እና ለማህበራዊ አገልግሎት የተፈቀዱ ቦታዎች ላይ የተሰሩት ቤቶችን የማፍረስ ስራ ባለፈው ሣምንት መጀመሩ ይታወቃል ለስምንት ቀናት ሲካሄድ የቆየው ሥራው መጠናቀቁን የከተማው አስተዳደር የመሬት አጠቃቀም እና አስተዳደር ሃላፍ የሆኑት አቶ ላልሳ ዋቅዋያ ገልጸዋል። እንደ ሀላፍው ገለጻ በዚህ ሥራም 800 ሰዎች የምኖሩበት ቤት:1000 ቤቶች ሰዎች ያልገቡባቸው እና 1700 አጥር በአጠቃላይ 3500 ቤቶች እና አጥር መፍረሱን ገልጸው በዚህም 36.5 ሄክታር መረት ማስከበሩንም ገልጸዋል። የለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኢንስፐክተር ግርማ ገላን በበኩላቸው ፖሊስ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጉን ገልጸው ይህም ሥራው በዕቅዱ እንድጠናቀቅ ማስቻሉን ተናግረዋል።

Via ለገጣፎ ኮሚኒኬሽን
©ኤልያስ መሰረት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Adwa123 #አድዋ123-አዲስ አበባ🔝

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለ123ኛ ጊዜ የሚከበረውን የዓድዋ ድል በዓል ለየት ባለ መልኩ እንደሚያከብር ቀደም ብሎ መግለፁ ይታወሳል፡፡

በዚህም የአድዋ ተጓዦችን በክብር ከመሸት የጀመረው የከተማ አስተዳደሩ ተግባር በዓሉን ለማድመቅ የተዘጋጁ ፕሮግራሞችን እና በዕለቱ የተዘጋጁ ስነ-ስርዓቶች ላይ የፕረስ ሴክረታሪዋ ወ/ሪት #ፌቨን_ተሾመ እና የከተማ አስተዳደሩ የባህል የኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ረ/ፕሮፌሰር #ነብዩ_ባዬ ለጋዜጠኞች ማብራርያ ሰጥቷል፡፡

በዚህም ሐሙስ(በ21-06-2011ዓ.ም) በብሄራዊ ቤተ-መዛግብት የፊልም ፌስቲቫል ይደረጋል፡፡

ዓርብ (በ22-06-2011ዓ.ም) በዓሉን በተመለከተ የስነ-ጥበብ ድግስ በጣይቱ ሆቴል ተዘጋጅቷል፡፡

በበዓሉ ዕለት ማለትም (በ23-06-2011ዓ.ም) ጠዋት ላይ በጊዮርጊስ አደባባይ የተለመደው የዓድዋ ሰመዓታትን የማስታወስ እና የማወደስ ስነ-ስርዓት ይደረጋል፡፡

በመቀጠልም በዓሉ ከሚደረግበት የጊዮርጊስ አደባባይ እስከ ዓድዋ ድልድይ የሚደረገው የእግር ጉዞ እና ዓርበኞችን እና የበዓሉ ታዳሚዎችን ግብር የማብላት ስነ-ስርዓትም በቅደም ተከተል ከዚህ ቀድሞ በነበረው መልኩ የሚከናወን ይሆናል፡፡

በመጨረሻም የበዓሉ ቀን ከሰዓት ከ8:00 ሰዓት ጀምሮ በከተማ አስተዳደሩ አዘጋጅነት የ"አድዋ ፌስቲቫል!" የሙዚቃ ድግስ ተዘጋጅቷል፡፡

የሙዚቃ ድግሱ መግቢያ በነፃ ሲሆን በፌስቲቫሉ ላይ በርካታ የሃገራችን የኪነ-ጥበብ ፈርጦች የሚሳተፉ ይሆናል፡፡

ስለዚህ የከተማችን ነዋሪዎች በዚህ የሃገራችን ህዝቦች የድል በዓል የሆነውን የዓድዋ ድል በዓል ፌስቲቫል ላይ እንዲታደሙ እና በዓሉን በደማቅ ሁኔታ በጋራ እንድናከብር ሲል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጥሪውን ያቀርባል፡፡

Via @mayorofficeAA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና‼️

በኢሉአባቦር ዞን #መቱ ከተማ በደረሰ የግንብ አጥር #መደርመስ አደጋ የአንድ ቤተሰብ አባል የሆኑ ሰባት ሰዎች ህይወት አለፈ። የመቱ ከተማ ፖሊስ ጽህፈት ቤት የወንጀል ምርመራና ፍትህ አሰጣጥ ሥራ ሂደት መሪ ኮማንደር ተሾመ ታደሰ ለኢዜአ እንደገለጹት አደጋው ትላንት ከሌሊቱ 8፡00 ሰዓት ላይ የደረሰው በከተማው ቀበሌ 01 ውስጥ ነው፡፡

የሰዎቹ ሕይወት ሊያልፍ የቻለው በከፍታ ተሰርቶ የነበረው አንድ የንግድ ድርጅት የግንብ አጥር በጎረቤት መኖሪያ ቤት ላይ ድንገት በመደርመሱ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡

በአደጋው በእንቅልፍ ላይ የነበሩ እናትና ስድስት ልጆቻቸው ሕይወት ወዲያውኑ ማለፉን ኮማንደር ተሾመ ተናግረዋል፡፡

ሕይወታቸውን ካጡ የቤተሰቡ አባላት አምስቱ ዕድሜያቸው ከ15 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊ ህጻናት ናቸው፡፡

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለተቃዋሚዎችም በሩ ክፍት ነው...‼️

የኢሕአዴግ መሥራች የሆኑትን አራት ድርጅቶችና አጋሮችን በማካተት በጥቂት ወራት ውስጥ እንደሚመሠረት በተገለጸው አንድ አገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲ ውስጥ፣ #መካተት ለሚፈልጉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በሩ ክፍት መሆኑን ግንባሩ አስታወቀ።

ከጥቂት ቀናት በፊት ከኢሕአዴግ አጋር ድርጅቶች ከፍተኛ አመራሮችና አጋር ፓርቲዎቹ ከሚመሯቸው ክልሎች ከተወጣጡ የማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አዳራሽ የተወያዩት የኢሕአዴግ ሊቀመንበርና ጠቅላይ ሚኒስትር #ዓብይ_አህመድ (ዶ/ር)፣ ኢሕአዴግ አጋር ድርጅቶችን አካቶ በመዋሀድ አንድ አገር አቀፍ ፓርቲ በጥቂት ወራት ውስጥ እንደሚመሠረት መግለጻቸው ይታወሳል።

በኢሕአዴግ ውሳኔ ብቻ የሚመረጥ #የአገር_መሪ የመሰየም አካሄድ እንደሚያበቃና የአጋር ድርጅቶች ሲያነሱ የቆዩት የፓለቲካ ውክልና ጥያቄም በዚህ እንደሚመለስ የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ‹‹ከጥቂት ወራት በኋላ የአፋር፣ የቤኒሻንጉል ጉምዝ፣ የሶማሌ፣ የኦሮሞ፣ የአማራ ... ፓርቲ እያልን አንሄድም። እንደ ኢሕአዴግ ከጫፍ ጫፍ ያሉ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን በነፃነት የሚሳተፉበት አንድ አገራዊ ፓርቲ እንመሠርታለን፤›› ብለዋል።

ይኼንን ጉዳይ በተመለከተ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ #ሳዳት_ነሻ የኢሕአዴግንና የአጋሮቹን ውህደት በተመለከተ የተከናወነው ጥናት መጠናቀቁን ገልጸው፣ በጥናቱ የተለዩት ግኝቶችን መሠረት በማድረግ ሁሉም የኢሕአዴግ አባልና አጋር ድርጅቶች በቅርቡ ከሚመሩት ማኅበረሰብ ጋር በተናጠል ውይይት ማድረግ እንደሚጀምሩ አስረድተዋል። በውይይት ከዳበረ በኋላም መሟላት የሚገባውን ሥነ ሥርዓት ተከትሎ በዓመቱ መገባደጃ ላይ አንድ አገር አቀፍ ፓርቲ ለመመሥረት የሚያስችለው ውሳኔ ይተላለፋል ተብሎ እንደሚገመት ገልጸዋል።

በኢሕአዴግና በአጋሮቹ ውህደት በሚወለደው አዲስ አገር አቀፍ ፓርቲ ውስጥ አባል ለመሆን የሚፈልጉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ካሉ መካተት እንደሚችሉ፣ ለዚህም ኢሕአዴግ በሩን ክፍት እንደሚያደርግ አቶ ሳዳት ገልጸዋል።

በሚመሠረተው አገር አቀፍ ፓርቲ ውስጥ አባል ለመሆን የሚፈልጉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ካሉ ማሟላት የሚጠበቅባቸው፣ የኢሕአዴግን መሠረታዊ ባህሪያት መቀበል እንደሆነ አስረድተዋል።

#ኢሕአዴግና አጋሮቹ የሚያደርጉት ውህደትም ነባር የኢሕአዴግ መሠረታዊ ባህርያትን ሳይለቅና እነዚህን መሠረታዊ ባህሪያትም ለሚመሠረተው አገር አቀፍ ፓርቲ በማውረስ የሚፈጸም መሆኑን  ገለጸዋል፡፡ የብሔርና የቋንቋ ማንነቶች፣ እንዲሁም የፌዴራሊዝም ሥርዓት መርሆች ተጠብቀው፣ ከሚቀጥሉት የኢሕአዴግ መሠረታዊ ባህርያት መካከል ዋናዎቹ መሆናቸውን ለአብነት ጠቁመዋል።

ምንጭ፦ ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሰባት የፖለቲካ ፓርቲዎች በግንባር ለመስራት የሚያስችላቸውን #ጥምረት ለመፍጠር የመግባቢያ ሰነድ #ተፈራረሙ#ሰነዱን የተፈራረሙት የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ)፣ የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢህአፓ)፣ የኢትዮጵያ ዴሞክራቲክ ህብረት (ኢዴህ)፣ የኢትዮጵያ ብሄራዊ አንድነት ፓርቲ (ኢብአፓ)፣ የአፋር ህዝቦች ፍትሃዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ የአፋር ህዝቦች ነፃነት ፓርቲ እና የኦሮሞ ህዝቦች ፍትሃዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ናቸው። ጥምረቱ በሃገሪቱ ያለውን የመድብለ ፓርቲ ጅምር ስራዎችን በማጠናከር እየመጣ ያለውን ለውጥ ለማጠፍ የሚጥሩ አካላትን ለመመከት እንደሚያግዝ ስምምነቱን በተፈራረሙበት ወቅት ገልፀዋል፡፡ ግንባሩ ከሁሉም ፓርቲዎች የተውጣጡ ኮሚቴ አቋቁሞ ከሁለት ወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ #በተመረጡ አጀንዳዎች ላይ ወደ ስራ ይገባል ተብሏል።

Via fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሙሐመዱ ቡሓሪ ተመረጡ🔝

የናይጀሪያው ፕሬዝዳንት #ሙሐመዱ_ቡሓሪ በተካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የአገሪቱ መሪ ሆነው ዳግም ተመረጡ፡፡ ፕሬዝዳንት ቡሓሪ ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ስልጣን መምጣት ያስቻላቸውን ድምፅ ያገኙተ ባለፀጋውን ተቀናቃኛቸውን #አቲኩ_አቡበከርን በአራት ሚሊዮን ድምፅ በመብለጥ ነው፡፡የድምፅ ልዩነቱ ብዙ ሰፊ ልዩነት ያለው አለመሆኑም ተመልክቷል፡፡ይሁን እንጂ ከተቀናቃኙ ጎራ ተፎካካሪ የሆኑት አቲኩ አቡበክር ውጤቱን ውድቅ አድርገውታል፡፡

የአገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን እንዳስታወቀው በምርጫው ውጤት መሰረት በስልጣን ላይ ያለው የፕሬዝዳንት ቡሓሪ ፓረቲ ከናይጀሪያ 36 ግዛቶች የ19ኙን ግዛቶች አሽንፏል፡፡ ተፎካካሪ የሆነው የአቲኩ አቡበክር PDP ፓርቲ ደግሞ 17 ግዛችን በበላይነት አጠናቋል፡፡ የምርጫው መራዘምና በወቅቱ ሁከት መከሰቱ ምርጫውን እንከን እንዲገጥመው አድርጓል ቢባልመ ምርጫውን ከታዘቡት ወገኖች ውስጥ መጨበርበሩን እስካሁን የገለፀ አካል አለመኖሩን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

የ76 ዓመቱ አዛውንቱ ፐሬዝዳንት ሙሐመዱ ቡሓሪ በቅዳሜው ምርጫ ማሸነፋቸው ናይጀሪያን ለሚቀጥሉት አራት ዓመታት ለሁለተኛ ጊዜ መምራት ያስችላቸዋል፡፡

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የገቢዎች ሚኒስቴር‼️

የ14 ቢሊየን ብር የታክስ ስወራ እና ማጭበርበር የፈፀሙ 105 ግለሰቦች #በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ሚኒስትሯ ወይዘሮ #አዳነች_አቤቤ በሰጡት መግለጫ የህዝብን ሀብት በመበዝበር እና የታክስ ማጭበርበር በመፈፀም የተለዩ 135 ድርጅቶች መለየታቸውን አስታውቀዋል፡፡ በታክስ ስወራው ከተጠረጠሩት 105 ግለሰቦች መካከል 64 የሚሆኑት ፍርድ ቤት መቅረባቸውን ነው ሚኒስትሯ የተናገሩት፡፡

ሚኒስትሯ በመግለጫቸው 9 ቢሊየን ብሩ 100 ቀናቱ የተለዩ መሆናቸውን የገለፁ ሲሆን ቀሪው 4 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በጥርና የካቲት ወር የተለየ እንደሆነ አንስተዋል፡፡ የታክስ ስወራና ማጭበርበር ላይ በዋነኝነት ተሳታፊ ሆነው የተገኙት አከፋፋዮች እና አስመጪዎች ሲሆኑ ቀሪዎቹ ማለትም 30 በመቶዎቹ ብቻ ቸርቻሪ መሆናቸውን በመግለጫቸው ተናግረዋል፡፡

ሚኒስትሯ በታክስ #ስወራና #ማጭበርበር የተለየውን 14 ቢሊየን ብር ድርጅቶቹ ለመንግስት ገቢ እንዲያደርጉ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡ ከዚህ ባለፈ ህግ የማስከበሩ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የተናገሩት ሚኒስትሯ ውጤቱ ለህዝብ ይፋ እንደሚሆን አስታውቀዋል፡፡

Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በክቡር የኢፌድሪ ጠ/ሚንስተር #አብይ_አህመድ(ዶ/ር) ሃሳብ አመንጪነት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሊተገበር የታቀደው የወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክትን ለመደገፍ የቻይና መንግስት #ፍላጎት እንዳለው ገለፀ፡፡ ለዚህም የቻይና መንግስት የባለሞያ ልዑካን ቡድን የከተማ አስተዳደሩ የጀመረውን የወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክትን በገንዘብ እና የቴክኒክ ዕገዛ በሚደረግበት ሁኔታ ላይ ከኢ/ር #ታከለ_ኡማ ጋር በዛሬው ዕለት ተወያይተዋል፡፡ በዚህም የቴክኒክ ቡድኑ የቻይና መንግስት ፕሮጀክቱን የሚደግፍበት ሁኔታ ላይ ጥናት የሚያደርግ ይሆናል፡፡

Via @mayorofficeAA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጨፌ ኦሮሚያ ለሁለት ቀናት ሲያካሂድ የነበረውን 9ኛ መደበኛ ስብሰባ በዛሬው እለት #አጠናቋል። በትናንትናው እለት 9ኛ መደበኛ ስብሰባውን ማካሄድ የጀመረው ጨፌው በዛሬው ውሎውም የተለያዩ ሹመቶችን እና አዋጅ በማጽደቅ ተጠናቋል። ጨፌው የኦሮሚያ ህብረት ስራ ማህበራት ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ እና የ290 ዳኞችን ሹመትም ተቀብሎ ከኦሮሚያ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

Via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Alert ወላይታ ሶዶ‼️

"ሰላም ፀግሽ በወላይታ ሶዶ ከተማ ዙሪያ ህገ ወጥ ቤቶችን #ከማፍረስ ጋር ተያይዞ ወላይታ ሶዶ ከተማ ውስጥ አለመረጋጋት እየተከሰተ በመሆኑ መንግስት አፋጣኝ መፍትሄ ይፈልግ፡፡ እስካሁን ባለው ሁኔታ የታክሲ አገልግሎት እና አጠቃላይ ትራንስፖርት አገልግሎት ተቋርጧል፡፡" ታሪኩ ከወ/ሶዶ

@tsegabwolde @tikvahethiopia