TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.5K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"የህዋ ሳይንስ #ቅንጦት_ሳይሆን የህዝብ ጥቅም #ማስጠበቂያ መንገድ ነው::"- ዶ/ር ሹመቴ ግዛው:- የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ
.
.
የመጀመሪያው የአፍሪካ የፈለከ-ፕላኔት እና የህዋ ሳይንስ ጅማሮ አለም አቀፍ አውደ ጥናት እየተካሄደ ነው፡፡

በአውደ ጥናቱ ከተለያዩ ሀገራት፣ ከዩኒቨርሲቲና ከምርምር ተቋማት የመጡ የዘርፉ ምሁራን እየተሳተፉ ሲሆን ሌሎች ሀገራት ከደረሱበት የህዋ ሳይንስ የእድገት ደረጃ ለመድረስ የተለያዩ ልምዶችን ለመለዋወጥ ያለመ ነው፡፡

በህዋ ሳይንስ የተሻለ ደረጃ ላይ የደረሱ ሀገራት ዘርፉን ገና ኢኮኖሚያቸው ሳያድግ የተቀላቀሉ ሲሆን ኢትዮጵያ ዘግይታም ቢሆን ለመቀላቀል እየሠራች መሆኗ ተጠቁሟል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሹመቴ ግዛው የአለም ሀገራት ከደረሱበት የህዋ ሳይንስ ቴክኖሎጂ በመጀመር የራሳችንን የህዋ ሳይንስ ቴክሎጂ ለመዘርጋት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

‹‹ህዋን የምናስሰው ለህዝባችን ጥቅም ስንል ብቻ ነው›› ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው የህዋ ሳይንስ ሃሳብና ህልማችን እንዲሳካ የተለመደውን አካሄድ መስበር እንደሚስያፈልግ ጠቁመዋል፡፡

ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው አውደ ጥናቱ ለ4 ቀናት የሚቆይ ሲሆን የጠለያዩ ጥናታዊ ፅሁፎች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል፡፡

ምንጭ፦ ኢ.ፕ.ድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሰላም ሚኒስቴር‼️

ከ1 ሚሊየን በላይ #ተፈናቃዮች ወደ መኖሪያ ቀያቸው መመለሳቸውን የኢፌዴሪ ሰላም ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የኢፌዴሪ ሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ #ሙፈሪያት_ካሚል የተቋማቸውን የ6 ወራት አፈፃፀም ሪፖርት ለህዝብ ተወካች ምክር ቤት ለውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ዛሬ አቅርበዋል፡፡

የሰላም ሚኒስትሯ በሪፖርታቸው ከህብረተሰቡ ጋር በተቀናጀ ተግባር 1 ሚሊየን 20 ሺህ ያህል ዜጎችን ወደ ቀያቸው መመለስ መቻሉን ገልጸዋል፡፡

ሚኒስቴሩ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ቀሪ ተፈናቃዮችን በሚቀጥሉት ሁለት ወራት ሙሉ በሙሉ የማቋቋም ስራ እንደሚያከናውንም ተናግረዋል፡፡

በጋምቤላ፣ ደቡብና ኦሮሚያ ክልሎች በተመረጡ 12 ወረዳዎች ግጭቶች ከመከሰታቸወው በፊት የግጭት መንስኤዎችን የመለየትና ቀድሞ መከላከል ስራ መጀመሩንም ጠቁመዋል፡፡

በተለያዩ ግጭቶች ለተፈናቀሉ ዜጎች እለታዊ እርዳታና ድጋፍ ከማድረግ ባለፈ በዘላቂነት ለማቋቋም የሚያስችሉ ስራዎች ባለፉት 6 ወራት መሰራታቸውንም አንስተዋል፡፡

ለሰላም ግንባታ መሰረት መጣሉን የተናገሩት ሚኒስትሯ ግጭቶች ከመከሰታቸው በፊት የግጭት መንስኤዎችን ለመለየት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

ከ900 በላይ በግጭት ወንጀል ድርጊት የተጠረጠሩ ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው ክትትል እየተደረገ ነው ያሉት ሚኒስትሯ፥ ክልሎች በወንጀሉ በዋናነት በመሳተፍ ለተጠረጠሩ ግለሰቦች ሽፋን ከመስጠት ይልቅ አሳልፈው ለህግ እንዲሰጡም ጠይቀዋል።

ኤፍ ቢ ሲ እንደዘገበው የተዘረፉ ንብረቶችን ለማስመለስ እየተሰራ ሲሆን÷ በቃጠሎና ሌሎች ምክንያቶች የወደሙ ንብረቶችን አቅም በፈቀደ መጠን ለመገንባት ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡

የጦር መሳሪያ ዝውውርን ለማስቆም ምንጩን የማጥራት ስራ መጀመሩን ጠቅሰው፥ ህገ ወጥ የገንዘብና የሰዎች ዝውውርም ከሌሎች #የወንጀል ድርጊቶች ጋር ተመጋጋቢ ስለሆነ÷ ወደ ፊት በትኩረት ከሚሰራባቸው ነጥቦች መካከል መሆኑንም ጠቅሰዋል።

via epa
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአማራ እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የህዝብ ለህዝብ የሠላም ኮንፈረንስ ዛሬ #በእንጅባራ ከተማ መካሄድ ጀምሯል። በኮንፈረንሱ የአማራ ክልል ፕሬዝደንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸውና የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ፕሬዝደንት አቶ አሻድሊ ሀሰን ተገኝተዋል።

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የካንሰር ቀን‼️

በኢትዮጵያ ያለው #የካንሰር ህክምና ደካማነት የተነሳ በየአመቱ 65 ሺ ያህል ዜጎች በበሽታው ሕይወታቸውን እንደሚያጡ ተነገረ፡፡

ከቲቢ እና ወባ በሽታዎች ይልቅም በካንሰር ህይወታቸውን የሚያጡ ዜጎች ቁጥር ከፍተኛ ነው ተብሏል፡፡

የበሽታው ስርጭትና የሚያደርሰው ጉዳት ከሌሎች ዓለማት ይልቅ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ #ደሀ አገራት ላይ #ይበረታል ተብሏል፡፡

ህሙማኑ የካንሰር ተጠቂ እንደሆኑ የሚያውቁት እጅግ ዘግይተው በመሆኑና ለህክምና አስቸጋሪ በሆነ ጊዜ ወደ ህክምና ተቋም መምጣታቸው ካንሰርን የመከላከል ስራ ፈታኝ እንዲሆን አድርጎታል ተብሏል፡፡

ዛሬ የጤና ሚኒስቴር ከአጋሮቹ ጋር በመሆን የአለም የካንሰር ቀንን ምክንያት በማድረግ ባሰናዱት ምክክር ላይ ነው ይሄን የሰማነው፡፡
በኢትዮጵያ በየአመቱ 65 ሺ ያህል ሰዎች በካንሰር ይያዛሉ፡፡ በተመሳሳይ ሌሎች 65 ሺ ያህል ሰዎችም ይሞታሉ፡፡

ለህክምና የሚሆኑ ግብአቶች አለመሟላት እና የህክምና ተቋማቱ አነስተኛ መሆን ካንሰርን ለመከላል የሚሰራውን ስራ ፈታኝ እንዲሆን እንዳደረገው የጤና ሚኒስትር ድኤታዋ ዶ/ር #ሊያ_ታደሰ ተናግረዋል፡፡

የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከላትን ማስፋፋት ልዩ ትኩረት የተሰጠው በመሆኑ በ3 ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከላት ግንባታቸው እየተጠናቀቀ እንደሆነና የህክምና ግብአቶች እየተሟሉላቸው ነው መባሉን ተሰምቷል፡፡

ምንጭ፦ ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከባድ የመኪና አደጋ ተከሰተ‼️

በ21 #ቦሆሮ_ቀበሌ ልዩ ስሙ #አሚድ በተባለ ቦታ #ከጧቱ 1፡00 አካባቢ በተከስተ #የመኪና_አደጋ እስካሁን ባለው መረጃ መሰረት 2 (ሁለት) የሰዉ ህይወት ማለፍና ከባድ የአካል ጉዳት እንዲሁም የንብረት መዉድም መድረሱን ለመስማት ተችሏል።

ምንጭ፦ North Wollo RayaKobo Communication Office
@tsegabwolde @tikbahethiopia
ምስራቅ ዕዝ~መከላከያ‼️

ሰራዊቱ ከህዝቡ ጋር የጀመረውን ሰላምና ልማትን የማስቀጠል ስራዎችን #በተጠናከረ መንገድ እንደሚያስቀጥል የምስራቅ ዕዝ አመለከተ። 7ኛውን ዙር የመከላከያ ሰራዊት ቀንን በማስመልከት በህዝባዊ ውይይቶች፣ በጽዳት ዘመቻና በሌሎች በጎ እድራጎት ስራዎች በመከበር ላይ ነው።

የምስራቅ ዕዝ የኢንዶክትሬሽንና የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮረኔል ፍስሐ ተክለሐይማኖት ዛሬ እንደገለጹት በዓሉ ሰራዊቱንና ህዝቡን የሚያገናኝ በዓል ነው። 7ኛው ዙር የመከላከያ ሰራዊት ቀን ባዓልም እስከ የካቲት 6 ቀን 2011 በምስራቁ አገሪቱ ክፍል በሚገኙ ዞኖች፣ክልሎችና አስተዳደር ከተሞች በፓናል ውይይት፣በጽዳት ዘመቻና በተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎች እየተከበረ ይገኛል፤ ሰራዊቱም የሰላምና የልማት ሐይል እንደመሆኑ ችግሮች ወደ ከፋ ደረጃ እንዳይደርስ እንደከዚህ ቀደሙ ከህብረተሰቡ ጋር የሚያከናውነውን የሰላምና የልማት ስራዎችን የሚያጠናክርበት እና የሚያጎለብትበት በዓል ነው።

በተለይ በተለያዩ አካባቢዎች በአዋሳኝ ስፍራዎች፣ በመልካም አስተዳደርና በሌሎች የተነሱት አለመግባባቶች በእርቅና እንዲፈቱ የሰላም አምባሳደር ወጣቶችን ከክልልና ዞንና አመራር አካላት ጋር በመመልመልና ስልጠና በስጠት እንዲፈቱ የሚደረግበት መሆኑን ተገልጿል። እንዲሁም በየቦታው የሚታዩ አለመግባባቶች፣ ስርዓት አልበኝነት፣ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ገንዘብ ዝውውርና ሌሎች በህዝቡ ላይ ጉዳት በሚያደርሱ ተግባራትን ከአመራሩና ከህዝቡ ጋር ሰፊ የጋራ ግንዛቤ ተፈጥሮ ችግሩ የሚወገድበት መንገድ የሚመቻችበት እንደሆነ አመልክተዋል።

ሰራዊቱም #ህዝባዊነቱን የተቸገሩ ወገኖችን #የሚረዳበት፣ በሆስፒታል የሚገኙ #ህሙማንን የሚጎበኙበት በደም እጦት እናቶች ህይወታቸውን እንዳያጡ ደም የሚለግሱበትና ሌሎች የበጎ አድራጎስ ስራዎች የሚከናወኑበትና አለኝታነቱን የሚያስመሰክርበት ነው ሲሉ አብራርተዋል፤ ህዝቡም ከሰራዊቱ ጋር እየተወያየ በየአካባቢው እየታየ የሚገኘውን ሰላምን የማጠናከር ስራ ማጠናከር ይጠበቅበታል ብለዋል። “ህገ መንግስታዊ ታማኝነታችንንና ህዝባዊ ባህርያችንን ጠብቀን የተጀመረውን ለውጥ እናስቀጥላለን” በሚለው መሪ ቃል በሚከበረው 7ኛው ዙር የመከላከያ ሰራዊት ቀን በዓል የካቲት 7 ቀን 2011 በአየር ሐይል እና በኦሮምያ ክልል አዘጋጅነት በአገር አቀፍ ደረጃ በድምቀት #በአዳማ ከተማ ይከበራል።

ምንጭ፦ የሀረሪ ክልል ኮሚኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሜቴክ አመራሮች ላይ ክስ ተመሰረተ‼️

ለሁለት ስኳር ፋብሪካዎች የውሃ መርጫ መሳሪያ ሳያስፈልግ በራሳቸው ፍቃድ እንዲገዛ በማድረግ ከ15 ሚሊየን ብር እንዲባክን አድርገዋል የተባሉ ሶስት ግለሰቦች ላይ #ክስ ተመሰረተ።

ክሱ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 15ኛ የወንጀል ችሎት ለተከሳሾቹ እንዲደርሳቸው ተደርጎ በችሎት ተነቧል።

ተከሳሾቹ 1ኛ የብረታብረትና ኢንጂነሪንግ የማኑፋክቸሪንግ እና ማሽን ግንባታ ስራ አስኪያጅ ሌተናል ኮሎኔል ተሰማ ግደይ፣ 2ኛ በሜቴክ ማኑፋክቸሪግና ግንባታ ስራ ምክትል ስራ አስኪያጅና የግብይትና ሽያጭ ክፍል ሃላፊ ሻለቃ መስፍን ስዩም እንዲሁም 3ኛ በንግድ ስራ የተሰማሩት አቶ ክፍላይ ንጉሴ ናቸው።

1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች ከ2004 እስከ 2008 ዓ.ም ባሉት ጊዜያት ለፊንጫና ወንጂ ስኳር ፋብሪካዎች የውሃ መርጫ መሳሪያ ሳያስፈልግ በራሳቸው ፍላጎትና በወቅቱ የማምረት ፍቃድ ከሌለው ከ3ኛ ተከሳሽ ክፍላይ ንጉሴ ውል በመዋዋል ግዥ እንዲፈጸም ማድረጋቸው በክሱ ተጠቅሷል።

በዚህ መልኩ በተፈጸመ ያለአግባብ ግዥ ከ15 ሚሊየን ብር በላይ እንዲባክን ማድረጋቸውን እና የውሃ መርጫ መሳሪያው እስካሁን አገልግሎት ላይ ሳይውል መቀመጡ በክሱ ተመላክቷል።

ተከሳሾቹ የተነበበላቸው ክስ ላይ መቃወሚያ ካላቸው ለመመልከት ችሎቱ ለየካቲት 6 ቀን 2011 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ምንጭ፦ FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መቀለ🔝

የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ልዑክ አባላት ዛሬ ጠዋት ከአዲስ አበባ ተነስቶ መቀሌ ሲደርስ ሞቅ ያለ አቀባበል ተደርጎለታል። የመቀለ 70 እንደርታ ደጋፊዎችም በመቀሌ አሉላ አባ ነጋ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት ተቀብለዋቸዋል። በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 3ኛ ሳምንት ላይ መካሄድ የነበረበት እና በይደር ተራዝሞ የቆየው የፋሲል ከነማ እና የመቀሌ 70 እንደርታ ጨዋታ ሀሙስ ጥር 30/2011 ዓ.ም በተስተካካይ መርሃ ግብር ከቀኑ 9:00 በትግራይ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ይካሄዳል፡፡

ምንጭ፦ የፋሲል-ከነማ-ስፖርት-ክለብ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን‼️

32ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በሠላም እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

ጉባኤው በሠላም ተጀምሮ በሰላም እንዲጠናቀቅ የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን እና የፀጥታ ሃይሎችን ያሳተፈ ኮማንድ ፓስት መቋቋሙን የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር #ዘላለም_መንግስቴ ተናግረዋል።

ምክትል ኮሚሽነሩ ህብረተሰቡ ለፀጥታ ስራው እየሰጠ ያለው ድጋፍ አበረታች መሆኑን ጠቁመው፥ ይህ ትብብር ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

የሀገሪቱን ብሎም የከተማዋን መልካም ገፅታ ከመገንባት አኳያም ጉባኤው የራሱ ጉልህ አስተዋፅኦ የሚያበረክት በመሆኑ፥ ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ ህብረተሰቡ ከፀጥታ አካላት ጐን በመቆም ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል።

ህብረተሰቡ የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘትም ይሁን አጠራጣሪ ጉዳዩች ሲያጋጥሙት በስልክ ቁጥር፤ 011-126-43-77፣ 011-126-43-59፣ 011-827-41-51 ፣ 011-111-01-11 እና 991 ነፃ የስልክ መስመሮችን መጠቀም እንደሚችልም ኮሚሽኑ ገልጿል።

ጉባኤው ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስም በሚከተሉት መንገዶች ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ የተከለከለ ነው፤

ከአየር መንገድ – ቦሌ ቀለበት መንገድ – ፍሬንድ ሺፕ – ጃፓን ኤምባሲ – ወሎ ሰፈር – ኦምሎፒያ – ፍላሚንጎ – መስቀል አደባባይ – በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር – 1ኛ/ ከፓርላማ መብራት – ሜክስኮ አደባባይ – አፍሪካ ህብረት አዳራሽ ዙሪያ።

ከብሄራዊ ቲያትር – በፍልውሃ – በብሄራዊ ቤተ መንግስት – በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፤

ከፓርላማ መብራት – ፍልውሃና አምባሳደር ቲያትር ዙሪያውን – በሸራተን ሆቴል ቁልቁለቱን፤

ከንግድ ምክር ቤት ጀምሮ በሱዳን ኤምባሲ እስከ አፍሪካ ህብረት ዋናው በር ድረስ በሁለቱም አቅጣጫዎች ከነገ ጥር 29 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ እንግዶች ተጠቃለው እስከ ሚመለሱ ድረስ ግራና ቀኝ በሁለቱም አቅጣጫ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ጊዜ ተሸከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ መሆኑን ኮሚሽኑ አስታውቋል።

ከጦር ሃይሎች – በሜክሲኮ አደባባይ ለሚመጡ ተሸከርካሪዎች፤
በኮካኮላ ድልድይ – በአብነት ተክለኃይማኖት ወይም በሞላ ማሩ ጌጃ ሰፈር ጎማ ቁጠባ፤

ከሳር ቤት ወደ ሜክሲኮ ለሚመጡ፥ ሳር ቤት በቴሌ አድርገው ቀለበት መንገድ በሳር ቤት ወደ ቄራ ጎተራ፤

የቦሌ መንገድ ተጠቃሚዎች፥ በአትላስ ዘሪሁን ህንፃ ሲግናል – ቀለበት መንገድ ቦሌ ሚካኤል ሃኪም ማሞ ወደ ጎተራ  ቀለበት መንገድ – መገናኛ ዲያስፖራ አደባባይ እንግሊዝ ኤምባሲ – ቀለበት መንገድ መገናኛ አድዋ ጎዳና አዋሬ አራት ኪሎ – ከፍላሚንጎ ደንበል ጀርባ ወደ መስቀል ፍላወር መጠቀም ይቻላል።

ከዚህ በተጨማሪም እንግዶች በአጀብ በሚያልፉበት ወቅት አሽከርካሪዎችም ሆኑ እግረኞች ለፖሊስ አባላት አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉም ኮሚሽኑ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

ምንጭ፦ ፋና ብሮድስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዝግ የሚሆኑ መንገዶች‼️

የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ተጀምሮ# እስከሚጠናቀቅ ዝግ የሚሆኑና አማራጭ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ዘርዝሯል።

በዚህም መሠረትዝግ የሚሆኑት መንገዶች፦

1ኛ. ከፓርላማ መብራት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ መስቀል አደባባይ፣ ፍላሚንጎ፣ ኦምሎፒያ፣ ወሎ ሰፈር፣ ጃፓን ኤምባሲ፣ ፍሬንድ ሺፕ፣ ቦሌ ቀለበት መንገድ፣ ኤርፖርት

2ኛ. ከፓርላማ መብራት፣ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ በብሄራዊ ቤተ መንግስት፣ በፍልውሃ፣ ብሄራዊ ቲያትር፣ ሜክስኮ አደባባይ - አፍሪካ ህብረት አዳራሽ ዙሪያ

3ኛ. ከፓርላማ መብራት፣ በሸራተን ሆቴል ቁልቁለቱን፣ ፍልውሃና አምባሳደር ቲያትር ዙሪያውን

4ኛ. ከንግድ ም/ቤት ጀምሮ በሱዳን ኤምባሲ እስከ አፍሪካ ህብረት ዋናው በር ድረስ በሁለቱም አቅጣጫዎች ከነገ ጥር 29 ቀን 2011 ዓ/ም ጀምሮ እንግዶች ተጠቃለው እስከ ሚመለሱ ድረስ ግራና ቀኝ በሁለቱም አቅጣጫ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ጊዜ ተሸከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ መሆኑን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

አማራጭ መንገዶች፦

• ከጦር ሃይሎች - በሜክሲኮ አደባባይ ለሚመጡ ተሸከርካሪዎች፡፡
በኮካኮላ ድልድይ - በአብነት ተ/ኃይማኖት ወይም በሞላ ማሩ ጌጃ ሰፈር ጎማ ቁጠባ

• ከሳር ቤት ወደ ሜክሲኮ ለሚመጡ
ሳር ቤት በቴሌ አድርገው ቀለበት መንገድ
በሳር ቤት ወደ ቄራ ጎተራ

• የቦሌ መንገድ ተጠቃሚዎች
በአትላስ ዘሪሁን ህንፃ ሲግናል
ቀለበት መንገድ ቦሌ ሚካኤል ሃኪም ማሞ ወደ ጎተራ
ቀለበት መንገድ መገናኛ ዲያስፖራ አደባባይ እንግሊዝ ኤምባሲ
ቀለበት መንገድ መገናኛ አደዋ ጎዳና አዋሬ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ትብብር‼️

ኢትዮ ቴሌኮም(ዋናው መስሪያ ቤት) ውስጥ ወይም ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ውስጥ በየትኛውም የስራ እርከን የምትሰሩ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ካላችሁ ወይም እዛው የሚሰሩ ወዳጆች ካሏችሁ በ @tsegabwolde መልዕክት አኑሩልኝ። ትብብራችሁ ያስፈልገኛል!

@tsegabwolde @tikvahethiopia