TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"ዓምዶም ገብረስላሴ አልታሰረም።" አብርሃ ደስታ
.
.
ESAT ትላንት ምሽት ዓምዶም ታሰረ የሚል ዘገባ አውጥቶ ነበር።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዓምዶም አልታሰረም...

"ወዳጆቼ ዓምዶም ታስረዋል የሚለው መረጃ #ትክክል_ኣይደለም። ኣልታሰርኩም። ስላሰባቹልኝ ኣመሰግናለው!" ዓምዶም በፌስ ቡክ ገፁ ላይ እንዳሰፈረው።

@tsegabwolde @tkivahethiopia
Alert‼️በአሁን ሰዓት በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ እየሆነ ያለውን ጉዳይ የሚመለከተው አካል በአስቸኳይ እንዲመለከተው ተማሪዎች ጥሪ እያቀረቡ ይገኛሉ።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር #የዜጎችን_ደህንነት ለመጠበቅ መብታቸውን ለማስከበር በሚያደርገው እንቅስቃሴ ህይወታቸው ለአደጋ ተጋልጦ የነበሩ ዜጎችን ከታንዛንያ እና ሊቢያ መመለስ ጀምሯል። በዚህም መሰረት የታንዛንያ መንግስት ህጋዊ የጉዞ ፈቃድ ሳይኖራቸው ወደ ሀገሩ የገቡ 231 ኢትዮጵያውያን ክሳቸው ተቋርጦ ምህረት እንዲያደርግላቸው ዲፕሎማሲያዊ ጥረት በማድረጉ ዛሬ ጠዋት 65 ዜጎች ተመልሰዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ድሬዳዋ‼️የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መንግስት መፍትሄ ይፈልግልን ዛሬም አለመረጋጋት አለ እያሉ ይገኛሉ። የተቋሙ ሰራተኛ ወይም ተማሪ ያልሆኑ የተለያዩ አካላት ግቢው ውስጥ ገብተው እንዳዩ የገለፁት ተማሪዎቸ መንግስት አስቸኳይ #እርምጃ ሊውስድ ይገባል ብለዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Alert‼️የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በግቢው ውስጥ ያለው ችግር እንዳልተፈታ እየገለፁ ናቸው። ጉዳይ የሚመለከተው አካል አፋጣኝ መፍትሄ እንዱፈልግ ተማሪዎች ጥሪ እያቀረቡ ይገኛሉ።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሁን‼️

የቀድሞ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ አስክሬን ወደ ሚሊኒዬም አዳረሽ እያቀና ነው።

የቀድሞ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ በዛሬው ዕለት የቀድሞ የስራ ባልደረቦቻቸው፣ ቤተሰቦቻቸውና፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትና አድናቂዎቻቸው በተገኙበት በሚሊኒዬም አዳረሽ የስንብት ፕሮግራም ይካሄዳል፡፡

በመቀጠልም በክብር ሰረገላና በወታደራዊ ማርሽ ባንድ አስክሬናቸው ወደሚያርፍበት ቅድስት ስላሴ ያመራል፡፡ ለክብራቸውም መድፍ ይተኮሳል፡፡

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ የሰላምና የአብሮነት ተምሳሌት በሁሉም ህዝቦች የላቀ ርብርብ ዳግም ይገነባል!

የኢፌዲሪ የሰላም ሚኒስቴር እና ኢትዮ ቴሌኮም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በትናትናው ምሽት በኦስሎ ቀላል #አደጋ ገጥሞት እንደነበረ አስታወቀ፡፡ B787-900 በተሰኘው አውሮፕላኑ ላይ አደጋው የደረሰው ከመነሳቱ በፊት ክንፉ ላይ የነበረውን ግግር በረዶ እየተራገፈ በነበረበት ወቅት ከአንድ ቋሚ ጋር በመጋጨቱ ነው መሆኑን ገልጿል፡፡ በዚህም በአውሮፕላኑ የቀኝ ክንፍ ላይ  ነው ቀላል ጉዳት ስለማጋጠሙ የገለጸው፡፡ አደጋው ቀላል መሆኑን ያስታወቀው አየር መንገዱ ሁሉም ተጓዦች ወደ ሆቴል ማምራታቸውን ባወጣው መግለጫ ጠቅሷል፡፡ አየርመንገዱ በተፈጠረው ነገር ተጓዦችን ይቅርታ የጠየቀ ሲሆን፥ ጉዞዋቸውንም ማመቻቸቱን ገልጿል፡፡

Via~fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሞያሌ‼️

ኢትዮጵያን ከኬንያ የሚያዋስነዉን የሞያሌ ከተማን ካለፈዉ ሳምንት ጀምሮ ሲያብጥ የነበረዉ ግጭት ከትናንት ጀምሮ #ጋብ ማለቱን የዞኑ ባለሥልጣናት አስታወቁ።

በገሪ (ሶማሌ) እና በቦረና (ኦሮሞ) ታጣቂዎች መካከል ካለፈዉ ዕሮብ ጀምሮ ዳግም ባገረሸዉ ግጭት ቢያንስ 41 ሰዎች ተገድለዋል። ከ84 ሺሕ በላይ ሕዝብ ከቤት ንብረቱ ተፈናቅሏል።

የቦረና ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ #ጴጥሮስ_ዋቆ ዛሬ ለDW እንደነገሩት ትናንት የኢትዮጵያ መከላከያ ጦር ጣልቃ ከገባ ወዲሕ በከተማይቱ አንፃራዊ ሠላም ሰፍኗል። መደብሮች፣ አገልግሎት መስጪያ ተቋማት እና የመንግስት መስሪያ ቤቶች ዛሬም ዝግ ናቸዉ። መስተዳድራቸዉ ለተፈናቃዩ ሕዝብ አስቸኳይ ርዳታ ለማከፋፈል እየጣረ ነዉ። አብዛኛዉ ተፈናቃይ ድሬ፣ሜጋ፤ሚዮ እና ሠርባ በተባሉት የሞያሌ አጎራባች ከተሞች እና ወረዳዎች መጠለሉን ምክትል አስተዳዳሪዉ ገልጠዋል።

ግጭቱ በሰዉ ሕይወት እና አካል ላይ ካደረሰዉ ጥፋት በተጨማሪ የሞያሌ ሆስፒታልን ጨምሮ ግምቱ በዉል ያልታወቀ ንብረት አዉድሟል።

የሞያሌ ከተማን ለመቆጣጠር በተቀናቃኝ ጎሳ ታጣቂዎች መካከል ባለፉት ሁለት ዓመታት በተደረገዉ ግጭት በመቶ የሚቆጠር ሕዝብ ተገድሏል። በብዙ ሺሕ የሚቆጠር ሕዝብ ወደ ኬንያ ተሰድዶም ነበር።

ሰሞኑን እንዳዲስ ያገረሸዉ ግጭት ትክክለኛ መንስኤ እስካሁን በዉል አልታወቀም።ታዛቢዎች ግን ከዚሕ ቀደም የነበረዉ ግጭት ሁነኛ መፍትሔ ባለማግኘቱ የቀጠለ ነዉ ይላሉ።

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና‼️

ከበኒሻንጉል ጉሙዝ መስተዳድር ርዕሠ-ከተማ አሶሳ 18 መንገደኞችን አሳፍሮ ቶንጎ ወደተባለዉ ልዩ ወረዳ ይጓዝ የነበረ መለስተኛ የሕዝብ ማመላለሻ አዉቶቡስ በተቀበረ ፈንጂ ጋይቶ 10 ተሳፋሪዎች ሞቱ፣ቁጥራቸዉ በዉል ያልታወቀ ቆሰሉ።

የበኒ ሻንጉል ጉሙዝ መስተዳድር ፖሊስ እንዳስታወቀዉ አዉቶቡሱ በተቀበረ ፈንጂ የጋየዉ ቶንጎ-ጎሬ በተባለዉ አካባቢ ጠጠራማ ጎዳና ላይ ሲጓዝ ነዉ።

በፍንዳታዉ የቆሰሉ ሰዎች ቤጊ ሆስፒታል ዉስጥ ሕክምና እየተደረገላቸዉ ነዉ።መኪናዉ የግለሰብ ነዉ።

የአሶሳዉ የDW ዘጋቢያ ነጋሳ ደሳለኝ በስልክ እንደገለጠው የበኒሻንጉል ጉሙዝ መስተዳድን ከምዕራብ ወለጋ (ኦሮሚያ) ጋር በሚያዋስነዉ ቶንጎ ልዩ ወረዳ ባለፈዉ ሰኔ በተቀሰቀሰ ጎሳን የተባለበስ ግጭት ሰዎች ተገድለዉ ነበር። ያሁኑ የፈንጂ አደጋ ካለፈዉ ግጭት ጋር ሥለ መያያዝ አለመያያዙ ግን የታወቀ ነገር የለም። ፈንጂዉን የቀበረዉ ወገን ማንነትም እስካሁን ግልፅ አይደለም።

ምዕራብ ኦሮሚያን ከበኒ ሻንጉል መስተዳድር ጋር በሚያዋስኑ ድንበሮች ሰኔ የተጀመረዉ ደም አፋሳሽ ግጭት ከመስከረም አጋማሽ ወዲሕ ተባብሶ የበርካታ ሰዎች ተገድለዋል።በመቶ ሺሕ የሚቆጠሩ ተፈናቅለዋል።

ምንጭ፦ DW የአማርኛው አገልግሎት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የቀድሞው ርዕሰ ብሄር ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ ቀብር ስነ ሥርዓት ሲከናወን ውሏል፡፡ በቅድሥት ሥላሴ ካቴድራል በተከናወነው የቀብር ስነ ሥርዓት ላይ የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ፣ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ፣ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት ተገኝተዋል፡፡ ቀደም ሲል ቤተሰቦቻቸው፣ ወዳጆቻቸው፣ ሚንስትሮች፣ ከፍተኛ ሌሎች የመንግሥት ባለስልጣናት እና የውጭ ሀገራት አምባሳደሮች በተገኙበት በሚለኒዬም አዳራሽ ስንብት ተደርጎላቸዋል፡፡

Via~WazemaRadio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ ተስፋዬ እና አቶ ማርክስ‼️

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 10ኛ የወንጀል ችሎት በቀድሞዎቹ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ባልደረቦች አቶ ተስፋዬ ኡርጌ እና አቶ ማርክስ ፀሃዬ ላይ ፖሊስ የጠየቀውን የጊዜ ቀጠሮ ፈቀደ።

ማርክስ ፀሃዬን በተመለከተ መርማሪ ፖሊስ ከዚህ በፊት በተሰጠው ጊዜ ተገቢውን ስራ መስራቱን ገልጾ፥ ቀሪ ስራዎችን ለመስራት የ14 ቀን ጊዜ ጠይቆ ችሎቱ በከፊል ተቀብሎታል።

ከሰኔ 16ቱ ጥቃት ጋር በተያያዘ የቀረበባቸው አዲስ የወንጀል ተሳትፎን በተመለከተ ማቅረብ አይገባም የሚል የህግ ክልከላ አለመኖሩን በመጥቀስም፥ መርማሪ ፖሊስ ይቀረኛል ያለውን ስራ አጠናቆ እንዲመጣ ከታህሳስ 8 ቀን ጀምሮ የሚታሰብ 14 ቀን የምርመራ ጊዜ ፈቅዷል።

በከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰትና ሙስና ወንጀል የተጠረጠሩት አቶ ተስፋዬ ኡርጌ ጋር በተያያዘም ፖሊስ የጠየቀውን የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ ችሎቱ ፈቅዷል።

ተጠርጣሪው በእስር ቦታ ላይ ሰብዓዊ መብቴ እየተጣሰ ነው በሚል ያቀረቡትን አቤቱታ ፖሊስ አጣርቶ እንዲያቀርብ ችሎቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

ከዚህ ባለፈም ግለሰቡ ደመወዛቸው በፍርድ ቤት ሳይታገድ እየተከፈላቸው አለመሆኑን ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል።

ፍርድ ቤቱ መርማሪ ፖሊስ ጉዳዩ እንዲፈታ እንዲያግዛቸው ትዕዛዝ አስተላልፏል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥብቅ ማስታወቂያ🔝ለሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች...
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥብቅ ማስታወቂያ🔝ለቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች...
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሜጀር ጀኔራል ክንፈ ዳኛው‼️

በሜጀር ጀኔራል #ክንፈ_ዳኘው ላይ መርማሪ ፖሊስ የጠየቀው 14 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተፈቀደ።በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ፍርድ ቤት የቀረቡት ቀድሞው የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው ላይ ፖሊስ የጠየቀውን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ፍርድ ቤት ፈቀደ።

አመልካች መርማሪ ፖሊስ ተጠርጣሪው ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው ላይ ተጨማሪ የሙስና ወንጀል ድርጊት ማግኘቱን ከትናንት በስቲያ ለችሎቱ አመልክቶ ተጨማሪ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቆ ነበር።

ድርጅቱ የሚያከናውናቸውን ስምምነቶች 90 በመቶ በተጠርጣሪ የሚፈጸሙ መሆኑን በመግለጽ፣ ተጠርጣሪው ቢወጡ አጠቃላይ የምርመራውን ሂደት ያደናቅፋሉ በሚል የተጠርጣሪ ጠበቆች ያቀረቡትን ዋስትናም ተቃውሞ ነበር።

ምንጭ፦ ena
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በዚምባብዌ የተካሄደውን ምርጫ ተከትሎ በተፈጠረ ተቃውሞ የአገሪቱ መከላከያ ሰራዊት የወሰደው እርምጃ ተመጣጣኝ እንዳልነበረ ጉዳዩን ሲያጣራ የቆየው አጣሪ ኮሚቴ ዛሬ ባወጣው ሪፖርት ይፋ አደረገ፡፡ በዝምባብዌ የተደረገውን ፕሬዘዳንታዊ ምርጫን ተከትሎ በዋና ከተማዋ ሀራሬ በምርጫ ውጤት ጋር ተያይዞ ግጭትና ብጥብጥ መነሳቱ ይታወሳል፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ መንግስት የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት በሚል ባለፈዉ ዓመት የደነገገዉ #የምህረት_አዋጅ ሊጠናቀቅ ጥቂት ቀናት ቀርተዉታል። የኢትዮጵያ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ዛሬ እንዳስታወቀዉ አዋጁ የወጣዉ የዜጎችን ፖለቲካዊ ተሳትፎ ለማሳደግ ታስቦ ስለሆነ፤ አዋጁ ቀነገደቡ ከመጠናቀቁ በፊት መጠቀም የሚፈልጉና የሚመለከታቸዉ ሰዎች ማመልከቻ እንዲያቀርቡ የጠቅላይ አቃቤ ሕግ ፅሕፈት ቤት አሳስቧል።

ምንጭ፦የጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia