TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
መቀለ ዩኒቨርሲቲ🔝

የኢትዮጵያ የሰላም አምባሳደር እናቶች #በመቐለ_ዩኒቨርስቲ ተገናኝተው ነበር።

"በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የሰላም #እናቶች ልብ በሚነካ መልኩ በተማሪዎች መማሪያ ክፍል እየገቡ ተንበርክከው ስለ ሰላም አልቅሰዋል፤ ተማሪዎችንም ቃል አስገብተዋል።"

©ቀኔ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
እነ ጎሃ አፅብሀ‼️

በሰብዓዊ መብት ጥሰት ተጠርጥረው ፍርድ ቤት የቀረቡት እነ ጎሃ አጽብሃ ላይ 14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ተፈቀደ።

ከትናንት በስቲያ ጀምሮ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 10ኛ ወንጀል ችሎት ጉዳያቸው እየታየ የነበሩ 33 ተጠርጣሪዎች ናቸው ጊዜ ቀጠሮ የተሰጠባቸው።

ተጠርጣሪዎቹ የአዲስ አበባና ፌዴራል ፖሊስ፣ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት እና የማረሚያ ቤት ኃላፊዎችና አባላት መሆናቸው ታውቋል።

ችሎቱ በዛሬ ውሎው የፖሊስን ጥያቄ ማብራሪያ፣ የተጠርጣሪዎችና ተከላካይ ጠበቆችን የተቃውሞ ክርክር መሰረት በማድረግ በነ ጎሃ አጽብሃ መዝገብ ተጠርጣሪዎች ላይ የ14 ቀናት ጊዜ ቀጠሮ ሰጥቷል።

በዚህም ፖሊስ ምርመራውን አከናውኖ እንዲቀርብ ለታህሳስ 2 ቀን 2011 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል።

በሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀል ተጠርጥረው ዛሬ በፌዴራሉ ፍርድ ቤት ቀርበው የነበሩት ተጠርጣሪዎች ውስጥ 16ቱ መንግስት ጠበቃ እንዲያቆምላቸው ከትናንት በስቲያ መፈቀዱ ይታወሳል።

ተጠርጣሪዎቹ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ የማረሚያ ቤትና የፖሊስ አባልና ሃላፊ ሆነው ባገለገሉበት ወቅት የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንደፈጸሙ ፖሊስ ለችሎቱ ማስረዳቱም ይታወሳል።

ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ እንዳስረዳው ተጠርጣሪዎቹ በሽብር የተፈረጁ ግለሰቦችን በማፈን፣ ስውር እስር ቤት አስገብቶ ኢሰብአዊ የሆነ ድርጊት እንዲፈጸምባቸው ማድረጋቸውን ለፍርድ ቤቱ ገልጿል።

በጳጉሜ 2006 ዓ.ም የኢትዮጵያና ናይጄሪያ እግር ኳስ ቡድን ጨዋታ ባደረጉበት ዕለት ቦንብ አፈንድተዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎችን በማሰቃየትና የአንድ ሰው ህይወት እንዲያልፍ ማድረግና ሌሎች የሰብዓዊ መብት ጥሰት መፈጸማቸውን ፖሊስ ለፍርድ ቤት ማስረዳቱም ይታወሳል።

 ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ በዛሬው ዕለት ከፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ወይዘሮ #መዓዛ_አሸናፊ ጋር ተወያይተዋል፡፡ የውይይቱ ዓላማ የህግ የበላይነትንና ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ ተባብሮ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ለመምከር ነው፡፡ ፍትህን ማስፈን ልማትን ማረጋገጥ በመሆኑ የከተማ አስተዳደሩ አስፈጻሚ አካል ለዚህ ተግባራዊነት ጠንክሮ እንደሚሰራ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ገልፀዋል፡፡

ምንጭ፡- የአዲስ አበባ ከንቲባ ጽ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የነበሩት የዶክትር ኡሞድ ኡቦንግ ስርዓተ-ቀብር በጋምቤላ ከተማ ቅዱስ ሚኪኤል ቤተ ክርስቲያን ዛሬ ተፈፅሟል።

©ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጠ/ሚ ዶክተር አብይ አህመድ🔝

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ ለአፍሪካ የአመራር መጽሔት የዓመቱ ምርጥ አፍሪካዊ ሽልማት እጩ ሆነው ተመረጡ

ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ለአፍሪካ የአመራር መጽሔት 2018 የዓመቱ ምርጥ አፍሪካዊ ሽልማት እጩ ሆነው ተመረጡ፡፡

በየዓመቱ በሚካሄደው በዚህ የሽልማት ዘርፍ የነዳጅ ላኪ አገራት ድርጅት ዋና ጸሐፊ ናይጄሪያዊው መሐመድ ሳኑሲ ባርኪንዶ እና የቀድሞው የቦትስዋና ፕሬዝዳንት ሴሬትሳ ካማ ኢያን ካማ የዶ/ር ዐቢይ ተፎካካሪዎች ናቸው፡፡

የሽልማቱ አሸናፊ የሚለየው በመጽሔቱ ድረ-ገፅ ላይ በኢንተርኔት በሚሰጥ ድምፅ ሲሆን እስካሁን ዶ/ር ዐቢይ 87 በመቶ የሚጠጋውን ድምጽ በማግኘት ተፎካካሪዎቻቸውን እየመሩ ይገኛሉ፡፡

ድምጽ የሚሰጥበት ጊዜም እስከ ታህሳስ 1/2011 ድረስ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ይህ ታዋቂ ሽልማት በተለያዮ ዘርፎች የላቀ አስተዋፅዖ ላበረከቱ የአፍሪካ የቢዝነስ፣ የፖለቲካና የዲፕሎማሲ መሪዎች እውቅና የሚሰጥ ነው፡፡

ምንጭ፦ africanleadership.co.uk

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሜቴክ‼️

በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩት የቀድሞ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) አመራሮች ላይ ፖሊስ የጠየቀውን የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ለመፍቀድ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 10ኛ ወንጀል ችሎት ለነገ ቀጠረ።

ብርጋዴር ጄኔራል ጠና ቁሩንዴን ጨምሮ ከሜቴክ ጋር በተያያዘ በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ 26 ሰዎች ላይ ለተጨማሪ ምርመራ 14 ቀን እንዲፈቀድለት ፖሊስ ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።

ከፍተኛ ፍርድ ቤት 10ኛ ወንጀል ችሎት ከጠበቆቻቸው ጋር የቀረቡት ተጠርጣሪዎች ፖሊስ ያቀረበው ተጨማሪ የምርመራ ቀናት ተገቢነት እንደሌለው ለፍርድ ቤቱ ገልጸዋል።

ምርመራው ለአምስት ወራት ተካሂዶ መጠናቀቁን በፌዴራል ዐቃቤ ህግ መገለጹን ጠበቆቹ ለችሎቱ አስረድተዋል።

ለሁሉም ተጠርጣሪ ተመሳሳይ የጊዜ ቀጠሮ መጠየቅ የለበትም፤ በእያንዳንዱ ተጠርጣሪ ላይ በግልጽ ድርጊቱ አልቀረበም ሲሉም ተቃውመዋል።

ተቋሙን ከለቀቁ የቆዩ ስላሉ የሰነድ ማስረጃ የሚያሸሹበት ምክንያት የለም፤ ማስረጃ ከመንግስት ተቋም ስለማይጠፋ ተጠርጣሪዎቹን አስሮ ማቆየት ተገቢነት የለውም በማለት የተከራከሩት ጠበቆቹ በተጠርጣሪ ቤተሰቦች ላይ ጫና እያሳደረ መሆኑንም አስረድተዋል።

ተጠርጣሪዎቹን በተናጠል በመጥቀስ ከጤናና መሰል ግላዊ ምክንያቶች ጋር በተያያዘ የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው ለፍርድ ቤቱ ጥያቄ አቅርበዋል።

ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹ ቢለቀቁ ሐብት ያሸሻሉ፣ የሰነድ ማስረጃ ያጠፋሉ እንዲሁም ምስክሮችን ያባብላሉ ሲልም ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ በማቅረብ ጠበቆቹ የጠየቁትን የዋስትና ጥያቄ ተቃውሟል።

በመርማሪ ፖሊስና በተጠርጣሪ ጠበቆች መካከል የነበረው ክርክር መደበኛ የችሎት ሰዓት ባለመጠናቀቁ ፖሊስ በጠየቀው የጊዜ ቀጠሮ ላይ ብይን ለመስጠት ችሎቱ ለነገ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ምንጭ፦ ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አስቸኳይ‼️

ሳሪስ አቦ አካባቢ ከባድ #የመኪና_አደጋ ደርሷል። በአካባቢው በቂ አምቡላንስ የለም። የሚመለከታቹ አካላት የሰው ህይወት ለማትረፍ ርብብር እድታደርጉ እንጠይቃለን።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አብዴፓ‼️

የአፋር ብሄራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አብዴፓ) 7ኛ መደበኛ ጉባኤውን ከህዳር 24 እስከ 26 ቀን 2011 ዓ.ም እንደሚያካሂድ አስታወቀ።

የፓርቲው ጽህፈት ቤት ምክትል ሃላፊ አቶ አሊ አብደላ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ፓርቲው በጉባኤው  ያለፉት ሶስት አመታት የስራ አፈጻጸም በመገምገም የቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ።

ነባር አመራሮችን በክብር በመሸኘት ብቃት ያላቸው ወጣቶችን ወደ ኃላፊነት እንደሚያመጣም አመላክተዋል።

“በጉባኤው 593 ሰዎች በድምፅና 107ቱ ያለድምጽ ይሳተፋሉ” ብለዋል ።

በፓርቲው የከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች የአመራርነት ዘመን ከ10 አመት በላይ እንዳይበልጥ የሚገድብ ሰነድ ቀርቦ በአባላት ይፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ አመላክተዋል ።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ...

"ሠላም ፀግሽ! ባለፈው እኛ የአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨረሲቲይ ተማሪዎች በትምህርት ጥራት እና በዪኒቨረሲቲው ቃል የተገባው እና በሀገር ደረጃ የተጣለበትን ሀላፍነት ለመወጣት ባለመቻሉ የተቃውሞ ሰልፍ መውጣታችን ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ጥያቄያችን ለሚዲያ ካቀረብን በሗላምእስከ ዛሬ Class ያልገባን መሆናችንን የሚመለከተው አካል አውቆ መፍትሄ እንድሰጠን ስንል እንጠይቃለን፡፡"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከዱራሜ...

"በከምባታ ጠምባሮ ዞን ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል። ምክንያቱም ለህዳሴ ግድብ መምህራን እስከ ዛሬ ከደሞዛቸው የተቆረጠ ብር ለህዳሴ ግድቡ ገቢ ይደረግ አይደረግ ምንም ማረጋገጫ የለንም በማለት ወይ ቦንድ ይሰጠን ፣ ከልሆነም የሚመለከተው አካል ሚላሽ ካለው በሚል ነው። በዚህ የተነሳ ተማሪዎች ትምህርት መማር አልቻሉም። Teg ነኝ ከዱራሜ"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update አዋሽ ባንክ #በጣና_ሀይቅ ላይ የተጋረጠውን እንቦጭ ለማስወገድ የ10 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀዋሳ🔝

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር #ታከለ_ኡማ ከሀዋሳ ከተማ ወጣቶች ጋር ተወያዩ።

ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በውይይታቸው ለሀዋሳ ከተማ ወጣቶች እንደተናገሩት #ኢትዮጵያዊነት ከፍታ ነው ብለዋል።

የከፍታችን ዋና ምሰሶው ፍቅር ሲሆን፥ ሀዋሳ ከተማ የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች በመተሳሰብ እና በመፈቃቀድ ከፍታቸውን ጠብቀው በጋራ የሚኖሩባትና በምሳሌነትም የምትጠቀስ ከተማ ነች ብለዋል።

የሀዋሳ ከተማ ወጣቶች ይህን አረዓያነት የማስቀጠል ኃላፊነት እንደለባቸውም አሳስበዋል።

ወጣቱ ትውልድ ተራራ ለመውጣት ብሎም አስፈለጊ ሆኖ ሲገኝ መናድ የሚችለው ኢትዮጵያዊ ከፍታውን ሲጠብቅ ብቻ ነውም ብለዋል።

አልፎ አልፎ ከዚህ ከፍታችን የሚያወርዱ ትርክቶች ተከትሎ የሚፈጠሩ ችግሮች ለችግር የሚዳርጉ መሆናቸውን አስገንዝበዋል።

እነዚህን ችግሮች ለማስወገድ ደግሞ አብሮነት፣ ፍቅር መተሳሰብ፣ መፈቃቀድ መሆኑን ነው ያመላከቱት።

አባቶቻችን የኢትዮጵያ ዳር ድንበር በማስከበር የተዋደቁት የኢትዮጵያን ከፍታ ለዚህ ትውልድ ለማስተላለፍ ነው ብለዋል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia