አሳዛኝ ዜና‼️
በቻይና አንድ የኬሚካል ፋብሪካ ላይ በደረሰ #ፍንዳታ 22 ሰዎች ሞቱ
በቻይና በኬሚካል ፋብሪካ ላይ በደረሰ ፍንዳታ 22 ሰዎች ሲሞቱ 22 የሚሆኑት ጉዳት ተርሶባቸዋል።
ፍንዳታው የተከሰተው በቻይና ሰሜናዊ የሂቤ ግዛት በሚገኝ ስፍራ ውስጥ ሲሆን በዚሁ አደጋ ሀምሳ የሚሆኑ ተሸከርካሪዎች ወድመዋል፡፡
በኬሚካል ፍንዳታው በአካባቢው ዓየር ላይ የጠቆረ ጭስ እና ነበልባል በማስከተል ለብክለት መንስኤ መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡
እንደ ሀገሪቱ መንግስት ባለስልጣናት ገለፃ 50 ያህል የእሳት አደጋ መከላከያ መኪኖች በማሰማራት ቃጠሎውን በቁጥጥር ስር ለማዋል ጥረት ማድረጋቸውን ጠቁመዋል፡፡
የሀገሪቱ የዜና አውታር እንደዘገበው ፍንዳታው ነኬቢ የሻንዩ ኬሚካል ኢንዱስትሪ እኩለ ለሊት ላይ መከሰቱን ጠቁማል፡፡
ከቤጂንግ ሰሜን ምዕራብ 156 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው ጂንግጂካኩ በአውሮፓውያን አቆጣጠር በ2022 የሚካሄደውን ኦሎምፒክ ውድድር ለማስተናገድ ዝግጅት ላይ እንደነበረችም ነው የተጠቆመው፡፡
የአደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ እንደሚገኝም ነው የአካባቢው ባለስልጣናት ያስታወቁት፡፡
ቻይና ባለፉት ሶስት አስርት አመታት ከፍተኛ እድገት ካዝመዘገቡ ሀገራት ተርታ የምትመደብ ሲሆን በማእድን ማውጫዎች፣ በኢንዱስትሪና ፋብሪካዎቿ አካባቢ ያለውን ደህንነት ሁኔታ የበለጠ ለማሻሻል እየሰራች መሆጓንም ነው የሀገሪቱ ባለስልጣናት የተናገሩት፡፡
በ2015 ነሀሴ ወር በቲያንጂ ወደብ ከተማ የኬሚካል መጋዘን ፍንዳታ ተከስቶ 165 ሰዎች መሞታቸው ሚታውስ ነው ሲል አልጀዚራ በድረገጹ አስነብቧል።
ምንጭ፦ አልጀዚራ(ena)
@tsegabwolde @tikvahethiopia

ኢትዮጵያ ጀግና ልጇን አጣች!
ኢትዮጵያ ሆይ! ~ ብርታቱን፤ ጽናቱን ይስጥሽ!
የቤቴል ቲቺንግ ሆስፒታል መሥራች እና ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር #ይገረሙ_አስፋው ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል። እሳቸው በሀገራችን የብዙ ነገር ጀማሪ ናቸው።
አሁን ላይ ብዙ ሆስፒታሎች ለማድረግ የሚጥሩት እንደ አይቪኤፍ (መውለድ የማይችሉ ሰዎች እንዲወልዱ የሚያደርግ ህክምናን) ሆስፒታሉ የራሱን ኦክሲጅን በራሱ ጊቢ ውስጥ እንዲያመርት ማደረግ፣ ዘመናዊ የሆስፒታል ቆሻሻ አወጋገድ፣ የግል የህክምና ትምህርት፣ የቲችንግ ሆስፒታል ኮንሴፕት፣ የህክምና ቁሶችን በራስ ማስመጣት እና የሌሎችም ብዙ ተፅእኖ ፈጣሪ ሥራዎች ጀማሪ ነበሩ።
ለአገር እና ለሕዝብ የሰሩት ዶ/ር ይገረሙ የወለዱት ልጅ ባይኖራቸውም የሚያሳደጓቸው ብዙ ልጆች ነበሩ።
ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ጌጡ ተመስገን፣ ማ.እ
TIKVAH-ETH በዶክተር ይገረም ህልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ለወዳጅ ቤተሰቦቻቸው መፅናናትን ይመኛል!

ኦዴፓ እና ኦዴግ ተዋሀዱ‼️
በአቶ #ሌንጮ_ለታ የሚመራው የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ODF) ከኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ( ODP) ጋር መዋሃዱ እየተነገረ ነው።
ይኸው የሁለቱ ፓርቲዎች ውህደት በዛሬው ዕለት ለህዝብ #ይፋ እንደሚደረግም ተሰምቷል።
የአርትስ ቴሌቪዥን ምንጮች እንደጠቆሙት የሁለቱን ፓርቲዎች ውህደት በተመለከተ የፓርቲዎቹ አመራሮች አቶ ለማ መገርሳ እና አቶ ሌንጮ ለታ ዛሬ ከቀትር በኋላ በኦሮሚያ ፕሬዚዳንት ቢሮ መግለጫ ይሰጣሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው።
ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) መከፋፈል በኋላ የቀድሞ አመራሩ አቶ ሌንጮ ለታ አሁን ከኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዲፒ) ጋር ሊዋሃድ መሆኑ የተነገረውን የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኦዴግ) መስርተው መንቀሳቀስ መጀመራቸው ይታወሳል።
በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ወደሃገር ቤት ከገቡት የፖለቲካ ፓርቲዎች ቀዳሚውም ይኸው የአቶ ሌንጮ ፓርቲ ኦዴግ ነው።
በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ከመንግስት ጋር በተደረገ ድርድር ትጥቅ ፈትቶ በሰላማዊ መንገድ ለመንቀሳቀስ በመወሰን ወደኢትዮጵያ መግባቱም አይዘነጋም።
ምንጭ፦ አርትስ ቴሌቪዥን

#Update የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ እና የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ተዋህደው አብረው ለመስራት የሚያስችላቸውን የጋራ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡
@Tsegabwolde @tikvahethiopiA
@Tsegabwolde @tikvahethiopiA
ደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ🔝ዛሬ የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ እና የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ሊቀመንበር ኦባንግ ሜቶ በደብረ ብርሀን ዩኒ ቨርሲቲ ፕብሊክ ሌክቸር ሠጥተዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኦዴፓ🤝ኦዴግ!
የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) እና የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኦዴግ) የውህደት ስምምነት ፈረሙ።
ስምምነቱ የተፈረመው በኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) ምክትል ሊቀ መንበር አቶ ለማ መገርሳ እና እና በኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኦዴግ) ሊቀመንበር አቶ ሌንጮ ለታ መካከል ነው።
የሁለቱ ፓርቲዎች የስምምነት ፊርማ በክልል ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ነው የተደረገው።
ኦዴግ የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጥሪ በመቀበል በቅርቡ ከውጭ አገር የተመለሰ የፖለቲካ ፓርቲ ሲሆን የአመራር አባላቱ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር መስራቾች ነበሩ።
ከአመራር አባላቱ መካከል ዶክተር ዲማ ኖጎ እና አቶ ሌንጮ ለታ ናቸው ፡፡

ነቀምት🔝ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልልን ከኦሮሚያ በሚያዋስነው ድንበር ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ የኦሮሚያ ፖሊስ አባላት #መገደላቸው ተሰምቷል። የፖሊሶች አስክከሬን ነቀምት ከተማ ሲገባ ብዛት ያለው ህዝብ ሀዘኑንና ቁጣውን ገልጿል። በጥቃቱ የተገደሉ የኦሮሚያ ፖሊስ አባላት 17 እንደሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።
ምንጭ፦ ኢትዮጵያ ላይቭ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፦ ኢትዮጵያ ላይቭ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቴፒ⁉️
በደቡብ ክልል በቴፒ ከተማ ለወራት በዘለቀው ራስን የማስተዳደር ጥያቄ ምክንያት በርካታ ወጣቶች መደብደባቸውን እና መታሰራቸውን ነዋሪዎች ለDW ተናገሩ። በከተማይቱ በሰፈነው ውጥረት የግልም ሆነ የመንግስት ተቋማት ለቀናት አገልግሎት ማቋረጣቸውንም ገልጸዋል።
ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ አንድ የከተማይቱ ነዋሪ የሰሞኑ ውጥረት በድጋሚ የተቀሰቀሰው ከደቡብ ክልል የመጡ ባለስልጣናት ላይ የአካባቢው ነዋሪዎች ባሰሙት ተቃውሞ ነው ብለዋል። ነዋሪዎቹ ፍርድ ቤትን የመሳሰሉ የመንግስት ተቋማት ሊያስከፍቱ የሞከሩ የክልሉ ባለስልጣናት በመጀመሪያ በአግባቡ ያቀረብነውን ራስን የማስተዳደር ጥያቄ ይመለሱ የሚል ተቃውሞ ማቅረባቸውን ነዋሪው ተናግረዋል።
የክልሉ ልዩ ኃይል አባላት እና የአካባቢው ባለስልጣናት ተቃውሞ ለማሰማት የወጡ ወጣቶችን ክፉኛ መደብደባቸውን እና ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ማሰራቸውን ገልጸዋል።
ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ድብደባ የደረሰባቸው ወጣቶች በቴፒ ሆስፒታል ጭምር ተኝተው ሲታከሙ ቆይተዋል ብለዋል። የታሰሩት ወጣቶች ደግሞ አሁንም በቴፒ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ እና በቴፒ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ እንደሚገኙ አስረድተዋል። እስርን ፍራቻ እርሳቸውን ጨምሮ በርካቶች ለቀናት አካባቢያቸውን ለቅቀው ወደ አጎራባች ዞኖች እና ጫካዎች መሸሻቸውን እና እስካሁንም ወደ ቴፒ ከተማ ያልተመለሱ እንዳሉ ተናግረዋል።
በአካባቢው ካለው ውጥረት እና ተቃውሞ ጋር በተያያዘ ባለፈው እሁድ ቴፒ ከተማ አቅራቢያ 19 ገደማ ቤቶች መቃጠላቸውን የዓይን እማኙ ገልጸዋል።
ቤቶቹን አቃጥለዋል ተብለው የተጠረጠሩ አራት ሰዎች ትላንት በቴፒ ከተማ በተደረገባቸው ጥቆማ በመከላከያ ሰራዊት አባላት አማካኝነት በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም አክለዋል። ከአካባቢው ነዋሪዎች የተወከሉ 14 ሰዎች በወጣቶች ላይ የደረሰውን ጥቃት፣ ድብደባ እና እስር እንደዚሁም የቤቶች ቃጠሎ አቤት ለማለት ወደ ደቡብ ክልል መቀመጫ ሀዋሳ ተጉዘዋል።
ተወካዮቹ ባለፈው አርብ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሚሊዮን ማቲዎስን አግኝተው ወደ አካባቢው ጸጥታ የሚያስከብር ኃይል እንዲላክላቸው ጠይቀዋል።
የክልሉ መንግስት ነዋሪዎቹ ያቀረቡትን ጥያቄ የሚመለከት ከፍተኛ የአመራር ቡድን ወደ አካባቢው እንደሚላክ ቃል ገብቶ ነበር።
በአካባቢው ራስን የማስተዳደር ጥያቄ የሚያነሱት የሸኮ እና የማጃንግ ብሄረሰብ አባላት አሁን በሸኮ እና በቤንች ማጂ ዞን ውስጥ ለሁለት ተከፍለው መኖራቸውን ሲቃወሙ ቆይተዋል። ጥያቄ አቅራቢዎቹ ሁለቱ ብሔረሰቦች በአንድ ዞን ውስጥ እንዲደራጁ ይሻሉ።
በአዲሱ ዞን ውስጥ እንዲካተቱ የሚፈለጉት አካባቢዎች የኪ፣ ጉራፈርዳ፣ ሸኮ እና አይና አምባ የተባሉ አካባቢዎች ናቸው።
ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ

ዊዳት አህመድ‼️
በሰብዓዊ መብት ጥሰት ተጠርጥረው የሚፈለጉት የዶክተር #ሀሽም_ቶፊቅ ባለቤት ዊዳት አህመድ ላይ የ7 ቀናት ጊዜ ቀጠሮ ፍርድ ቤት ፈቀደ።
በህግ የሚፈለጉ ሰብዓዊ መብት ጥሰት ተጠርጣሪን በማሸሽና የተጠርጣሪን ማስረጃ በመሰወርና በማሸሽ ወንጀል የተጠረጠሩት ወይዘሮ ዊዳት አህመድና ወንድማቸው ሰሚር አህመድ በፌዴራሉ ፈርድ ቤት 10ኛ ወንጀል ችሎት ቀርበው ጉዳያቸው ታይቷል።
በዚህም ፍርድ ቤቱ በወይዘሮ ዊዳት ላይ ፖሊስ የጠየቀውን የ14 ቀናት ጊዜ ቀጠሮ ውድቅ በማድረግ የሰባት ቀናት ጊዜ ቀጠሮ ሰጥቷል።
እንዲሁም በህግ የሚፈለጉትን ተጠርጣሪ ዶክተር ሀሽም ቶፊቅን መቀሌ ያደረሰና በአውሮፕላን በቦሌ አየር ማረፊያ በኩል ሲመለስ የተያዘው ተጠርጣሪ ሰሚር አህመድ ላይ ተጨማሪ ምርመራ ለማድረግ ፖሊስ የጠየቀውን ተጨማሪ ጊዜ ውድቅ በማድረግ በ30 ሺህ ብር ዋስ እንዲወጣ ፍርድ ቤቱ ፈቅዷል።
ወይዘሮ ዊዳት ተጠርጣሪ የሆኑት ባለቤታቸው እንዲያመልጡ መሸኘታቸውንና በፖሊስ ሲያዙም ከሁለት ሽጉጥ ጋር እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን ፖሊስ አስረድቷል። በመሆኑም ወይዘሮ ውዳት ለህዳር 26 ቀን 2011 ዓ.ም ፍርድ ቤቱ ቀጠሩ ሰጥቷል።
ምንጭ፦ ena

#Update የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻ አውጭ ግንባር (ኦብነግ) ከፍተኛ አመራሮች በመጭው ቅዳሜ አዲስ አበባ እንደሚገቡ ኦብነግ አስታውቋል፡፡ የኦብነግ ቃል አቀባይ በሰጡት መግለጫ የግንባሩ ሊቀመንበር መሃመድ ኦማር ከ20 በላይ ከሚሆኑ ከፍተኛ አመራሮቻቸው ጋር ነው የሚገቡት፡፡
©wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
©wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia