#udate አርበኞች ግንቦት 7⬇️
በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ለውጥ እንዲመጣ የሁሉም ሀሳብ አራማጆች #ለዘለቄታዊ ለውጥ ቁጭ ብሎ መወያየት እንደሚገባ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለፁ።
ሊቀመንበሩ በቦሌ አየር ማረፊያ በሰጡት መግለጫ #የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ለመጠበቅ ከመጣር ይልቅ #ትክክለኛ ምርጫ ማካሄድ የሚችል ስርዓትና #ተቋማት መኖራቸውን ማረጋገጥ ቅድሚያ ሊሰጠው እንደሚገባ ገልፀዋል።
የለውጡ ኃይል የሀገሪቱን ረጅም የመከራ ቀን በመሳጠርም ትልቅ አስተዋፅኦ ማድረጉንም አስታውቀዋል።
ከሁሉ በላይ ሁላችንም ለሀገር ለውጥ #እንወያይ የሚል ሀሳብ አንግቦ ለተግባራዊነቱም መስራቱ መጪው ጊዜ #ብሩህ ይሆናል የሚል ተስፋ እንዳሰነቃቸውም ገልፀዋል።
የአርበኞች ግንቦት ሰባት ከሁሉም ኃይሎች ጋር ተመካክሮ የተገኘውን ይህን እድል መጠቀም እንደሚሻም ነው ያሰትወቁት ።
በፖለቲካ ምክንያት ሰውን እንደጥላት የማየት አስተሳሰብ ከህብረተሰቡ ሊወጣ ይገባል #መረጋጋት ያስፈልጋል ብለዋል ፕሮፌሰሩ።
የሀገሪቱን ዘለቂ ሰላም ለማምጣትና ዲሞክራሲያዊ ባህልን ለማጎልበት ህብረተሰቡ ለመወያየትና ለመደማመጥ የሚቻልበት ሁኔታ መፍጠር አለበት ስለዚህም ለሁሉም ነገር ነገሮችን #ተረጋግቶ ማሰብ ይገባል ብለዋል።
እኛ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲመጣ ከማድርግ ውጪ ሌላ ዓለማ የለም ይህን ስራ ለመተግበር ግን ብዙ ስራ ይጠይቃል ይህንንም ከሁሉም ጋር በጋራ ለመስራት ፍቃደኛ ነን ብለዋል ሊቀመንበሩ በመግለጫቸው።
ፕሮፌሰር ብርሃኑ እኛ በህብረ ብሔራዊ ስሜት ሀገርን ለመገባት አስበን ብንመጣም #በብሔር ከተደራጁ አካት ጋርም ቢሆን በዲሞክራሲያዊ መልኩ #ለመወያየት ዝግጁ ነን ብለዋል።
©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia

#update ከቡራዩ ከተፈናቀሉ ዜጎች በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ከተማ ያሉ #ተፈናቃይ ዜጎች ቁጥር 1 ሺህ 514 ብቻ ናቸው፡፡ በቡራዩ በአሁኑ ወቅት በተፈጠረው #መረጋጋት በአዲስ አበባ ጊዜያዊ የመጠለያ ጣቢያዎች ተጠልለው ከነበሩ 11 ሺህ 902 ያህሉ ወደመጡበት የመኖሪያ ቀያቸው በአዲስ አበባ አስተዳደር አማካይነት ተመልሰዋል፡፡
©የአዲስ አበባ ኮሚኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
©የአዲስ አበባ ኮሚኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በቅርቡ ግጭት በተከሰተባቸው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና የኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ ቦታዎች ላለፉት 2 ቀናት በአብዛኛዎቹ #መረጋጋት የታየባቸው ቢሆንም ሆሮ ሊሙና ያሶ በተባሉት ቦታዎች ግን አሁንም የፀጥታ ሥጋት መኖሩን የምሥራቅ ወለጋ ዞን የፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ታከለ ቶሎሣ ለኢቲቪ ገልጸዋል፡፡ በአካባቢው ያለና #ማንነቱን በግልፅ ለመለየት ያልተቻለ የተደራጀ እና የታጠቀ ኃይል ሕዝቡን ሥጋት ውስጥ ከቶታል ያሉት ኃላፊው ችግሩን ለማስቆም መንግሥት አፋጣኝ እርምጃ ሊወስድ እንደሚገባው ተናግረዋል፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update በቤንሻንጉል ካማሺ ዞን #መረጋጋት እየተፈጠረ ይገኛል ተባለ። በዚህም ድጋፍ ለሚሰፈልጋቸው ወገኖች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ነው የተሰማው።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቦንጋ እየተረጋጋች ነው‼️
በካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ ከቡና መገኛነት ጋር ተያይዞ በድረ-ገጽ በተላለፈ መረጃ የተፈጠረው ችግር በመቃለሉ ወደ #መረጋጋት መመለሱን የዞኑ ባህል፣ ቱሪዝምና መንግስት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ አስታወቀ፡፡
የመምሪያው ኃላፊ አቶ #አስረስ_አዳሮ ለኢዜአ እንደገለጹት በተፈጠረው ችግር ምክንያት በከተማዋ ላለፉት አምስት ቀናት ትራስንፖርትና ማህበራዊ አገልግሎቶች ተቋርጠው ነበር፡፡
ይህም የአካባቢውን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴ እንደሚጎዳ የዞኑ አስተዳደር ከወጣቱንና ከሌላውም የህብረተስብ ክፍል ጋር ተወያይቶ መግባባት ላይ በመድረሱ ከትናንት ማምሻውን ጀምሮ ከተማዋ ወደ መረጋጋት መመለሷን አስረድተዋል፡፡
የትራንስፖርት አገልግሎትም ጀምሯል፡፡
የቡና መገኛነት ጉዳይ መነሻ ሆኖ ለዓመታት የቆየው የቡና ሙዚየም ስራ አለመጀመር ህዝቡን እንዳስቆጣውም ኃላፊው ጠቁመዋል፡፡
ከኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ልማትና ግብይት ባለስልጣን የተሰጠው ይቅርታና የቡና ሙዚየም ግንባታ ስራው እንደሚጀምር የሰጠው መግለጫ ህዝቡን እንዳረጋጋው ተናግረዋል፡፡
ከህዝቡ የተነሱ ጥያቄዎች ከክልልና ከፌደራል መንግስት ጋር በመነጋገር ምላሽ እንዲያገኙ ለመስራት መስማማት ላይ በመድረሳቸው የግልና የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ወደቀድሞ ስራቸው መግባታቸውን ገልጸዋል፡፡
አካባቢውን ወደ ሰላማዊ ሁኔታ ለመመለስና መንገዱን ለማስከፈት በተደረገው ጥረት የወጣቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ድርሻ ከፍተኛ እንደነበረ አስታውቀዋል፡፡
ከከተማዋ ነዋሪዎች መካከል አቶ ገብረሚካኤል ወልደማርያም በሰጡት አስተያየት በታሪክ የሚታወቀው የከፋ ቡና መገኛነት በተለያዩ ተቋማት የተሳሳተ መረጃ በመሰጠቱ ህዝቡን ማስቆጣቱን ተናግረዋል፡፡
ህዝቡ ያነሳቸውን ጥያቄዎች የዞኑ አስተዳደር ኃላፊነት ወስዶ እንደሚያስፈጽም ሃላፊነት በመውሰዱ ተፈጥሮ የነበረው አለመረጋጋት ወደ ነበረበት መመለሱን ገልጸዋል፡፡
መንግስት የሀዝቡን ጥያቄ በፍጥነት መመለስ እንዳለበትና ጉዳዩ ዳግም ጥያቄ የሚያስነሳ መሆን እንደሌለበት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ሌላኛው የከተማው ነዋሪ አቶ ረጋሳ ጸጋዬ በበኩላቸው ባለፉት ቀናት የተካሄደው ሰልፍ ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ መጠናቀቁን ገልጸው ጥያቄው ተገቢነት ያለው በመሆኑ በመንግስት በኩል ምላሽ ያገኛል ብለው እንደሚጠብቁ ተናግረዋል፡፡
“ቡናና ከፋ ከስያሜው ጀምሮ ጥብቅ ቁርኝት ያለው እና ታሪካዊ የሰነድ ማስረጃዎች የሚያረጋግጡ ሆኖ ሳለ የተላለፈው መረጃ መዛባት ለችግሩ ምንጭ ሆኗል “ያሉት ደግሞ አቶ ብርሃኑ ገብሬ ናቸው፡፡
የዞኑ አስተዳደር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ጉዳዩ የመጨረሻ እልባት እንዲያገኝ ማድረግ እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡
ምንጭ፦ ኢዜአ