TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Update 20ኛው የአፍሪካ ህብረት የሚኒስትሮች #አስቸኳይ ስብሰባ መካሄድ ጀምሯል። ስብሰባው በአፍሪካ ህብረት መሰብሰቢያ አዳራሽ በህብረቱ ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፈቂ መሃመት በይፋ ተከፍቷል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የቀድሞው የሜቴክ ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄነራል ክንፈ ዳኘውን ጨምሮ ዘጠኝ ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት ቀረቡ። በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 10ኛ ወንጀል ችሎት ከቀረቡት ተጠርጣሪዎች ሰባቱ በሙስና ሲሆን ሁለቱ ደግሞ በሰብአዊ መብት ጥሰት ነው። የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 10ኛ ወንጀል ችሎት ከደቂቃዎች በኋላ የፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ በተጠርጣሪዎች ላይ የሚያቀርበውን የአቤቱታ የምርመራ መዝገብ የሚመለከት ይሆናል።

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሜ/ጄ ክንፈ ወንድም አቶ ኢሳያስ ዳኘው የማይገባ የጥቅም ትስስር በመፍጠር ሃብት አንዲባክን በማድረግ ወንጀል ተከሰው ፍ/ቤት ቀርበዋል። የሜጀር ጄነራል ክንፈ ዳኘው ወንድም አቶ ኢሳያስ ዳኘው የኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ የስራ ኃላፊ ሆነው ሳሉ የግዢ ስርአቱን በጣሰ መልኩ ሜቴክ ጨረታ እንዲያሸንፍ በማድረግ ወንጀል ተጠርጥረው ፍረድ ቤት ቀረቡ። ተጠርጣሪው የማይገባ የጥቅም ትስስር በመፍጠር የህዝብና የመንግስት ሃብት አንዲባክን አድርገዋል በሚል ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት። በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 10ኛ ወንጀል ችሎት ጉዳያቸው እየታየ ያሉት ሁለቱ ወንድማማቾች አቅም ስለሌለን መንግስት ጠበቃ ያቁምልን ሲሉ ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሜጀር ጄነራል ክንፈ ዳኘው‼️

የፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቡድን የቀድሞው የብረታብረት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄነራል ክንፈ ዳኘው ላይ ያቀረበው የአቤቱታ መዝገብ ዋና ዋና ጭብጦች፦

• ሜቴክ ባሉት 10 ኢንዱስትሪዎች ድጋፍ እንዲሰሩ የተያዙ ፕሮጀክቶችን ማጓተት
o ያዩ ማደበርያ
o የስኳር ፋብሪካዎች
o ታላቁ የህዳሴ ግድብ

• በዚህ ሳቢያም የህዝብና የመንግስት ንብረት እንዲባክን ማድረግ

• የጨረታ ህግን በመጣስ ጨረታ ስራ ያጓትታል በሚል ያለ ጨረታ ህገወጥ ግዢ መፈፀም

• ከኢትዮጵያ ባህር ትራንዚት አገልግሎት 28 ዓመት በማገልገላቸው ለሜቴክ ብረታቸው ቀልጦ ለግብአትነት እንዲውሉ የተሰጡ መርከቦችን የስራ ኃላፊው ያለሙያቸው በመግባት ከ29 ሚሊዮን ዶላር በላይ በሆነ ወጪ በማድረግ ተጠግነው በህገወጥ መልኩ ለንግድ
አገልግሎት ስራ ላይ እንዲውሉ አድርገዋል፤

• በኋላም መርከቦቹን በ2 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዶላር እንዲሸጡ አድርገዋል፤ ለጥገና ወጪ ቢያስወጡም ስራ ላይ ሲሰማሩም ሆነ በመጨረሻ ሲሸጡ መርከቦቹ ለሀገሪቱ አንድም ሳንቲም ገቢ አላስገቡም፤ በዚህም በሀገር ሀብት ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሰዋል፤

• ለያዩ ማዳበሪያ ከተያዘው 11 ቢሊዮን ብር 25 በመቶውን 2.5 ቢሊዮን ብር ሜቴክ ቢወስድም ምንም ስራ አልሰራም

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው ጡረታ የወጣሁ በመሆኔ በወር የማገኘው 4000 ብር ብቻ ስለሆነ የሰው ፊት ከማይ መንግስት ጠበቃ ያቁምልኝ ሲሉ ፍርድ ቤቱን ጠይቀው ተፈቀደላቸው። ፍርድ ቤቱ ወንድማቸው አቶ ኢሳያስ ዳኘውም በተመሳሳይ አቅም ስለሌለኝ መንግስት ጠበቃ ያቁምልኝ ሲሉ ያቀረቡትን ጥያቄ ተቀብሎ መንግስት ተከላከይ ጠበቃ እንዲመድብላቸው ትዕዛዝ ሰጥቷል። የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 10ኛ ወንጀል ችሎት ተጠርጣሪዎቹ ከተመደበላቸው ጠበቃ ጋር በመሆን ሀሳበቸውን እንዲሰጡ ለነገ ቀጠሮ ሰጥቷል።

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኦነግ እና ODP‼️

የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ODP) እና የኦነግ አመራሮች ዛሬ በጋራ በሰጡት መግለጫ በሁለቱ መካከል ያለውን ስምምነት በማጠናከርና ችግሮችን በመፍታት #አብረው ለመስራት #ተስማምተዋል፡፡

የODP ምክትል ሊቀመንበር አቶ #ለማ_መገርሳ ከዚህ በኋላ ከኦነግ ጋር በመደማመጥ ለአገር እድገት በጋራ እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡

አቶ ለማ ከኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ጋር አብሮ ለመስራትና የኦነግ ሰራዊት የመንግስት አካል ሆኖ ተጨማሪ አቅም እንዲሆን በአስመራ ስምምነት መደረሱን ገልጸዋል፡፡

በዚህ ስምምነት መሰረት ኦነግ ወደ አገር ገብቶ ስራ መጀመሩን የገለጹት አቶ ለማ፣ አለመረጋጋት የተፈጠረው ስምምነቱ ፈርሶ ሳይሆን ካለመረዳዳት የመነጫ ነው ብለዋል፡፡

ከእንግዲህ ሰላምና መረጋጋት እንዲፈጠር ሁለቱ ፓርቲዎች መስማማታቸውን አቶ ለማ ተናግረው፣ የODP አባላትና የጸጥታ ኃይሎች ይህንን ስምምነት ተረድተው መንቀሳቀስ አለባቸው ብለዋል፡፡

ወደ ትናንትናው ላለመመለስ በጋራ ቃል ተገባብተው አብረው ለመስራት እንደተስማሙም አቶ ለማ ተናግረዋል፡፡

የኦነግ ሊቀመንበር አቶ #ዳውድ_ኢብሳ በበኩላቸው፣ በአስመራ የተደረሰውን ስምምነት በመተግበር ከODP ጋር አብሮ ለመስራት መስማማታቸውን ገልጸዋል፡፡

አቶ ዳውድ ኢብሳ ከODP አብረው ለመስራት መስማማታቸውንና የኦነግ አባላትና ደጋፊዎች ለዚህ ስምምነት የበኩላቸውን አስተዋዕኦ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡

ምንጭ:- OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክርቤት ኤርትራ ላይ ጥሎት የነበረውን #ማዕቀብ አንስቷል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ማዕቀቡ በመነሳቱ ለመላው የኤርትራ ህዝብ እንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፏል!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የቀድሞውን የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ምክትል እና የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀኔራል አቶ #ያሬድ_ዘሪሁንን አስመልጠዋል በሚል የተጠረጠሩ ግለሰቦች ፍርድ ቤት ቀረቡ። ዛሬ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 10ኛ የወንጀል ችሎት አቶ ያሬድን አስመልጠዋል የተባሉት የነብስ አባቱ አባ ሃይለማርያም ሃይለሚካኤል እና ሾፌራቸው አሸናፊ ታደለ ፍርድ ቤት ቀርበዋል። መርማሪ ፖሊስ ተጠርጣሪውን ለመያዝ በሚል ችሎቱን የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ጠይቋል። ችሎቱም መርማሪ ፖሊስ ያቀረበው ሃሳብ ተቀባይነት የለውም በሚል ፖሊስ በ10 ቀን ውስጥ #አጣርቶ እንዲያቀርብ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አስመራ🔝በኤርትራ ላይ ተጥሎ የነበረው ማዕቀብ በመነሳቱ የአስመራ ከተማ ነዋሪዎች ደስታቸው እየገለፁ ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለሚመለክተው አካል‼️

በሞያሌ አካባቢ ችግር እንዳለ የTIKVAH-ETH ተከታዮች እያሳወቁን ይገኛሉ። መንግስት ችግሩ ሳይከፋ አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስድ እና የተፈጠረውን ችግር እንዲፈታ ተጠይቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የረድዔት ድርጅቶች በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የጸጥታ ችግሩ ባለመሻሻሉ በካማሺ እና ኦዳ ዞኖች ላሉ ተፈናቃዮች ዕርዳታ ለማድረስ ተቸግረዋል፡፡ የተመድ አስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ ማስተባበሪያ ቢሮ (OCHA) በድረ ገጹ እንደገለጸው ላንድ ጊዜ ዕርዳታ ብቻ ለተፈናቃዮች የደረሱት በወታደር የታጀቡ የመንግሥት ባለሥልጣናት ብቻ ናቸው፡፡ ከሳምንታት በፊት በተከሰቱ ማንነትን መሠረት ባደረጉ ግጭቶች በካማሺ ዞን 42 ሺህ፣ በኦዳ ዞን ደሞ 15 ሺህ ተፈናቃዮች አስቸኳይ ዕርዳታ ይፈልጋሉ፡፡

©wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ትግራይ ክልል‼️

የትግራይ ህዝብ ለዓመታት የከፈለው መስዋዕትነት በሃገሪቱ የህግ የበላይነት እንዲከበርና በማንኛውም ወቅት ተጠያቂነት እንዲኖር መሆኑን የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አስታወቀ።

የክልሉ መንግስት ዛሬ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው መንግስት አሁን የጀመረው የህግ የበላይነትን የማስከበር ሂደት በተገቢው ጥንቃቄ ሊከናወን የሚገባው ነው።

ሰብአዊ ጥሰትና ሙስና በፈጸሙ ሰዎች ላይ በመንግስት ሰሞኑን እየተወሰደ ያለው እርምጃ የህግ ልዕልና ሳይሸራረፍ ከተጽዕኖ በጸዳ መልኩ ተግባራዊ መደረግ እንዳለበት መግለጫው አመልክቷል።

የትግራይ ህዝብ ለዓመታት የከፈለው መስዋዕትነት የህግ የበላይነት እንዲከበርና በማንኛውም ወቅት ተጠያቂነት እንዲኖር ለማድረግ መሆኑን ያመለከተው መግለጫው መንግስት እየወሰደ ያለውን እርምጃ በሁሉም ተጠርጣሪዎች ላይ እንዲያተኩር ጠቁሟል።

በሰብአዊ መብት ጥሰት፣ የሙስና ችግርና ህገ-መንግስታዊ ጥሰት ውስጥ እጃቸው ያለ አመራሮችና ተቋማት ስለመኖራቸው ቀደም ሲል በተካሔዱ የኢህአዴግ መድረኮች ውይይት መደረጉንም አመልክቷል።

ችግሩ በእኩል እንዲስተናገድ ከማድረግ ባለፈ እርቅና ይቅር ባይነትን መሰረት አድርጎ የተጀመረው ሂደት ወደ ኋላ እንዳይመለስ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ጠቅሷል።

“የህግ የበላይነትም ሳይሸራረፍ እንዲተገበር ከፍተኛ ጥንቃቄና ጥናት የሚጠይቅ መሆኑንም የክልሉ መንግስት ያምናል” ብሏል መግለጫው፡፡

የትግራይ ክልል ህዝብ ከሌሎች ብሔሮችና ብሔረሰቦች ጋር በመሆን የከፈለው መስዋዕትነት የዜጎች እኩልነትና ሰብአዊ መብት እንዲከበር እንጂ በማንም አካል እንዲጣስ እንዳልሆነ መግለጫው አመልክቷል።

ባለፉት ዓመታት ይታዩ የነበሩት የፍትህና የዲሞክራሲ መጓደሎች እንዲስተካከሉ ህዝቡ በፅናት እየታገለ መምጣቱንም መግለጫው አስታውሶ በጥልቅ ተሀድሶ ወቅት ህዝቡ ያሳየው ተሳትፎ አንዱ ማሳያ መሆኑን አስረድቷል።

ከሰብአዊ መብት አያያዝና ከሙስና ጉዳዮች ጋር በተያያዘ እየታየ ላለው ሁኔታ ተጠያቂዎቹ እጃቸው ያለበት አመራሮችና ተቋማት መሆናቸውንም መግለጫው አመልክቷል።

ምንጭ፡- ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥቆማ ለኢትዮጵያ መንግስት‼️

የደቡብ ክልል መንግስት እና የፌደራሉ መንግስት በጉራጌ ዞን ያለውን ሁኔታ አጣርቶ የመፍትሄ እርምጃ እንዲወስድ እና ችግሩን እንዲፈታ ጥሪ እናቀርባለን።

@tsegabwolde @tikvahethiopia