አምባሳደር ሱሌማን🔝ከ5 አመት በፊት በቅቱ ለነበሩት የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም የጻፉት ደብዳቤ። አምባሳደር ሱሌማን በወቅቱ በጅቡቲ የኢትዮዽያ አምባሳደር ነበሩ።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የምስራች!!
ውድ የ“TIKVAH-ETHIOPIA” ቤተሰቦች እንደሚታወቀው ቻናላችን ከአንድ አመት በላይ በቴሌግራም መረጃዎች፣ ዜናዎች፣ እንዲሁም መልዕክቶችን ሲያቀርብላችሁ ቆይቷል።
አሁን ደግሞ ተደራሽነቱን በተሻለ ሁኔታ ለማሳደግ ከ“Golden Gear" ጋር በመተባበር የሞባይል መተግበሪያ(Application) ለእናንተ ለማቅረብ ዝግጅት ላይ ነው።
በዚህ Application የሃገር ውስጥ እና የሃገር ውጭ ዜናዎች፣ የቢዝነስ ዘገባዎች፣ የስፖርትና የመዝናኛ ወሬዎች በቀላሉ ማግኘት ትችላላችሁ።
🔹መተግበሪያው(APPLICATION) በቀናት ውስጥ ይለቀቃል!!

ሜቴክ እና ኢንጂነር ስመኘው‼️
ኢንጂነር #ስመኘው_በቀለ የሕዳሴ ግድብ ስራ አስኪያጅነትን ሙሉ በሙሉ ጠቅለው እንዲይዙ የተደረገው የብረታብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽንን (ሜቴክ) ጥቅም አይጋፉም በሚል ተስፋ ነበር።
ኢንጂነር ስመኘው ከህልፈተ ህይወታቸው ጥቂት ቀናት አስቀድሞ ስለሚመሩት ፕሮጀክት ዝርዝር ሪፖርት አዘጋጅተው እንዲያቀርቡ ይታዘዛሉ። በተመሳሳይ ጊዜ የመንግስት የልዑካን ቡድን ወደ ሕዳሴው ግድብ መገናኛ ብዙሀንን ይዞ በመሄድ እንደሚጎበኝ መርሀ ግብር ይወጣል። ኢንጅነር ስመኘው ለመንግስት ለማቅረብ ለተዘጋጁት ሪፖርት ከእናት መስሪያ ቤታቸው የኤሌክትሪክ ሀይል ኮርፖሬሽንና ከተቋራጩ ሜቴክ የፋይናንስ መረጃዎችን ለማስታረቅ ወደላይ ወደታች እያሉ በነበረበት ወቅት ከሜቴክ ቀና ምላሽ አላገኙም። “አለቆች የሉም” ፣ “ለማዘጋጀት ጊዜ ያስፈልገናል” የሚሉ ምክንያቶች ተነግሯው ሲጠባበቁ የሪፖርት ማቅረቢያው ጊዜ ደረሰ።
ሌላው ተቋራጭ ሳሊኒ የራሱን ሪፖርት አስቀድሞ አስረክቦ ነበር። ኢንጂነር ስመኘው በእጃቸው ያለውንና የሚያውቁት የፋይናንስ መረጃ ብቻ አሰናዱ። ሪፖርቱን ለማቅረብ አንድ ቀን ሲቀራቸው በጠቅላይ ሚንስትሩ ቢሮ በኩል በርካታ መረጃ መሰባሰቡንና የህዳሴው ግድብ ስራ ከተቋረጠ ከዓመት በላይ ማስቆጠሩ መሰማቱን ደረሱበት። በሜቴክ ላይም የሙስና ምርመራ ይደረጋል ኢንጂነር ስመኘውም ከሀላፊነታቸው እንደሚነሱ ውሳኔ ላይ መደረሱን ስምተዋል። ይልቁንም ለምርመራ የሚያስፈልጉ ቁልፍ መረጃዎችን እንዲሰጡ እንደሚጠበቁ ተነግሯቸዋል። የሜቴክ አመራሮች ኢንጂነር ስመኘው መረጃ እንዳያገኙ ከመከላከል ባለፈ መንግስት ሊያደርገው ባሰበው ምርመራ እንዳይተባበሩ ጫና ለመፍጠርም ሙከራ ሲያደርጉ ነበር። ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ሀምሌ 19 , 2010 አ.ም መስቀል አደባባይ መኪናቸው ውስጥ ህይወታቸው አልፎ ተገኝተው ነበር። አጣብቂኝ ውስጥ የወደቁት ስመኘው ራሳቸውን ማጥፋታቸውን ፖሊስ አደረኩት ባለው ምርመራ ገልጿል።
ሜቴክ ለዓመታት ለፈፀመው ምዝበራ ኢንጂነር ስመኘውን በቀላሉ ማግባባትና ዝም ማሰኘት ችሎ ነበር። ኢንጂነር ስመኘው በተደጋጋሚ ሜቴክ ስራውን መስራት እንደተሳነው ለመስሪያቤታቸው ሪፖርት አድርገዋል። መረጃው ከጥቂት ሀላፊዎች ውጪ እንዳይወጣ ይጠነቀቁ ነበር። የሕዳሴው ግድብ ፕሮጀክት መጀመሪያ ላይ ሁለት ስራ አስኪያጆች ነበሩት። የእሳቸውን ህልፈተ ህይወት ተከትሎ የግድቡ ስራ አስኪያጅነት በጊዜያዊነት የኢንጂነር ስመኘው ምክትል በነበሩት ኤፍሬም ወልደ ኪዳን ሲመራ ከቆየ በሁዋላ በቅርቡ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ክፍሌ ሆራን ማግኘቱ ይታወቃል።
የህዳሴው ግድብ ዋና ስራ አስኪያጅ ሆነው የተሾሙት አቶ ክፍሌ ሆሮ ሜቴክ ኤሌክትሮ ሜካኒካል ስራን መስራት የለበትም በማለታቸው ከግድቡ ሀላፊነታቸው ተባረው የነበሩ ናቸው።
አቶ ክፍሌ ሆራ ለህዳሴው ግድብ ግንባታ ሂደት አዲስ አይደሉም ይልቅስ የግድቡን ግንባታ በበላይነት ሲመሩም የነበሩም ናቸው። የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በኢትዮጵያውያን አቆጣጠር በ2003 አ.ም ሲጀመር ኢንጂነር ስመኘው ብቻ አልነበሩም የኘሮጀክቱ ስራ አስኪያጅ እንዲያውም የግድቡ ፕሮጀክት ሁለት ስራ አስኪያጆች ነበረት።
ኢንጂነር ስመኘው የግድቡን የሲቪል ስራ በስራ አስኪያጅነት አቶ #ክፍሌ_ሆሮ ደግሞ የግድቡን የኤሌክትሮ ሜካኒካል ስራዎችን በስራ አስኪያጅነት እንዲከታተሉ ተመድበዋል።
አቶ ክፍሌ በስራ አስኪያጅነት ከአንድ አመት በላይ ሰርተዋል። ሆኖም ትንሽ ቆይቶ የህዳሴውን ግድብ የኤሌክትሮ ሜካኒካልና ሀይድሮ ሜካኒካል ስራዎችን ማን ይስራው የሚለው ጉዳይ ትልቅ አጨቃጫቂ ጉዳይ ሆኖ ብቅ ይላል። ያኔ የሲቪል ስራውን ያከናውን የጀመረው ሳሊኒ ኢምፕሪጂሎ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ስራው እንዲሰጠው በእጅጉ ቢፈልግም በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ትእዛዝ የተቋቋመው የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽንም : ሜቴክ : ስራውን ይውሰደው የሚል ሀሳብ ይቀርባል። ህዳሴው ግድብ ሲጀመር ግን ሜቴክ ገና ከተመሰረተ አንድ አመቱ ነው።
የግድቡ ኤሌክትሮ ሜካኒካል ስራዎች ስራ አስኪያጅ አቶ ክፍሌ ታድያ ለሜቴክ ኮንትራቱ መሰጠት የለበትም ሲሉ በጽኑ ተቃውመው እንደነበር ዋዜማ ያገኘችው መረጃ ያሳያል። የእሳቸውና ሌሎች ለፕሮጀክቱ የቅርብ የነበሩ የስራ ሀላፊዎችም ልምድና ብቃት ለሌለው ሜቴክ ውሉ ሊሰጠው አይገባም የሚል አቋም ይዘዋል። በአቶ ክፍሌ ሆሮ የከረረ ተቃውሞ ያልተስማሙት አለቆቻቸው የሜቴክን ጥቅም ለማስጠበቅ ሲባል ከሀላፊነታቸው እንዲነሱ አድርገዋቸዋል።
ኢንጂነር ስመኘውም ሁለቱንም ስራ ደርበው የህዳሴውን ግድብ ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅነት ይዘው ህይወታቸው እስካለፈበት ጊዜ ቀጥለዋል። የሳቸው ህይወት ሲያልፍ ታዲያ አቶ ክፍሌ ሆሮ ከነበሩበት የግል ስራ ተጠርተው የግድቡን ስራ በስራ አስኪያጅነት እንዲመሩ ተደርገዋል። ሜቴክ በአዲስ አለቆቹ እየተመራ ከግድቡ ስራ እየተቀነሰ ሲመጣ አቶ ክፍሌ ሆሮ ደግሞ ወደ ግድቡ ተመልሰዋል።
ምንጭ፦ ዋዜማ ሬዲዮ

እየለየን... በሜቴክ ጉዳይ‼️
ከዚህ ቀደም የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባል የሆኑ እና በሜቴክ ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች እየደረሰባቸው ስላለው በደል ተደጋጋሚ ቅሬታዎችን ሲያቀርቡ ነበር። ብዙ ተሰቃይትዋል፤ ብዙ ተጎድተዋል። ጥቂት ግለሰቦች በሰሩት ዘግናኝ ስራ ሁሉንም አንድ ላይ መውቀሱ ተገቢ አይደለም። ለፍተው የሚያድሩትን ወጣቶቹ የሜቴክ ሰራተኞችን በማህበራዊ ሚዲያ መዝለፍ፤ በእነሱ ላይ ማላገጥ እና መቀለድ ተገቢ አይደለም።
ሜቴክ ውስጥ የሚሰሩ ባለድንቅ አእምሮ ባለቤቶች ነገር ግን በአስተዳደሩ ክፉኛ የተበደሉ ዜጎች አሉና ሌባውን ከጨዋው እየለየለን ብንናገር መልካም ነው።
በቻናላችን ውስጥ የሚገኙ የሜቴክ ሰራተኞች ትላንትና እና ከትላንት በስቲያ ሲሰሟቸው በነበሩት ዜናዎች እጅጉን ተደስተዋል። ወንጀለኞቹም ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቀዋል።
የጅምላ ዘለፋ አሁኑኑ ይቁም‼️

#Update 20ኛው የአፍሪካ ህብረት የሚኒስትሮች #አስቸኳይ ስብሰባ መካሄድ ጀምሯል። ስብሰባው በአፍሪካ ህብረት መሰብሰቢያ አዳራሽ በህብረቱ ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፈቂ መሃመት በይፋ ተከፍቷል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የቀድሞው የሜቴክ ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄነራል ክንፈ ዳኘውን ጨምሮ ዘጠኝ ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት ቀረቡ። በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 10ኛ ወንጀል ችሎት ከቀረቡት ተጠርጣሪዎች ሰባቱ በሙስና ሲሆን ሁለቱ ደግሞ በሰብአዊ መብት ጥሰት ነው። የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 10ኛ ወንጀል ችሎት ከደቂቃዎች በኋላ የፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ በተጠርጣሪዎች ላይ የሚያቀርበውን የአቤቱታ የምርመራ መዝገብ የሚመለከት ይሆናል።
ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሜ/ጄ ክንፈ ወንድም አቶ ኢሳያስ ዳኘው የማይገባ የጥቅም ትስስር በመፍጠር ሃብት አንዲባክን በማድረግ ወንጀል ተከሰው ፍ/ቤት ቀርበዋል። የሜጀር ጄነራል ክንፈ ዳኘው ወንድም አቶ ኢሳያስ ዳኘው የኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ የስራ ኃላፊ ሆነው ሳሉ የግዢ ስርአቱን በጣሰ መልኩ ሜቴክ ጨረታ እንዲያሸንፍ በማድረግ ወንጀል ተጠርጥረው ፍረድ ቤት ቀረቡ። ተጠርጣሪው የማይገባ የጥቅም ትስስር በመፍጠር የህዝብና የመንግስት ሃብት አንዲባክን አድርገዋል በሚል ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት። በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 10ኛ ወንጀል ችሎት ጉዳያቸው እየታየ ያሉት ሁለቱ ወንድማማቾች አቅም ስለሌለን መንግስት ጠበቃ ያቁምልን ሲሉ ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሜጀር ጄነራል ክንፈ ዳኘው‼️
የፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቡድን የቀድሞው የብረታብረት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄነራል ክንፈ ዳኘው ላይ ያቀረበው የአቤቱታ መዝገብ ዋና ዋና ጭብጦች፦
• ሜቴክ ባሉት 10 ኢንዱስትሪዎች ድጋፍ እንዲሰሩ የተያዙ ፕሮጀክቶችን ማጓተት
o ያዩ ማደበርያ
o የስኳር ፋብሪካዎች
o ታላቁ የህዳሴ ግድብ
• በዚህ ሳቢያም የህዝብና የመንግስት ንብረት እንዲባክን ማድረግ
• የጨረታ ህግን በመጣስ ጨረታ ስራ ያጓትታል በሚል ያለ ጨረታ ህገወጥ ግዢ መፈፀም
• ከኢትዮጵያ ባህር ትራንዚት አገልግሎት 28 ዓመት በማገልገላቸው ለሜቴክ ብረታቸው ቀልጦ ለግብአትነት እንዲውሉ የተሰጡ መርከቦችን የስራ ኃላፊው ያለሙያቸው በመግባት ከ29 ሚሊዮን ዶላር በላይ በሆነ ወጪ በማድረግ ተጠግነው በህገወጥ መልኩ ለንግድ
አገልግሎት ስራ ላይ እንዲውሉ አድርገዋል፤
• በኋላም መርከቦቹን በ2 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዶላር እንዲሸጡ አድርገዋል፤ ለጥገና ወጪ ቢያስወጡም ስራ ላይ ሲሰማሩም ሆነ በመጨረሻ ሲሸጡ መርከቦቹ ለሀገሪቱ አንድም ሳንቲም ገቢ አላስገቡም፤ በዚህም በሀገር ሀብት ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሰዋል፤
• ለያዩ ማዳበሪያ ከተያዘው 11 ቢሊዮን ብር 25 በመቶውን 2.5 ቢሊዮን ብር ሜቴክ ቢወስድም ምንም ስራ አልሰራም
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን

#update ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው ጡረታ የወጣሁ በመሆኔ በወር የማገኘው 4000 ብር ብቻ ስለሆነ የሰው ፊት ከማይ መንግስት ጠበቃ ያቁምልኝ ሲሉ ፍርድ ቤቱን ጠይቀው ተፈቀደላቸው። ፍርድ ቤቱ ወንድማቸው አቶ ኢሳያስ ዳኘውም በተመሳሳይ አቅም ስለሌለኝ መንግስት ጠበቃ ያቁምልኝ ሲሉ ያቀረቡትን ጥያቄ ተቀብሎ መንግስት ተከላከይ ጠበቃ እንዲመድብላቸው ትዕዛዝ ሰጥቷል። የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 10ኛ ወንጀል ችሎት ተጠርጣሪዎቹ ከተመደበላቸው ጠበቃ ጋር በመሆን ሀሳበቸውን እንዲሰጡ ለነገ ቀጠሮ ሰጥቷል።
©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኦነግ እና ODP‼️
የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ODP) እና የኦነግ አመራሮች ዛሬ በጋራ በሰጡት መግለጫ በሁለቱ መካከል ያለውን ስምምነት በማጠናከርና ችግሮችን በመፍታት #አብረው ለመስራት #ተስማምተዋል፡፡
የODP ምክትል ሊቀመንበር አቶ #ለማ_መገርሳ ከዚህ በኋላ ከኦነግ ጋር በመደማመጥ ለአገር እድገት በጋራ እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡
አቶ ለማ ከኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ጋር አብሮ ለመስራትና የኦነግ ሰራዊት የመንግስት አካል ሆኖ ተጨማሪ አቅም እንዲሆን በአስመራ ስምምነት መደረሱን ገልጸዋል፡፡
በዚህ ስምምነት መሰረት ኦነግ ወደ አገር ገብቶ ስራ መጀመሩን የገለጹት አቶ ለማ፣ አለመረጋጋት የተፈጠረው ስምምነቱ ፈርሶ ሳይሆን ካለመረዳዳት የመነጫ ነው ብለዋል፡፡
ከእንግዲህ ሰላምና መረጋጋት እንዲፈጠር ሁለቱ ፓርቲዎች መስማማታቸውን አቶ ለማ ተናግረው፣ የODP አባላትና የጸጥታ ኃይሎች ይህንን ስምምነት ተረድተው መንቀሳቀስ አለባቸው ብለዋል፡፡
ወደ ትናንትናው ላለመመለስ በጋራ ቃል ተገባብተው አብረው ለመስራት እንደተስማሙም አቶ ለማ ተናግረዋል፡፡
የኦነግ ሊቀመንበር አቶ #ዳውድ_ኢብሳ በበኩላቸው፣ በአስመራ የተደረሰውን ስምምነት በመተግበር ከODP ጋር አብሮ ለመስራት መስማማታቸውን ገልጸዋል፡፡
አቶ ዳውድ ኢብሳ ከODP አብረው ለመስራት መስማማታቸውንና የኦነግ አባላትና ደጋፊዎች ለዚህ ስምምነት የበኩላቸውን አስተዋዕኦ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡
ምንጭ:- OBN

#Update የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክርቤት ኤርትራ ላይ ጥሎት የነበረውን #ማዕቀብ አንስቷል።
የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ማዕቀቡ በመነሳቱ ለመላው የኤርትራ ህዝብ እንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፏል!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ማዕቀቡ በመነሳቱ ለመላው የኤርትራ ህዝብ እንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፏል!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የቀድሞውን የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ምክትል እና የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀኔራል አቶ #ያሬድ_ዘሪሁንን አስመልጠዋል በሚል የተጠረጠሩ ግለሰቦች ፍርድ ቤት ቀረቡ። ዛሬ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 10ኛ የወንጀል ችሎት አቶ ያሬድን አስመልጠዋል የተባሉት የነብስ አባቱ አባ ሃይለማርያም ሃይለሚካኤል እና ሾፌራቸው አሸናፊ ታደለ ፍርድ ቤት ቀርበዋል። መርማሪ ፖሊስ ተጠርጣሪውን ለመያዝ በሚል ችሎቱን የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ጠይቋል። ችሎቱም መርማሪ ፖሊስ ያቀረበው ሃሳብ ተቀባይነት የለውም በሚል ፖሊስ በ10 ቀን ውስጥ #አጣርቶ እንዲያቀርብ ትዕዛዝ ሰጥቷል።
ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia