TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ሀዋሳ-ወቅታዊ ጉዳይ⬇️

ያልተጣራ ወሬ በህዝቦች መካከል ጥርጣሬ እንዲፈጠር ያደርጋል።

ከተማችን ሀዋሳ በርካታ ብሄሮችና ብሄረሰቦች #ተቻችለው እና #ተከባብረው የሚኖሩባት እንደሆነ ማንም የሚያውቀው ሀቅ ነው።

ይሁንና በቅርቡ በከተማው የተከሰተውን የፀጥታ ችግር መነሻ በማድረግ በከተማው ነዋሪዎቾ መካከል #ጥርጣሬ እና #አለመደማመጥ እንድፈጠር እንዲሁም ለዘመናት የከተማችን እሴቶች የሆኑት መከባበርና መቻቻል እንድሸረሸሩ እኩይ አላማ ያላቸው ግለሰቦች የተለያዪ የውሸት መረጃዎችን በማህበራዊ ገፅ ላይ እየለቀቁ እንዳሉ መረጃዎች ያሳያሉ።

ለአብነትም በ13/12/2010 በሀዋሳ ከተማ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችን የጫነ ተሽከሪካሪ ተይዟል ተብሎ የተለቀቀው #የሀሰት ወሬ እንደሆነ #ከፓሊስ የተገኘ መረጃ ያሳያል።

#እውነታው የተያዘው ተሽከሪካሪ 15 ቦንዳ በህገ ወጥ መልኩ /ኮንትሮባንድ/ የገባ እቃ የጫነ እንደሆነ የተረጋገጠ ሲሆን ሌላው በህገ ወጥ መልኩ የተገነቡ ቤቶችን ለማፍረስ የተንቀሳቀሱ ፖሊሶች ተገደሉ ተብሎ የተለቀቀው ፎቶግራፍ የጥፋት ሀይሎች አቀነባብረው የለቀቊት
#የሀሰት_መረጃ እንደሆነ ለመጠቆም እንወዳለን።

በመጨረሻም የከተማችን #ፀጥታ እና #ሰላም እንዳይደፈርስ እንዲሁም በከተማው ህዝብ መካከል ጥርጣሬና አለመተማመን እንዳይፈጠር በዚህ በውሸት መረጃ ህብረተሰቡን በስጋት ላይ የሚትጥሉ አካላት #ከእኩይ ዲርጊታችሁ እንድትታቀቡ እያለ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር #ያሳስባል

የከተማችን ህዝብ በማህበራዊ ገፅ የፌክ አካውንት የከፈቱ አካላት በየጊዜው በሚያሰራጬት #የአሉባልታ ወሬ #እንዳይሸበር እናስታውቃለን።

©አቶ ደስታ ዶጊሶ #ሼር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን⬆️

‹‹ … በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የዶሮ እንቁላል ነው በማለት የተለያዩ የተሳቢ እንስሳትን እንቁላል ሲሸጡ የተገኙ ነጋዴዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ …. ›› ተብሎ በማህበራዊ ሚዲያዎቸና ( በፌስቡክ ) የሚሰራጩ ዜናዎች #የሀሰት መሆናቸው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዲቪዥን ኃላፊ ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ ተናግረዋል፡፡ ህብረተሰቡ መሰል ዜናዎችን ከማጋራት እንዲቆጠብና #እንዳይረበሽም ጭምር አሳስበዋል፡፡
.
.
.
ከሰዓታት ቀደም ብሎ ከጋዜጠኛ #ጌጡ_ተመስገን የተገኘ የሀሰት መረጃ ቀርቦ ነበር ይቅርታ ጠይቃለሁ።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥንቃቄ⬆️አዲስ አበባ ከተማን ፍፁም የብጥብጥ አውድማ ለማስመሰል በርካታ ሰዎች በፌስቡክ እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ ከነዚህም መሀል በአክቲቪስት #ጃዋር_መሀመድ ስም #የሀሰት ገፅ ተከፍቶ ህዝቡን ለማበጣበጥ የሚሰሩ ሰዎች ስላሉ ጥንቃቄ ይደረግ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቅርቡ ማጣራት በጀመረባቸውና ያለ ስራ ታጥረው የተቀመጡ መሬቶችን ለልማት የማዋል ስራ ላይ ሁሉም ቦታዎች ለተደራጁ ወጣቶች ይሰጣሉ የሚለው መረጃ ከእውነት የራቀ ነው ሲል የከተማ አስተዳደሩ ለሽገር FM ገልጿል። የአዲስ አበባ ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ እንደተናገረው በቦሌ ክፍለ ከተማ በሚገኙ ወረዳዎች በመንግስት ታጥረው የሚገኙ ቦታዎች በማህበር ለተደራጁ ወጣቶች ይሰጣሉ በሚል #የሀሰት_መረጃ እየተሰራጨ በመሆኑ ነዋሪዎች በሀሰተኛ መረጃ መደናገር የላባቸውም ብሏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ ተወልደ‼️

"አቶ ተወልደ ገ/ማሪያም ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ሀላፊነት ተነስተዋል የሚለውን ነገር ለማጣራት የአየር መንገዱ Chief Operating Officer (COO) የሆኑት አቶ መስፍን ጣሰው ጋር አሁን ደውዬ ነበር። በመልሳቸውም: "እኔ የማውቀው ነገር የለም። #የሀሰት ዜና ይመስለኛል። ቀኑ ሙሉውን ከአቶ ተወልደ ጋር ነው የዋልኩት።" ሌላ የአየር መንገዱ ሰራተኛ ጋር ጥይቄም "He is in duty" የሚል መልእክት ደርሶኛል። የቦርድ ስብሰባ ግን በዚህ ሰአት እየተካሄደ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል። እስካሁን ያለው ነገር ይህን ይመስላል።"

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update ኢሳት የተሰኘው የቴሌቭዥን ጣብያ በቢቢሲ በአመቱ #የሀሰት_ዜና ካሰራጩ ድርጅቶች ዝርዝር ውስጥ ገብቷል። ኢሳት የኦሮሞ ተወላጆች ሶማሌዎችን ጉድጓድ ውስጥ ሲከቱ የሚያሳይ ብሎ የለቀቀው ቪድዮ የሀሰት እንደነበርና ይህም በወቅቱ በኦሮሞዎች ላይ ጥቃት እንዲደርስ ምክንያት ሆኖ እንደነበር ዘግቧል።

🔹በወቅቱ ኢሳት ያሰራጨው የሀሰት ቪድዮ እንደሆነ እና ይቅርታ እንደጠየቀ አይዘነጋም።

A year in fake news in Africa:

https://www.bbc.co.uk/news/world-africa-46127868?fbclid=IwAR3-iV_hmwcfkRd9_hFFhDrYuvWSUynsLGPWoy0wWIFwLky1lZQYIC7MAJw

@Tsegabwolde @tikvahethiopia